TIKVAH-ETHIOPIA
በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከሰኞው የቀጠለ ጥቃት ተፈፅሞ ሰዎች መገደላቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። ከሁለት ቤት ውስጥ ብቻ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል አባላቶቻችን። ዛሬ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ለእርዳታ ከመጡ 12 ሰዎች መካከል 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት መሆናቸውን የቲክቫህ አባል የሆነ ሀኪም ገልጿል። መልዕክታቸውን…
#UPDATE
በ2 ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አልፏል !
በጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 5 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
1 ሺህ 480 አባወራዎች ተፈናቅለው በቢፍቱ ከተማ የተጠለሉ ሲሆን ጊዜያዊ እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ (FBC)
PHOTO : TIKVAH FAMILY (GuraFerda)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#DrLiaTadesse
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,676
• በቫይረሱ የተያዙ - 575
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 754
በአጠቃላይ በሀገራችን 91,693 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,396 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 45,260 ከበሽታው አገግመዋል።
306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ዛሬ ጥቅምት 12 የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ መግለጫ አውጥቷል።
ቢሮው በመግለጫው ፦
- የፌዴራሉ መንግስት የትግራይ ህዝብ ድርሻ የሆነውን የድጎማ በጀት መከልከሉ ባስታወቀበት ማግስት ፣ ከበረሃ አንበጣ መንጋ ጋር እየተናነቀ ያለውን የትግራይ ህዝብ ዓመት ሙሉ የለፋበት ቡቃያ የአንበጣ ሲሳይ እንዲሆን በይኖበታል ብሏል።
- ጸረ-አንበጣ መድሓኒት በአውሮፕላን እንደረጨ የሃሰት መረጃ አስተላልፏል ሲል ወቅሷል።
- ከዓለም ኣቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም ለጋሽ አገሮች ለገበሬዎች ሲሰጥ የቆየውን የሴፍቲኔት ፕሮግራም ማለት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት መላክ የነበረበት 285 ሚልዮን ብር እንደከለከለ ጥቅምት 10/2013 ዓ/ም በይፋ ኣሳውቀዋል ሲል ገልጿል፡፡
- የመቐለ ከተማ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ፣ ገረብ ግባ ግድብ ፕሮጀክት ኩንትራት ወስዶ እየሰራ ያለውን የቻይና ኩባንያ (CHAINA GEZHOUBA GROUP COMPANY LIMITED) የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 2 ዲዛይነሮች ከቻይና ተነስተው በትራንዚት ወደ መቐለ ከተማ እንዳይመጡ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ቦሌ ዓለምኣቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አግቶ አስቀርታቸዋል ብሏል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ወረዳ ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሠራር ዝግጅት አጠናቅቂያለሁ አለ።
በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው የበጀት ድጎማ አሠራር በሚቀጥለው ሣምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል።
በዚህም በጀቱ በወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ አስተዳደር አካላት የባንክ ሂሳብ በኩል እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
አስተዳደር አካላቱ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፊያ ደብተር ካላቸው በዚያው በኩል ከሌላቸው ደግሞ አዲስ የባንክ ሂሳብ በመክፈት በጀቱ እንዲደርሳቸው ይደረጋል ነው የተባለው።
ሚኒስቴሩ የትግራይ ሕዝብ እንደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክልል ሕዝቦች የትምህርት ፣ የጤና ፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፣ የምግብ ዋስትና እንዲሁም ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል። (ENA)

#NEBE
የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን አስመልክቶ ፓለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ለምርጫው የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢሽን ማዕከል እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡
በዛሬው ዕለት የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ ቀደም የሚዲያ አካላት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
PHOTO : TIKVAH FAMILY (A.A)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#FDREDefenseForce
በአሁኑ ሰዓት የ10ኛ ዙር ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ዕጩ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን በሀዋሳ እያሳዩ ይገኛሉ።
የሠራዊቱ አባላት በልዩ ዘመቻዎች ኃይል የሰለጠኑ ሲሆኑ በነገው ዕለት የሚመረቁ ናቸው።
እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ትርዒት ፣ የሽብር ጥቃትን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም በከተሞች እና ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ተልዕኮን እንዴት መወጣት እንደሚያስችል ያሳየ ነው።
ምንጭ፦ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሁኑ ሰዓት የ10ኛ ዙር ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ዕጩ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን በሀዋሳ እያሳዩ ይገኛሉ።
የሠራዊቱ አባላት በልዩ ዘመቻዎች ኃይል የሰለጠኑ ሲሆኑ በነገው ዕለት የሚመረቁ ናቸው።
እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ትርዒት ፣ የሽብር ጥቃትን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም በከተሞች እና ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ተልዕኮን እንዴት መወጣት እንደሚያስችል ያሳየ ነው።
ምንጭ፦ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀዋሳ አዲስ ምክትል ከንቲባ ተሾመላት !
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው በዛሬው ዕለት ተሹመዋል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤው እየተካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በአቶ አብርሀም ማርሻሎ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቅራቢነት ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬን በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሹመት ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የሆነበሩት አቶ ጥራቱ በየነ ከ2 ቀን በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው የሚታወቅ ነው።
Via Hawassa City Communication

#Hawassa
በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የከተማውን ቁልፍ ተረክበዋል።
PHOTO : SIDAMA MEDIA NETWORK

#NEBE የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን አስመልክቶ ፓለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ለምርጫው የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢሽን ማዕከል እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡ በዛሬው ዕለት የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ቀደም የሚዲያ አካላት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ PHOTO : TIKVAH FAMILY (A.A) @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ዛሬ አካሂዷል፡፡
ማዕከሉ በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ ፓርቲዎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እንዲያከናውኑበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ቢሮው የኮምፒውተር ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም መጠነኛ መሰብሰቢያ ቦታን ያካተተ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ የሴት ፓለቲከኞች የጋራ ምክር ቤት በማዕከሉ ውስጥ ቢሮ ተሰጥቷቸው ከቦርዱ ቁልፍ ተረክበዋል፡፡
ማዕከሉ የራሱ ሰራተኞች ይኖሩታል፤ የሚተዳደረው በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይሆናል ተብሏል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች አገልግሎቱን ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር በመነጋገርና ቀጠሮ በማሲያዝ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
PHOTO : TIKVAH FAMILY

#UPDATE በ2 ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አልፏል ! በጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት…
#UPDATE
- የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ፣
- የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው፣
- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣
- የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው፣
- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬዓለም ሽባባው እና ሌሎችም የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ተገኝተው ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና ሌሎች የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል። (ENA)

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 510 ኩንታል ስኳር ለሸማቾች ሊከፋፈል ነው !
(የሸዋ ሮቢት ከተማ ኮሚኒኬሽን)
ከሰሞኑን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሲዘዋወር በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለ 510 ኩንታል ስኳር ከዛሬ ጀምሮ ለሸማች ማህበረሰቡ እንደሚከፋፈል የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳዳር ገልጿል።
እንደ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለጻ ከሆነ ከቀናት በፊት 2 የጭነት ተሸከርካሪዎች ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በህገ ወጥ መንገድ 510 ኩንታል ስኳር ይዘው ሲንቀሳቀሱ በከተማው የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የከተማው የህገወጥ ተከላካይ ግብረ ኃይል ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው መረጃ መሰረት ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ግብር ኃይሉ ስኳሩ ለሸማች ማህበረሰብ ተሸጦ ገንዘቡ በአደራ መልክ እንዲቀመጥ ውሳኔ አሳልፏል።
ስኳሩ ለሸማችና ለቸርቻሪዎች የተሰራጨ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ማህበረሰቡ ኩፖኑን በመያዝ በተመደበት ሱቅ እና ሸማች ማህበር በመሄድ ስኳሩን መወሰድ የሚችል መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።