TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስ (COVID- 19) የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት ለተመርማሪዎች በ8335 በእጅ ስልካቸው የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚያስችል ስራ መጀመሩ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

EPHI ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የላቡራቶሪ ናሙና የተወሰደላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ የናሙና ምርመራ ውጤት ከተረጋገጠ በኋላ ከሶስት (3) ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በ8335 በጠቀም ተመርማሪዎች ውጤቱን በSMS እንዲደርሳቸው እየተደረገ ይገኛል።

ውጤቱ በትክክል መድረሱን የሚያረጋግጥ የአሰራር ዘዴ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እየተሰራ ሲሆን ፣ ተመርማሪዎች ግን ትክክለኛ የስልክ ቁጥራቸውን ማስመዘገብ እንዳለባቸው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ የተመረቀው ኃይሌ ሪዞርት አዳማ ፦

- 500 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል

- ግንባታውን ለማጠናቀቅ 2 ዓመታትን ወስዷል

- ለ300 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል

- የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን አካቷል

- ባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 28/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 600 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 32 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,021 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 142 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 35 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 14 ከአዳማ ከተማ
- 12 ከምስራቅ ሸዋ
- 9 ከነቀምቴ ከተማ
- 6 ከሞጆ ከተማ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 449 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው (የባምቢስ ወረዳ ነዋሪ) በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 7,176 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 12 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 11 ከሰ/ወሎ ዞን
- 7 ከደሴ ከተማ
- 7 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 594 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ20 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 20,778 የላብራቶሪ ምርመራ 804 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 380 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 55,213 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 856 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,283 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 28/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,802 የላብራቶሪ ምርመራ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከከምባታ ጠምባሮ ዞን)

በቫይረሱ የተያዙት፦
• ከደቡብ ኦሞ 34 ( 11 ከጂንካ ከተማ፣ 9 ከማሌ፣ 5 ከባካዳውላ፣ 3 ከሐመር፣ 2 ከበናፀማይ፣ 2 ከኡባአሪ፣ 1 ደቡብ አሪ እና 1 ከኛጋቶም)፣
• ከጋሞ 13 ( 8 ከአርባምንጭ ዙሪያ፣ 3 ከቁጫ አልፋ እና 2 ከአርባምንጭ ከተማ) ፣
• ከቤንች ሸኮ 12 (11 ከሚዛን ከተማ እና 1 ከደቡብ ቤንች)
• ከጉራጌ 11 (11ዱም ከቡኢ)፣
• ከወላይታ 6 (4 ከሶዶ ከተማ፣ 1 ከቦሎሶ ቦንቤ እና 1 ከዱጉና ፋንጎ ፣
• ከጌዴኦ 5 (2 ከጮርሶ፣ 2 ከረጲ እና 1 ከኮቾሬ) ፣
• ከጎፋ 4 (4ቱም ከመለኮዛ) ፣
• ከካፋ 1 (ቦንጋ) ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 377 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 64 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 438 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 187 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,108 ላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 91 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 982 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,769 የላብራቶሪ ምርመራ 982 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 322 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 29,876 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 528 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 12,359 ደርሷል።…
ከ17 ቀናት በኃላ የተመዘገበው ዝቅተኛ ኬዝ!

በኢትዮጵያ ከ17 ቀናት በኃላ በ24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከ1,000 በታች ሆኖ ዛሬ ተመዝግቧል።

ነሃሴ 10/2012 በ24 ሰዓት 982 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ሪፖርት ተደርጎ ነበር ፤ ከዛ በኃላ እስከ ትላንት ነሃሴ 27 ድረስ በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 1,000 በላይ ሆኖ ሲመዘገብ ቆይቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikvahFamilyAfar

በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ ውስጥ በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያስፋጋቸው በአሚባራ ወረዳ የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

- በወረር 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጠለሉት 2,000 ይደርሳሉ ፤ እንዲሁም በየሰው ግቢ ነው የተጠለሉ አሉ።

- የሸለቆ ህብረተሰብ ተራራ ላይ ነው ያሉት። በግምት 2,000 ይጠጋሉ። እነሱም ጋር ደርሷል።

- የሰርካሞ ነዋሪዎች በተመሳሳይ ተከበዋል። በግምት 500-1500 የሚሆኑ ናቸው።

- የአምባሽ ነዋሪዎች ደሞ ወደ ጋራ አምባሽ ተራራ ወተዋል። ውሀው ወደነሱ በመድረስ ላይ ስለሆነ ወደ ተራራ ወተዋል።

- ገበያ ሰፈር፣ እርሻ ምርምር፣ ድርቅ ቀበሌ እነዚህ ሙሉ ለሙሉ ገብቶባቸው ተፈናቅለው። ያሉትም በወረር 1ኛ እና 2ተኛ ትምህርት ቤት እና ውሃ ባልደረሰባቸው የወረር አካባቢ በየሰው ግቢ ይገኛሉ።

27/12/2012 የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸውና ስጋት ላይ ያሉ የአሚበራ ወረዳ ቀበሌዎች እና አከባቢዎች :–

1. ገበያ ሰፈር
2. እርሻ ምርምር
3. ኡንደዳ
4. ከዲጋ ዶራ
5. ሸለቆ
6. አምባሽ
7. አራጌ
8. ክፍል ሶስት
9. ሰርከሞ
10. ሃሶባ
11. አልጌታ
12. ሀላይ ሱመሌ
13. ኤኤብሌ

1 እና 2 ቁጥር የወረር ወረዳ አካባቢዎች ናቸው። የቀሩት ግን አጎራባች ቀበሌዎች መሆናቸውን አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

#TikvahFamilyAmibaraAfar

@tikvahethiopiaBOT
የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሶስተኛ ዓመት ነገ ሊከበር ነው!

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነገ ቅዳሜ ነሃሴ 30 3ተኛ ዓመቱን እንደሚያከብር አሳውቋል።

ሬድዮ ጣቢያው የተመሰረተበትን ሶስተኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶ እንደሚያከብር የገለፀ ሲሆን ነገ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ልዩ የሬድዮ ዝግጅቶችን አዘጋጅቷል።

በዚሁ እለት (ነሃሴ 30) ከሰዓት በEBS (ኢቢኤስ) ቴሌቪዥን የምስረት ሶስተኛውን ዓመት የምስረታ በዓሉን እንደሚያከብር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈው ነርስ!

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት (ሀሙስ ነሃሴ 28/2012) በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። ነርሱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው ማለፉ ሆስፒታሉ አሳውቋል።

ምንጭ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌደሬሽን ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቻኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2ዐ12 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገው ዕለት የሚካሄደው የፌደሬሽን ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ካልታወቀ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይገኙ የክልሉ ም/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ መግለጫ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ምርጫ ለማደናቀፍ ውሳኔ የሚያስተላልፍ ከሆነ የጦርነት አዋጅ እንደማወጅ መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ የጥፋት ድርጊቱ እንዲቆጠብ የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ ትላንት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

የትግራይ ክልል መንግስት ካቢኔ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የትግራይ ክልላዊ ምርጫ በህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የሚካሄደ እስከሆነ ድረስ የማንም ጣልቃገብነትና ጫና ለደቂቃዎችም ቢሆን ሊያስቆመው አይችልም ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውሃን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመለሱ!

የዉሀን ከተማ ከሰባት ወራት በኋላ ትምህርት ቤቶች ዳግም ተከፍተው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ተመልሰዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙት ከ2,800 በላይ የትምህርት ተቋማት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህል ተማሪዎችን ተቀብለው ትምህርት ጀምረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ መነሻ በምትባለው ዉሀን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ቢጀምሩም ወላጆችና መምህራን ግን አሁንም ያላቸውን ስጋት እየገለጹ ነው።

በሌላ መረጃ፦

የዚምባብዌ መንግሥት በሚቀጥሉት ሁለት (2) ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱና በዓመቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና እንደሚቀመጡ አስታወቀ።

'ካምብሪጅ' ለሚባለው ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች በፈረንጆቹ መስከረም 14 ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ ተብሏል።

ለዚምባብዌ ትምሀርት ቤት ፈተናዎች የሚቀመጡ ተማሪዎች ደግሞ መስከረም 18 ትምህርታቸው የሚጀምሩ ሲሆን ፈተናውን ደግሞ ታህሳስ ወር ላይ እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።

መንግሥት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ከትምህርት ኃለፊዎችና የጤና ባለስልጣናት ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ እና ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቡሬ ኢንደስትሪ ፓርክ ስራ የጀመረው ሪችላንድ የመጀመሪያውን ዙር የአኩሪ አተር ዱቄት ምርት ለኤክስፓርት አዘጋጀ።

በየቀኑ አራት መቶ ቶን ኤክስፖርት ያደርጋል $200,000 እንደሚያስገኝ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። የሀይልና የጥሬ እቃ አቅርቦቱ ልዩ ድጋፍ እንደሚጠይቅም አቶ መላኩ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጳጉሜ 3 ተማሪዎቹን ያስመርቃል!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ትምህርት ዘመን በመደበኛ የድህረ ምረቃ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር በቅድመ ምረቃ ያስተማራቸውን 938 ተማሪዎችን ጷጉሜ 03/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኦንላይ (Online) እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም እንዲያቀርብ የመጨረሻ ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

ፖሊስ ለዛሬ ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት የነበር ቢሆንም ሳያቀርብ ቀርቷል።

በዛሬው ችሎት ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የተከሳሾች ጠበቃ ፖሊስ በተደጋጋሚ እያስቀጠረ መረጃ ማቅረብ አለመቻሉን ጠቅሰው ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ተጨማሪ ሶስት (3) ቀን ሰጥቶታል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነአርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እስካሁን ከእስር አልተፈቱም ሲሉ ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል!

እነኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ምስክሮች ቃላቸዉን እንዲቀይሩ ሲያባብሉ ነበር ተብለው በቀጥጥር ስር የዋሉት አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ቢያዝም ፓሊስ እንዳልፈታቸው ጠበቃቸው ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

- ነሃሴ 25/2012 እና ነሃሴ 26/2012 በዋስትና ጉዳይ ሰፊ ክርክር ተደርጎ ዳኛው ጊዜ ያስፈልገኛል በሚል ሁለት ቀን ወስዶ ትላንት ብይን ተሰጥቷል፤ የዋስትና መብታቸው በህጉ የሚያስከለክል አይደለም ጠበቆችም ያነሱት የህግ መሰረት ያለው ነው በሚል የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤት ወስኗል።

- ትላንት ለዋስትና የሚስፈልጉ ሁሉንም መስፈርቶች ተሟልቶ ካለቀ በኃላ ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሲኬድ አቃቤ ህጓ ይግባኝ ልትል ስለምትችል በሚል ሰበብ ፌደራል ፖሊስ ቤተሰቦችን አትገቡም ብሎ ከልክሏል።

- ትላንት 6:00 ሰዓት ፍርድ ቤት ይፈቱ ብሎ ትዕዛዝ ቢሰጥም ዛሬም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። ፖሊስ እያደረገ ያለው ድርጊት ከህግ አግባብ ውጭ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈው ነርስ! በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት (ሀሙስ ነሃሴ 28/2012) በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። ነርሱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው…
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባልደረባ የነበሩት ነርስ አምበሳአውድም ዮሃንስ የአስክሬን ሽኝት በሆስፒታሉ ሰራተኞችና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በ28-12-2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየተዋል፡፡

ምንጭ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia