ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!
ተማሪዎች ወደ ሚማሩበት የትምህርት ተቋም መመለሻ ጊዜ ታውቋል ፣ ትምህርትም የሚጀምርበት ቀን ተቆርጣል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።
የዩኒቨርሲቲዎችን ስም እና የዩኒቨርሲቲዎችን ሎጎ አስመስሎ የተዘጋጁ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች (የቀጣዩን ትምህርት መርሃ ግብር የሚያሳዩ ምስሎች) በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ስለሚገኙ እንዳትታለሉ።
የኢፌዴሪ ሳይንሳና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው የሚመለሱበትን ቀን ያላሳወቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ወደፊት #ከMoSHE የምናገኘውን መረጃ እናካፍላችኃለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ዶ/ር አብይ ከፖለቲካ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው!
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ እንደሚገኙ ኢብኮ ዘግቧል።
ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
በቀጣይ አገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ተደርጎ ከነበረው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በዚህም እስከ ሰባት በሚደርሱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ለማድረግ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ፣ በመጀመሪያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎች መለየታቸው ተገልጿል።
በቅድሚያ ' አገራዊ መግባባት ' ላይ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው የተገለፀ ሲሆን ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች መመረጣቸውን ከኢብኮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
PHOTO : FILE

"...የቸልተኝነት ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አስከፊው ጊዜ መምጣቱ የማይቀር ነው" - ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን
በሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ማዕከል ከፅኑ ህሙማን መለስተኛ የሆኑ የሚታከሙበት ኦክስጅን ያላቸው 130 የህምሙማን አልጋዎች በሙሉ #መሙላታቸው ተገለፀ።
በኢትዮጵያ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ አስፈሪ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው ተብሏል።
የማዕከሉ ኃላፊ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እንደተናሩት ከዚህ ቀደም የበሽታው ምልክት የሌላቸው ሰዎችን ሲቀበል ነበር ፤ ከተቀበላቸው 74 % ያህሉ አገግመው የወጡበት ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ኦክስጅን ያላቸው 130 አልጋዎች ሞልተው ሌላ አማራጭ እስከመውሰድ ተደርሷል ብለዋል።
አሁን የሚታየው የቸልተኝነት ሁኔት በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አስከፊው ጊዜ መምጣቱ የማይቀር እንደሆነም ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አሳውቀዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያገናኙ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን በማስቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት #ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልፀዋል።
ዶክተር አብይ ቀጣዩ ምክክር በ "ሀገራዊ መግባባት" ላይ የሚያተኩር ይሆናል ያሉ ሲሆን ሀገሪቱ ተረጋግታ በብልጽግና ጎዳና ግስጋሴዋን እንድትቀጥል ሰላማዊ ተሳትፎ ፣ ሀሳቦችን በግልጽ ለውይይት ማቅረብ እና የፖለቲካ አመራሮች መከባበር በእጅጉ አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያገናኙ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን በማስቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት #ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልፀዋል።
ዶክተር አብይ ቀጣዩ ምክክር በ "ሀገራዊ መግባባት" ላይ የሚያተኩር ይሆናል ያሉ ሲሆን ሀገሪቱ ተረጋግታ በብልጽግና ጎዳና ግስጋሴዋን እንድትቀጥል ሰላማዊ ተሳትፎ ፣ ሀሳቦችን በግልጽ ለውይይት ማቅረብ እና የፖለቲካ አመራሮች መከባበር በእጅጉ አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጉባ ግድያ ፈፅመዋል የተባሉ 4 ግለሰቦች ተይዘዋል!
ከትናንት በስቲያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጥቃት በመፈጸም ሰዎችን ገድለዋል ከተባሉ ግለሰቦች መካከል አራቱ መያዛቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ቀሪ ወንጀለኞችን ይዞ እርምጃ ለመውሰድ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀች እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ/ም በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ በተፈፀመው ጥንቃት አስራ አራት (14) ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

የአቶ ጃዋር መሃመድ የፍርድ ቤት ውሎ!
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በማየት 12 ቀን ፈቅዶ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከኢብኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሁከት እና ብጥብጥ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተሰማራው የምርመራ ቡድን በርካታ የሰው ሞት እና የንብረት ውድመት የተመለከተ መረጃ መላኩንም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
አቶ ጃዋር በበኩላቸው ተከሰተ የተባለው ወንጀል እሳቸውን እንደማይመለከትና እሳቸው የሚፈልጓቸው ሚዲያዎች ችሎቱን እንዲዘግቡ እና ለሁሉም እንዲፈቀድ ያ ካልሆነ ግን ሁሉም ሚዲያዎች ችሎቱን እንዳይዘግቡ ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸው የኢብኮ መረጃ ያሳያል።
አቶ ጃዋር ያቆሟቸው 9 ጠበቆች የምርመራ ሥራው አዲስ አለመሆኑንና ፖሊስ የጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ እንዲሆን ወይም ጥቂት ቀን እንዲሆንም ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ቀደም ሲል በተሰጠው 13 ቀናት ውስጥ ምርመራውን በአግባቡ በማከናወኑ እና ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ አይቶ 12 ቀን በመፍቀድ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 610 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,760 የላብራቶሪ ምርመራ 610 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 159 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 15,810 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 253 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,685 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,760 የላብራቶሪ ምርመራ 610 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 159 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 15,810 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 253 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,685 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION
በሀገራችን ኢትዮጵያ ትላንት ሐምሌ 21/ 2012 እንዲሁም ዛሬ ሐምሌ 22 /2012 በወጡት ሪፖርቶች መሰረት (በ2 ቀን ብቻ) 25 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ጋር በተገናኘ ህይወታቸው አልፏል።

ችሎት!
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የ9 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለነሐሴ 1/2012 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የባይቶና የዛሬው መግለጫ!
የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ በአጭሩ ባይቶና የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በትግራይ በሥልጣን ላይ የሚገኘው ህወሀት 'በትግራይ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም' አድርጓል ያለውን እንቅስቃሴ አወግዟል።
ፓርቲው ዛሬ በሰጠው መግለጫ 'የትግራይ ህዝብ በጦርነት ስነ ልቦና እንዲኖር ፓርቲው እየወሰደ ነው' ያለውን እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ሲል ኮንኗል።
የባይቶና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክብሮም በርኽ ዛሬ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ወደ ኤርትራ አካሄድ የሚያመራ አዝማሚያ እየታየም ነው ብለዋል።
ባይቶና ምርጫን በማጓተትና የክልሉን ዴምክራሲ እና የፖለቲካ ባህል ግንባታ ወደ ኋላ በመመለስም ህወሀትን ከሷል።
የገዥው ፓርቲ አመራሮች ፣በትግራይ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ነው ሲልም ወንጅሏል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (https://p.dw.com/p/3g8A6?maca=amh-RED-Telegram-dwcom)

#Hajj
ከእስልምና አበይት አዕማደ ሥርዓት አንዱ የሆነው ሃጅ ዛሬ በመካ ፤ ሳውዲ አረብያ መጀመሩን ቪኦኤ ዘግቧል። የኮሮና ቫይረስ መዛመት ባሳደረው ሥጋት ምክንያት ዘንድሮ የሃጅና ዑምራ ተጓዦች ቁጥር ከወትሮ ያነሰ ነው።

በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ17 ሚሊዮን አለፉ!
በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 17,036,211 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 666,132 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 10,562,467 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 17,036,211 ደርሷል፤ ከነዚህ መካከል 666,132 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 10,562,467 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ጃዋር መሃመድ የፍርድ ቤት ውሎ ዝርዝር ፦
መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ሰራው ያለው አዲስ ስራ ለፍርድ ቤት አቅርቧል ፦
• በአቶ ጃዋር ቤት በድጋሚ በተደረገው ፍተሻ የቴሌኮም መሳሪያዎች፣በግለሰብ እጅ የማይገኙ የኤሌክትሮኒክስና የሳተላይት ጨምሮ ሌሎችንም አግኝቷል።
• በዕለቱ አቶ ጃዋር በOMN ተጠቅመው ብሄርን ከብሄር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ባስተላለፉት ጥሪና ትዕዛዝ በርካታ ጉዳት ደርሷል።
አቶ ጃዋር መሃመድ በዛሬው የፍርድ ቤት ብሎ የሰጧቸው ምላሾችና ያነሷቻቸው ጥያቄዎች መካከል በጥቂቱ፦
• የችሎት ውሎውን የምንፈልገው ሚዲያ እንዲዘግቡልን ይደረግ የመንግስት ሚዲያዎች ብቻ ነው እየዘገቡ ያሉት እነሱም የፖሊስ ምርመራ ብቻ ነው የሚያቀርቡት ሚዛናዊ አይደለም ስለዚህ እኛ የምንፈልጋቸው ይዘግቡልን ሁሉም ይፈቀድ አልያም ሁሉም ይከልከሉልን ሲሉ ጠይቀዋል።
• ከኤሌክትሮኒክስ እቃ ጋር በተያያዘ የተነሳው በጉሙሩክ በኩል አስፈላጊው ቀረጥ ከፍዬ ያስገባሁት ነው።
• የሃይማኖት ግጭት ፈጠረ ስለተባለው እናቴ ኦርቶዶክስ ናት ፣ ባለቤቴ ፕሮቴስታንት ናት፣ ከእኔ ጋር የተያዙት በተለይ አጃቢዎቼ ግማሹ ኦርቶዶክስ ግማሹ ደግሞ ፕሮቴስታንቶች ናቸው።
ይህ የፖለቲካ ጉዳይ ነው የፖለቲካ ችግርን ደግሞ በፖለቲካ መድረክ መፍታት እንጂ በዚህ ልክ ሊሆን አይገባም፤ እኔንም ሌሎችንም ከምርጫ ለማስቀረት ታስቦ ነው የታሰርኩት፤ እኔን የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ከማድረግ የጠበቆችን ጊዜም ማባከን አይገባም እኔና እስክንድር ነጋ የተለያየ አመለካከት ነው ያለን ነገር ግን በአንድ አይነት ክስ ላይ ነው እየተከሰስን ያለነው ይህ ተገቢነት የለውም። ዝርዝር የችሎት ውሎ: https://telegra.ph/JawarMohammed-07-29

የአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ ዝርዝር ፦
(DW)
የዛሬው (ሃምሌ 22/2012 ዓ/ም) መዝገብ የተቀጠረበት ጉዳይ ፖሊስ ምርመራ አልጨረስኩም ብሎ ፍርድ ቤትን በማስፈቀዱ የደረሰበትን የምርመራ ደረጃ ለማየት ነበር።
መርማሪ ፖሊስ ፦
• አሁንም ምስክሮችን እየሰማሁ ነው፤ በአዲስ አበባ ከተማ የደረሰውን ጉዳት የ6 ክፍለ ከተማ ነው የመጣልኝ የሌሎች ክፍለ ከተሞች እየተጣራ በመሆኑ እስካሁን አልደረሰልኝም።
• አሁንም የምንይዛቸው አባሪዎች አሉን ፣ የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ልከናል።
• አቶ እስክንድር ነጋ በሚያዝበት ጊዜ ላፕቶፕ እንዲሁም ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮቻቸውን ልንይዝ አልቻልንም ይህ አፈላልገን ለመያዝ የጊዜ ቀጠሮ ያስፈልገናል።
የአቶ እስክንድር ነጋ ጠበቆች ፦
• ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ብሎ የጠየቃቸው ምክንያቶች በሙሉ በመጀመሪያው ቀን የቀረቡ ናቸው። ስለዚህ ፖሊስ ስራውን እየሰራ አይደለም። በዚህ መካከል አቶ እስክንድር አላግባብ ታስረዋል ብለዋል።
• ከመንግስት እና ለመንግስት ቅርበት ካላቸው ሚዲያዎች ውጭ ችሎት እንዳይገቡ መደረጉ ተገቢ አይደለም ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ ሚዲያዎችን በሚመለከት የአቶ እስክንድር ጠበቆች አቤት ያሉትን ተመልክቶ ፍርድ ቤቱ ይህ ትክክል አይደለም ፤ ፖሊስ ሁሉንም ጋዜጠኞች ማስገባት አለበት ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አቶ እስክንድር ነጋ በዚህ ጉዳይ እኛ የምንፈልገው የህዝብ ፍትህ ስለሆነ ጋዜጠኞች በነፃነት ገብተው መዘገብ አለባቸው ብለዋል።
ፍርድ ቤት ፦
ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ተመልክቶ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ውድቅ በማድረግ 9 ቀን ፈቅዶ ለነሃሴ 1/2012 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ከምንጊዜውም በላይ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ነን!
- ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታዎች አይገኙ
- አፍዎን፣ አፍንጫዎንና አይንዎን ባልታጠቡ እጆችዎ አይንኩ
- እጆን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በሳሙና ለ20 ሰከንድ ይታጠቡ
- ከሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን እቃዎች ወይም ቦታዎች በተገቢው መልኩ ያፅዱ
በየትኛድም ቦታና ጊዜ ከማንኛውም ሰው የኮሮና ቫይረስ ሊይዘን ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ!
ይህ መልዕክት በቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) እና በመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል /CARD ትብብር የተዘጋጀ ነው።

#UPDATE
ሐምሌ 20/2012 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር መዋለቸውን BBC ዘገበ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ እንደገለጹት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በትላንትናው ዕለት ነው።
እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገለፀ ከሆነ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል እርምጃ እየወሰደባቸው ነበር።
እርምጃውን ተከትሎ ተበታትነው በመንቀሳቀስ 13 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።
ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ 20 ሰዎች ትናንት መያዛቸውን አቶ አብዱላዚዝ አስታውቀዋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 12 መሣሪያዎችም መያዙን ነው የተናገሩት - #BBC

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚላን በረራ ጀመረ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ጣልያን ሚላን ከተማ አቋርጦ የነበረውን በረራ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ በማድረግ መጀመሩን ገልጿል።