TIKVAH-ETHIOPIA
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አዲስ አበባ ገቡ። የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ገልጿል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለ2 ቀን ያደረጉትን ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።
ዛሬ ጠዋት ወደ ካርቱም ተመልሰዋል።
ሌ/ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፣ የግብርና የኢንቨስትመንት ስራዎችን መጎብኘታቸው ኤፍ ቢ ሲ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል" - አውሮፓ ህብረት
የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው #BBC ዘግቧል።
የሕብረቱ ምክትል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ባወጡት መግለጫ ነው የሕብረቱን አቋም ያንፀባረቁት።
"ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው" ያለው መግለጫው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች እና ጎረቤት አገራት ውጥረት ለመቀነስ መጣር እንዳለባቸው አሳስቧል።
ሁሉም ቡድኖች "ግጭት ቀስቃሽ ቃላት" መጠቀም ማቆም እንዳለባቸውና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን መግታት እንዳለባቸው አሳስቧል። "ይህ መሆን ካልቻለ ግን ጉዳቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውም ነው" ብሏል።
መግለጫው ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር አገር አቀፍ ውይይቶች እንደሚያስፈልጉ አትቷል። በዚህ ውይይት ላይ ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
ለኢትዮጵያ ሕዝብ መፃዒ ተስፋና ብልፅግና ብሔራዊ መግባባት እንጂ ግጭት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ምክትል ፕሬዝደንቱ በመግለጫቸው ገለፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጉሊሶ ወረዳ የተፈፀመውን ጥቃት አውግዟል።
ድርጅቱ መንግሥት ለዜጎች ጥበቃ እንዲያደርግ እና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቋል።
አምነስቲ የሰብዓዊ ጉዳይ ተመልካቾችን እና የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ብሔር ተኮር በሆነዉ በጉሊሶዉ ግድያ ቢያንስ 54 ሰዎች ሕይወታቸዉን አጥተዋል ብሏል።
ባለፈዉ እሁድ አካባቢዉ ላይ የነበረዉ የመንግሥት መከላከያ ሰራዊት ለቆ ከወጣ በኃላ አምነስቲ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ሲል የገለፀዉ ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን በንፁሐን ላይ መፈፀሙን የዓይን እማኞችን ገልጾ አስቀምጦአል።
በጥቃቱ ሕጻናት ሴቶች፤ እና አባወራዎች ተገድለዋል፤ መኖርያ ሕንጻዎች መገልገያ ቁሳቁሶች መቃጠላቸውን ገልጿል።
Via Amnesty International (DW)

#MoussaFaki
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሓመት በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ አውግዘዋል።
ሊቀ መንበሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች ሀዘናቸው ገልፀው የቆሰሉትም ፈጥነው እንዲያገግሙ ተመኝተዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹን መንግስት ተከታትሎ ተጠያቂ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ሊቀመንበሩ ሁሉም ወገኖች ግጭቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።
በተጨማሪ ሁሉን አካታች የሆነ ብሄራዊ ንግግር በፖለቲከኞች መካከል በማካሄድ ቁልፍ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ ስምምነት መድረስ ይገባል ብለዋል።
ይህ ካልሆነ ችግሩ በኢትዮጵያ ሳይወሰን ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ በቀጠናው ላይ ያስከትላል ሲሉ አሳስበዋል።
Via Moussa Faki (Addis Maleda)

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መረጃ በጉሊሶ ወረዳው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ 2 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን ገልጿል።
ኮሚሽኑ በአጠቃላይ በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 34 ደርሷል ብሏል።
12 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተገልጿል።
ከ50 እስከ 60 የሚደርሱ ቤቶች መቃጠላቸው፤ እና አንድ ት/ቤት መቃጠሉ ተገልጿል።
ጄኔራል አራርሳ ፥ “በዜጎች ላይ ጥቃቱን ያደረሰው አካል ኦነግ ሸኔ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ከጀርባ ህወሃት መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝተዋል" ብለዋል።
በሌላ በኩል ፦
በጥቅምት 22/2013 ጉጂ ዞን ጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ መሸጋገሪያ ድልድይ እየሰሩ በነበሩ ሰዎች ላይ "የኦነግ ሸኔ" አባላት በፈፀሙት ጥቃት 4 ሰዎች ሞተዋል ፣ በ3ቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ አስታውቀዋል፡፡
በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል የተባሉ አስራ አንድ (11) "የኦነግ ሸኔ" አባላት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የጉጂ ዞን የፀጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወልዴ ዱጎ ለOBN ገልፀዋል።

#UPDATE ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ህክምና እንዲያገኙ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህንን ተከትሎ አቶ ልደቱ ነገ ህክምና እንደሚያገኙ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለBBC አማርኛ ክፍል ተናግረዋል። አቶ አዳነ ስለ አቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ ተከታዩን ብለዋል ፦ "በእውነት ምንም ሳልደብቅ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የህመም ስሜት ይታይባቸዋል። ሰውነታቸው ትንሽም…
አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋል።
የኢዴፓ ፕሬዜዳንት አቶ አዳነ ፥ "አጠቃላይ በወሰዱት የጤና ምርመራ አንዳንድ የመዳህኒት ማስተካከያዎች ተደርጎላቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልፆልናል" ብለዋል።
በአሁን ሰዓት ለህይወታቸው ያሰጋቸዋል ተብሎ በሚታሰበው "ከልባቸው ጋር ተያይዞ ባለባቸው ህመም" የተለየ ህክምና ስለሚያስፈልጋቸው ሃኪም በተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ተመልሰው እንዲመጡ አሳውቋቸዋል።
Via Ato Adane Tadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢዴፓ ፕሬዜዳንት አቶ አዳነ ፥ "አጠቃላይ በወሰዱት የጤና ምርመራ አንዳንድ የመዳህኒት ማስተካከያዎች ተደርጎላቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልፆልናል" ብለዋል።
በአሁን ሰዓት ለህይወታቸው ያሰጋቸዋል ተብሎ በሚታሰበው "ከልባቸው ጋር ተያይዞ ባለባቸው ህመም" የተለየ ህክምና ስለሚያስፈልጋቸው ሃኪም በተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ተመልሰው እንዲመጡ አሳውቋቸዋል።
Via Ato Adane Tadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,364
• በበሽታው የተያዙ - 560
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 849
በአጠቃላይ በሀገራችን 97,502 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,494 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 55,254 ከበሽታው አገግመዋል።
346 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህ የ25 MB ቪድዮ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።
ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ሊያደርግ የተሰበሰበው ፓርላማ በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት ዙሪያ ረጅም ሰዓት ወስዶ ተነጋግሯል።
አባላት በእንባ የታጀበ ከፍተኛ ቁጣቸውንም ገልፀዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው አካል ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥና ቀጣይ እርምጃውን እንዲያሳውቅ ምክር ቤቱ ወስኗል።
ቪድዮውን ለማውረድ WiFi ተጠቀሙ።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ሊያደርግ የተሰበሰበው ፓርላማ በጉሊሶ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት ዙሪያ ረጅም ሰዓት ወስዶ ተነጋግሯል።
አባላት በእንባ የታጀበ ከፍተኛ ቁጣቸውንም ገልፀዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው አካል ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥና ቀጣይ እርምጃውን እንዲያሳውቅ ምክር ቤቱ ወስኗል።
ቪድዮውን ለማውረድ WiFi ተጠቀሙ።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የህ/ተ/ም/ቤት አባሉ ጥያቄ !
"አንድ ሰራዊት ከአንድ ቦታ ሲነሳ በፊት ስጋት አለበት ተብሎ ያ ስጋት የለም ተብሎ የሚኒሳ ከሆነ በአካባቢው የሚገኝ ታጣቂ ያንን ቦታ እንዲቆጣጠረው የመረካከብ ስነ ስርዓት መደረግ ነበረበት።
ይሄ ሳይደረግ መቅረቱ ለምንድ ነው ? የሚለውን መከላከያ ሰራዊትም አጠቃላይ መንግስት ይህን ጉዳይ ለምን እንደዚህ አይነት ክፍተት ሊከሰት ቻለ የሚለውን ተገምግሞ ለምክር ቤቱ ሊቀርብለት ይገባል።" - አቶ ተስፋዬ ዳባ

#ሰበር_ዜና
ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ፦
"ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው።
ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ። የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታት እና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል።
ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።
የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።
ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል ፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝ እና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።"

4 ኪሎ ቤተ መንግስት ስር ባለው "አዋሬ ገበያ" የእሳት አደጋ ተነስቷል።
አደጋው ሁለት ሰዓት እንዳለፈው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
በርካታ ንብረትም እንደወደመ ገልፀዋል።
ከኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተገኘው መረጃ በቦታው ከ2 ያልበለጡ የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ደርሠው የነበረ ቢሆንም አንዱ መኪና በቂ ውሀ አልያዝኩም ብሎ ተመልሶ ነበር፤ በዚህም በቦታው ካሉት ወጣቶች ጋር መጠነኛ አላግባባት እንዲፈጠር አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት ከ4-5 የሚደርሱ መኪኖች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየጣሩ እንደሚገኙ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አደጋው ሁለት ሰዓት እንዳለፈው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
በርካታ ንብረትም እንደወደመ ገልፀዋል።
ከኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተገኘው መረጃ በቦታው ከ2 ያልበለጡ የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ደርሠው የነበረ ቢሆንም አንዱ መኪና በቂ ውሀ አልያዝኩም ብሎ ተመልሶ ነበር፤ በዚህም በቦታው ካሉት ወጣቶች ጋር መጠነኛ አላግባባት እንዲፈጠር አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት ከ4-5 የሚደርሱ መኪኖች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየጣሩ እንደሚገኙ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በetv እየሰጡ በሚገኙት መግለጫ ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ጥቃት እንደተፈፀመበት አስታውቀዋል።
ጥቃቱን የፈፅሙት "ካሃዲ ኃይሎች እና ያደራጁት ኃይል" ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ "ጥቃቱ በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በተለያየ ሀገር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት እንኳን በውጭ ኃይሎች ያልደረሰበት ጥቃት በገዛ ወገኖቹ ከጀርባው እንዲመታ ተደርጓል" ብለዋል።
በተፈፀመው ጥቃት ብዙዎች የሰራዊቱ አባላት ተሰውተዋል ፤ ቆስለዋል ፤ ንብረቶች እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።
በትግራይ ክልል መቐለ እና ሌሎች አባባቢዎች ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በአማራ ክልል በዳንሻ በኩል ጥቃት ተፈጽሟል ፤ በአማራ ክልል የነበረው ኃይል ጥቃቱን መክቷል ብለዋል።

4 ኪሎ ቤተ መንግስት ስር ባለው "አዋሬ ገበያ" የእሳት አደጋ ተነስቷል። አደጋው ሁለት ሰዓት እንዳለፈው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል። በርካታ ንብረትም እንደወደመ ገልፀዋል። ከኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተገኘው መረጃ በቦታው ከ2 ያልበለጡ የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ደርሠው የነበረ ቢሆንም አንዱ መኪና በቂ ውሀ አልያዝኩም ብሎ ተመልሶ ነበር፤ በዚህም በቦታው ካሉት ወጣቶች ጋር መጠነኛ አላግባባት እንዲፈጠር አድርጓል።…
4 ኪሎ አዋሬ የተነሳውን እሳት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
ፖሊስ እና መከላከያ ህዝቡን እያረጋጉ ይገኛል።
በሌላ በኩል ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የደረሰው ጉዳት መጠንና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል።
PHOTO : Haileab (Tikvah Family)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ፖሊስ እና መከላከያ ህዝቡን እያረጋጉ ይገኛል።
በሌላ በኩል ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው የደረሰው ጉዳት መጠንና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል።
PHOTO : Haileab (Tikvah Family)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Internet
ለሊት ጠ/ሚር ዶክተር አብይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ከገለፁ በኃላ በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።
የስልክ ጥሪም እየወጣ አይደለም።
TIKVAH-ETH በትግራይ ክልል ስላሉ አባላቱ ያሉበት ሁኔታ እየተከታተለ ለመግለፅ ጥረት ያደርጋል።
PIC : NetBlocks
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሊት ጠ/ሚር ዶክተር አብይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ከገለፁ በኃላ በትግራይ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።
የስልክ ጥሪም እየወጣ አይደለም።
TIKVAH-ETH በትግራይ ክልል ስላሉ አባላቱ ያሉበት ሁኔታ እየተከታተለ ለመግለፅ ጥረት ያደርጋል።
PIC : NetBlocks
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፦
ከ50 የአሜሪካ ግዛቶች በ31 ግዛቶች የትኛው እጩ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተገምቷል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 192 ለ 114 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከ50 የአሜሪካ ግዛቶች በ31 ግዛቶች የትኛው እጩ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተገምቷል።
በዚህም መሠረት ከተሰጠው ድምጽ ጆ ባይደን 192 ለ 114 ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ሆኖ ለመመረጥ 270 ድምጽ ያስፈልጋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀጥታ ችግር የሆኑ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ስትመለከቱ ከላይ በተዘረዘሩት ስልኮች በፍጥነት ደውሉ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
@TIKVAHETHIOPIA
@TIKVAHETHIOPIA