TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዒድ ሙባረክ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Ethiopia) እንኳን ለ1441ኛው ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!

በዚህ አጋጣሚ በዓሉን ስናከብር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን መተግበር #እንዳንዘነጋ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 915 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,957 የላብራቶሪ ምርመራ 915 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 187 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 17,530 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 274 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,950 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በአማራ ክልል ከዛሬ ሐምሌ 24 ጀምሮ በሁሉም አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ መሆኑን የኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠሪያ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

በክልሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማያደርጉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

የእምነት ተቋማት ፣ መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ማህበረሰቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መልዕክት ለወጣቶች!

"ከዚህ በፊትም ተናግረናል አሁንም እንደገና እንናገራለን ፥ ወጣቶች በበሽታው (COVID-19) የማይበገሩ አይደሉም ፤ ወጣቶች በበሽታው ሊጠቁ ፣ ሊያስተላልፉና ሊሞቱ ይችላሉ" - ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም (የWHO ዋና ዳይሬክተር)

Via Doctor Lia Tadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰተማራቸውን ከ1 ሺህ በላይ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቹን በኢንተርኔት በተካሄደ የቀጥታ ሥርጭት (በቨርቹዋል) ዛሬ ሐምሌ 25/2012 ዓ/ም አስመርቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ASTU

አዳማ ሳይንሳና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት መምህራንና ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለፕሮፌሰር አሰፋ አባሁና እና ለፕሮፌሰር አማን ደቀቦ መሆኑን ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ2012 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ለ2 ወራት ተምረው እንዲመረቁ አቅጣጫ ተቀመጠ!

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው በቤታቸው የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎችን ያቋረጡትን ትምህርት ከ45 ቀን እስከ 2 ወር በሆነ ጊዜ ውስጥ ተምረው በማጠናቀቅ እንዲመረቁ አቅጣጫ መቀመጡን 'አዲስ ማለዳ ጋዜጣ' በዛሬው ዕትሙ መረጃውን ይዞ ወጥቷል።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለፀው ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች በተቀመጠው ጊዜ ያለፋቸውን ትምህርት አጠናቀው ወደ 2013 የትምህርት ዘመን እንዲሸጋገሩ ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው አቅጣጫ ተማሪዎች መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመለሱ ቀን እንዳልተቆረጠለት ተመላክቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለስ እንዳለባቸው ኮቪድ-19 ያለበትን ደረጃ ያገናዘበ የመንግስትን ውሳኔ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 469 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,358 የላብራቶሪ ምርመራ 469 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 245 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 17,999 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 284 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 7,195 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‘ማንም’ የተሰኘ አገር አቀፍ የኮቪድ-19 መከላከል ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በይፋ ተጀመረ!

‘ማንም’ የተሰኘ አገር አቀፍ የኮቪድ-19 መከላከል ንቅናቄ እና ምርመራ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

በዘመቻው በነሃሴ የመጀመሪያዎቹ ሁለት (2) ሳምንታት 200 ሺህ ሰዎችን የመመርመር ዕቅድ ተይዟል።

የብሄራዊ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከል ሚኒስትሮች ኮሚቴ የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ ውይይት አካሂዷል።

ኮሚቴውን የሚመሩት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ዘመቻው ከነገ ጀምሮ በይፋ እንደሚጀመር ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት!

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 61,997 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ ሀገራት የ1,597 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 29,712 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'One Voice for Our Dam'

ለግድባችን ያለንን ድጋፍ ነገ እሁድ ሐምሌ 26/2012 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሁላችንም በአንድ ላይ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በያለንበት ሆነን በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምፃችንን እናሰማለን!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ለሚመለከተው አካል!

ለኮቪድ-19 ፈጣን ምላሽ በኮንትራት ተቀጥረው እየሰሩ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የተላከ መልዕክት ፦

"ለህዝባችን ስንል ነፍሳችን ሁሉ ከመስጠት ወደኃላ ሳንል ፣ ቀንና ሌሊት ፣ ሰንበትን ጨምሮ የዓመት በዓላት ለህዝባችን ስንል እየሰራን ነዉ። ሞትን እየተጋፈጥን ቢሆንም ስራዉን በአግባቡ እየሰራን እንገኛለን።

ነገር ግን ከ70% በላይ ስራ የሚሰራዉ ኮንትራት ተቀጣሪ ሆኖ ሳለ የተጋላጭነት ክፍያ ፣ የማበረታቻ አበል ፣ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ የሚሆኑት ቋሚ ተቀጣሪዎች ናቸዉ።

የራስ መጠበቂያ ቁሳቁስ (mask,sanitizer...) እራሱ ባግባቡ እየተሰጠን አይደለም። ምንድነዉ ችግራችሁ የሚለን ባለስልጣንም የለም። ለህዝብ እንዲሁም ለመንግስት ድምጻችን ሊያሰማ የሚችል ሚድያም አጥተናል። ነፍስ ለሰጠ ምላሹ ይህ ነዉ ወይ ?"

እናመሠግናለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ18 ሚሊዮን አለፉ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 18,045,009 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 689,203 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 11,343,229 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ 10:00 ሰዓት - ድምፃችን ለግድባችን!

ዛሬ በ 10:00 በመላው ዓለም የምንገኝ የኢትዮጵያ ዜጎች በጋራ ሆነን ድምፃችንን ለግድባችን የምናሰማ ይሆናል።

በተለያዩ የጋራ የመኖሪያ ቤቶች መንደር የምንኖር፣ በስራ ቦታ ያለን፣ በተለያየ አጋጣሚ የምንገኝ ሁሉ ግድባችንን የሚገልፅ የተለያዩ ፅሁፎችን በማዘጋጀት ድምፃችንን በመላው ዓለም እናሰማለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችን የብሄር ብሄረሰቦች ሀገር ናትና የባህላዊ አልባሳት ማግኘት የምንችል በባህል ልብሳችን በየቤታችን ተውበን ድምፃችንን የምናሰማ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ሁላችንም በያለንበት ቦታ ሆነ ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን ድምፃችንን ስናሰማ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የጥንቃቄ ተግባራትን እንዳንዘነጋ አደራ ለማለት እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ድምፃችን ለግድባችን!

ዛሬ ከ10:00 ጀምሮ የኢትዮጵያውያን ዜጎች በያሉበት ሆነው ድምፃቸውን ባማረ እና በደመቀ መልኩ በጋራ አሰምተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የነበረው ድባብ እጅግ የሚያምር ነበር።

ለህዳሴ ግድባችን ድምፃችሁ ስታሰሙና ድስታችሁ ስትገልፁ የነበራችሁ ኢትዮጵያውያን በርካታ ፎቶዎችና ቪድዮዎችን አጋርታችሁናል እናመሰግናለን።

በዚህ የደስታ መግለጫ ስነ ስርዓት ወቅት በአንዳንድ ቦታዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ሊያባብስ የሚችል የመሰባሰብና ደስታን ጥንቃቄ ሳያደርጉ የመግለፅ ሁኔታ በእጅጉ ታይቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከነገ ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩ በማህበራዊ ሚዲያው እየተነገረ ይገኛል፡፡

በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ፓሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ "ህዝባችን በልማት ሥራ ላይ ይገኛል የሚዘጋም መንገድ የለም" ሲል ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የ28 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,607 የላብራቶሪ ምርመራ 707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 406 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 18,706 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 310 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 7,601 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Telegram!

ከዚህ ቀደም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETHIOPIA @tikvahethiopia) ይፋዊ ገፅ ላይ ተነስቶ የነበረው ፐብሊክ ሊንክ ቴሌግራም ወደቦታው እንዲመለስ አድርጓል ፤ በቀጣይ በቲክቫህ ስም የተከፈቱና ሀሰተኛ መረጃዎች የሚያሰራጩ ገፆችን ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ እንሰራለን።

በድጋሚ የቴሌግራም አስተባባሪዎችን እናመሰግናለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ትላንት በሀገራችን በኮቪድ-19 ህይወታቸው ካለፈ 28 ሰዎች መካከል ሃያ ስድስቱ (26) ከአ/አ ከተማ ናቸው። 24 በአስክሬን ምርመራ እና 2 ከጤና ተቋም እንደሆኑ ተገልጿል።

- በኦሮሚያ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,425 ደርሰዋል፤ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 21 ነው።

- በደቡብ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 201 ደረሱ ፤ እስካሁን የ3 ሰው ህይወት አልፏል፤ 52 ሰዎች አገግመዋል።

- በትግራይ ክልል አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 836 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 489 ሰዎች አገግመዋል።

- በአማራ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 565 ደርሰዋል፤ 6 ሞት ሲመዘገብ 446 ሰዎች አገግመዋል።

- በቤኒሻንጉል ክልል በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 213 ደርሰዋል ፤ ስልሳ ሁለቱ (62) ከበሽታው አገግመዋል።

- በሲዳማ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 224 ደርሰዋል፤ ትላንት ብቻ 40 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ሃያ ሁለቱ (22) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።

- በአፋር ክልል እስከዛሬ 284 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፥ ከነዚህ መካከል 117 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሌ ክልል አጠቃላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 705 ደርሰዋል፤ 406 ሲያገግሙ 18 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሚመለከተው አካል! ለኮቪድ-19 ፈጣን ምላሽ በኮንትራት ተቀጥረው እየሰሩ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የተላከ መልዕክት ፦ "ለህዝባችን ስንል ነፍሳችን ሁሉ ከመስጠት ወደኃላ ሳንል ፣ ቀንና ሌሊት ፣ ሰንበትን ጨምሮ የዓመት በዓላት ለህዝባችን ስንል እየሰራን ነዉ። ሞትን እየተጋፈጥን ቢሆንም ስራዉን በአግባቡ እየሰራን እንገኛለን። ነገር ግን ከ70% በላይ ስራ የሚሰራዉ ኮንትራት ተቀጣሪ ሆኖ ሳለ የተጋላጭነት…
ቅሬታ ላቀረቡ የጤና ባለሞያዎች የተሰጠ ምላሽ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኮንትራት ሰራተኞች የተጋላጭነት ክፍያ የዘገየው ሰፊ በጀት የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ስለነበር መሆኑን ለአሶሼትድፕሬስ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ ፥ "ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የሁለት ወራት ክፍያ ተጀምሯል ፣ ወደፊትም ይቀጥላል። ስራው አንድ ስለሆነ የተጋላጭነት ክፍያው ከቋሚ ሰራተኞች ጋር እኩል ይሆናል። ጊዜያዊ መኖርያም አቅም በፈቀደ መጠን ለሁሉም ይሰጣል" ብለዋል።

የራስ መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በተመለከተ ለተነሳው ቅሬታም ዶክተር ሊያ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል : "ለቋሚዎች ሰጥተን ለኮንትራት ሰራተኞች የምንከለክልበት አሰራር የለንም። ያለንን ለሁሉም እኩል እናዳርሳለን ፣ ግን እጥረት ስላለብን የምናቀርበው በቂ አይደለም"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ዓለም አቀፍ በረራዎች ዳግም ተጀመሩ!

በሱማሊያ ኮቪድ-19 ለመቆጣጣር ታሳቢ በማድረግ ከ 4 ወር ከ15 ቀን በፊት ቆመው የነበሩት ዓለም አቀፍ በረራዎች ከዛሬ ጀምሮ ዳግም ጀምረዋል።

ከዚህ ቀደም ብሎ ከባለፈው ሰኔ 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ የሀገር ውስጥ በረራዎች ተጀምረው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia