TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዓረና በትግራይ በሚደረገው ምርጫ አልሳተፍም አለ!

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና) ሓምለ 17 ባወጣው መግለጫ ነፃ ፣ ፍትሓዊና ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ ምርጫ አልሳተፍም ሲል አስታውቋል።

ፓርቲዊው በዚህ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰንኩበት አንዱ ምክንያት ህወሓት ሕገ-መንግስቱን በግላጭ የሚፃረር የምርጫ አካሄድ በመምረጡ ነው ብሏል።

በተጨማሪ ህወሓት አካሂደዋለሁ በሚለው ሕገ-ወጥ ምርጫ ከተቋቋመ 12 ዓመታትን ያስቆጠረውና በትግራይ ፖለቲካ ተፅዕኖ ያለውን ዓረናን አግልሎ ራሱ የመረጣቸው ፓርቲዎች አቅፎ ለመሄድ በመወሰኑ ነው ሲል ገልጿል።

ዓረና ባወጣው መግለጫው የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው ያለውን ያቀረበ ሲሆን ከመፍትሄዎቹ የመጀመሪያው ነጥብ ህወሃት እየሄደበት ያለው የምርጫ እንቅስቃሴ ኢ-ሕገ መንግስታዊና ኢ-ሕጋዊ በመሆኑ ይህን ውሳኔውን በማጤን ሊቀለብሰው እንደሚገባና በዚህ ምትክም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን እና በተናጠል ከፌዴራሉ መንግስት ጋር የምር ድርድር እንዲያካሂድ የሚጠይቅ ነው።

ፓርቲው 'ነፃ ፣ ፍትሓዊ እና ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ ምርጫ አልሳተፍም' በሚል ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ሃሳብ በ : https://telegra.ph/TigrayElection-07-25 ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ምርጫ እንሳተፋለን ያሉ ፓርቲዎች!

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ እስካሁን ድረስ ካሳወቁ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ፣ ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ፣ ባይቶና ትግራይና ውድብ ናፅነት ትግራይ ይገኙበታል።

ከዚህ በተቃራኒ ዓረና ትግራይ እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በሂደቱ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት!

' ሞደርና ' የተባለው የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ አንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት በ30,000 ጎልማሶች ላይ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከብሄራዊ የአለርጂ እና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በመተባበር ሙከራው ትላንት የተጀመረው በሳቫና ጆርጂያ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል። ሳቫና በሀገቱ ዙሪያ ካሉት፣ በርካታ የሙከራ ቦታዎች፣ አንዱ ነው ተብሏል።

ክትባቱ እንዲሞከርባቸው ከቀረቡት ስዎች ግማሾቹ እውነተኛው ክትባት እንደሚሰጣቸው የተቀሩት ግን የውሸት ክትባት እንደሚከተቡ አሶሼተድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሞደርና እስካሁን ባለው ጊዜ ባደረጋቸው የክትባቱ መድሃኒት ሙከራዎች ጠንካራ የመከላከል ምላሽ ማሳየቱን በያዝነው ወር ቀደም ሲል አስታውቋል።

ድካምን ፣ ራስ ምታት ፣ የብርድ-ብርድ የማለት እንዲሁም የሰውነት መቀጥቀጥን የመሳሰሉት ቀለል ያሉ የጎንዮሽ ስሜቶች ማስከተሉ #ከቪኦኤ የተገኘው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ 'ከፋና ትግርኛ' ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ፦

የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልልን መንግስትን ወይም የትግራይ ክልል ህዝብን ሊያጠቃ ይችላል ብሎ ማሰብ በራሱ እብደት ነው።

እኔ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም ፤ ካሰቡት አካላት ይልቅ ይሄንን እንደ ቁምነገር አንስተው የሚያወሩት ናቸው እኔም የሚያስገርሙኝ።

ከትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኤርትራ ፣ ከሱዳንም ሆነ ከሱማሊያ ጋር ምንም አይነት ግጭት አንፈልግም። በሰላም ልማትን ማምጣት ብቻ ነው የምንፈልገው እያልን የፌደራል መንግስት የትግራይን ህዝብ ሊያጠቃነው ማለት ምን ማለት ነው ?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የህወሓት እና ፌደራል መንግስት አለመግባባት!

ዶ/ር አብይ አህመድ 'ከፋና ትግርኛ' ጋር በነበራቸው ቆይታ በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል መካከል ስላለው አለመግባባት/የአቋም ልዩነት ተከታዩን ብለዋል ፦

በእኔ በኩል ያለው አለመግባባት መፈታት አለበት ብዬ ነው የማምነው፤ መፈታትም አለበት። ከዚህ በኃላ ችግሩን ፈተን በተሻለ የልማትና የዴሞክራሲ መንገድ መቀጠል አለብን ብዬ ነው የማምነው።

በቶሎ መግባባት ላይ እንዲደረስ የትግራይ ህዝብ በአመራር ቦታ ላይ ላሉ እንደነ ዶ/ር ደብረፅዮን የመሰሉ ልማትና ሰላም ፈላጊ የሆኑ አመራሮችን መደገፍ አለበት።

እነዶክተር ደብረፅዮን ከመጀመሪያው ጀምሮ ቢሆን ከፌደራል መንግስት ጋር ቁጭ ብለው በእኛም ሆነ በነሱ በኩል ባሉ ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት ዝግጁ ናቸው ፤ ለዚህ የትግራይ ህዝብም ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብዬ አምናለሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
2 ልጆቿን በኮቪድ-19 ያጣችው እናት! ፍሎሪዳ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ' ሞንቴ ሂክስ ' የምትባል እናት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሁለት (2) ልጆቿን ህይወት አጥታለች። የመጀመሪያው የ20 ዓመት ልጇ ሲሆን እሱ ህይወቱ ካለፈ ከ11 ቀን በኃላ ደግሞ የ22 ዓመት ሴት ልጇን በዚህ አስከፊ በሽታ ተነጥቃለች። እስካሁን ድረስ እጅግ መሪር በሆነ ሀዘን ውስጥ የምትገኘው ሞንቴ ሂክስ ከ NBC ጋር በነበራት…
እናትና አባታቸውን በኮቪድ-19 ያጡት ልጆች!

በሂውስተን ነዋሪ የሆኑት ሁለት ልጆች እናት እና አባታቸውን በ15 ቀናት ልዩነት በአስከፊው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሽታ ተነጥቀዋል።

በአሁን ሰዓት ሁለቱም ልጆች ጃኮብ ሜንዶዛ (ከእናታቸው ወንድም) እና ባለቤቱ ጋር በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ለመኖር ተገደዋል።

ኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም ልጆችን ያለወላጅ ፤ ወላጆችን ያለልጅ እያስቀረ ነውና እባካችሁ ፣ እባካችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንጠይቃለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ15 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,503 የላብራቶሪ ምርመራ 653 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 170 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 15,200 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 239 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,526 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል።

ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል።

ስለዛሬው የነአቶ ሃምዛ ቦረና የችሎት ውሎ በዝርዝር መረጃ ማግኘት : https://telegra.ph/HamzaB-07-28

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዕለቱ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን ቁጥር መቁጠር ከጀመረች በርካታ ሳምንታት አልፈዋል።

የ3 ቀናት ሪፖርት ብቻ ብንመለከት በአጠቃላይ ሰላሳ (30) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው አልፏል።

በዚህ አስከፊ በሽታ የምትወዷቸውን ሰዎች ከአጠገባችሁ ያጣችሁና የተነጠቃችሁ ወገኖቻችን በሙሉ #መፅናናትን እንመኝላችኃለን።

አሁንም ስልቹነታችን፣ መዘናጋትችን፣ ቸልተኝነታችን መፍትሄ ካላገኘ የነገ ህይወታችንን ያጨልማልና ከፍተኛ ጥንቃቄ እናድርግ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግብጽ በግድቡ ጉዳይ ከወታደራዊ ይልቅ ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን እንደምትጠቀም አስታወቀች!

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ሃገራቸው በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ከወታደራዊ ይልቅ ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን እንደምትጠቀም ማስታወቃቸውን አልዓይን ዘግቧል፡፡

ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ይህን ያሉት የተለያዩ የልማት ፕሮጄክቶችን መርቀው ንግግር ባደረጉበት ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡

ግብጽ የኢትዮጵያን ልማት ትደግፋለች ያሉት ፕሬዝዳንቱ ድጋፉ ታሪካዊ ባሉት የውሃ ድርሻዋ ላይ እንደማይሆን ግን ተናግረዋል፡፡

በግብጻውያን ጽናት እና ድጋፍ የሃገራቸውን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ከስምምነት እንደርሳለን ብለው እንደሚያስቡም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፡፡

ግብጽ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁንም በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት በመደራደር ላይ ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፍርድ ቤት ውሎ! ዛሬ የህወሃት ፅህፈት ቤት የአዲስ አበባ አገናኝ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃዲቅ ከሁለት ሹፌሮች ጋር ፣ የአቃቂ ክፍለ ከተማ የደህንነት ሹም አቶ አፅብሃ አለማየሁና በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የህግና ፍትህ ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋለም ይህደጎ ችሎት ቀርበው ነበር። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ጠበቆቻቸው ለጀርመን ሬድዮ እንደተናገሩት ከተያዙ 2 ሳምንት የሆናቸው ተጠርጣሪዎች…
የህወሓት አመራሮች የፍርድ ቤት ውሎ!

ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሽብር ቡድኖች መረጃ አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ተጠርጥረዋል ያለው ፖሊስ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው የህወሓት የአዲስ አበባ አገናኝ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃዲያ ፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕግ እና ፍትህ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር አቶ ተስፋአለም ይህደጎና ሌሎች ሁለት ሹፌሮች ናቸው።

ፖሊስ ዛሬ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ሪፖርት የባንክ ሂሳባቸውን እያስመረመርኩ ነው፣ በአቶ ተስፋአለም ቤት የተገኘው ክላሽ ህጋዊ ፍቃድ የለውም የሚል ሃሳብ አቅርቧል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ እስካሁን የሰራቸው ስራ የሚያሳይ ዝርዝር መዝገብ ይዞ አልቀረበም ስለዚህ ደንበኞቻችን በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

ችሎቱ ለምን የምርመራ መዝገቡን ይዞ እንዳልቀረበ የጠየቀ ሲሆን ለሐምሌ 23 መዝገቡን ይዞ እንዲቀርብና የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ይሰጥ አይሰጥ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል - #ዶቼቨለ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

ዛሬ ፍርድ ቤት የኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ጉዳይ ተመልክቷል።

የዛሬው ቀጠሮ መርማሪ ፖሊስ ባለፈው በነበረው ቀጠሮ ተጠርጣሪዎችን ከወንጀሉ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለብቻ ነጥሎ ለማቅረብና የደረሰበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለፍርድ ቤት ለማሳወቅ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ሰራዋቸው ያለው ስራ ፦

- ተጨማሪ ምስክሮችን ሰምቻለሁ፣ከወንጀሉ ጋር የተያዙ እቃዎቻቸውን ለምርመራ ለፌደራል ፖሊስና ለብሄራዊ ደህንነት ልኪያለሁ ውጤት እየጠበኩ ነው ብሏል።

- የንብረት ግምት እንዲላክ ፣ የአስክሬን ምርመራ ሪፖርት እንዲላክልኝ ለሚመለከታቸው አካላት ልኪያለሁ ብሏል ፤ እነዚህ ስራዎች ስለሚቀሩኝ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሏል።

የኢንጂነር ይልቃል ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ፦

ኢንጂነር ይልቃል ከወንጀል ጋር ያላቸው ግንኙነት ፣ በምን ሁኔታ፣ እንዴትና መቼ እንደተፈፀመ ፖሊስ እንዲያቀርብ ነበር የታዘዘው።

የ14 ሰው ህይወት አልፏል ለዛም ውጤት እጠብቃለሁ ፣ ንብረት ወድሟል ከማለት ያለፈ ተለይቶ የተሳትፎ ደረጃቸው ስላልተገለፀ ለ27 ቀናት በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ሲያደርግ ነበር ተጨማሪ ጊዜ አያስፈልግም መዝገቡ ተዘግቶ #በነፃ ይለቀቁ ብለዋል።

ፍርድ ቤት ፦

- የተጠርጣሪ ጠበቃን አቤቱታ ሰምቶ ፣ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ጥያቄ ተመልክቶ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አስፈላጊነው ፣ አይደለም የሚለውን ለመወሰን ለሐምሌ 24 ቀጠሮ ሰጥቷል #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የዕርቅ ሀሳብ አለኝ የተሰኘው በባህላዊ የዕርቅ ሥርዓቶች ላይ ያተኮረው የአጭር ገለጻ የጹሑፍ ውድድር ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በውድድሩ ላይ 327 የግል ተወዳዳሪዎች እና 40 የቡድን ተወዳዳሪዎች ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን ጹሑፋቸውም ተሰብስቦ ከኮሚሽኑ አባላት በተወጣጡ ልምድ ባላቸው ዳኞች እንዲገመገም እየተደረገ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የምዘና ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን በተያዘው የጊዜ ሰሌዳም መሰረት ምዘናው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ነሐሴ 8 የውድድሩ አሸናፊዎች የሚገለጹበት ቀን ይሆናል፡፡

በቀጣይ የተመረጡ ሥራዎችን የማደራጀት ሥራ ከተከናወነ በኀላ ልዩ የሽልማትና የዕውቅና መርኃግብር በመስከረም 11 የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ በውድድሩ ጹሑፋቸውን በመላክ የተሳተፉ በሙሉ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት የሚያገኙ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ምርጫ መቼ ይደረጋል ?

በትግራይ ክልል የሚደረገው ምርጫ የሚካሄድበት ትክክለኛ ቀን ከሚመዘገቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር በመወያየት እንደሚወሰን የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል ለሚደረገው ምርጫ ከዛሬ ማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012 ዓ/ም) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012 ዓ/ም) ባሉት 3 ቀናት ውስጥ ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 10,703 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• ቦሌ - 1,652 ሰዎች
• አዲስ ከተማ - 1,329 ሰዎች
• ጉለሌ - 1,308 ሰዎች
• አራዳ - 923 ሰዎች
• የካ - 901 ሰዎች
• ልደታ - 883 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 876 ሰዎች
• ቂርቆስ - 855 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 831 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 614 ሰዎች
• በለይቶ ማቆያ - 317 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 214 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!

ተማሪዎች ወደ ሚማሩበት የትምህርት ተቋም መመለሻ ጊዜ ታውቋል ፣ ትምህርትም የሚጀምርበት ቀን ተቆርጣል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

የዩኒቨርሲቲዎችን ስም እና የዩኒቨርሲቲዎችን ሎጎ አስመስሎ የተዘጋጁ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች (የቀጣዩን ትምህርት መርሃ ግብር የሚያሳዩ ምስሎች) በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ስለሚገኙ እንዳትታለሉ።

የኢፌዴሪ ሳይንሳና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው የሚመለሱበትን ቀን ያላሳወቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ወደፊት #ከMoSHE የምናገኘውን መረጃ እናካፍላችኃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ ከፖለቲካ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው!

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ እንደሚገኙ ኢብኮ ዘግቧል።

ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

በቀጣይ አገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ተደርጎ ከነበረው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዚህም እስከ ሰባት በሚደርሱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ለማድረግ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ፣ በመጀመሪያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎች መለየታቸው ተገልጿል።

በቅድሚያ ' አገራዊ መግባባት ' ላይ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው የተገለፀ ሲሆን ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች መመረጣቸውን ከኢብኮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

PHOTO : FILE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...የቸልተኝነት ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አስከፊው ጊዜ መምጣቱ የማይቀር ነው" - ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን

በሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ማዕከል ከፅኑ ህሙማን መለስተኛ የሆኑ የሚታከሙበት ኦክስጅን ያላቸው 130 የህምሙማን አልጋዎች በሙሉ #መሙላታቸው ተገለፀ።

በኢትዮጵያ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ አስፈሪ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው ተብሏል።

የማዕከሉ ኃላፊ ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እንደተናሩት ከዚህ ቀደም የበሽታው ምልክት የሌላቸው ሰዎችን ሲቀበል ነበር ፤ ከተቀበላቸው 74 % ያህሉ አገግመው የወጡበት ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ኦክስጅን ያላቸው 130 አልጋዎች ሞልተው ሌላ አማራጭ እስከመውሰድ ተደርሷል ብለዋል።

አሁን የሚታየው የቸልተኝነት ሁኔት በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አስከፊው ጊዜ መምጣቱ የማይቀር እንደሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አሳውቀዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያገናኙ ተመሳሳይ የውይይት መድረኮችን በማስቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት #ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልፀዋል።

ዶክተር አብይ ቀጣዩ ምክክር በ "ሀገራዊ መግባባት" ላይ የሚያተኩር ይሆናል ያሉ ሲሆን ሀገሪቱ ተረጋግታ በብልጽግና ጎዳና ግስጋሴዋን እንድትቀጥል ሰላማዊ ተሳትፎ ፣ ሀሳቦችን በግልጽ ለውይይት ማቅረብ እና የፖለቲካ አመራሮች መከባበር በእጅጉ አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia