TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት በቪድዮ እና በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ አሳውቀዋል። በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ መንገዶች ተዘግተው እንደነበረ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው በመግባት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠርና፣ መንገዶችን ለመክፈት እየሞከረ እንደሆነ ሰምተናል። በድምፅ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት በከተማይቱ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ…
#UPDATE
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸውን አል ዓይን አረጋግጧል፤ አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ከነበሩበት የተያዙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በከተማው ሁከት መከሰቱም ገልጿል።
የዞኑ አመራሮች ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከፌዴራል እና ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።
የዞኑ ክልል የመሆን ጥያቄ በደቡብ ክልል መንግስት ተገቢው ምላሽ አልተሰጠውም በሚል ተቃውሞ በክልሉ ምክር ቤት የዞኑ ተወካዮች ራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት ራሳቸውን ካገለሉ ከ6 በላይ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
የዞኑ ተወካዮች ወደ ም/ቤት እንዲመለሱ በክልሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስካሁን አልተቀበሉም። የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በራሱ ጊዜ ዞኑን በክልል ለማደራጀት ወስኖ ይህን ስራ የሚያስፈጽም ምክር ቤት ማቋቋሙ ይታወሳል።
Via AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!
የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገልጿል።
ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉችን አሳልፏል።
የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል።
የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለOBN ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል።
እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል።
አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

Photo
#UPDATE
'በወላይታ ሶዶ ክርስትያን ሆስፒታል' የጤና ባለሞያ የሆነ የቲክቫህ አባል ባለፈው 1 ሰዓት ውስጥ ከ15 በላይ በጥይት የተመቱ ሰዎች እንዳየ ገልጿል። አንዳንዶች በፀና የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉም ብሏል።

#UPDATE የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸውን አል ዓይን አረጋግጧል፤ አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ከነበሩበት የተያዙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በከተማው ሁከት መከሰቱም ገልጿል። የዞኑ አመራሮች ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከፌዴራል እና ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የዞኑ ክልል የመሆን ጥያቄ…
#UPDATE
የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት ባወጣው መግለጫ የዎላይታ ዞን አመራሮች እና ከተለያየ አደረጃጀት የተወጣጡ የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት በዎላይታ ጉታራ ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት ድንገት በመጣ የመከላከያ ኃይል ታፍነው ታስረዋል ሲል ገልጿል፡፡
የዎላይታ ዞን ኮር አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች፣ የድርጅቱ (ዎብን) አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ ፣ የዎህዴግ ም/ሊቀመንበር ፣ የተለያዩ አክቲቪስቶች እና ሌሎች የክልል ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አባላት ታፍነው ታስርዋል ሲል ዎብን አስታውቋል።
ዎብን የፌዴራልና የደቡብ ክልል መንግሥታት የዎላይታ ሕዝብ ሠላማዊ ጥያቄ ወደ ሁከት ለመቀየር የሚያደርጉትን ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲያቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለንም ብሏል።

በቤሩት የአንዲት ኢትዮጵያዊት ህይወት አለፈ!
በሊባኖስ መዲና ቤይሩት ከተማ በቅርቡ በተከሰተው ፍንዳታ ተጨማሪ አንድ ኢትዮጵያዊት ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል።
ህይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት በፍንዳታው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት በጽኑ ህሙማን ክፍል የህክምና እርዳታ ሲደረግላት ቆይታ ትላንት ሕይወቷ አልፏል።
በፍንዳታው ሕይወታቸው አልፎ ማነታቸው እና ዜግነታቸው ያልታወቁ ዜጎች ላይ በተደረገ የማጣራት ስራ ኢትዮጵያዊያን እንደማይገኙ ተረጋግጧል።
በቤሩቱ ፍንዳታ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ሁለት መድረሱን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ አስታውቋል።

ዛሬ አመሻሹን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች ለደቡብ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ የዎላይታ ዞን አመራሮች በዞኑ ኮማንድ ፖስት ዛሬ ከሰዓት መያዛቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አለማየሁ ባውዲ እንዳሉት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ህገወጥ አደረጃጀቶችን ፈጥረው ግጭት የመቀስቀስ ፍላጎታቸውን እንዲያስፈጽሙ እያደረጉ ነበር ብለዋል።
አመራሮቹ በፓርቲ ደረጃ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ሀገር ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ ይገኛሉም ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ አለማየሁ ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ በማለት ከገለጿቸው ህወኃትና ኦነግ ሸኔ አካላት ጋር በድብቅ ሰው እየላኩ ስብሰባ እንደሚያደርጉ እና ተልዕኮ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል፤ለዚህም ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት መረጃዎች ተገኝተዋል ብለዋል።
የኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ በመተላለፍ ህገወጥ ስብሰባዎች እንዲሁም ሰልፎችን እንዳደረጉ ተገልጿል። ህብረተሰቡ የሰጡትን አመራር ቢቀበላቸው አካባቢው ግጭቶች ይፈጠሩ እንደነበር አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።
አቶ አለማየሁ ከህገ መንግሥት ውጭ በመንቀሳቀስ ክልሉን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልፀው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም በእኩይ ድርጊታቸው መቀጠሉን ምረጣቸውን አብራርተዋል።
የዞኑ ህዝብ የአመራሩን የጥፋት ተልዕኮ ሳይቀበል መቆየቱን በመጥቀስ ሃላፊው ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት ዞኑ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ህዝቡ የሰላም እሴቱን እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችን ጨምሮ 26 ግለሰቦች መሆናቸውን አል አይን ዘግቧል።
@tikvahethiopia

ነሀሴ 4/2012 ዓ/ም - ወላይታ ሶዶ!
ወላይታ ሶዶ ከተማ ሙሉ በሙሉ #አለመረጋጋቷን ማረጋገጥ ችለናል። አሁንም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀዋል።
በዛሬው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውን ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
በተጨማሪም ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የንግድ እንዲሁም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመኖሩን የቲክቫህ ኢትዮ. አባላት አሳውቀዋል።
ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ተለያዩ ወረዳዎች የሚደረግ ጉዞ ተቋርጧል/የለም። አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊትና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል በከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የአቶ ልደቱ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል!
በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የኢዴፓ አመራር የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የ7 ቀን ጊዜ መፍቀዱን ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የኢዴፓ አመራር የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የ7 ቀን ጊዜ መፍቀዱን ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ20 ሚሊዮን አለፉ!
በዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 20,040,924 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 734,247 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 12,911,386 ሰዎች አገግመዋል። በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል 1,052,094 ሰዎች ከአፍሪካ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 20,040,924 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 734,247 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 12,911,386 ሰዎች አገግመዋል። በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል 1,052,094 ሰዎች ከአፍሪካ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
የቦዲቲ ከተማ ቲክቫህ አባላት ዛሬም አለመረጋጋቱ መቀጠሉን አሳውቀዋል ፤ በከተማው የሰዎች ህይወት ማለፉንም አረጋግጠዋል ፤ የንግድና ትራንስፖርት እንቅስቃሴም ቆሟል።
PHOTO : የቦዲቲ ከተማ ቲክቫህ አባላት

ችሎት!
የኢሃን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እና ም/ቤት አባል አቶ ወንዳለው አስናቀ ዛሬ ነሃሴ 4 ቀን በቀጠሯቸው መሰረት ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል።
ፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን ፍ/ቤቱ 9 ቀናት ፈቅዷል።
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እና አቶ ወንዳለው አስናቀ በፖሊስ ታስረው ክስ ሳይመሰረትባቸው አርባ (40) ቀናት መቆጠሩን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ። በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በልደታ አዳራሽ ነው መስማት የጀመረው።
Via Tarik Adugna (FBC)

በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸውን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) አስነብቧል።
ችሎቱ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በልደታ አዳራሽ መስማት ተጀምሮ ነበር።
ይሁን እንጅ እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ጉዳያችንን ገለልተኛ ሆኖ ላይመለከትልን ስለሚችል ከመዝገባችን ላይ ይነሳልን ሲሉ ባለ 7 ገጽ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ተመልክቶ ዳኛው መዝገቡ እንዲመረመር እና በመዝገቡ ላይ ትዕዛዝ እስከሚሰጥበት ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲቆዩ እና መጥሪያ ሲደርሳቸው የሚመጡ ይሆናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል፡፡
Via Tarik Adugana (FBC)

ኦነግ 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት እንደታሰሩበት አስታወቀ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል፤ ኦነግ በመግለጫው 600 የሚሆኑ አባላቶቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታውቋል።
ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ብንወስንም የድርጅታችን አመራሮች እና አባላትን ማሰር እና ማጠልሸት እየተሰራ ነው ብሏል።
በኦነግ እና በሕወሓት መካከል አለ እየተባለ የሚወራው ግንኙነት ፍፁም ሀሰትና የሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት የጦርነት ግንኙነት ነው ሲልም ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ ኦነግ በርካታ አባላት ስላሉን 100 በመቶ ሰላማዊ ትግሉን ተቀብለው ይንቀሳቀሳሉ የሚል ሙሉ እምነት የለንም ሲል መናገሩን አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

ዛሬ ከአዲስ ዘመን ወደ ጎንደር በሚወስደውና ቋላ ዮሐንስ ከሚባለው ዳገታማ ሥፍራ ላይ በናዳ ምክንያት መንገዱ ተዘግቶ ነበር፤ ይህ መንገድ በአሁን ሰዓት ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia