TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መረጃ በጉሊሶ ወረዳው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ 2 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በአጠቃላይ በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 34 ደርሷል ብሏል።

12 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተገልጿል።

ከ50 እስከ 60 የሚደርሱ ቤቶች መቃጠላቸው፤ እና አንድ ት/ቤት መቃጠሉ ተገልጿል።

ጄኔራል አራርሳ ፥ “በዜጎች ላይ ጥቃቱን ያደረሰው አካል ኦነግ ሸኔ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ከጀርባ ህወሃት መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝተዋል" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፦

በጥቅምት 22/2013 ጉጂ ዞን ጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ መሸጋገሪያ ድልድይ እየሰሩ በነበሩ ሰዎች ላይ "የኦነግ ሸኔ" አባላት በፈፀሙት ጥቃት 4 ሰዎች ሞተዋል ፣ በ3ቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ አስታውቀዋል፡፡

በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል የተባሉ አስራ አንድ (11) "የኦነግ ሸኔ" አባላት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የጉጂ ዞን የፀጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወልዴ ዱጎ ለOBN ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ህክምና እንዲያገኙ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህንን ተከትሎ አቶ ልደቱ ነገ ህክምና እንደሚያገኙ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለBBC አማርኛ ክፍል ተናግረዋል። አቶ አዳነ ስለ አቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ ተከታዩን ብለዋል ፦ "በእውነት ምንም ሳልደብቅ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የህመም ስሜት ይታይባቸዋል። ሰውነታቸው ትንሽም…
አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋል።

የኢዴፓ ፕሬዜዳንት አቶ አዳነ ፥ "አጠቃላይ በወሰዱት የጤና ምርመራ አንዳንድ የመዳህኒት ማስተካከያዎች ተደርጎላቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልፆልናል" ብለዋል።

በአሁን ሰዓት ለህይወታቸው ያሰጋቸዋል ተብሎ በሚታሰበው "ከልባቸው ጋር ተያይዞ ባለባቸው ህመም" የተለየ ህክምና ስለሚያስፈልጋቸው ሃኪም በተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ተመልሰው እንዲመጡ አሳውቋቸዋል።

Via Ato Adane Tadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,364
• በበሽታው የተያዙ - 560
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 849

በአጠቃላይ በሀገራችን 97,502 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,494 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 55,254 ከበሽታው አገግመዋል።

346 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህ የ25 MB ቪድዮ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።

ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ሊያደርግ የተሰበሰበው ፓርላማ በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት ዙሪያ ረጅም ሰዓት ወስዶ ተነጋግሯል።

አባላት በእንባ የታጀበ ከፍተኛ ቁጣቸውንም ገልፀዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚው አካል ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥና ቀጣይ እርምጃውን እንዲያሳውቅ ምክር ቤቱ ወስኗል።

ቪድዮውን ለማውረድ WiFi ተጠቀሙ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የህ/ተ/ም/ቤት አባሉ ጥያቄ !

"አንድ ሰራዊት ከአንድ ቦታ ሲነሳ በፊት ስጋት አለበት ተብሎ ያ ስጋት የለም ተብሎ የሚኒሳ ከሆነ በአካባቢው የሚገኝ ታጣቂ ያንን ቦታ እንዲቆጣጠረው የመረካከብ ስነ ስርዓት መደረግ ነበረበት።

ይሄ ሳይደረግ መቅረቱ ለምንድ ነው ? የሚለውን መከላከያ ሰራዊትም አጠቃላይ መንግስት ይህን ጉዳይ ለምን እንደዚህ አይነት ክፍተት ሊከሰት ቻለ የሚለውን ተገምግሞ ለምክር ቤቱ ሊቀርብለት ይገባል።" - አቶ ተስፋዬ ዳባ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ፦

"ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው።

ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ። የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታት እና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል።

ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።

የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።

ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል ፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝ እና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
4 ኪሎ ቤተ መንግስት ስር ባለው "አዋሬ ገበያ" የእሳት አደጋ ተነስቷል።

አደጋው ሁለት ሰዓት እንዳለፈው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።

በርካታ ንብረትም እንደወደመ ገልፀዋል።

ከኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተገኘው መረጃ በቦታው ከ2 ያልበለጡ የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ደርሠው የነበረ ቢሆንም አንዱ መኪና በቂ ውሀ አልያዝኩም ብሎ ተመልሶ ነበር፤ በዚህም በቦታው ካሉት ወጣቶች ጋር መጠነኛ አላግባባት እንዲፈጠር አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት ከ4-5 የሚደርሱ መኪኖች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየጣሩ እንደሚገኙ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በetv እየሰጡ በሚገኙት መግለጫ ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ጥቃት እንደተፈፀመበት አስታውቀዋል።

ጥቃቱን የፈፅሙት "ካሃዲ ኃይሎች እና ያደራጁት ኃይል" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ "ጥቃቱ በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በተለያየ ሀገር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት እንኳን በውጭ ኃይሎች ያልደረሰበት ጥቃት በገዛ ወገኖቹ ከጀርባው እንዲመታ ተደርጓል" ብለዋል።

በተፈፀመው ጥቃት ብዙዎች የሰራዊቱ አባላት ተሰውተዋል ፤ ቆስለዋል ፤ ንብረቶች እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል መቐለ እና ሌሎች አባባቢዎች ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በአማራ ክልል በዳንሻ በኩል ጥቃት ተፈጽሟል ፤ በአማራ ክልል የነበረው ኃይል ጥቃቱን መክቷል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Internet

ለሊት ጠ/ሚር ዶክተር አብይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ከገለፁ በኃላ በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።

የስልክ ጥሪም እየወጣ አይደለም።

TIKVAH-ETH በትግራይ ክልል ስላሉ አባላቱ ያሉበት ሁኔታ እየተከታተለ ለመግለፅ ጥረት ያደርጋል።

PIC : NetBlocks
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፦

ከ50 የአሜሪካ ግዛቶች በ31 ግዛቶች የትኛው እጩ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተገምቷል።

በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 192 ለ 114 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።

ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ጆ ባይደን - 209
ዶናልድ ትራምፕ - 118

ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ችግር የሆኑ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ስትመለከቱ ከላይ በተዘረዘሩት ስልኮች በፍጥነት ደውሉ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

@TIKVAHETHIOPIA
#UPDATE

ጆ ባይደን - 223
ዶናልድ ትራምፕ - 212

ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#በጣም_አስቸኳይ

ጥሪ የተደረገላችሁ የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር ለደህንነታችሁ ሲባል ባላችሁበት እንድትቆዩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ወደፊት የመግቢያ ቀናችሁ በሚወጣ ተለዋጭ ማስታወቂያ ይገለፃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

እስካሁን የ40 ግዛቶች ውጤት ታውቋል።

በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 225 ለ 213 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።

ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TigrayTikvahFamily

በትግራይ ክልል የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ እስካሁን ከትግራይ ቲክቫህ አባላቶቻችን ጋር መገናኘት አልቻልንም።

ልጆቻቸውን ዩኒቨርሲቲ የላኩ ወላጆች ስለልጆቻቸው አሁናዊ ሁኔታ ማወቅ ባለመቻላቸው መጨነቃቸውን እየገለፁልን ነው።

በተጨማሪ ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል የሚኖሩ አባላት ተጨንቀው በርካታ መልዕክቶችን እያስቀመጡ ይገኛሉ።

በትግራይ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ስላሉ ተማሪዎች ጉዳይ በቻልነው አቅም አጣርተን ለማሳወቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለጊዜው ወደ ግቢ እንዳይመጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

አገሪቱ በገጠማት ወቅታዊ የሆነ የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው ተማሪዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ መልዕክት እየተላለፈ የሚገኘው።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ሲሆኑ ጥሪዎችን በጊዜያዊነት የሚቆሙበትን ውሳኔ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። (አሐዱ ቴሌቪዥን)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሟል።

ግብረኃይሉ ተጠሪነቱ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን ‘‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሀይል’’ ተብሎ እንደሚጠራ ተገልጿል።

አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸው ተጨማሪ አካባቢዎችን ግብረኃይሉ በሚያወጣው በመመሪያ ይወስናል።

አዋጁን አስመልክቶ ዝርዝር መርጃ በየጊዜው ለህብረተሰቡ የሚሰጡ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ለዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች

ከኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት ፦

በሀገሪቱ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መግታት አስፈልጓል፡፡ በዚሁ መሰረት :-

1. እስካሁን ዩኒቨርሲቲወቻችሁ ላይ የደረሳችሁ ተማሪዎች በግቢያችሁ እንድትቆዩ እና በየግቢያችሁ የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ ፤ አካባቢያችሁ ያለ የትኛውም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ሃላፊዎች እንድታሳውቁ ፤

2. እስካሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ከወላጆቻችሁ ጋር እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትናንት ምሽት ጀምሮ የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት እንዲሁም በማክሸፍ የህዝቦችን ደህንነት እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ገለፀ።

የመከላከያ ሰራዊት ፥ "እየፈፀመን ያለውን ስኬታማ ተግባር በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር በትብብር እየሰራን ነው" ሲል አሳውቋል።

ምንጭ፦ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር (ENA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia