በኦሮሚያ ክልል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከ1,900 አለፉ!
በኦሮሚያ ክልል ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት በእጅጉ እየጨመረ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 2,139 የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 111 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከአንድ መቶ አስራ አንዱ (111) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል ሰላሳ ሁለቱ (32) ሰዎች ነቀምቴ ከተማ ናቸው።
በአጠቃላይ በክልሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,932 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የቲክቫህ የትዊተር ገፅ!
ትዊተር ላይ የምታዘወትሩ የቲክቫህ አባላት የኢትዮጵያን ሀገር አቀፍና የክልል የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ከታች ባለውን ሊንክ ማግኘት ትችላላሁ።
TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia):

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ22 ሺህ አለፉ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 10,919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 292 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,253 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 390 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,707 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 10,919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 292 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,253 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 390 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,707 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት!
በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 71,297 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ ሀገራት የ1,780 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 36,080 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።
በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የትዊተር ገፅ አማራጭ!
ምንም እንኳን ከ8 ዓመት በፊት የትዊተር ገፁ የተከፈተ ቢሆንም አክቲቭ ሳይሆን እስከዛሬ ቆይቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ለመላው የቲክቫህ አባላት ትዊተር ላይ አማራጭ የመረጃና የሀሳብ መለዋወጫ ሆኖ ቀርቧል።
በተለይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦቻችሁ ለመስጠትና እርስ በእርስ ፍፁም መከባበር በተሞላበት መልኩ ለመነጋገር የትዊተር ገፁን እንደ አማራጭ ተጠቀሙት።
የትዊተር ተጠቃሚዎች ገፁን TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia): ታገኛላችሁ!

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ የምርመራ አቅምን ለማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ከፍቶ ትናንት ስራ ማስጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።
ዩኒቨርሲቲው በጎባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለማስጀመር እንዲቻል የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያውን በድጋፍ ያገኘው ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የምርመራ መሳሪያ በቀን እስከ አራት መቶ ናሙና የመመርመር አቅም አለው ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ የምርመራ አቅምን ለማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ከፍቶ ትናንት ስራ ማስጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።
ዩኒቨርሲቲው በጎባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለማስጀመር እንዲቻል የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያውን በድጋፍ ያገኘው ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የምርመራ መሳሪያ በቀን እስከ አራት መቶ ናሙና የመመርመር አቅም አለው ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአማራ ክልል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከ700 ሲያልፉ፤ በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ከ2,000 አልፈዋል!
አማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 2,542 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 4 ከደሴ ፣ 3 ከባህር ዳር ፣ 6 ከደ/ወሎ ዞን ፣ 4 ከሰ/ሸዋ ዞን፣ 5 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን፣ 1 ከአዊ ብ/ሰብ ዞን፣ 1 ከሰ/ወሎ ዞን ይገኙበታል።
በአጠቃላይ በአማራ ክልል አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 703 ደርሰዋል፤ 489 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 7 ሰዎች ህወታቸው አልፏል።
በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 2,010 ደርሰዋል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ከ976 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከሰባ ስምንቱ (78) መካከል 36 ሰዎች ከምስራቅ ሸዋ፣ 11 ሰዎች ከቡራዩ ፣ 8 ሰዎች ከለገጣፎ ፣ 8 ሰዎች ከነቀምቴ፣ 4 ሰዎች ከዱከም ፣ 3 ሰዎች ከሆለታ ይገኙበታል።
ትዊተር የምትጠቀሙ TIKVAH-ETHIOPIA : https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia):

#COVID19
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግስታቸው 100,000 መመርመሪያ ኪቶችን በዛሬው ዕለት መረከቡን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፉን ላደረጉ የኢትዮጵያ አጋሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት በቪድዮ እና በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ አሳውቀዋል።
በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ መንገዶች ተዘግተው እንደነበረ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው በመግባት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠርና፣ መንገዶችን ለመክፈት እየሞከረ እንደሆነ ሰምተናል።
በድምፅ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት በከተማይቱ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሆነም ገልፀዋል።
የከተማይቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት እንደሚናገሩት መነሻው በስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ተሳታፊዎች መታሰራቸው በመሰማቱ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,035 የላብራቶሪ ምርመራ 565 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 499 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,818 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 407 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,206 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,035 የላብራቶሪ ምርመራ 565 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 499 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,818 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 407 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,206 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ አለመረጋጋት መፈጠሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ አባላት በቪድዮ እና በፎቶ አስደግፈው በላኩት መረጃ አሳውቀዋል። በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ መንገዶች ተዘግተው እንደነበረ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው በመግባት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠርና፣ መንገዶችን ለመክፈት እየሞከረ እንደሆነ ሰምተናል። በድምፅ መልዕክታቸውን ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት በከተማይቱ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ…
#UPDATE
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸውን አል ዓይን አረጋግጧል፤ አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ከነበሩበት የተያዙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በከተማው ሁከት መከሰቱም ገልጿል።
የዞኑ አመራሮች ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከፌዴራል እና ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።
የዞኑ ክልል የመሆን ጥያቄ በደቡብ ክልል መንግስት ተገቢው ምላሽ አልተሰጠውም በሚል ተቃውሞ በክልሉ ምክር ቤት የዞኑ ተወካዮች ራሳቸውን ከምክር ቤት አባልነት ራሳቸውን ካገለሉ ከ6 በላይ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
የዞኑ ተወካዮች ወደ ም/ቤት እንዲመለሱ በክልሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስካሁን አልተቀበሉም። የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በራሱ ጊዜ ዞኑን በክልል ለማደራጀት ወስኖ ይህን ስራ የሚያስፈጽም ምክር ቤት ማቋቋሙ ይታወሳል።
Via AlAin

የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!
የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገልጿል።
ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉችን አሳልፏል።
የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል።
የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለOBN ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል።
እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል።
አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

Photo
#UPDATE
'በወላይታ ሶዶ ክርስትያን ሆስፒታል' የጤና ባለሞያ የሆነ የቲክቫህ አባል ባለፈው 1 ሰዓት ውስጥ ከ15 በላይ በጥይት የተመቱ ሰዎች እንዳየ ገልጿል። አንዳንዶች በፀና የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉም ብሏል።

#UPDATE የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኮምቤን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በመከላከያ ሰራዊት መያዛቸውን አል ዓይን አረጋግጧል፤ አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ከነበሩበት የተያዙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በከተማው ሁከት መከሰቱም ገልጿል። የዞኑ አመራሮች ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከፌዴራል እና ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። የዞኑ ክልል የመሆን ጥያቄ…
#UPDATE
የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት ባወጣው መግለጫ የዎላይታ ዞን አመራሮች እና ከተለያየ አደረጃጀት የተወጣጡ የዎላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት በዎላይታ ጉታራ ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት ድንገት በመጣ የመከላከያ ኃይል ታፍነው ታስረዋል ሲል ገልጿል፡፡
የዎላይታ ዞን ኮር አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች፣ የድርጅቱ (ዎብን) አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ ፣ የዎህዴግ ም/ሊቀመንበር ፣ የተለያዩ አክቲቪስቶች እና ሌሎች የክልል ምሥረታ አስተባባሪ ካውንስል አባላት ታፍነው ታስርዋል ሲል ዎብን አስታውቋል።
ዎብን የፌዴራልና የደቡብ ክልል መንግሥታት የዎላይታ ሕዝብ ሠላማዊ ጥያቄ ወደ ሁከት ለመቀየር የሚያደርጉትን ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲያቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለንም ብሏል።