TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ሀሳብን በሙሉ ድምጽ አፀደቀ! የዳውሮ ዞን ምክር ቤት በ 4ኛ ዙር 7ኛ ሥራ ዘመን 17 መደበኛ ጉባዔው ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ሀሳብን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡ የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ፀሀይ ገሉ ፥ በሚመሰረተው አዲስ ክልል ዋና ከተሞች በክላስተር የሚደራጁ ሲሆን ህዝቡ ፍትህን…
#UPDATE

#1 ምዕራብ ኦሞ ዞን

የምዕራብ ኦሞ ዞን በ5 ዙር 5ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ጋር በአንድ ክልል የመደራጀት ውሳኔ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቆል ፡፡

ዞኑ በቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን ለ2 ሳይካፈል ክልል እንዲሆን የወሰነ ቢሆንም አሁን እራሱን ችሎ የወጣ በመሆኑና መንግስት ጥናት በማድረግ የተሻለ ምክረ ሃሳብ ይዞ በመምጣቱ አዲስ ውሳኔ ማሳለፍ አስፈልጓል ተብሏል።

#2 ሸካ ዞን

የሸካ ዞን ምክር ቤት በ4ተኛ ዙር 5ተኛ አመት የሥራ ዘመን 14ተኛ መደበኛ ጉባዓዉ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች በክልል መደራጀትን አስመልክቶ ለሸካ ዞን ምክር ቤት ለውሳኔ መነሻ ሃሳብ ቀርቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።

#3 ቤንች ሸኮ ዞን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲደራጅ የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ተኛ ዙር 8ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

#4 ኮንታ ልዩ ወረዳ

የኮንታ ልዩ ወረዳ ም/ቤት በጠራው 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ለመደራጀት የቀረበውን ማሻሻያ ሞሽን በአባላት ሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የደቡብ ክልል ፐ/ሰ/ሰ/ሀ/ልማት ቢሮ ኃላፊና የምክር ቤቱ አባል አቶ ተዘራ ወ/ማሪያም ከሀገራዊ ምርጫ በፊት የክልሎች አደረጃጀት አልቆ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ቀርቦ በፌደራል በሚደረገው ጉባኤ ስለሚፀድቅ በሌሎቹም አደረጃጀቱ እየፀደቀ ይገኛል ብለዋል።

ምንጭ፦ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የኮንታ ልዩ ወረዳ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በዛሬው ዕለት በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀድሞ የዎላይታ ዞን አመራሮች ዋስትናቸው ታግዶ ዎላይታ ሶዶ ማረሚያ ይቆዩ ሲል ፍርድ ቤት ወስኗል ፤ ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 21/1/2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ የችሎት መረጃ ፦

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው አቃቤ ህግ ላቀረበባቸው የዋስትና ክልከላ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2013 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via Hailemichael T Lemma , EDP
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አትሌት ደጊቱ እና አሰልጣኝ ሀጂ አዴሎ በኮቪድ ተያዙ!

የአይሪሽ ኢንዲፐንደንቱ ጋዜጠኛ ካቴል ዴንሀይ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና የአትሌቲክስ አሰልጣኙ ሀጂ አዴሎ "የለንደን ማራቶንን" ለመሳትፍ ወደ ለንደን ከማቅናታችው በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እና ውድድሩን እንደማይሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቀነኒሳ በቀለና ሌሎች አትሌቶች የጤና ሁኔታ በምን ደረጃ ይገኛል ?

ከቀናት በኋላ በመጪው ዕሁድ ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ታላለቅ አትሌቶች በተገኙበት ይካሄዳል ።

ከሰዓታት በፊት በዓለም አቀፍ ሚዲያ የወጣውን መረጃ ተመርኩዘን በለንደን የከተሙት አትሌቶቻችን ጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታማኝ የውስጥ ምንጭ ለማጣራት ሞክረናል።

አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ከቀናት በፊት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦልናል ።

በለንደን የከተሙት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ ሞስነት ገረመው እንዲሁም ሌሎች አትሌቶቻችን በሙሉ ጤንነት ላይ ሲገኙ ልምምዳቸውን በመስራት ላይ እንደሚገኙ ቲክቫህ ስፖርት ለማረጋገጥ ችሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
መስከረም 19/2013 ዓ/ም

የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 63 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 207 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,25 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከወልዲያ ሆስፒታል)

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 138 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 21 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል (17ቱ ከሀዋሳ ከተማ ናቸው)

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 189 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 92 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 505 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 46 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ1 ሰው ህይወት አልፏል (ከመቐለ ህክምና ማዕከል)

#DireDawa

በድሬዳዋ 237 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 76 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 481 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 84 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 451 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
ባለፉት 24 ሰዓት የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 640 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,284 የላብራቶሪ ምርመራ 640 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 199 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 74,584 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,191 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 30,952 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት 264 ሴቶች እና 35 ህፃናት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

@TIKVAHETHIOPIABOT @TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
አትሌት ደጊቱ እና አሰልጣኝ ሀጂ አዴሎ በኮቪድ ተያዙ! የአይሪሽ ኢንዲፐንደንቱ ጋዜጠኛ ካቴል ዴንሀይ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው እና የአትሌቲክስ አሰልጣኙ ሀጂ አዴሎ "የለንደን ማራቶንን" ለመሳትፍ ወደ ለንደን ከማቅናታችው በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እና ውድድሩን እንደማይሳተፉ ለማወቅ ተችሏል። @tikvahethsport @tikvahethiopia
"በመልካም ጤንነት ላይ እገኛለሁ" - አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተገለፀው የአትሌቲክስ አሰልጣኙ ሀጂ አዲሎ ከቲኪቫህ ስፖርት (@tikvahethsport) ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ፥ ያለፉትን ስምንት (8) ቀናት ራሳቸውን አግልለው በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚገኙና አሁን በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሆኑ አሳውቀውናል።

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHSPORT
#DrTsionFirew

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማብቃት ፥ የኮሮና ቫይረስ ማብቃት ማለት አይደለም። ይልቁንም ማስክ በማድረግ ፥ ርቀታችንን በመጠበቅ እና እጃችንን በመታጠብ ፥ የገጠመንን ተግዳሮት ለመሻገር ራሳችንን በበለጠ እንድንጠብቅ የሚያደርግ ነው።

ከበአላት እና ፌሽታ ጋር ተያይዞ ፥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ግልጽ ነው። ይሄ ግዴለሽነት ለጤና ባለሙያዎችን የሚያሳዝን ተግባር ነው!

ቫይረሱ መልከ-ብዙ ነው። ምን ጥሎ ምን አንስቶ እንደሚሄድ ገና አልታወቀምና ራሳችሁን ጠብቁ።

የጤና ባለሙያዎችን ልፋት ፥ የእናት የአባት ጸሎትንም ዋጋ አታሳጡ። እባካችሁ!

ዶክተር ፅዮን ፍሬው
መስከረም 19/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰሩ ህይወታቸው ያለፈው ትላንት ምሽት 5 ሰዓት አካባቢ እንደሆነ ቤተሰቦቸው እና የቀርብ ሰዎቻቸው ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን በኮሮና በሽታ ተይዘው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ሆስፒታል ላለፉት 11 ቀናት ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ልጃቸው መቅደስ መስፍን ተናግረዋል።

እስከ ትላንት ድረስ ከአባታቸው ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት መቅደስ መስፍን እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ በደህና ሁኔታ ላይ እንደነበሩ አስረድተዋል።

የፕሮፌሰር መስፍን የቀብር ስነ ስርዓት መቼ እንደሚከናወን ገና እንዳልተወሰነ የገለጹት ልጃቸው እርሳቸውን ጨምሮ በውጭ ሀገር የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚፈጸም ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገፅ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (1922 -2013)

- ከዛሬ 91 ዓመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፣

- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል፣

- ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል፣

- በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በጂኦግራፊ ዲፓርትመንት በመምህርነት ና በትምህርት ክፍሉ ኃላፊነት አገልግለዋል፣

- በጊምቢ አውራጃ አስተዳዳሪነት ሰርተዋል።

- በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች በርካታ መጽሀፍትን አሳትመዋል፣

- ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት አንስቶ መንግስትን በመተቸትና ሂስ በመስጠት የሚታወቁ አንጋፋ የፖለቲካ ሰው ነበሩ ፣

- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) መስራችና ሊቀመንበር ነበሩ፣

- ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ ናቸው፣

- በአደባባይ ምሁርነታቸው፣ በፖለቲካ ተሳትፏቸው፣ በበርካታ ጹሑፎቻቸው፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነታቸው ይታወቃሉ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
በብዛት እየተመረቁ የሚወጡት ወጣት ሀኪሞች ሥራ ማግኘት አልቻሉም!

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

ከፍተኛ የሀኪሞች እጥረት ካለባቸው ሀገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሀኪሞች ተመርቀው ሥራ ማግኘት እንዳልቻሉና አንዳንዶቹም ተስፋ ቆርጠው ሥራ ለመቀየር መገደዳቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ሀኪሞች ሥራ በማጣታቸው ለከፍተኛ የኢኮኖሚና ስነ-ልቦና ችግር እንደተጋለጡም ተናግረዋል።

ጤና ሚኒስቴር ችግሩ የተፈጠረው በበጀት አቅም ማነስ ምክንያት ክልሎች ተፈላጊውን የህክምና ባለሙያ መቅጠር ባለመቻላቸው ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዛሬው ዕለት 264 ሴቶች እና 35 ህፃናት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። @TIKVAHETHIOPIABOT @TIKVAHETHIOPIA
እስካሁን ምን ያህል ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ ?

እስካሁን ድረስ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ 964 ዜጎቻቸውን ወደ ሀገራቸው እንደሚለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት 964 ዜጎች መካከል 58 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል!

የ2012 የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና በኮሮና በሽታ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ ፈተናውን በ2013 ለመስጠት የፍትሕ እና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወገን ለወገን የቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ ወጥቷል!

የወገን ለወገን የቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ በትላንትናው ዕለት በብሔራዊ ሎቶሪ አዳራሽ ወጥቷል። 

ቶምቦላ ሎተሪው በ2010 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ከሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም በኦሮሚያ ልማት ማህበር የተዘጋጀ ነው።

በግንቦት 2010 ዓ.ም ይፋ የተደረገውን ሎተሪ በስድስት (6) ወራት ሸጦ ለማጠናቀቅ ነበር የታሰበው።

ያም ሆኖ ከሁለት ዓመታት በላይ ዘግይቶ ትላንት መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም መውጣት ችሏል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

- ሎቶሪው ጊዜዉን ጠብቆ የልወጣው በአገሪቷ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ነው።

- ከተሰራጨው 39 ሚሊዮን የሎተሪ ትኬት የተሸጠው 12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሲሆን ይህም 30 በመቶው ነው።

- 12 ሚሊዮን 79 ሺህ 331 ሎተሪ ተሸጦ 241 ሚሊዮን 586 ሺህ 620 ብር ገቢ ተገኝቷል።

- በሎቶሪው ዕጣ 447 ሰዎች ዕድለኞች ሆነዋል።

- ከወጡት ዕጣዎች መካከል በአይነት የመኖሪያ ቤት፣ ገልባጭ ሲኖትራክ፣ ሚኒባስ፣ ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ባጃጅ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ፎን የሞባይል ስልክና ፍሪጅ ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወሻ !

አዲሱን የገንዘብ ኖት የመቀየሪያ ጊዜ ሊያበቃ ፦

- ከ100 ሺህ ብር በታች ለሆነ 74 ቀን ቀርቶታል።

- ከ100 ሺህ ብር በላይ ለሆነ 14 ቀን ቀርቶታል።

Via Hibret Bank
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Irreecha2013

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ በኢሬቻ በዓል ወቅት መደረግ ስለባቸው ጥንቃቄዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር መንግስቱ በመግለጫቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

- የኮቪድ 19- ወረርሽኝ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጊዜ በላይ እየተስፋፋ በመሆኑ የሆረ ፊንፊኔም ሆነ የሆረ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጥንቃቄ በዓሉን ሊያከብሩ ይገባል።

- በኢሬቻ በዓል የሚሳተፉ ሰዎች አካላዊ ርቀትን ሊጠብቁ እንዲሁም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሊያደርጉ ይገባቸዋል።

- በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጤና ችግሮች ለመከላከል ቢሮው 7 ኮሚቴዎችን አዋቅሮ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

- በበዓሉ ወቅት ከጤና ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ችግር እርዳታ ማግኘት የፈለገ ሰው በነፃ 6955 ላይ ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላል። (etv)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia