TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የግል ትምህርት ቤቶች በ2013 አመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ ምንም አይነት ክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ለSRTV አስታውቀዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ፋታህ፦

"እንደሚታወቀው ከነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቃል። ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ በፌደራል እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ መሰረት ነው።

አሁን መግለፅ የምፈልገው ግን በግል ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ወቅት ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመምህራን ደሞዝ ለመሸፈን ወላጆችን ክፍያ እንዲፈፅሙ መጠየቁ የሚታወስ ነው።

ዛሬ ላይ ድግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የወቅቱን ሁኔታ በማየት ክፍያ የመጨመር አዝማሚያ የሚታይ በመሆኑ ጉዳዩ ከህግና ስርዓት ውጭ መሆኑን ሊረዱ ይገባል።

በዚህም ከአንዳንድ ወላጆች የደረሱን መረጃዎች በመኖራቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ይህን ጉዳይ የሚከታተል ይሆናል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ሁለት ከተሞች አነስተኛ መጠን ያለው ርዕደ - መሬት መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

ጳጉሜ 3 እና 4 /2012 ዓ/ም በሎግያ-ሰመራ ከተማ በተለያዩ ሰአቶች ሶስት ጊዜ በሬክተር እስኬል መለኪያ ከአንድ እስከ ሁለት የሚለካ ቀላል ርዕደ-መሬት መከሰቱን ዩኒቨርሲቲው ለኢዜአ ገልጿል።

ምንም እንኳን በክስተቱ በአካባቢው የደረሰ ጉዳት ባይኖርም በቀጣይ በአካባቢዉ ተጨማሪ ክትትል እና ጥናቶችን ማድረግ አስፈላጊ ስለመሆኑ አመላካች ነገሮች መኖራቸዉ ተገልጿል።

ርዕደ-መሬቱ የተከሰተዉ በተለይም ጳጉሜ 3 በተለያዩ ሰዓታት መሆኑ የተነገረ ሲሆን ትናንትናም ማምሻውን ጨምሮ በተለያዩ ሰአታት አራት ጊዜ ርእደ-መሬቱ በተመሳሳይ አካባቢዎች ተመዝግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በላሬ ወረዳ ከ5,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል!

በጋምቤላ ክልል በላሬ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ከአምስት ሺ (5,000) ሰዎች በላይ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እደሚገኙ ከጋምቤላ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ጎርፉ ከአቅም በላይ በመሆኑ ህብረተሰቡ ላይ ችግር እየደረሰ ስለሆነ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊቺ ቢየል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የላሬ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ኛዳክ ፓች በተደጋጋሚ በሚጥለው ዝናብ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው እደሚኖሩ ተናግረዋል።

ወይዘሮዋ አክለውም ጎርፉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የአልባሳትና የምግብ ፍጆታ አቅርቦት መንግስት ድጋፍ እንድያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በበኩላቸው በተመሳሳይ ጎርፉ በወረዳው ባሉ 28 ቀበሌዎች ለጊዜው ቁጥራቸው ባይታወቅም ከተጠቀሰው ቁጥር ባላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተጎጅዎቹ ባለባቸው የመጠለያ እና የምግብ ችግር ለተለያዩ በሽታዎች አደሚዳረጉ ገልጸው ችግሮችን ለመቅረፍ የባለድርሻ አካላት ርብርብ እደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa

የሀዋሳ ከተማ ትራንስፓርት እና መንገድ ልማት መምሪያ በትራንስፓርት ዘርፍ ተጥሎ የነበረው ታሪፍ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊት ወደነበረበት መመለሱን ገልጿል።

አሽከርካሪዎች በወንበር ልክ መጫን አለባቸው ተብሏል ፤ ባጃጅ ሾፌሩን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ማሳፈር እንዳለበት ተገልጿል ፤ ከወንበር በላይ በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ሞተር ሳይክልን በተመለከተ አሽከርካሪው ብቻ መጠቀም እንዳለበት ከሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤምሲ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ በበርካታ የንግድ ሱቆች ፣መጋዘኖች እና ሬስቶራንቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዛሬ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች በዛሬው ዕለት የ6 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል።

በተጨማሪም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 600ሺህ ብር እና ለአዲስ አመት በዓል ሁለት በሬዎችን በስጦታ አበርክቷል፡፡

ምንጭ፦ Mayor Office of AA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ከሳዐዲ አረቢያ 147 የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት ገብተዋል። በቀጣይ 5 ሳምንታት 2,000 የሚሆኑ የዛሬን ጨምሮ ሴቶችና ህጻናትን ይመጣሉ።

#Tsion
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ!

የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዛሬ ጳጉሜ 05/2012 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር------0216884

2ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር---------0837305

3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1811984

4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1956837

5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር ---------1958358

6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1265001

7ኛ.300,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር -------1313492

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------ 16554

9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------33425

10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------63841

11ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------0839

12ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------7003

13ኛ.2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----063

14ኛ.20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----14

15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር----- 5

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 5/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 94 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 136 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,532 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 103 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 735 የላብራቶሪ 68 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 134 የላብራቶሪ 13 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,034 የላብራቶሪ 52 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT