TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ጥሪ ፦

(በአብመድ)

ዛሬ በአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን የበርሃ አንበጣ መንጋ የመከላከል እንቅስቃሴውን በቦታው በመገኘት ተከታትሏል።

ልዑኩ ከአርሶ አደሮች እና ባለሙያዎች ጋርም ተነጋግሯል።

ልዑኩ የበርሃ አንበጣ መንጋው የተከሰተባቸው የራያ ቆቦ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች 41 አዲስ ዓለም እና 06 መንደፈራ ተገኝቶ የመከላከል ሥራውን ምልከታ አካሂዷል፡፡

በቀበሌዎቹ አንበጣው በጤፍና ማሽላ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

አርሶ አደሮች ኅብረተሰቡን ያሳተፈ መከላከል ሥራ ቢጠናከር የተሻለ እንደሆነ የመፍትሔ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

የፀጥታ አካላት ፣ ተማሪዎች ፣ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶች እንዲሳተፉና የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ እንዲተባበሯቸው ማስተባበር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ👏

የአርሶ አደሩን ህይወት መታደግ የራስን ህይወት መታደግ ነው !

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ፣ ሰራተኞች ፣ መምህራን እንዲሁም የደብረ ብርሃን ወጣቶች ትላንት በቀወት ወረዳ የደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎችን በመሰብሰብ የአንበጣ መንጋ የሚያደርሰውን ጉዳት የመከላከል ሥራ አከናውነዋል።

የአርሶ አደሩ ህይወት አደጋ ላይ ነው ማለት የከተማው ነዋሪ የመኖር ህልውና አደጋ ላይ እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው ሲሉ የዘመቻው አስተባባሪ ዶ/ር ታምራት ቸሩ ተናግረዋል።

ዘመቻው በአጭር ጊዜ የታቀደ ቢሆንም ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። በቀጣይም ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖሊስ መወሰዱ ተሰማ !

ዛሬ 8:00 አካባቢ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ፖሊሶች ' ፍትህ መፅሄት ' የሚገኝበት ቢሮ በመገኘት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በወቅቱ ቢሮ ስላልነበር ካለበት በስልክ በመጥራት ይዘውት እንደሄዱ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በፍትሕ መጽሔት ላይ ' አባ ብላ ገመዳ ' በሚል ርዕስ በተጻፈ ጹሑፍ ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ለብሮድካስት ባለስልጣን የቅሬታ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጋዜጠኛ ተመስገን ታስሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገባ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል !

ታሪኩ ደሳለኝ ተከታዩን ብሏል ፦

"ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰሩን በር ላይ ያሉት ፖሊሶች ነግረውናል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቢሮ መወሰዱን እንደሰማን ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያመራን ሲሆን እዛ በር ላይ ያሉት ፖሊሶች ተመስገንና የመፅሔቱ አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤ ተይዘው መግባታቸውን ገልፀውልናል።

ከዚያ ውጪ ምንም ዓይነት መረጃን ያላገኘን ሲሆን ምናልባት ምግብና ልብስ ካመጣን ለማስገባት እንደሚተባበሩን ነግረውናል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቅምት 4/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሶማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 146 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አልተገኘም።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 765 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰው ህይወት አልፏል (1 ከእንጅባራ ህክምና ማዕከል፣ 1 ከሃይቅ)

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 579 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 102 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 142 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 94 የላብራቶሪ ምርመራ 13 ሰዎች በቫረረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1304 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 55 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአ/አ ባለፉት 24 ሰዓት 3,246 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 308 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

* ያልተካከቱ የክልል ሪፖርቶችን ቆይት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ !

@tikvahethiopiaBOT
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ40 ሺህ አለፉ!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,121 የላብራቶሪ ምርመራ 712 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 858 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 86,430 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,312 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 40,165 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኒኮላስ የተሰኘው የመቐለ ልዩ ት/ቤት ወጣት የኬሚስትሪ እና የስነ ህይወት ባለሙያዎች አዲስ የአንበጣ ማጥፍያ ኬሚካል ሰሩ።

ከ3-5 ደቂቃ ባለዉ ጊዜ አንበጣ ይገድላል የተባለዉ ኬሚካል ከሰሞኑን በመስክ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።

ወጣቶቹ ምርምር ማድረግ የጀመሩት የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ሥለ አንበጣ መንጋ ሥርጭትና አደገኛነት ያወጣውን ማስጠንቀቂያ አከል ትንበያ በመስማታቸው ነው።

አዲሱ ፀረ አንበጣ ኬሚካል በቅርብ ከሚገኙ ዕፅዋት የተቀመመ ፣ በብዛት ሊመረት የሚችል እና የተፈጥሮ አካባቢን የማይጎዳ ነው ተብሏል። (DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሹመት !

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (የፍትህ ማናጂንግ ዳይሬክተር) ከእስር መፈታቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፍትህ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤም ከእስር መፈታቱ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ የሶስት ቀን የሥራ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ልዑካቸው ዛሬ ወደ ኤርትራ ተመልሰዋል።

ከፕሬዜዳንቱ እና ልዑካቸው ጋር በልዩ ልዩ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ካተኮረ ውይይት መደረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ ያስመረተውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተረከቧል።

- የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተረክበው ለየክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ተወካዮች አስረክበዋል።

- በወረዳና ከዚያ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት እንዲጀምሩ ይደረጋል። በቦታዎች ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዳይጀምሩ ማሰስቢያ ተሰጥቷል።

- እስከ ጥቅምት 30/2013 ዓ/ም ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቀመጡት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የማስክ አቅርቦት ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ነው።

- በሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመረተው ማስክም ወደየትምህርት ቤቶች የማድረስ ስራ እየተሰራ ነው።

#MoE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ችሎት!

ዛሬ ረፋድ በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው ተሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝ ተመልክቷል።

በትዕዛዙ የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ተቀይሯል መባሉን ተከትሎ ተወካይ ወይም የክፍል ሃላፊ ለምን እንዳልቀረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርበው እንዲያብራሩም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡ በህገወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ በተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትና መሰረት ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤቱ አዟል። (ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጋምቤላ ክልል ሰኞ ትምህርት ይጀምራል !

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በስተቀር 257 ትምህርት ቤቶች የፊታችን ሰኞ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራቸው እንደሚጀምሩ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

አቶ ሙሴ ጋጄት (የቢሮው ኃላፊ) ለኢዜአ ከተናገሩት ፦

- ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንዲጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

- የመማር ማስተማር ሥራው በ257 ትምህርት ቤቶች ይጀምራል።

- በክልሉ በኑዌር እና በአኝዋክ ዞኖችና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው 86 ትምህርት ቤቶች ግን ትምህርት መስጠት የሚጀምሩት በሂደት ነው።

- ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች በተቻለ ፍጥነት ተስተካክላው ሥራ እንዲጀምሩ እተሠራ ነው።

- በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የማስክ ድጋፍ እንዳለ ሆኖ የውኃና ሌሎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት እየተሰራ ይገኛል።

- በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ጨምሮ ከ173,000 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቢሮው እየሠራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሰሜን ወሎ ዞን ከ286 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል!

ከነሐሴ 28/2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ውሎ ዞን የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ፣ በእንስሳት መኖ እና በቁጥቋጦ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

እስከ መስከረም 27 ቀን 2013 ድረስ በተመዘገበው የጉዳት መጠን 286 ሺህ አርሶ አደሮች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አብመድ የዞኑን አስተዳደሪ ወልደትንሳኤ መኮንንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ሥርጭቱን በፍጥነት መከላከል ካልተቻለም ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ይጨምራል ተብሏል፡፡

የአንበጣ መንጋው በዞኑ ከተከሰበት ጊዜ አንስቶ አርሶ አደሩ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እየተከላከለ መሆኑን ተገልጿል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሥርጭት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን እየከበደ መጥቷል።

ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው። (AMMA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል እና የተቋረጠውን ትምህርት በጥንቃቄ ለማስቀጠል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዛሬ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስላደረገው ዝግጅት እንደሚከተለው አሳውቆናል ፦

- ከወዲሁ የተመራቂ ተማሪዎች የዶርም ድልድል ተጠናቋል ፣ የተመደቡበት የመኝታ ቁጥር በቴሌግራም በኩል እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በአንድ ዶርም 2 ተማሪ ብቻ ይኖራል።

- በዋናው ጊቢ ዛሬ ተማሪዎች በሚመላለሱባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ተካሂዷል።

- በቀጣይ የፀረ ተዋህስ ኬሚካል ርጭት በተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሾች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ቢሮዎች ይካሄዳል።

- ግቢ ውስጥ ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ መታጠቢያ በየቦታው እንዲቀመጥ ተደርጓል።

- በ1 ክፍል ውስጥ ከ25 ያልበለጠ ተማሪ ይማራል፣ በእያንዳንዱ ወንበር ላይ የተማሪዎች ስም ይፃፋል ፣ ተማሪዎች ስማቸው ከተፃፈበት ወንበር ሌላ መቀመጥ አይችሉም።

ቲክቫህ ላለፉት አመታት ሲያደርግ እንደቆየው የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቀናትን እና አሁን ደግሞ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ ዝግጅቶቻቸውን እየተከታተለ ለወላጆች እና ለተማሪዎች ያሳውቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia