TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግድያ እና መፈናቀል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል!

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረጋጋት የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ሰሞነኛ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦

- በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ አልነበረም ሊከሰትም አይገባው ነበር።

- ችግሩ በተፈጠረበት ሰዓት መከላከያ የራሱ ተልዕኮ ላይ ነበር ሠራዊቱ ወደ ስፍራው በማቅናት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራ በጀግንነት ተሰርቷል።

- መከላከያ ከገባ በኋላ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰዱ አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ወደ ቀድሞ ሰላማዊና መረጋጋት እንቅስቃሴ ተመልሷል።

- በማህበራዊ ሚዲያዎች “መካላከያ ቀድሞ ወደ ስፍራው አልደረሰም” በሚል እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

- በክልሎች የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ የማረጋጋት ግዴታ በዋናነት የክልልና የወረዳ የጸጥታ ኃይል ነው መከላከያ የራሱ ግዳጆች ቢኖሩትም ከክልሎቹ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

- በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መከላከያ ግዳጅ እንደተሰጠው ከ150 ኪሎ ሜትር ውስጥ 50 ኪሎ ሜትሩን በእግሩ በመጓዝ በታጣቂዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል። (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TikvahFamilyBulen

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ቲክቫህ አባላት ሚዲያዎች በወቅቱ መረጃ ይፋ ባለማድረጋቸው ቅር እንደተሰኙ ገልፀውልናል።

ሚዲያዎች ጳጉሜ ወር ውስጥ የነበረውን ጥቃት ከሳምንት በኃላ ይቆይተው ትላንት እየተቀባበሉት መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

መረጃዎች በወቅቱ ህዝቡ ጋር መድረስ አለባቸው ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሳይሆን ሁሉም ሚዲያ ዜጎችን በእኩል አይን አይተው በዜጎች ላይ የተፈጠረውን ማሳወቅ ፣ መንግስትም ችግሩን ለመፍታት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በቶሎ ማሳወቅ አለባቸው ብለዋል።

በአሁን ሰዓት ያሉበት አካባቢ ወደ ሰላም እየተመለሰ እንደሆነ ገልፀዋል።

ጳጉሜ ወር ውስጥ በአካባቢው ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን የገለፁልን አባላቶቻችን ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸው አሳውቀውናል።

PHOTO : FDRE DEFENSE FORCE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሶሳ ከተማ 243 ህገ-ወጥ የሽጉጥ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ!

በክልሉ አሶሳ ከተማ 243 ህገ-ወጥ የሽጉጥ ጥይት የያዘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለጸ።

ዛሬ መስከረም 7 የሸርቆሌ ወረዳ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በአሶሳ ከተማ ወረዳ 1 ቀጠና 3 ከመነሀሪያ በስተጀርባ በሚገኝ አንድ መኝታ ቤት ከያዘው ክፍል ውስጥ 243 ፍሬ ህገ-ወጥ የሽጉጥ ጥይት ይዞ በመገኘቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

የከተማ ፖሊስ ተጠርጣሪው ህገ-ወጥ ድርጊቱን የፈፀመው ለግል ጥቅም ለማዋል በማሰብ እንደሆነ ገልጾ ፣ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመስከረም 7 የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 10,605
በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 689
ከበሽታው ያገገሙ - 420
ህይወታቸው ያለፈ - 15

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አቶ እስክንድር እና አቶ ስንታየሁ ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዘዋወሩ!

የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከዚህ ቀደም ታስረውበት ወደ ነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መዛወራቸውን ጠበቃቸው ሔኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ (BBC) ገልፀዋል።

ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ለBBC ከተናገሩት ፦

- ሁለቱ ተጠርጣሪዎች (አቶ እስክንድርና አቶ ስንታየሁ) ብቻ ሳይሆኑ ሌላ አንድ ግለሰብም ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተወስደዋል።

- ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ እስክንድር ላይ ክስ ተመስርቶ ነበር ፤ ፍርድ ቤት ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ አዟል።

- በትናንትናው ዕለት መስከረም 06/2013 ዓ/ም ከነበሩበት የፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት በተለምዶ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ሚባለው ተዘዋውረዋል።

- አቶ እስክንድር ከዚህ ቀደም ከስድስት ዓመታት በላይ በታሰሩበት ስፍራ እና ክፍል ዳግም መታሰራቸውን ተናግረዋል።

- አቶ አስክንድር ከሁለት ወራት በላይ ከቆዩበት ሌላ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ በተለምዶ ዋይት ሐውስ ወደ ሚባለው ክፍል አስገብተዋቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ! በዛሬው እለት ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል። በተጨማሪ…
በሶማሌ ክልል የጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ስራ ተጀመረ!

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎችና የሚመለከታቸው አካላት በስተቀር በሌሎች የክልሉ ነዋሪዎች እጅ የሚገኙ የጦር መሳሪያዎችን መሰብሰብ ጀምሯል።

አሁን በተመረጠ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ይህ የጦር መሳሪያ ስብሰባ ወደፊት በሁሉም የክልሉ ዞኖች ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።

የሱማሌ ክልል ፍትህና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላሂ መሃመድ አብዲ ለቪኦኤ (ጋዜጠኛ አዲስ ቸኮል) ተከታዩን መረጃ ሰጥተዋል ፦

- የክልሉ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በጎሳ ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ በመሆኑ ነው።

- ባለፈው ሳምንት በጎሳ ግጭት የተነሳ የታጠቁ ሰዎች በቱሉ ጉሌድ ወረዳ 7 ሰዎች ላይ ግድያ ፈፅመዋል።

- አሁን ላይ በቱሉ ጉሌድ ወረዳና እና ኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኘው አጎራባች የጭናክሰን ወረዳ ላይ ትጥቅ የማስፈታቱ ስራ በሁለቱ ክልሎች ትብብር እየተሰራ ነው።

- እስካሁን ከምን ያህል ሰዎች ትጥቅ ማስፈታት እንደተቻለ ባይገለፅም አብዛኞቹ AK 47 (በተለምዶ ክላሽንኮቭ) የጦር መሳሪያ ናቸው። ነገር ግን መትረየስን ጨምሮ በግለሰቦች እጅ መኖር የሌለባቸው ከባድ መሳሪያዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ይገኛሉ።

- አሁን በቱሉ ጉሌድ ወረዳ በ4 ቀበሌዎች የተጀመረው ትጥቅ የማስፈታት ስራ ወደፊትም ህዝቡን የማሳመን ስራ እየተሰራ በሁሉም የክልሉ ዞኖች ይተገበራል።

- ድንበር አካባቢ የሚካሄዱ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአስሩ ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት ቁጥራዊ መረጃ ፦

#Afar

በቫይረሱ የተያዙ - 1,408
ያገገሙ - 231

#Amhara

በቫይረሱ የተያዙ - 3,388
ህይወታቸው ያለፈ - 34
ያገገሙ - 2,224

#BenishangulGumuz

በቫይረሱ የተያዙ - 1138
ያገገሙ - 382

#Harari

በቫይረሱ የተያዙ - 1,505
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 693

#Oromia

በቫይረሱ የተያዙ - 9,415
ህይወታቸው ያለፈ - 63
ያገገሙ - 4,415

#SNNPRS

በቫይረሱ የተያዙ - 2,211
ህይወታቸው ያለፈ - 16
ያገገሙ - 1,656

#AddisAbaba

በቫይረሱ የተያዙ - 36,939
ህይወታቸው ያለፈ ድምር - አልተገለፀም
ያገገሙ ሰዎች ድምር - አልተገለፀም

#Tigray

በቫይረሱ የተያዙ - 5,403
ህይወታቸው ያለፈ - 27
ያገገሙ - 4,275

#Somali

በቫይረሱ የተያዙ - 1,375
ህይወታቸው ያለፈ - 26
ያገገሙ - 1,076

#Sidama

በቫይረሱ የተያዙ - 1,897
ህይወታቸው ያለፈ - 22
ያገገሙ - 1,449

#DireDawa

በቫይረሱ የተያዙ - 1,246
ህይወታቸው ያለፈ - 21
ያገገሙ - 1,041

#Gambela

በቫይረሱ የተያዙ - 954
ያገገሙ - 506
ህይወታቸው ያለፈ - አራት በኮሮና ተቋም፣ አምስት ከአስክሬን፣ አስራ አንድ ላብራቶሪ ውጤት በመጠበቅ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እየተካሄደ ነው!

የኢፌዴሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል። የመወያያ አጀንዳዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የጤና ሚኒስቴር አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች በተመለከተ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው 'የ2012 ሀገራዊ ምርጫ' አሁን ላይ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

በጤና ሚኒስቴር በቀረበው መክረ ሀሳብ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እየሰጡ ሲሆን ፥ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጤና ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ!

የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር እንደየአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ምክረ ሀሳብ ማቅረቡን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ፦

- ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በአግባቡ መከናወናቸው የሚያረጋግጥ ግብረ ኃይል በየትምህርት ቤቶቹ ሊቋቋም እንደሚገባ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

- የሰዎችን ቁጥር በመመጠን እና የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መስፈርቶችን በመተግበር ስብሰባ ፣ ሲኒማ ፣ ቲያትር ፣ የስፖርት ዝግጅቶች ፣ ማህበራዊና ሐይማኖታዊ በዓላት፣ የአደባባይ በዓላት፣ ሊፈቀዱ እንደሚገባ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።

- ጤና ሚኒስቴር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በመላ ሀገሪቱ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል ብሏል።

- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በጤና ሚኒስቴር በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በዋነት ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴ እና ለህግ ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ መርቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጽእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በመስቀል አደባባይ የደመራ በአል ማክበሪያ ስፍራን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱም የከተማዋ የከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የቤተክርስቲያኒቷ የሃይማኖት አባቶችም ተሳትፈዋል፡፡

አሁን ላይ ስፍራው የመስቀል ደመራ በአልን ማከበር በሚያስችል መልኩ ተዘጋጀቶ ማየታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጽእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው ደመራ በዓል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በአነስተኛ ቁጥር ሰዎች እንደሚከበር መገለፁን አዲስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሚሌኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ማዕከል እስካሁን ድረስ የ64 ሰዎች ህይወት ማለፉን ማዕከሉ ገለጸ።

ማህበረሰቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አደገኛ መሆኑን በመገንዘብ ጥንቃቄ ከማድረግ እንዳይዘናጋ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን ለኢዜአ የተናገሩት ፦

- ማዕከሉ ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ትናንት ጠዋት በነበረው መረጃ 2 ሺህ 961 ህሙማን አገልግሎት አግኝተዋል፤ ከነዚህም ውስጥ 64 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል። 2 ሺህ 385 ሰዎች አገግመዋል።

- ባለፈው ሶስት ሳምንት በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። የሟቾች ቁጥር መጨመር ብቻ ሳይሆን የጽኑ ታማሚዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው።

- በማዕከሉ አሁን ያሉት ታማሚዎች ሁሉም በመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው።

- በአሁኑ ሰአት 200 ህሙማን በሚሊኒየም አዳራሽ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህክምና ማዕከል ይገኛሉ።

- 224 ቀላልና መካከለኛ የቫይረሱ ምልክት ያለባቸው ህሙማንም ወደ ሌላ የህክምና ማዕከል እንዲዘዋወሩ ተደርጓል።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia