TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ትላንት ህይወታቸው ያለፈው የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ሥነ ስርዓት ሀሙስ በቢሾፍቱ እንደሚፈፀም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ሰኔ 16/2010 ለጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት ያጠፉ አምስት (5) ግለሰቦች በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ከ5 እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን etv ዘግቧል። @tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
ሰኔ 16/2010 ዓ/ም በዶከተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተከሰሱ 5 ተጠርጣሪዎች ተፈርዶባቸዋል ፦

• 1ኛ ተከሳሽ (ጌቱ ግርማ) 23 አመት ጽኑ እስራት፣
• 2ኛ ተከሳሽ (ብርሃኑ ጁፋር) 22 አመት ጽኑ እስራት፣
• 3ኛ ተከሳሽ (ጥላሁን ጌታቸው) የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣
• 4ኛ ተከሳሽ (ባህሩ ቶላ) 17 አመት ጽኑ እስራት፣
• 5ኛ ተከሳሽ (ደሳለኝ ተስፋዬ) 5 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ለነገ የተጠራው ሰልፍና የመንግስት ምላሽ !

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ እና ጥቃት ለመቃወም ነገ ጥቅምት 18 በአማራ ክልል ከተሞች እና ጥቅምት 22 በአ/አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል።

ፓርቲው ስለጠራው ሰልፍ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቀኑ 8:00 ላይ በዋና ጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በሌላ በኩል ፦

በትላንትናው ዕለት የአማራ ክልል መንግስት በአማራ ክልል የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አይደለም፤ ወቅቱንም ያላገናዘበ ነው ብሎታል።

ሰልፉ ህጋዊ ባለመሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች መደበኛ የእለት ከእለት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪውን አቅርቧል።

ይህንን ተላልፎ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ ግን የጸጥታ አካላት ፤ ፓሊስና ሚሊሻ ስርዓት እንዲያስይዙ የክልሉ መንግስት ትዕዛዝ መስጠቱን ገልጿል።

የአማራ ክልራ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ፥ "የገጠመን ችግር ሰልፍ በማድረግ ብቻ የምንፈታው አይደለም ፤ በሰልፍ ለውጥ የሚመጣ ቢሆን የክልሉ መንግሥት ፊት ሁኖ ይመራው ነበር" ብለዋል።

የተጠራውን ሰልፍ በራሳቸው መንገድ ለመጠቀምና አማራ ክልልን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ እየሠሩ የሚገኙ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች አሉ የክልሉ መንግሥትም ተጨባጭ መረጃ ደርሶታል ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪ ከክልሉ ውጭ የሚኖረው አማራ ደኅንነቱ የሚጠበቀው በበሰለ የፖለቲካ ውይይት እና ድርድር እንዲሁም ህገወጦችን በአንድነት ሁኖ በመታገል ለዘላቂ መፍትሔ በመስራት ነው እንጂ በሰልፍ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

እንዲህ አይነት ሁኔታ በዘፈቀደ የሚጠራ ሰልፍ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ዜጎችን ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርግ ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ሊሆን የሚችል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

*የከሰዓቱን የአብንን መግለጫ ተከታትል እናሳውቃለን!

@tikvahethiopiaBOT
#UPDATE

በጉራፈርዳ ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ 7 ከዞን እስከ ቀበሌ መዋቅር ያሉ አመራሮችን እና 2 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 54 ሠዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንች ሸኮ ዞን አሳውቋል።

ድጋፍን በሚመለከት ፦

በወረዳው በተፈፀመው ጥቃት ለተፈናቀሉት 5 ሺህ 4 መቶ 33 ወገኖች የሚዛን አማን የንግዱ ማኅበረሠብ በአይነት እና በገንዘብ ድጋፍ እያሰባሰበ ነው።

የቢፍቱ ከተማ ማኅበረሰብ ለተፈናቀሉ ዜጎች በተደራጀ ሁኔታ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

የዞንና የወረዳው መንግስት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ አስፈላጊው ሠብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ዞኑ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት ምን ያስፈልገኛል ?

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት አመልካቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ይህን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሰነዶች ማዘጋጀት ፦

• ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ
• የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት/ማስረጃ

2. የሚያመለክቱት ለአስቸኳይ አገልግሎቶች ከሆነ ከሚከተሉት መካከል ቢያንስ አንዱ ሊኖርዎት ይገባል ፦

• የሕክምና ደብዳቤ
• የትምህርት እድል እና ዲቪ
• ከተፈቀደለት ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ
• የውጭ ሀገር የነዋሪነት ፍቃድ
• የግብዣ ደብዳቤ
• አስቸኳይ የስራ ጉዞ
• በሀዘን/ጋብቻ ምክንያት የሚደረግ ጉዞ

3. ለአዲስ ፓስፖርት የሚከፈለውን ክፍያ ያረጋግጡ ፦

• ለ32 ገጽ ፓስፖርት - 600
• ለ64 ገጽ ፓስፖርት - 2186 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍላችሁ online አድራሻ ላይ አባሪ ያደርጉታል።

ኦንላይ ላይ "ለአዲስ ፖስፖርት" አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎት ለማግኘት ይህን ሊንክ ተጠቁሙ👇
www.ethiopianpassportservices.gov.et

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
ለነገ የተጠራው ሰልፍና የመንግስት ምላሽ ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ እና ጥቃት ለመቃወም ነገ ጥቅምት 18 በአማራ ክልል ከተሞች እና ጥቅምት 22 በአ/አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል። ፓርቲው ስለጠራው ሰልፍ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቀኑ 8:00 ላይ በዋና ጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በሌላ በኩል ፦ በትላንትናው ዕለት የአማራ…
#UPDATE

አብን ጥቅምት 18 በአማራ ክልል እና ጥቅምት 22/2013 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፎችን መጥራቱ ይታወቃል ፤ ዛሬ 8:00 መግለጫ እንደሚሰጥም ተገልጾ ነበር።

ፓርቲድ ከፍተኛ አመራሮቹ ስለሰልፉ ዝርዝር ሁኔታዎች በዋና ጽ/ቤት ውስጥ እየመከሩ ባሉበት ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበባ መፈፀሙን እና መግባትና መውጣት አትችሉም መባሉን ገልጿል።

አብን፥ የታቀደው ሰልፍ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራትና ለሰልፉ የተዘጋጁ ሎጂስቲኮችን ለማንቀሳቀስም ሆነ ሰልፉን ለመምራት ስራ አስፈፃሚው ወደ ክፍለ ሀገር እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩን ገልጿል።

በዚህ ምክንያትም አብን የጠራውን ሰልፍ በኃላፊነት መምራት የማይችል መሆኑን ለድርጅቱ አባላት ፣ ደጋፊዎች እና ለህዝቡ አሳውቋል።

አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፥ "መንግስት አማራ ማዘን እንኳን አይችልም በሚል እርቃን የወጣ አምባገነንነት ውስጥ በመግባቱ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው የትግል አካሄዶች በተመለከተ እናሳውቃለን" ብሏል።

* የአማራ ክልል መንግስት ለነገ የተጠራው ሰልፍ ህጋዊነት እንደሌለው እንዲሁም ወቅቱን ያላገናዘበ እንደሆነ ትላንት መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ! የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው እንደታገዱ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቶቹ የታገዱት የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው…
#UPDATE

ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ባለመከተልና ወላጆች ባቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ ትምህርት ቤቶች ላይ እገዳ ጥሎ እደነበር ይታወሳል።

ዛሬ እገዳ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የግሪክ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እገዳው እንደተነሳለት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ቤቱ እገዳው የተነሳለት በትምህርት ሚኒስቴር (MoE) በተቋቋመው ቡድን በተደረገ የሱፐርቪዝን ስራ ትምህርት ቤቱ አስፈላጊው መስተካከያ ማድረጉ እንዲሁም ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁ በመረጋገጡ ነው ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራውን ማከናውን ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በCOVID-19 ቫይረስ ወረርሺን ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ት/ት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ ውይይት ማካሄዱን ገልጾልናል።

በዩኒቨርሲቲው ባሉ ሁሉም ኮሌጆች የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠልን በተመለከተ ፦

• ከመግበያ በሮች ጀምሮ በማደሪያ ክፍሎች፤
• በቤተመፃህፍት፤
• ቤተ ሙከራዎች እንዲሁም በካፍቴሪያዎች የተዘጋጀውን የCOVID19 መመሪያ በመከተል አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት የማድረግ ስራው በአብዛኛው ተጠናቋል።

በቀሩት ጥቂት ቀናት ደግሞ የተቀሩትን የዝግጅት ስራዎች በማጠናቀቅ ተማሪዎችን በታቀደው መርሀግብር መቀበል እንደሚቻል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ተጨማሪ ፦

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምዝገባቸውን በ Online እንደሚያደርጉና ምንም አይነት የገጽ ለገጽ ምዝገባ እንደማይኖር ዩኒቨርሲቲው በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

የተማሪ መታወቂያ እድሳትን በተመለከ በትምህርት ክፍሎች በሚወጣው መርሀግብር መሠረት ብቻ የሚፈጸም ይሆናል ተብሏል።

የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ተማሪዎች መመሪያውን ካልተገበሩት ዝግጅቱ ፋይዳ የለውም፤ ተማሪዎች የሚናፍቁትን የምርቃት ቀን ለማየት እንዲሁም ሌሎችን ለመጠበቅ ፤ መመሪያዎችን በጥብቅ ዲስፒልን እንዲፈፅሙ ከአደራ ጭምር ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ያለውን ዝርዝር መረጃ በቅርብ ቀን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሀመድ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ከተናገሩት ፦

"መኖሪያ ቤቴ ውስጥ ከ100ሺህ ብር በላይ ፣ ወርቅ ፣ የእጅ ሰዓት እና በሽልማት ያገኘኋቸው የተለያዩ ሜዳሊያዎች ፖሊስ ወስዶ የራሱ ንብረት አድርጎታል። ለምንድነው የምዘረፈው ?

ከእኔ ጋር ለአንድ ቀን ሻይ የጠጡ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል ፤ አሁን ስልጣን ላይ ካሉ ባለስልጣናት ጋር ግን አብሮ ሻይ መጠጣት ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ነገር አብሬያቸሁ ሰርቻለሁ። እግዱ እውነተኛ ከሆነ ለምን የእነሱ የባንክ ሂሳብ አልታገደም?"

አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የተናገሩት ፦

"እኔ ለ37 ዓመታት ያህል የመንግሥት ሰራተኛ ሆኜ የሰራሁ ሰው ነኝ። ይህን ያክል ዓመት የሰራ ሰው እንዴት አሮጌ መኪና ይኖረዋል ማለት ትክክል አይደለም።

ወደ አዳማ እና ነቀምቴ በሄድኩ ጊዜም ሕዝቡ ምን ዓይነት አቀባበል እንዳደረገልኝ ታውቃላችሁ። ወደ ውጪ በሄድኩ ጊዜም መኪና ተሸልሜ ነበር። ይህችን አሮጌ መኪና ንብረት አፈራ ተብሎ ማገዱ ትክክል አይደለም"

ተጨማሪ : https://telegra.ph/BBC-10-27 (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዳሸን ባንክ ለተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 3 ሚሊየን ብር አበርክቷል!

"ዳሽን ባንክ" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥሪ ተከትሎ በከተማው የሚገኙ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል፡፡

ባንኩ ባለፈው አመት ለዚሁ መርሃ ግብር 1 ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር ማበርከቱ ይታወሳል፡፡

ባለፈው በጀት አመት በአጠቃላይ 170 ሚሊየን ብር ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች አውሏል።

Via Ermiyas (Tikvah Family)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ መልዕክት👆

ሀሙስ 1 ሺህ 495ኛው መውሊድ በዓል ይከበራል።

ይህን በማስመልከት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MesfinIndustrialEngineering

በትግራይ ክልል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ተገልጿል።

"መስፍን ኢንድስትሪያል ኢንጂነሪንግ" 20 ሜትር ወደላይ ኬሚካል መርጨት የሚችሉ 6 ማሽኖችን ሰርቶ አቅርቧል።

ማሽኖቹ በሰው ጉልበት የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ እስካሁን ድረስ በተደረገው ሙከራ ውጤታማነታቸው ተረጋጧል ተብሏል።

አሁንም በትግራይ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአርሶ አደሩ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሁሉም ትግራዋይ ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,884
• በበሽታው የተያዙ - 511
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 818

በአጠቃላይ በሀገራችን 94,218 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,445 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 48,968 ከበሽታው አገግመዋል።

314 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በቬርቿል ተጀምሯል።

የዛሬው ስብሰባ ሊጀመር የቻለው በደ/አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጥቅምት 11 ቀን 2013 ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነው።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቨርቷል ስብሰባ ከቀኑ10 ስዓት ላይ ተጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ጉዳይ ዙሪያ የሚመክር ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በሩስያ !

ሩስያ ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ፤ የቫይረሱ ስርጭትም እየተባባሰ ነው።

ዛሬ ብቻ ሦስት መቶ ሃያ (320) ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሞተዋል።

ወረርሽኙ ሃገሪቱ ውስጥ ከገባ ወዲህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቁ ቁጥር መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት 16,550 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ፦

- ሰው በሚበዛባቸው ስፍራዎች ፣
- በህዝብ ማጓጓዣዎች፣
- በታክሲዎች እንዲሁም በፎቅ መውጫ ኤሌቪተሮች ውስጥ በጭንብል ፊትን መሸፈን ግዴታ መሆኑ ታውጇል።

ከዚህም ሌላ ምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ከማታው አምስት እስከ ንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት እንዲዘጉ ታዟል። (VOA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በቬርቿል ተጀምሯል። የዛሬው ስብሰባ ሊጀመር የቻለው በደ/አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጥቅምት 11 ቀን 2013 ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነው። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ፣…
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ !

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መሰኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጋራ ፕሬስ መግለጫ)

የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ቀደም ብሎ በጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ/ም ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ እና ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት ጥቅምት 17 በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂዷል፡፡

ስብሰባው አፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሯል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ክቡር ሲይርል ራማፎዛ ቀደም ብሎ በጥቅምት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች ጋር በስልክ ባደረጓቸው ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ድርድሩን ለመቀጠል #ስምምነት ተደርሷል።

ሀገራቱ በሰባት (7) ቀናት ውስጥ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ የድርድሩ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ስምምነት መድረስ፣ ሀገራቱ ላይ ልዩነት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነቶችን ለማጥበብ እና ውጤቱንም ለውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀጣይ ስብሰባ ለማቅረብ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

የመጀመሪያው የቴክኒክ ስብሰባ በሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትር ሰብሳቢነት እደሚከናወን ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia