TIKVAH-ETHIOPIA
4 ኪሎ ቤተ መንግስት ስር ባለው "አዋሬ ገበያ" የእሳት አደጋ ተነስቷል። አደጋው ሁለት ሰዓት እንዳለፈው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል። በርካታ ንብረትም እንደወደመ ገልፀዋል። ከኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተገኘው መረጃ በቦታው ከ2 ያልበለጡ የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ደርሠው የነበረ ቢሆንም አንዱ መኪና በቂ ውሀ አልያዝኩም ብሎ ተመልሶ ነበር፤ በዚህም በቦታው ካሉት ወጣቶች ጋር መጠነኛ አላግባባት እንዲፈጠር አድርጓል።…
4 ኪሎ አዋሬ የተነሳውን እሳት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
ፖሊስ እና መከላከያ ህዝቡን እያረጋጉ ይገኛል።
በሌላ በኩል ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የደረሰው ጉዳት መጠንና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል።
PHOTO : Haileab (Tikvah Family)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Internet
ለሊት ጠ/ሚር ዶክተር አብይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ከገለፁ በኃላ በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።
የስልክ ጥሪም እየወጣ አይደለም።
TIKVAH-ETH በትግራይ ክልል ስላሉ አባላቱ ያሉበት ሁኔታ እየተከታተለ ለመግለፅ ጥረት ያደርጋል።
PIC : NetBlocks
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፦
ከ50 የአሜሪካ ግዛቶች በ31 ግዛቶች የትኛው እጩ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተገምቷል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 192 ለ 114 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከ50 የአሜሪካ ግዛቶች በ31 ግዛቶች የትኛው እጩ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተገምቷል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 192 ለ 114 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ችግር የሆኑ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ስትመለከቱ ከላይ በተዘረዘሩት ስልኮች በፍጥነት ደውሉ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
@TIKVAHETHIOPIA
@TIKVAHETHIOPIA
#በጣም_አስቸኳይ
ጥሪ የተደረገላችሁ የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር ለደህንነታችሁ ሲባል ባላችሁበት እንድትቆዩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ወደፊት የመግቢያ ቀናችሁ በሚወጣ ተለዋጭ ማስታወቂያ ይገለፃል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጥሪ የተደረገላችሁ የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር ለደህንነታችሁ ሲባል ባላችሁበት እንድትቆዩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ወደፊት የመግቢያ ቀናችሁ በሚወጣ ተለዋጭ ማስታወቂያ ይገለፃል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
እስካሁን የ40 ግዛቶች ውጤት ታውቋል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 225 ለ 213 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
እስካሁን የ40 ግዛቶች ውጤት ታውቋል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 225 ለ 213 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TigrayTikvahFamily
በትግራይ ክልል የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ እስካሁን ከትግራይ ቲክቫህ አባላቶቻችን ጋር መገናኘት አልቻልንም።
ልጆቻቸውን ዩኒቨርሲቲ የላኩ ወላጆች ስለልጆቻቸው አሁናዊ ሁኔታ ማወቅ ባለመቻላቸው መጨነቃቸውን እየገለፁልን ነው።
በተጨማሪ ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል የሚኖሩ አባላት ተጨንቀው በርካታ መልዕክቶችን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
በትግራይ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ስላሉ ተማሪዎች ጉዳይ በቻልነው አቅም አጣርተን ለማሳወቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው።

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለጊዜው ወደ ግቢ እንዳይመጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።
አገሪቱ በገጠማት ወቅታዊ የሆነ የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው ተማሪዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ መልዕክት እየተላለፈ የሚገኘው።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ሲሆኑ ጥሪዎችን በጊዜያዊነት የሚቆሙበትን ውሳኔ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። (አሐዱ ቴሌቪዥን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አገሪቱ በገጠማት ወቅታዊ የሆነ የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው ተማሪዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ መልዕክት እየተላለፈ የሚገኘው።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ሲሆኑ ጥሪዎችን በጊዜያዊነት የሚቆሙበትን ውሳኔ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። (አሐዱ ቴሌቪዥን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።
ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሟል።
ግብረኃይሉ ተጠሪነቱ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን ‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሀይል’’ ተብሎ እንደሚጠራ ተገልጿል።
አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸው ተጨማሪ አካባቢዎችን ግብረኃይሉ በሚያወጣው በመመሪያ ይወስናል።
አዋጁን አስመልክቶ ዝርዝር መርጃ በየጊዜው ለህብረተሰቡ የሚሰጡ ይሆናል።

#ለዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች
ከኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት ፦
በሀገሪቱ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መግታት አስፈልጓል፡፡ በዚሁ መሰረት :-
1. እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪዎች በግቢያችሁ እንድትቆዩ እና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ ፤
2. እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም

#FDREDefenseForce
ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትናንት ምሽት ጀምሮ የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት እንዲሁም በማክሸፍ የህዝቦችን ደህንነት እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ገለፀ።
የመከላከያ ሰራዊት ፥ "እየፈፀመን ያለውን ስኬታማ ተግባር በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር በትብብር እየሰራን ነው" ሲል አሳውቋል።
ምንጭ፦ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር (ENA)

የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት የገቡበትን ውጥረት እንዲያረግቡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ጥሪ አቅርቧል።
ኤምባሲው 2ቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት እንዲጠብቁ አሳስቧል።
የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ እና በመቐለ መካከል በተካረረው ውጥረት ሳቢያ ወደ ትግራይ እና ሰሜን አማራ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ተጓዦች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል።
በሌላ በኩል ፦
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የፌድራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል በአፋጣኝ ውጥረቱን ሊያረግቡ ይገባል ብሏል።
"ሁሉንም ወገኖች ለሰላማዊ ሰዎች ደሕንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ አጥብቀን እናበረታታለን" ሲል ገልጿል።
(DW)

#BREAKING
ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ትዕዛዛ የተሰጣቸው ፦
1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል
3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው።
#PMOEthiopia

በመቐለ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ያለው።
ባንኮች፣ መስሪያ ቤቶች እና ቴሌ ግን ዝግ ሆነው ነው የዋሉት።
የነዋሪዎች መደበኛ ህይወት እንደወትሮው ሁሉ ሰላም ነው።
PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ባንኮች፣ መስሪያ ቤቶች እና ቴሌ ግን ዝግ ሆነው ነው የዋሉት።
የነዋሪዎች መደበኛ ህይወት እንደወትሮው ሁሉ ሰላም ነው።
PHOTO : ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
መቐለ አሁን ያለችበት ሁኔት ከቢቢሲ ጋዜጠኛ ፦
"ትላንት ማክሰኞ እኩለ ለሊት ገደማ መቐለ ከተማ ተኩስ ይሰማ ነበር።
የከተማው ሰው እየሆነ ባለው ነገር ተደናግጦ ነበር። ይሄኔ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ፀጥታ ኃይል ሰዎች ስደውል 'አሁን ልናናግርህ አንችልም፤ቢዚ ነን' አሉኝ።
ከደቂቃ በኋላ የስልክ መስመር ተቋረጠ። ስልኬ 'ኖ ሰርቪስ' የሚል ምልክት ያሳየኝ ጀመር።
በመቀጠል የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ።
ጥዋት ስንነሳ ከተማዋ የኤሌክትሪክ አገልግሎቷ እንደተቋረጠ ተረዳሁ።
መብራት የጠፋው መቐለ ብቻ ሳይሆን ትግራይ ክልል ሙሉ እንደሆነ ማረጋገጥ ችያለሁ።
ወደ ከተማ ወጣ ስል የሰዎች ፊት ላይ ግራ መጋባት ተመለከትኩ። አብዛኛው ሰው በእግሩ ነበር ሲንቀሳቀስ የነበረው።
ከተማዋ ላይ ያሉ የባንክ ቅርንጫፎች ተዘግተው ነበር።
ሁለት የባንክ አስተዳዳሪዎች እንደነገሩኝ አገልግሎት ያቋረጡ የበይነ መረብ [ኢንተርኔት]አገልግሎት ስለሌለ ነው።
ረፋድ ላይ የኢትዮቴሌኮም ሠራተኞች መስሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ሰብሰብ ብለው ቆመው ነበር።
ከረፋፈደ በኋላ ከፀጥታ ኃይል ሰዎች እንደተረዳሁት ተኩሱ የተሰማው የትግራይ ክልል ወታደሮች ከሰሜን ዕዝ ጋር በነበራቸው የተኩስ ልውውጥ መሆኑን ተረድቻለሁ።
ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮና ወደ ሌሎች የጉዞ ወኪሎች አምርቼ ለጊዜው በረራ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን መረዳት ችያለሁ።
መቀሌ ከተማ ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ሆቴሎች አካባቢ ከበድ ያለ የፀጥታ ኃይል ይታያል።
የክልሉ መንግሥት ክልሉ ውስጥ ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር አግዷል።
የትራንስፖርት አገልግሎትም ሙሉ በሙሉ ቆሟል። የክልሉ አየር ክልልም ከበረራ ውጭ እንዲሆን ታዟል።
መቐለ አሁን ላይ ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።"
@tikvahethiopia