TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ውስጥ ሜታ ወረዳ ቁልቢ ከተማ 5 ሺ 100 ሀሰተኛ የብር ኖቶች ይዘው ለመገበያየት ሞክረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን መያዙን ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

የሜታወረዳ ፖሊስ፥እንደገለፀው በከተማው ባለፈው ቅዳሜ በተለያዩ ሱቆች ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ይዘው ለመገበያያት ሲሞክሩ የተያዙት  ተጠርጣሪዎች ሁለት ናቸው።

በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ባካሄደው ክትትል ከተጠርጣሪዎቹ እጅ የተገኙት  ሀሰተኛ የብር ኖቶች  25 አዲሱ ባለ 200 እና እና አንድ ደግሞ ባለ አንድ መቶ  መሆናቸው ተገልጿል።

በከተማው በሚገኘው ንግድ ባንክ የብር ኖቶቹ ሀሰተኛ መሆናቸውን  መረጋገጡንና ለእግዚቢትነትም  በፖሊስ ጽህፈት ቤቱ እንደሚገኙም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,546
• በቫይረሱ የተያዙ - 723
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 500

በአጠቃላይ በሀገራችን 89,860 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,365 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,149 ከበሽታው አገግመዋል።

269 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሰሜን ሸዋ ዞን ' ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ' የአንበጣ መንጋ ተከስቶ በሰብል ከተሸፈነው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ማውደሙ ተገልጿል።

መንጋው በወረዳው 27 ቀበሌዎች በሰብል ከለማው 48 ሺህ 700 ሄክታር መሬት ውስጥ በ13 ቀበሌዎች ተከስቶ 12 ሺህ ሄክታር የደረሰ ሰብልን ነው ያወደመው፡፡

በዚህም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የጤፍ ሰብል 95 በመቶ በአንበጣ መንጋ መውደሙ ታውቋል፡፡

ወረርሽኙ ከመስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መታየት ቢጀምርም ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የጀመረው ግን ከጥቅምት 5 ቀን ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡ (FBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በዛሬው ዕለት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን አስታውቋል።

አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል።

ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ ፣ ሰሜን ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትላንት ጥቅምት 9/2013 ጀምሮ በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

ተማሪዎቹ በአንድ ወንበር ለብቻቸው እንዲቀመጡ ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ ፣ የእጅ ንፅህናቸውንም በአግባቡ እንዲጠብቁ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት በዶ/ር ኣብርሃም ተኸስተ የተመራ ቡድን በትምህርት ቤቶች ተዘዋውሮ ተማሪዎች በጥንቃቄ ትምህርት መጀመራቸውን ተመልክቷል።

PHOTO : TIGRAY COMMUNICATION
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትምህርት ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ መሰረት ትላንት 30 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ትምህረት ጀምረዋል።

በቀጣይም ሌሎች ትምህርት ቤቶች ወደ ማስተማሩ ሂደት ይገባሉ።

ተማሪዎች በትህርት ቤት በሚኖራቸው ቆይታም አስፈላጊው ጥንቃቄ እያደረጉ ትምህርት እንድትከታተሉ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

በጎንደር ከተማ ውስጥ ከ31,000 ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር መዋሉ የ3ኛ ዋና ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የተያዙት በከተማ አስተዳደሩ በማራኪ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኮሌጅ ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች በፀጥታ ሃይል በተደረገ ክትትል ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2013 ከጧቱ 2 ስዓት ላይ መያዙ ተገልጿል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ እየተከታተላቸው መሆኑ በማወቃቸው በመታተም ላይ የነበረ ፦
• 27 ሺህ ብር አዲሱ ባለ 200 የብር ኖት
• 4 ሺህ 600 ብር ነባሩ ባለ 100 የብር ኖቶችን በባጃጅ በመጫን ከወሰዱ በኃላ ውሃ ቦይ ላይ ጥለው አምልጠዋል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎችና ተባባሪዎቻቸውም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የሞባል ካርድ በመግዛት ፣ ምግብ ቤት በመጠቀም እንዲሁም የሱቅ ሸቀጣሸቀጦችን በመግዛት እያዘረዘሩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሃሰተኛ የብር ኖት ሲያጋጥም ተጠያቂ ከመሆን በፊት ለፓሊስ ሊጠቁም እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

በህገ ወጥ መንገድ እየተመረተ ያለው ሃሰተኛ የብር ኖቶች ከአዲሱ የብር ኖቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው እና በሁሉም የብር ኖቶች ዓይነቶች ሃሰተኛ የብር ኖቶች እየተሰሩ ወደ ገበያ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይታለል መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳትጭበረበሩ አዲስ ታትመው ስለተሰራጩት የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች መረጃ ይኖራችሁ ዘንድ ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱ።

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በበረኸት ወረዳ ውስጥ የአንበጣ መንጋ ውድመት አድርሷል !

(በረኸት ወረዳ)

በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በበረኸት ወረዳ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ ወድመት አድርሷል።

መንጋው በተለይ በ08 ቀበሌጎሜንሣ፣ ታች ዳንሴ እና በ07 ቀበሌ ዳዊት ን/ቀበሌ ሰድአሰን/ቀበሌ፣ በ06 ቀበሌ ጋድማያ ገበሮች ን /ቀበሌ ጉዳት አድርሷል።

የወረዳ አመራርና መላው ህ/ሰብ በተለያየ የመከላከል ዘዴ ቢታገልም ከአቅም በላይ ሰለሆነ ሠብልን ማዳን አልተቻለም።

መንግስት በፕሌን እንዲሁ በመኪና ኬሚካል እየረጨ ቢሆንም የአካባቢው አቀማመጥ አሰቸጋሪ በመሆኑ የታሠበውን ቦታ መረጨት አልተቻለም።

አሁን ያለው አማራጭ አንበጣ መንጋ ባልደረሳባቸው ቀበሌዎች "ሰብልን መሠብሠብ" ወሳኝ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ወ/ሮ ዘርፈሸዋል ንጉሴን አፈጉባኤ አድርጎ በአብላጫ ድምፅ ሰይሟል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬ እለት እያካሄደ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አስቻለው አባይነህ መግለጫ መስጠታቸውን አል ዓይን ዘግቧል።

ም/ዳይሬክተሩ በመግለጫቻው ተከታዩን ብለዋል ፦

- እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከሚያዙት 57 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15-34 ሲሆን ከሟቾች ውስጥ ደግሞ 51.9 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ነው።

- በቫይረሱ የሞት ምጣኔ በኢትዮጵያ 1.52 በመቶ ፣ በአፍሪካ 2.4 በመቶ ፣ በዓለም ደግሞ 2.8 በመቶ ነው።

- በአሁኑ ወቅት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ውስጥ 63 በመቶው ምልክት የማያሳዩ ናቸው።

- ከሐምሌ እና ነሐሴ በላይ አሁን ላይ ወደ ፅኑ ሕሙማን የሚገቡ ታማሚዎች ብዛት እየጨመረ መጥቷል።

- 1.4 በመቶ የሚሆኑት በሆስፒታል የሚገኙ ታማሚዎች በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡

- በኢትዮጵያ ሁሉም ወረዳዎች ቢያንስ አንድ በኮቪድ የተያዘ ሰው ሪፖርት አድርገዋል፡፡

- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ ኦሮሚያ ክልል ፣ ትግራይ ክልል ፣ አማራ ክልል ፣ ደቡብ ክልልና ሲዳማ ክልል በቅደም ተከተል ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች የተገኙባቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ኮቪድ-19 በተመለከተ "የአስከሬን ምርመራ" ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ መቆሙን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የኮሮና ምርመራ ኪቶችን በተመለከተ ቢጂአይ የተባለ የቻይና ኩባንያ ባሳለፍነው ሳምንት ኪቶችን ማምረት ስለመጀመሩም አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda Newspaper
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የትምህርት ቤቶችን መከፈትን አስመልክቶ በሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ማሳሰቡን አዲስ ቲቪ ዘግቧል።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን ወረርሽኙን እንደጠፋ አድርጎ በመመልከት ህብረተሰቡ በግዴለሽነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል፤ ይህም በአሁኑ ወቅት እየተመዘገበ ያለው የታማሚ ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀዋል።

ተቋርጦ የነበረው የትምህርት መርሐ ግብር እንዲጀመር ከመደረጉ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለው ግዴለሽነት ህፃናትና ታዳጊዎች ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው መሆኑን ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል።

ይህንንም ከቤተሰብ ጀምሮ በሚደረግ ጥንቃቄ መከላከል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ የሚመለሱበት ቀን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተማሪዎች በ2012 የ2ኛ ወሰነ ትምህርት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ያለፋቸዉን የትምህርት ይዘት ክለሳ መደረግ ያለበት እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ/ም መሆኑ ተገልጿል።

የትምህርት ዘመኑ (2013) የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥለዉ ከታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን ክፍለ ከተሞች ይህን አውቀው ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ከዚህም መርሃ ግብር ውጪ የሚፈጽም ተቋም አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PASSPORT ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል። *አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA) @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የኔትወርክ ችግር ምክንያት የኦንላይን (online) አገልግሎቱን ዛሬ ጠዋት መጀመር እንዳልተቻለ ለ 'ኢትዮጵያ ቼክ' ገልጿል።

አገልግሎቱ ከሰአት አካባቢ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅና ፣ ስራው ሲጠናቀቅ አገልግሎቱ ማግኘት የሚቻልበት ሊንክ ይፋ እንደሚደረግ ኤጀንሲው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia