TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ ከአራተኛ እስከ 14ኛ የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ…
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነሃሴ 22 ቀን በነበረ ችሎት ሸምሰዲን ጠሃ ያጋጠማቸውን የጆሮ ህመም በመረጡት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ ማዘዙ ይታወሳል።
ተጠርጣሪው በመረጡት የህክምና ተቋም ህክምና እንዳላገኙና ፖሊስ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪው በመረጡት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ እንደጠየቃቸውና እንዳማከራቸው አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪው ምርጫቸውን ባለማሳወቃቸው ወደ ሌላ ሆስፒታል እንዳልወሰዳቸውም ገልጿል፡፡ ነገር ግን ጆሮአቸውን በመታመማቸው መጎዳት ስለሌለባቸው ወደ ፖሊስ ሆስፒታል በመውሰድ ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ዐቃቤ ህግ ለአፈጻጸም እና ለክትትል እንዲያመች ተጠርጣሪው ህክምና የሚያገኙበትን ተቋም ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቁ ጠይቋል፡፡
በዚህም ተጠርጣሪው 'በዋሽንግተን ሆስፒታል' ለመታከም በመምረጣቸው ይህንኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ችሎት! የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች ለአቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ሊሰጥ አይገባም ያሉ ሲሆን ፥ ለደንበኞቻቸው የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ እና የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለጳጉሜ 2 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ…
ተጨማሪ መረጃ ፦
በዛሬው ዕለት (ነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ/ም) ፍርድ ቤት የቀረቡለትን አራት አቤቱታዎች መርምሮ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
• 1ኛ ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሀመድና 2ኛ ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ በእስር በሚቆዩበት ጊዜ ተቀላቅለው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
• 11ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና ሚዲያዎች ዘመቻ ጀምረውብናል በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ማንኛውም መገናኛ ብዙሃን ተጠርጣሪዎቹ ነፃ ሆነው የመገመት መብታቸውን እንዳይጥሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
• ከዚህ ቀደም ተጠርጣሪዎች ከእምነት አባቶች ጋር ለ40 ደቂቃ እንዲገናኙ ያስተላለፈው ትዕዛዝ በጥብቅ እንዲፈጸም አሳስቧል፡፡
• ከሶስተኛ እስከ ዘጠነኛ ድረስ ያሉ ተጠርጣሪዎች የታሰርንበት ቦታ መጸዳጃ ቤት አጠገብ በመሆኑ ይስተካከልልን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ካሉበት ቦታ እንዲዘዋወሩ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለ4 እና 5 ዓመታት ሲያስተማራቸው የነበሩ አራት (4) የአፋን ኦሮሞ የ3ተኛ ዲግሪ / ዶክትሬት ተማሪዎችን ባለፈው ሳምንት አስመርቋል።
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው 4 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በአፋን ኦሮሞ በማቅረብ ታሪክ ሰሩ ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው 4 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በአፋን ኦሮሞ በማቅረብ ታሪክ ሰሩ ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕ/ር ሳሙኤል ሳህሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!
ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ከወጣትነታቸው ጀምሮ በአስተማሪነት እንዲሁም በተመራማሪነት አገልግለዋል፡፡ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ከወጣትነታቸው ጀምሮ በአስተማሪነት እንዲሁም በተመራማሪነት አገልግለዋል፡፡ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስድስት (6) የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ከሚያደርገው ድጋፍ ውስጥ 130 ሚልዮን ዶላር መቁረጡን ተቃውመው ደብዳቤ ፅፈዋል!
ለአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ማይክ ፖምፔዎ የተፃፈ ደብዳቤ "የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ ነው ፣ በኢትዮጵያውያን የገንዘብ አስተዋፅኦ እየተገነባ ያለ ነው።
በዚህ ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ለማቋረጥ መወሰን የአሜሪካ መንግስት በግልፅ ለአንድ ወገን እንዳደላ መገለጫ ነው" ይላል።
Via Elias Meseret (Associated Press)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ማይክ ፖምፔዎ የተፃፈ ደብዳቤ "የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ ነው ፣ በኢትዮጵያውያን የገንዘብ አስተዋፅኦ እየተገነባ ያለ ነው።
በዚህ ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ለማቋረጥ መወሰን የአሜሪካ መንግስት በግልፅ ለአንድ ወገን እንዳደላ መገለጫ ነው" ይላል።
Via Elias Meseret (Associated Press)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዝግ እየመከረ ነው!
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ ምንግስት ትርጉም እና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ እየመከረ ነው።
MORE : https://telegra.ph/FANA-09-05
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ ምንግስት ትርጉም እና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ እየመከረ ነው።
MORE : https://telegra.ph/FANA-09-05
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
CONGRATULATIONS!
የቡሌ ሆራ ዩንቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ መርሀ ግብር ያሰለጥናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎች መካከል 47ቱ በሁለተኛ ድግሪ ሲሆን 236ቱ ደግሞ በመጀመሪያ ግድሪ መርሀ ግብር የተመረቁ ናቸው፡፡
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ (2) ዲግሪ መርሀ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በበይነ መረብ ሲከታተሉ የቆዩ 40 የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ነው ዛሬ ያስመረቀው።
በሌላ መረጃ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በድህረ-ምረቃ እና በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ከCOVID 19 ወረርሽኝ በፊት በቅዳሜ እና እሑድ እንዲሁም በክረምት መርሃ ግብሮች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸው ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ዛሬ ነሐሴ 30/ 2012 ዓ.ም በኦንላይን እያስመረቀ ይገኛል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ!
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አስታውቋል፡፡
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9 (1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡
ሙሉ መግለጫ : telegra.ph/HoF-09-05

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፦
1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤
2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤
3) የትግራይ ክልል ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላትና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በሚል የመጨረሻ ውሳኔ አሳልፏል።

ነሃሴ 30/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 422 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 366 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 5 ከአሶሳ ከተማ መናኸሪያ
- 1 ከጾሬ ስደተኛ መጠለያ
- 3 ከማኦ ኮሞ ጉራስምቦላ ስደተኛ መጠለያ
- 1 ከህዳሴ ኤርፖርት ይገኙበታል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 8,216 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 60 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 13 ከደ/ወሎ ዞን
- 13 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 8 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 6 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ይገኙበታል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 621 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
#Tigray
በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,265 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 101 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 80 ሰዎች ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot

#COVID19Ethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 24,544 የላብራቶሪ ምርመራ 950 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 164 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 57,466 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 897 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,776 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 24,544 የላብራቶሪ ምርመራ 950 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 164 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 57,466 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 897 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,776 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 30/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,315 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከጌዴኦ ዞን - በህክምና ማዕከል የነበሩ የ45 ዓመት ሴት)
በቫይረሱ የተያዙት፡-
• ከደቡብ ኦሞ ዞን 19 (ሰሜን አሪ 8፣ 5 ከኦሞራቴ፣ 4 ከበናጸማይ እና 2 ከሀመር)፣
• ከጋሞ ዞን 12 (6 ምዕራብ አባያ፣ 5 ከጋጮባባ እና 1 ከአርባምንጭ ዙሪያ) ፣
• ከአማሮ ልዩ ወረዳ 10፣
• ከወላይታ ዞን 9 (3 ከሶዶ ከተማ፣ 2 ከአባላ አባያ፣ 2 ከሆቢቻ ፣ 1 ከዳሞ ጋሌ እና 1 ከቦሎሶ ቦምቤ)፣
• ከከምባታ ጠምባሮ ዞን 7 (4 ከዱራሜ ከተማ እና 3 ከቀዲዳ ጋሜላ) ፣
• ከቤንች ሸኮ ዞን 6 (4 ከሚዛን ከተማ እና 2 ሰሜን ቤንች ) ፣
• ከደራሼ ልዩ ወረዳ 3
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 386 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Afar
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 470 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 37 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 813 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 42 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት፦
- 23 ከሀዋሳ ከተማ
- 13 ከሸበዲኖ ወረዳ
- 6 ከወንዶ ገነት
@tikvahethiopiaBOT