TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ !

* ለተመራቂ ተማሪዎች

ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሚቀበሉት ከ23/02/2013 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን የቅበላ መርሃ ግብር ከላይ የምትመለከቱን ይመስላል።

* ይህን መረጃ የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ አረጋግጠውልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
''ፓርኩ ላይ የተደቀነ አደጋ አለ'' - አቶ ብርሃኑ ዘውዴ

ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ከሰሞኑ ምን አጋጥሞት ይሆን ?

በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ 'አደጋ ላይ' መሆኑን እያነሱ መፍትሔ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ጉዳዩን በተመለከተ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን በስልክ አነጋግረናቸው ነበር።

አተ ብርሃኑ በሰጡን ምላሽ ሰሞኑን የተከሰተ አዲስ ጉዳይ ባይኖርም በተደጋጋሚ በፓርኩ የሚስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ፓርኩ በሰው ሰራሽ ችግሮች ለረጅም ጊዜ ሲፈተን እንደቆየ ያነሱት አቶ ብርሃኑ ፓርኩ በተለይ ነጭ ሳር ባለበት አከባቢ ሰዎች ለግጦሽ እየተጠቀሟቸው መሆኑ እንዲሁም በፓርኩ ተጠግቶ መስፈር ከበፊትም ጀምሮ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮች ናቸው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ፓርኩን ሲያስተዳድር የነበረው የደቡብ ክልል ሲሆን አሁን ላይ ፓርኩን የፌደራል መንግሥት ተረክቦታል ፤ በዋናነት የፌደራል የዱር እንስሳት ጥበቃና እንክብካቤ ባለሥልጣን እያስተዳደረው ይገኛል።

ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ በርግጥ አደጋ ላይ ነው ? ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ አቶ ብርሃኑ ከግጦሽ ፣ ከጥብቅ ደን እንክብካቤ እንዲሁም ከደለል ጋር ተያይዞ በሐይቆቹ የተደቀኑ ችግሮች መኖራቸውን የተናገሩ ሲሆን ''ፓርኩ ላይ የተደቀነ አደጋ አለ'' ሲሉም አረጋግጠዋል።

ዞኑ እንደ ባለ ድርሻ አካል ያሉት ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው በተለያየ ጊዜ እያነሳ መፍትሔ ተብለው የቀረቡትን እየተገበረ ይገኛል ያሉት አስተዳዳሪው ችግሩን ለመፍታት ፓርኩን ከሚያስተዳድረው ባለሥልጣን መስሪያ ቤት እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ'

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካፒቴን ቃልኪዳን የመጀመሪያዋ ሴት የኤር ባስ A350 ዋና አብራሪ በመሆን ባስመዘገበችው ስኬት ደስታውን ገለፀ።

አየር መንገዱ ለካፒቴን ቃልኪዳን ግርማ "እንኳን ደስ አለሽ" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ ! * ለተመራቂ ተማሪዎች ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሚቀበሉት ከ23/02/2013 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን የቅበላ መርሃ ግብር ከላይ የምትመለከቱን ይመስላል። * ይህን መረጃ የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ አረጋግጠውልናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተመራቂ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት !

ጥቅምት 23 እና 24 ቀን 2013 ዓ.ም ፦

• አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
• አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
• አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
• ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ
• ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ
• መቐለ ዩኒቨርስቲ
• ራያ ዩኒቨርስቲ
• ወሎ ዩኒቨርስቲ
• መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ
• ሠመራ ዩኒቨርስቲ

ጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2013 ዓ.ም ፦

• አርሲ ዩኒቨርስቲ
• ኮተቤ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርስቲ
• ሰላሌ ዩኒቨርስቲ
• ደብረ ብረሃን ዩኒቨርስቲ
• ዲላ ዩኒቨርስቲ
• መዳወላቡ ዩኒቨርስቲ
• አክሱም ዩኒቨርስቲ
• አዲግራት ዩኒቨርስቲ
• ወልዲያ ዩኒቨርስቲ
• አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ
• ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ
• ጂንካ ዩኒቨርስቲ
• አምቦ ዩኒቨርስቲ

ጥቅምት 27 እና 28 ቀን 2013 ዓ.ም ፦

• ጅማ ዩኒቨርስቲ
• ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ
• ቦንጋ ዩኒቨርስቲ
• ሐረማያ ዩኒቨርስቲ
• ኦዳቡልቱም ዩኒቨርስቲ
• ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ
• ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ
• ደባርቅ ዩኒቨርስቲ
• እንጂባራ ዩኒቨርስቲ
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ
• ወራቤ ዩኒቨርስቲ

ጥቅምት 29 እና 30 ቀን 2013 ዓ.ም፦

• ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ
• መቱ ዩኒቨርስቲ
• ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ
• ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
• ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ
• ወለጋ ዩኒቨርስቲ
• ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ
• አሶሳ ዩኒቨርስቲ

ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ፦

• ጎንደር ዩኒቨርስቲ
• ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
• ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ

መርሀ ግብሩን እንደ ማዕከል ማውጣት ያስፈለገው ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በተመሳሳይ ቀናት የሚጠሩና ከሆነ ካለው የትራንስፖርት እጥረት አንፃር ለኮሮና ወረርሽኝ የመጋለጥ ሁኔታ የሚጨምር ስለሆነ ነው።

@TIKVAHETHIOPIA
"ቤንዚን በሊትር 50 ብር እየገዛን ነው" - የሀዋሳ ቲክቫህ አባላት

በማደያዎች ቤንዚን ማግኘት ባለብን ሰዓት እያገኘን አይደለም ሲሉ የሀዋሳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ቅሬታ አሰምተዋል።

ይህ ችግር በከተማዋ በርካታት ሳምንታት ሆኖታል ዛሬም ድረስ የሚፈታው አካል አልተገኘም ፤ ነዋሪዎችም እየተቸገሩ ናቸው።

መልዕክታቸውን ካደረሱት አባላት መካከል ፦

"ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ቤንዚን የለም እየተባለ ማታ ማታ ግን ይሸጣል። ቀን ቀን ደግሞ በሊትር 50 እና ከዛ በላይ ነው። አንዱ ሲቀዳ አንዱ ጋር አይኖርም። በዚሁ ችግር ምክንያት ሞተር መጠቀም ካቆምኩኝ ቆይቷል።"

ለሀዋሳ ቲክቫህ አባላቶች ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት እና እውን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ይህ ያህል የሚቸገረው የቤንዚን እጥረት ተከስቶ ነው ? ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖራል ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት የሚመለከታቸው አካላት ለማነጋገር ብንሞክርም ለጊዜው ሊሳካልን አልቻለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በምስራቅ አማራ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አካባቢዎች 12 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ከራሱ በጀት በመቀነስ ነው 12 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በምስራቅ አማራ ሰብላቸው በአንበጣ ለወደመባቸው አካባቢዎች ድጋፍ ያደረገው።

ፎረሙ ያደረገው ድጋፍ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚያግዙ ግብአቶችን ለመግዛት እና ለማህበረሰቡ የምግብ ፍጆታ ለማቅረብ የሚውል መሆኑ ተገጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#እንተጋገዝ

በዛሬው ዕለት የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወጣቶች ወደ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ተጉዘው የደረሱ ሰብሎች በመሰብሰብ ገበሬዎችን ማገዛቸውን በላኩልን መልዕክት አሳውቀዋል።

የአርሶ አደሮች ህይወት አደጋ ላይ ነው ማለት የከተማ ውስጥ ነዋሪዎች የመኖር ህልውና አደጋ ላይ እንደሆነ በመረዳት ሁሉም ወጣት በአቅራቢያው ያሉ አርሶ አደሮችን ሊያግዝ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሰሜን ዕዝ የ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር አመራርና የሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል "ዕንደርታ ወረዳ" ለሚገኙ አቅመ ደካማ እማወራ እና አባወራዎች ሰብል የመሰብሰብ ድጋፍ ማድረጋቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,333
• በቫይረሱ የተያዙ - 628
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 868

በአጠቃላይ በሀገራችን 91,118 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,384 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 44,506 ከበሽታው አገግመዋል።

303 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንበጣ ማጥፊያ ኬሚካል ርጭት እንዲያገለግሉ የመጡ 3 ሄሊኮፕተሮች የመገጣጠም ስራ ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ሶስቱም ሄሊኮፕተሮች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ማእከል መውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot
#AFAR

በአፋር ክልል በጎርፍ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአፋር ክልል ገጠር ቀበሌዎች ከጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ ትምህርት ተጀምሯል።

በከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓም ትምህርት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጎርፍ በተጠቁ አካባቢዎች ሚገኙ 105 ትምህርት ቤቶችን ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ባለመቻሉ ተቋቅማቱን ትምህርት የማስጀመሪያ ጊዜ መራዘሙን ተገልጿል።

ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ፦

• 58ቱ  ሙሉ ለሙሉ በውሀ የተዋጡ ፣
• 18ቱ በውሀ የተከበቡ እንዲሁም
• 29ኙ በጎርፍ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የተጠለሉባቸው ናቸው።

በትምህርት ቤቶቹ የሚኖሩ 41 ሺህ 169 ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት እየተሰራ ነው።

በጎርፍ ጉዳት በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ምትክ የዳስና የቆርቆሮ ክፍሎችን በመገንባት ተማሪዎቹን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓም ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትናንት ከሌሊቱ 6 ሠዓት በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት መውደሙን የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

አደጋው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ራስ ደስታ አከባቢ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ስፖንጅ ፋብሪካ ውስጥ የደረሰ ነው።

በአደጋው ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማውደሙን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 62 የአደጋ ሠራተኞች እና 12 ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው በተደረገው ርብርብ 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማትረፍ ተችሏል።

የእሣት አደጋው መንስኤ አልታወቀም።

PHOTO : TIKVAH FAMILY (AB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ስፖርት ተቋማት ከፌደራል ስፖርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም የሚል ብዥታ ፈጥሮ የነበረ የውሳኔ ደብዳቤ መሻሩን የEthioFM 107.8 ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋ አሳውቋል።

ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በቀን 9/2/2013 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ "የመረጃ ክፍተት" ያለው በመሆኑ ተሽሯል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡ የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ትምህርት ይጀምራሉ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ዘላለም ፤ ኮቪድ-19 ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራታቸው የመልቀቂያ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ቀድመው ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል።

የፊታችን ሰኞ ትምህርት የሚጀመርባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ የፀረ ተዋህሲ ርጭት መካሄዱ እና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።

የሙቀት መለኪያ እና ጭምብል በሁሉም ትምህርት ቤቶች በመሰራጨት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

የ8ኛ እና 12 ክፍል የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 45 ቀን ከተማሩ በኋላ ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ትምህርት የሚጀምሩት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሆነም የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

ቢሮው እንዳስታወቀው ቅዳሜ የትምህርት ቀን እንደሚሆንና አንድ ተማሪ በሳምንት ሶስት (3) ቀን ትምህርት መማር ይጠበቅበታል። (etv)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ONLF

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት (3) ከፍተኛ አመራሮቹ መታሰራቸውን የፓርቲው ቃለ አቀባይ የሆኑት አብዱልከድር ሀሰን ኢርሞጌ አዳኒ ለBBC ሶማሊኛ ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፦

- መሃመድ ጂግሬ ገመዲድ (የቆራሄ ዞን ሊቀመንበር)
- ተማም መሃመድ ማህሙድ (የቆራሄ ዞን ም/ሊቀመንበር)
- መሃመድ ኢብራሂም ሙርሳል (የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ለረዥም አመታት በስራ አስፈፃሚነት የሰሩ) ናቸው።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኡመር ፋሩቅ ወርፋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አረጋግጠዋል።

ኦብነግ ፣ ከክልሉ መንግሥት እና ከፌደራል መንግሥት ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጿል ፤ ችግሩ በድርድር እንደሚፈታም ተስፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

More : telegra.ph/ONLF-10-22

Via BBC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia