TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤምሲ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ በበርካታ የንግድ ሱቆች ፣መጋዘኖች እና ሬስቶራንቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዛሬ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች በዛሬው ዕለት የ6 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል።

በተጨማሪም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 600ሺህ ብር እና ለአዲስ አመት በዓል ሁለት በሬዎችን በስጦታ አበርክቷል፡፡

ምንጭ፦ Mayor Office of AA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ከሳዐዲ አረቢያ 147 የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት ገብተዋል። በቀጣይ 5 ሳምንታት 2,000 የሚሆኑ የዛሬን ጨምሮ ሴቶችና ህጻናትን ይመጣሉ።

#Tsion
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ!

የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ ጳጉሜ 05/2012 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር------0216884

2ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር---------0837305

3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1811984

4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1956837

5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1958358

6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1265001

7ኛ.300,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር -------1313492

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------ 16554

9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------33425

10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------63841

11ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------0839

12ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------7003

13ኛ.2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----063

14ኛ.20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----14

15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----- 5

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 5/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 94 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 136 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,532 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 103 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 735 የላብራቶሪ 68 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 134 የላብራቶሪ 13 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,034 የላብራቶሪ 52 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

ጳጉሜ 5/2012 ዓ/ም

የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ - 16,665
በቫይረሱ የተያዙ - 878
ህይወታቸው ያለፈ - 8
ያገገሙ - 586

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውድ የቲክቫህ አባላት!

አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤና ፣ የስኬት ፣ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

2013 ዓ/ም በሀገራችን ክፉ የማንሰማበት ፣ የኮሮና ቫይረ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መፍትሄ አግኝቶ ወደ ቀደመው ህይወታቸን የምንመለስበት፣ አድንነታችን የሚጠነክርበት ይሁንልን።

ዓመቱ ሀገራችን እናቶች የማያለቅሱበት፣ አባቶች ማያዝኑበት ፣ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ብሩህ ተስፋ የሚያዩበት ዓመት ያድርግለን።

መልካም አዲስ አመት!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ጳጉሜ 4/2012 በተደረገው ክልላዊ ምርጫ ሕወሓት በአብላጫ ድምጽ አሸነፈ!

የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሕወሓት ከአጠቃላይ የመራጮች ድምጽ 98.2 በመቶ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል።

በዚህም የተነሳ የክልሉ ምክር ቤት ካለው መቀመጫ 152 ወንበር በሕወሓት የተያዘ ሲሆን 38 ደግሞ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።

ሕወሓት የምክር ቤቱን መቀመጫ 80 በመቶ ሲይዝ በቅርቡ በነበረው ውሳኔ መሰረት ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የምክር ቤቱ ምርጫ በምርጫ ተፎካካሪ ለነበሩ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።

80 በመቶውን የያዘው ፓርቲ ቀሪው 20 በመቶ ላይ ይፎካከራል ወይ የሚለው ላይ ድርድር እንደሚኖር ይጠበቃል።

በምርጫው ባይቶና ፣ ትግራይ ነጻነት፣ ሳልሳይ ወያነ እንዲሁም አሲምባ እንደ ቅደም ተከተላቸው ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል።

በክልሉ ምርጫ ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች መሳተፋቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የተደረገው ምርጫ ውጤት ፦

- ህወሓት : (98.2 %)

- ውድብ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) : (0.8%)

- ውድብ ናፅነት ትግራይ: (0.71%)

- ውድብ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ: (0.27%)

- ዴሞክራውያዊ ውድብ ዓሲምባ: (0.01%)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ምርጫ ውጤት (ግዝያዊ)

- ህወሓት 2,590,620 = 1ኛ

- ባይቶና 20,839 = 2ኛ

- ውናት 18,479 = 3ኛ

- ሳወት 3,136 = 4ኛ

- ዓዴፓ 774= 5ኛ

ምንጭ፦ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በዓድዋ ከተማ ህወሓትን ወክለው የቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል : 59,369

- በመቐለ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም : 154,226

- በኣላማጣ አቶ ጌታቸው ረዳ : 94,836

- በመቐለ የባይቶና ሊቀመንበር አቶ ኪዳነ አመነ : 12,048

- በቦራ ሰለዋ የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ጎደፋይ : 109

- በዓዲግራት የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ግርማይ በርሀ : 1,703

በዓኒቴና የዓሲምባ ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም : 156 ድምፅ በማግኘት ተመርጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia