TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ!

ትላንት በሀገራችን 704 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ይታወቃል ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ ከ10 በመቶ በላይ የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለኤፍ ቢ ሲ ሲናገሩ እንደተደመጡት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጅጉ እየጨመረ ነው ብለዋል።

ስንት ሰው ተመረመረ ? ስንት ሰው ተያዘ ? የሚለው ሲታይ ከዚህ ቀደም ፖዘቲቭ የሚሆኑት ከ1 በመቶ በታች የነበረ ሲሆን ሰሞኑን በሀገራችን በተከሰተው ሁኔታ ወደ 3 በመቶ ከፍ ብሎ ነበረ ፤ ትላንት ደግሞ 10 በመቶ ደርሷል ፤ የአ/አ ደግሞ ከ10 መቶ በላይ ሆኗል ሲሉ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጀ ይህ ፐርሰንት ስርጭቱ በደንብ በተስፋፋባቸው ሀገራት ላይ የሚገኝ እንደሆነም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ውጤታማ ነው ተባለ!

በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተሰራው የኮሮና ቫይረስ ክትባት የሰዎችን በሽታውን የመከላከል ሥርዓት እንደሚያጎለብትና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑ መገለፁን BBC ዘገበ።

በምርምር ሥራው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉ 1,077 ሰዎች ሲሆኑ የተሰጣቸው ክትባት ጸረ ተህዋስ [አንቲቦዲ] እንዲያዳብሩ እና ነጭ የደም ህዋሳቸው ኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲችል ሆኗል ተብሏል።

የዚህ ምርምር ውጤት ግኝት በጣም ተስፋ ሰጪ የተባለ ሲሆን ፤ ይህ ግን የመከላከል አቅምን ለማግኘት በቂ ስለመሆኑ አለመታወቁ ተገልጾ ሰፊ ሙከራ እየተካሄደ ነው።

ይህ ምርምር የተደረገው በቅድሚያ ክትባቱ ለበርካታ ሰዎች ቢሰጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ይሆናል ወይ የሚለውን ለማረጋገጥ ነው ተብሏል።

ክትባቱ ውጤታማ ሆኖ ለአገልግሎት የሚበቃ ከሆነ ዩናይትድ ኪንግደም አስቀድማ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ማዘዟ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
ለዘንድሮ ተፈታኞች ማስታወሻ!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን በወረቀት እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኦን ላይን ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን መረጃ ሰጥተናችሁ ነበር።

ተማሪዎች ለምትወስዱት ፈተና ዝግጅት እያደረጋችሁ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እስኪገለፅ እንድትጠብቁ ፤ ወላጆች ልጆችን በማበረታታት ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማድረጉን እንዳትዘነጉ #ለማስታወስ እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 304 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,056 የላብራቶሪ ምርመራ 304 ሠዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ እንዲሁም የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በቫይረሱ የተያዙት ሠዎች 157 ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 36 ከትግራይ ፣ 46 ከኦሮሚያ፣ 26 ከጋምቤላ ፣ 12 ከአማራ ፣ 17 ከአፋር ፣ 7 ከሱማሌ ፣ 2 ከሐረሪ እና 1 ከደቡብ ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች 10 ሺህ 511 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 173 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 5,290 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የፍርድ ቤት ውሎ!

ዛሬ የህወሃት ፅህፈት ቤት የአዲስ አበባ አገናኝ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃዲቅ ከሁለት ሹፌሮች ጋር ፣ የአቃቂ ክፍለ ከተማ የደህንነት ሹም አቶ አፅብሃ አለማየሁና በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የህግና ፍትህ ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋለም ይህደጎ ችሎት ቀርበው ነበር።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ጠበቆቻቸው ለጀርመን ሬድዮ እንደተናገሩት ከተያዙ 2 ሳምንት የሆናቸው ተጠርጣሪዎች ፖሊስ የመንግስትን መረጃ ለሀገር ውስጥና ለውጭ የሽብር ቡድኖች አሳልፎ መስጠት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት ገልፆ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸዋል።

በተለይ አቶ ተስፋለም ይህደጎ በታሰሩበት እስር ቤት 3 ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያለባቸው ታሳሪዎች በመገኘታቸው ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ ከቤተሰቦቻቸውና ጠበቆቻቸው ለመገናኘት እንዳልቻሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ተመልክቶ አያያዛቸው ለህይወታቸው በማያሰጋ መልኩ መሆን እንዳለበት ከቤተሰቦቸው እና ጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ፖሊስ ይህ ትዕዛዝ መፈፀሙን በቀጣይ ቀጠሮ ጊዜ ሪፖርት ይዞ እንዲቀርብ አዟል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን የ 14 ቀን ጊዜ ውድቅ በማድረግ የ8 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጀርመን ሬድዮ ጣቢያ በምሽት ስርጭቱ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከ7,000 በላይ ሆነዋል!

በኦሮሚያ ክልል ሁከት በመቀስቀስ፣ ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከ7,000 በላይ መድረሳቸውን አቶ ጌታቸው ባልቻ /የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ/ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ከነዚህ መካከል ተመክረው የሚለቀቁ እንዳሉ የገለፁ ሲሆን የወንጀል ድርጊታቸው የተረጋገጠባቸው በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል።

በአሁን ሰዓት የኦሮሚያ ክልል ወደ ቀደመ ሰላም ተመልሷል ፤ ንብረት የወደመባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በ2 ቀን ብቻ 1,008 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኢትዮጵያ ከትላንት በስቲያ እንዲሁም ትላንት በድምሩ 1,008 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ለወረርሽኙ መጨመር ከምክንያቶቹ ዋነኛው የህብረተሰቡ መዘናጋት እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

በትላንትናው ዕለት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችሁ ይህ ፅሁፍ ማንበብ የቻላችሁ የቲክቫህ አባላት በየአካባቢያችሁ ያለውን ሁኔታ እንዴት እየገመገማችሁት ነው ?

እየታየ ያለውን ከፍተኛ መዘናጋት ለመቅረፍ መፍትሄ የምትሉት ሃሳብ ምን ይሆን ? በ @tikvahethiopiaBot መጠቆም ይቻላል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኢንተርኔት መቋረጥና የትራንስፖርት አገልግሎት!

'ዛይራይድ' የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በሀገሪቱ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ኢንተርኔት በመቋረጡ በ2 ሳምንት ግማሽ ሚሊዮን ብር (500,000 ብር) ገቢ ማጣቱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
#GERD

የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ መሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ ይመክራሉ።

የዛሬው ውይይት ሰኔ 19 የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የሚካሄድ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚካሄደውን ስብሰባ ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

በስብሰባው ላይ የቢሮው አባላት የሆኑት የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ እና የማሊ መሪዎች እና ተወካዮችም ይሳተፉበታል።

የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ በዛሬው ስብሰባው ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያደርጉት በነበሩት የሶስትዮሽ ድርድር የደረሱበትን ደረጃ የሚመለከት ይሆናል - #FBC

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚመለሱበት ቀን ታውቋል ?

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ከትምህርት ተቋማት የወጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደትምህርት / ወደሚማሩበት ተቋም / የሚመለሱበት ቀን እስካሁን ድረስ በመንግስት ተወስኖ አልተገለፀም።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች 'የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚመለሱበት ቀን ታወቀ' ፣ 'የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን የምርቃት ቀናቸው ተወሰነ' በሚል የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

በቅርቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች እስኪጠሩ ድረስ ከቫይረሱ ራሳቸውን በመከላከል ባሉበት ሆነው ንባባቸውን እንዲቀጥሉና በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም በአከባቢያቸው ያሉ ወገኖችን እንዲያስተምሩ መልዕክት ማስተላለፉ ይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በአስሩ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ብዛት ቁጥራዊ መረጃ ፦

• አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር - 7,414 ሰዎች
• ሱማሌ ክልል - 602 ሰዎች
• ኦሮሚያ ክልል - 571 ሰዎች
• ትግራይ ክልል - 498 ሰዎች
• አማራ ክልል - 438 ሰዎች
• ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር - 319 ሰዎች
• ጋምቤላ ክልል - 274 ሰዎች
• አፋር ክልል - 180 ሰዎች
• ሲዳማ ክልል - 96 ሰዎች
• ሐረሪ ክልል - 78 ሰዎች
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 22 ሰዎች
• ደ/ብ/ብ/ሕ ክልል - 19 ሰዎች

በአጠቃላይ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠው ሰዎች ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 75.5 በመቶን እንደሚይዝ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
Thank You Telegram!

ውድ አባላት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ገፅ የነበረው ችግር ተፈቷል ፤ የቲክቫህ ፐብሊክ ሊንክ በቀጣይ ቀናት በቴሌግራም በኩል ወደነበረበት ይመለሳል።

በአጠቃላይ ' የቴሌግራም አስተባባሪዎችን ' በሙሉ ለሰጡን ፈጣን ምላሽ እና የተፈጠረውን ጉዳይ ለማጣራት ለሰሩት ስራ እናመሰግናለን።

በሌላ በኩል ቴሌግራም ባለው እጅግ ጥብቅ የሆነ አሰራር ምክንያት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም ለየትኛውም ወገን / ቲክቫህ አባል ሀሰተኛ መረጃ በውስጥ በኩል እንዳልተሰራጨ አረጋግጠናል።

በድጋሚ 'ቴሌግራም' የቲክቫህ አባላት መረጃ ለመለዋወጥ ፣ ለመደጋገፍ፣ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመመካከርና ለመነጋገር የተሰባሰቡበትን ትልቁንና ሁሉን አቃፊውን መድረክ ደህንነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቅ ስላደረገ እናመሰግናለን !

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሠጠ ማሳሰቢያ!

ከጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ በደቡብ ኦሞ ዞን ስር ለምትገኙ የዳሰነች ፣ ሰላማጎ ፣ ኛንጋቶም ፣ ሀመር ፣ ኦሞራቴ ፣ ካንጋቶን ከተማ ነዋሪዎችና የኦሞ ስኳር ፋብሪካ እንዲሁም በመስኖ ልማት ላይ የተሰማራችሁ ባለኃብቶች በሙሉ ከሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የግድቡ ውሃ ሊለቀቅ ስለሚችል ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው!

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊት ለፊት እና በኦንላይን ያስተማራቸውን ከ,5600 በላይ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ #በvirtual እያስመረቀ ይገኛል። የምርቃት ስነ ስርዓቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /etv/ በቀጥታ እየተላለፈ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!

ዛሬ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በ Virtual እየተመረቃችሁ ለሚትገኙ ተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ መጪው ጊዜ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ጥብቅ ማሳሰቢያ!

በኳታር ነዋሪ የሆናችሁ የኢትዮጵያ ዜጎች የኳታር መንግስት ያስቀመጠው የNational Address የምዝገባ ቀነ ገደብ #ነገ ይጠናቀቃል።

መንግስት ሊወስድ ከሚችለው ማንኛውም እርምጃ ራሳችሁን ለመጠበቅ እስካሁን መረጃውን ያልሞላችሁ ምዝገባውን በ #Metrash2 የሞባይል መተግበሪያ ወይም በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ ገጽ www.moi.gov.qa አማካኝነት እንድታከናውኑ በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጥብቅ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#FDREDefenseForce

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ እና ግጭት በመፍጠር ፣ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎችን እየፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ አይኖራቸውም ሲሉ አስታውቀዋል።

ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያጋጩ ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት ፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት #እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ሬድዋን አማና እና የሱፍ በሽር በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወሰነ!

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከስቶ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሦስት (3) የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል።

ከነዚሁ 3 የአሜሪካ ዜግነት ካለቸው መካከል በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ሬድዋን አማን እና ዩሱፍ በሽር የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው #ለBBC ተናግረዋል።

ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ እንደተናገሩት ፤ ሁለቱ ግለሰቦች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በ6 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከእስር እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል።

ሦስተኛው የአሜሪካ ዜግነት ያለው እና በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ ሚሻ ጪሪ የሚባል ሲሆን ፤ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ቴክኒሺያን ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

ሚሻ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት እንዳልተሳካለት ለፍርድ ቤት ተናግሮ እንደነበር #BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#Emirates

ኤሚሬትስ አየር መንገድ ከነሐሴ 1 ቀን 2020 ጀምሮ በሳምንት ሶስት በረራዎች ወደ አዲስ አበባ ማድረግ እንደሚጀምር ከ251 ኮሚኒኬሽን የተላከልን መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪ አየር መንገዱ ከትላንት ሐምሌ 17 ጀምሮ ወደ ቴህራን በረራ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ከሐምሌ 25 ጀምሮ ደግሞ ጉንጉዙ እና ኦስሎ በረራ ይጀምራል፡፡

የዱባይ ነዋሪዎች የወቅቱን የጉዞ መስፈርቶችን በ www.emirates.com/returntoDubai ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaOfficial @tikvahethmagazine
#GERD

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ 11 ተርባይኖች ተከላ በቀጣዩ አመት እንደሚካሄድ መናገራቸውን አል አይን ዘግቧል።

በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ዌቢናር (የኦንላይን ቨርቹዋል ውይይት) ለተሳተፉ አምባሳደሮች እና ምሁራን የግድቡን የድርድር ሂደቶች እና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ሰፊ ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት (2013 ዓ/ም) ኃይል እንደሚያመነጩ የሚሞከሩትን ሁለት (2) ተርባይኖች ውሃ ማስተላለፊያ ‘ፔንሰቶኮች’ እና ‘ቦተም አውትሌት’ ለማጠናቀቅ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የተርባይኖቹን እና የኤሌክትሪክ ስራዎቹን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ውሃው ሳይቋረጥ እንዲያልፍ ፣ የግድቡ ከፍታም ወደ 590 ሜትር እንዲያድግ ከማድረግ እና ተጨማሪ 13 ነጥብ 4 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ከመያዝ ባለፈ በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ የአስራ አንድ (11) ተርባይኖች ተከላ እንደሚካሄድም ማስረዳታቸውን ከአል ዓይን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማሳሰቢያ!

የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በነገው እለት የሚከበረውን ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል በየቤታቸው አንዲያከብሩ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአገራችን በተለይም በሀዋሳ ከተማ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመር በመምጣቱ ህብረተሰቡ ንክኪ ሊያስከትል ከሚችል መሰባሰብ ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል።

በነገው እለት (ሐምሌ 19) የሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓልም የእምነቱ ተከታዮች በየቤታቸው አንዲያከብሩት ከእምነቱ የሃይማኖት አባቶች ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን ኮሚሽነር መሳፍንት ተናግረዋል።

አገሪቱ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች ያሉት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የወጣውን አዋጅ በማክበር ራሱን ፣ ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial