ቀድመው ዝግጅት ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ጀምሮ 'ለተመራቂ ተማሪዎች' ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተወስኗል!
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ 'ለተመራቂ ተማሪዎች' ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የውይይት መድረክ ውሳኔ ተላልፏል።
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥሪ ከተደረገ በኋላ ከመጓጓዣ ሂደት ጀምሮ በየዩንቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይዛመት ከፍተኛ ዝግጅት መደረግ እንዳለበትም ተገልጿል።
በቀጣይነትም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ ተለዋዋጭ እቅዶችን በመያዝ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንደሚሠራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት!
(በፋና ብሮድካሲንግ ኮርፖሬት)
6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ ለማከናወን የሚያስችሉ ሁሉንም ቁሳቁሶዎች ከውጭ ሃገር ገዝቶ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገበት ዝግጁ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አድርጓል።
ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ (የብሄራዊ ምርጫ ቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ) ፦
- ቦርዱ ባለፉት 5 ወራት ሰዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የማያንቀሳቅሱ ሰራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
- ከስልጠና ጀምሮ በድምጽ መስጫ ቀን ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሙሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል ፦
• መየራጮች ምዝገባ ወረቀትና ካርድ ፣
• በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰልጠኛ መመሪያ፣
• የማሰልጠኛ ቁሳቁስ፣
• ስድተኛው ሃገራዊ ምርጫ እና አካባቢያዊ ምርጫዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ የድምጽ መስጫ ሳጥንም ዝግጁ ሆነወል።
- ምርጫ አስፈጻሚዎች ከመራጩና ከሌሎች ሰዎች የሚለዩበትን አልባሳት ጨምሮ በምርጫው ቀን ጥቅም ላይ የሚውሉ በርከት ያሉ ግብዓቶች ዝግጁ ሆነዋል።
- እስካሁን በሃገሪቱ የምርጫ ታሪክ ያልነበረ እና በምርጫው ታማኝነት ላይ ከፍተኛ ቦታ ያለው የድምጽ መስጫ ቦታ መከለያ ተዘጋጅቷል፤ ከዚህም ቀደም መራጮች በጨርቅና በላስቲክ በተከለሉ ቦታዎች ድምጽ ሲሰጡ የነበረበትን ሂደት በማስቀረት መራጮች በነጻነት ፍላጎታቸው በድምጽ መስጫዎቹ እንዲያሳርፉ ያደርጋል።
- በ50,900 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶችም ወደ ሃገር ውስጥ ገብተዋል።
- የቀሩ ስራዎች ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ታሳቢ በማድረግ ምርጫውን ለማስፈጸም አዲስ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ቦርዱ ይፋ ያደርጋል።
@tikvahethiopiaBOT

#UPDATE
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች እና ኮቪድ 19ን ከመከላከል አኳያ የነበሩ ተግባራዊ ምላሶች ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን ምክክር በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡
በመድረኩ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶክተር ሙሉ ነጋ የተቋረጠውን ስልጠና ለማስቀጠል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችና ስልጠናውን ለማስጀመር መደረግ ስላለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች በመመካከር ስልጠናው የሚጀምርበት አቅጣጫ ይቀመጣል ብለዋል።
(MoSHE)

ከመስከረም 24 ጀምሮ የዑምራ ጉዞና የመካ ቅዱስ ስፍራዎች ለሳዑዲ ዜጎች እና ነዋሪዎች ብቻ ክፍት እንደሚሆኑ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ማስታወቁን ዘናሽናን ዋቢ አድርጎ አል አይን (Al Ain) ዘግቧል።
አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ምዕመናን በጉዞው መሳተፍም ሆነ መጎብኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ሃይማኖታዊው ጉዞ በአራት ምዕራፎች ነው የሚከናወነው።
በመጀመሪያው ቀን ማለትም መስከረም 24 ስድስት ሺ የሳዑዲ ተወላጆችና ነዋሪዎች ብቻ በጉዞው ይሳተፋሉ፡፡
ቁጥር ጥቅምት 8/2012 ዓ/ም በቀን 15 ሺ ከጥቅምት 22 ጀምሮ ደግሞ በቀን ወደ 20 ሺ ያድጋል፡፡
የዑምራ ጉዞ እና በመካ ቅዱስ መስጊዶች የሚደረገው ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፉትን 4 ወራት ያህል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA
ቀድመው ዝግጅት ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ጀምሮ 'ለተመራቂ ተማሪዎች' ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተወስኗል! የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ 'ለተመራቂ ተማሪዎች' ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የውይይት መድረክ ውሳኔ ተላልፏል። ለከፍተኛ ትምህርት…
ተጨማሪ ፦
ጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውይይት መድረክ የተነሱ ኃሳቦችን ከመድረኩ ተሳታፊ አካላት ጠይቀን ተከታዩን መርጃ ሰጥተውናል ፦
- ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን የመቀበል ዝግጁነታቸውን እስከ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ድረስ እንዲያሳውቁ በመድረኩ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ዝግጁ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከመስከረም 25 ጀምሮ መጥራት ይችላሉ፡፡
- በቀድሚያ ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፡፡
- ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተወጣጣ የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ግብረ-ኃይል የተቋቋመ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ይመለከታል።
- ዩኒቨርሲቲዎች በጥሪ ጊዜ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይኖር ዩኒቨርሲቲዎች ተናበው እንዲሰሩ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለተማሪዎች እንዲያመቻቹ ኃሳብ ተነስቷል፡፡
- የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ እየተደረገ ይገኛል፡፡
- በዚህ ዓመት ሌላው ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው የዲሲፒሊን ጉዳይ ሲሆን ባለፈው ዓመት የተፈጠሩ ክስተቶች እንዳይደገሙ ሁሉም ባለድርሻ አካል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል።
በዚሁ መሰረት የትምህርት ቤት አከፋፈት ሂደቱ በሶስት ዙር እንደሚከናወን አስታውቀዋል ፦
- በመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በገጠር ወረዳ እና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ፤
- በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 በሁሉም የዞን እና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ፤
- በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።
(ENA)

የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው።
በተመሳሳይ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።
(MoE)

ችሎት!
እነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ፍርድ ቤት ማዘዙን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ዘግቧል።
በጥበቃ በኩል ስጋት ካለ እንደሚከታተልም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።
በተጨማሪም በችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾች እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ትዛዝ ሰጥቷል። በችሎት ያልቀረቡት ተከሳሾች ባሉበት ክስ ለማንበብ ለመስከረም 21 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተጨማሪ ፦ ጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውይይት መድረክ የተነሱ ኃሳቦችን ከመድረኩ ተሳታፊ አካላት ጠይቀን ተከታዩን መርጃ ሰጥተውናል ፦ - ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን የመቀበል ዝግጁነታቸውን እስከ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ድረስ እንዲያሳውቁ በመድረኩ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ዝግጁ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከመስከረም 25 ጀምሮ መጥራት ይችላሉ፡፡ - በቀድሚያ…
ዩኒቨርሲቲዎች እንዴት ተማሪዎችን ይጠራሉ ?
(ከMoSHE ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ)
- ዩኒቨርሲቲዎች እስከ መስከረም 25 ደረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን /ዝግጅት ማድረጋቸውን/ ለMoSHE ያሳውቃሉ።
- ከዚህ ቀጥሎ የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት የሚያረጋግጠው ግብረ-ኃይል በዩኒቨርስቲዎቹ በአካል በመገኘት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ይመለከታል /ያረጋግጣል/።
- ግብረ ኃይሉ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው ፕሮቶኮል መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተማሪዎቻቸውን እንዲጠሩ ፍቃድ ይሰጣል።
- ይህ ማለት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በአንድ ቀን/በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን ይጠራሉ ማለት አይደለም ፤ እንደየዝግጅታቸው ተረጋግጦ ተማሪዎችን ለመቀበል ፍቃድ ሲሰጣቸው ብቻ ይጠራሉ።
- ቅድሚያ የሚሰጣቸው የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ሲሆኑ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥሪ ይደረግላቸዋል።

#UPDATE ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ…
የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ!
ትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ-19ኝን ለመከላከል የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በ3 ሳምንታት ውስጥ ያሟሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ወስኗል።
የዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ወረርሽኙን ለመከላከል ባስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ መሰረት ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት ፦
• በመድሃኒት ማፅዳት፣
• የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድርግ
• የእጅ ማፅጃ ማሟላት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን ማስተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለሌሎች አገልግሎቶች ውልው የነበሩ ትምህርት ቤቶችም አስፈላጊውን የማስተካከያ ስራ ሊሰራላቸው ይገባል ተብሏል።
እንደየ ትምህርት ቤቶቹ ነባራዊ ሁኔታ ትምህርት በፈረቃ እና አንድ ቀን በመዝለል ተራ ሊያስተምሩም ይችላሉ፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች ማስተማር የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን በሚመለከት ፦
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ከ12ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ተከታዩን ብለውናል ፦
- የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
- ከፈተናው አስቀድሞ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር ይሰራል።
- ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ተቋማት፣ ወላጆች፣ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
- የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን አለባቸው።
- የ8ኛ ክፍል ተፈታኛ ተማሪዎች የ7ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁ እና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በሙሉ አቅም እንዲመለሱ የስነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን ይካሄዳል። ተማሪዎች የ45 ቀን የክለሳ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም ይኖራቸዋል።
- በነገራችን ላይ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ፣ ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ #ብቻ ነው።
- ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል።
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ ፦
- አቶ ሩፋዔል ሽፋረን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ
- ወ/ሮ ዘይነብ አብዱለጢፍን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ ፦
- አቶ ሩፋዔል ሽፋረን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ
- ወ/ሮ ዘይነብ አብዱለጢፍን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ…
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበትና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው በዛሬው ውይይት ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
- ትምህርት ከመጀመሩ በፊት መማር ማስተማር ለመጀመር የሚያስችል በቂ ዝግጅት መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
- በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ወላጅ፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ ትምህርት ቤቱን ለመክፈት የሚያስችል ግምገማ ማድረግ እና ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል።
- ትምህርት የሚጀመረው በዝግጅቱ ልክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
- የቆየውን ትምህርት ለማስጀመር ከጤና ባሻገር የሰላምና ደህንነት ጉዳይን ጨምሮ ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረግ ይገባል ብለዋል። (ENA)

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከትላንት በስቲያ ለአቶ ልደቱ አያሌው የፈቀደው የ100,000 ብር የዋስትና ፈቃድ መታገዱን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ዘገበ።
ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡ እግዱ በአዳማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ ተብሎ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል ሲል ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ አዟል፡፡

#COVID19Ethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,348 የላብራቶሪ ምርመራ 604 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 208 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 71,687 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,148 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 29,461 ደርሷል።

የዩኒቨርሲቲዎችን እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን ከተቋረጠበት ለማስቀጠል በመሪዎች ደረጃ ዛሬ በተካሄደው ስብሰባ የተቀመጠ አቅጣጫ!
- የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት መጨረሻ የተቋማትን ዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም በአካል እየተገኘ ገምግሞ በቂ የኮቪድ-19 መከላከል ዝግጅት ላደረጉት የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተማሪና ሰልጣኝ እንዲቀበሉ ይፈቅዳል።
- ያለ በቂ ዝግጅት እና ያለሚኒስቴሩ የመስክ ምልከታና ፈቃድ ተማሪዎችን ወይም ሰልጣኞችን ተቀብሎ መገኘት አግባብነት አይኖረውም።
- የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች እና የሥልጠና አጠናቃቂዎች እንዲሁም በሌሎች የትምህርት እና ሥልጠና እርከን ያላችሁ ሁሉ በቀጣይ በሚዲያ በሚታወጀው የተማሪ እና ሰልጣኝ ቅበላ መርሃግብር መሠረት በየተቋሞቻችሁ ጥሪ የሚደረግላችሁ በመሆኑ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ ይሁን።
ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር