TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'One Voice for Our Dam'

'ሊፍት ኢትዮጵያ' መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር 'One Voice for Our Dam' በሚል ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ሰዓት በያሉበት ሆነው ለግድቡ ድምፃቸውን የሚያሰሙበትን መርሃ ግብር እያዘጋጀ እንደሆነ በላከልን መግለጫ አሳውቆናል።

እንዴት ? መቼ ? በምን አይነት ሁኔታ ? ባያለንበት ሆነን /የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል ባደረገ ተግባር መሰረት/ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ድምፃችንን እናሰማለን የሚለውን በቀጣይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሲደርሰን የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መልዕክት ለወጣቶች!

በሀገራችን የኮቪድ-19 ወረሽኝ በእጅጉ እየተሰራጨ በመሆኑ ተሰባስባችሁ የውጭ እግር ኳስ ውድድሮችን ባትመለከቱ ይመረጣል።

ለእራሳችሁ ፣ ለቤተሰቦቻችሁ እና ለማህበረሰቡ ጤና ስትሉ የእግር ኳስ ውድድሮችን ተሰባስባችሁ ከማየት ተቆጥባችሁ ውጤቶችን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ብትከታተሉ የተሻለ ይሆናል።

እራሳችሁን ጠብቁ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኢስታንቡል አቋርጦ የነበረውን የመንገደኞች በረራ በሳምንት 3 ጊዜ ዳግም መጀመሩን አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ እለታዊ በረራዎችን ወደ አውሮፓ ከተሞች ብራሰልስ ፣ ፓሪስ ፣ ፍራንክፈርት እና ለንደን ማድረግ ጀምሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 704 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7, 334 የላቦራቶሪ ምርመራ 704 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ3 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገልጿል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 551 ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 39 ከትግራይ ክልል፣ 30 ከኦሮሚያ ክልል ፣ 26 ከጋምቤላ ክልል ፣ 21 ከአማራ ክልል ፣ 11 ከሲዳማ ክልል ፣ 10 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 5 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ 3 ከአፋር ክልል ፣ 3 ከሶማሌ ክልል ፣ 3 ከሐረሪ ክልል እና 2 ከደቡብ ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 የደረሰ ሲሆን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 170 ደርሷል፡፡

በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ ዘጠና ስድስት (196) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5,137 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ!

በኢትዮጵያ ትላንት የተመዘገበው በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር (704) ወረርሽኙ ሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

በአዲስ አበባ የተመዘገበው የ551 ሰዎች ኬዝ ወረርሽኙ በከተማይቱ ከገባ ጊዜ አንስቶ የመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ከዚህ ቀደም እንዳልናችሁ የሀገሪቱ የምርመራ አቅም በጨመረ ቁጥር በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ይገኛል።

የምትችሉ ከሆነ በSMS እና ስልክ በመደወል የኢንተርኔት አገልግሎትና መደበኛ ሚዲያዎችን በንቁ ለማይከታተሉ ወዳጆችሁ እየሆነ ያለውን አሳውቁ። እንዳይዘናጉ አሳስቡ!

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኮቪድ-19 ክትባት ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል!

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙክራ ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን #BBC ዘግቧል።

ክትባቱን መውሰድ ደህንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑ እንዲሁም ስለወጤታማነቱ ዛሬ ላንሴት የህክምና ጆርናል ላይ የሙከራው ውጤት ዝርዝር ይፋ ሲደረግ የሚታወቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የ2020 ባላንዶር ሽልማት አይኖርም ተባለ!

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በፈጠረው ቀውስ ሳቢያ የ2020 'የባላንዶር' ሽልማት እንደማይኖር / ለየትኛውም የእግር ኳስ ተጫዋች እንደማይሰጥ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በኬንያ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አለፈ ፤ ይህ እስከዛሬ በ24 ሰዓት ከተመዘገበው ሁሉ ከፍተኛው ነው። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 253 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
526 የጤና ባለሞያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

ዶ/ር ረሺድ አማን በሰጡት መግለጫ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኬንያ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 526 የጤና ባለሞያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
#ADDISABABA

' ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ' የምግብ ዘይት #በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ እንደሚገኝ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ታክስ እና ቀረጥ በማንሳቱ ነው 5 ሊትሩ የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች እየቀረበ የሚገኘው።

የምግብ ዘይቱ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት አራት ኪዊንስ ሱፐርማርኬት ለተጠቃሚዎች እየቀረበ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
#NaolDaba

በኢትዮጵያዊው ወጣት ናኦል ዳባ የተሰሩ ሁለት ድሮውንና አንድ የኮሮና ቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል።

በወጣት ናኦል ዳባ የተሰሩት ለግብርና እና ለተግባቦት ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት የድሮውንና ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ የኮሮናቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው።

የድሮውን ፈጠራ ውጤቶቹ ፀረ-አረም መድሃኒት መርጫና ከርቀት ሆኖ ለማኅበረሰቡ መልክዕት ማድረስ የሚያስችሉ ናቸው - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
TIKVAH-ETHIOPIA
በኬንያ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ! በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አለፈ ፤ ይህ እስከዛሬ በ24 ሰዓት ከተመዘገበው ሁሉ ከፍተኛው ነው። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 253 ደርሷል። @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CORRECTION

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት 19 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት እንደሞቱ ይህም እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጾ ነበር።

መረጃው ስህተት እንደሆነና ባለፉት 24 ሰዓት የሞቱ ሰዎች አራት (4) እንደሆኑ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ይቅርታ በመጠየቅ ማስተካከያ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ!

ትላንት በሀገራችን 704 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ይታወቃል ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ ከ10 በመቶ በላይ የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለኤፍ ቢ ሲ ሲናገሩ እንደተደመጡት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጅጉ እየጨመረ ነው ብለዋል።

ስንት ሰው ተመረመረ ? ስንት ሰው ተያዘ ? የሚለው ሲታይ ከዚህ ቀደም ፖዘቲቭ የሚሆኑት ከ1 በመቶ በታች የነበረ ሲሆን ሰሞኑን በሀገራችን በተከሰተው ሁኔታ ወደ 3 በመቶ ከፍ ብሎ ነበረ ፤ ትላንት ደግሞ 10 በመቶ ደርሷል ፤ የአ/አ ደግሞ ከ10 መቶ በላይ ሆኗል ሲሉ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጀ ይህ ፐርሰንት ስርጭቱ በደንብ በተስፋፋባቸው ሀገራት ላይ የሚገኝ እንደሆነም ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ውጤታማ ነው ተባለ!

በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተሰራው የኮሮና ቫይረስ ክትባት የሰዎችን በሽታውን የመከላከል ሥርዓት እንደሚያጎለብትና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑ መገለፁን BBC ዘገበ።

በምርምር ሥራው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉ 1,077 ሰዎች ሲሆኑ የተሰጣቸው ክትባት ጸረ ተህዋስ [አንቲቦዲ] እንዲያዳብሩ እና ነጭ የደም ህዋሳቸው ኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲችል ሆኗል ተብሏል።

የዚህ ምርምር ውጤት ግኝት በጣም ተስፋ ሰጪ የተባለ ሲሆን ፤ ይህ ግን የመከላከል አቅምን ለማግኘት በቂ ስለመሆኑ አለመታወቁ ተገልጾ ሰፊ ሙከራ እየተካሄደ ነው።

ይህ ምርምር የተደረገው በቅድሚያ ክትባቱ ለበርካታ ሰዎች ቢሰጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ይሆናል ወይ የሚለውን ለማረጋገጥ ነው ተብሏል።

ክትባቱ ውጤታማ ሆኖ ለአገልግሎት የሚበቃ ከሆነ ዩናይትድ ኪንግደም አስቀድማ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ማዘዟ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
ለዘንድሮ ተፈታኞች ማስታወሻ!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን በወረቀት እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኦን ላይን ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን መረጃ ሰጥተናችሁ ነበር።

ተማሪዎች ለምትወስዱት ፈተና ዝግጅት እያደረጋችሁ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እስኪገለፅ እንድትጠብቁ ፤ ወላጆች ልጆችን በማበረታታት ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማድረጉን እንዳትዘነጉ #ለማስታወስ እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 304 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,056 የላብራቶሪ ምርመራ 304 ሠዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ እንዲሁም የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በቫይረሱ የተያዙት ሠዎች 157 ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 36 ከትግራይ ፣ 46 ከኦሮሚያ፣ 26 ከጋምቤላ ፣ 12 ከአማራ ፣ 17 ከአፋር ፣ 7 ከሱማሌ ፣ 2 ከሐረሪ እና 1 ከደቡብ ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች 10 ሺህ 511 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 173 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 5,290 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የፍርድ ቤት ውሎ!

ዛሬ የህወሃት ፅህፈት ቤት የአዲስ አበባ አገናኝ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃዲቅ ከሁለት ሹፌሮች ጋር ፣ የአቃቂ ክፍለ ከተማ የደህንነት ሹም አቶ አፅብሃ አለማየሁና በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የህግና ፍትህ ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋለም ይህደጎ ችሎት ቀርበው ነበር።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ጠበቆቻቸው ለጀርመን ሬድዮ እንደተናገሩት ከተያዙ 2 ሳምንት የሆናቸው ተጠርጣሪዎች ፖሊስ የመንግስትን መረጃ ለሀገር ውስጥና ለውጭ የሽብር ቡድኖች አሳልፎ መስጠት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት ገልፆ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸዋል።

በተለይ አቶ ተስፋለም ይህደጎ በታሰሩበት እስር ቤት 3 ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያለባቸው ታሳሪዎች በመገኘታቸው ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ ከቤተሰቦቻቸውና ጠበቆቻቸው ለመገናኘት እንዳልቻሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ተመልክቶ አያያዛቸው ለህይወታቸው በማያሰጋ መልኩ መሆን እንዳለበት ከቤተሰቦቸው እና ጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ፖሊስ ይህ ትዕዛዝ መፈፀሙን በቀጣይ ቀጠሮ ጊዜ ሪፖርት ይዞ እንዲቀርብ አዟል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን የ 14 ቀን ጊዜ ውድቅ በማድረግ የ8 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጀርመን ሬድዮ ጣቢያ በምሽት ስርጭቱ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከ7,000 በላይ ሆነዋል!

በኦሮሚያ ክልል ሁከት በመቀስቀስ፣ ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ከ7,000 በላይ መድረሳቸውን አቶ ጌታቸው ባልቻ /የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ/ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ከነዚህ መካከል ተመክረው የሚለቀቁ እንዳሉ የገለፁ ሲሆን የወንጀል ድርጊታቸው የተረጋገጠባቸው በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል።

በአሁን ሰዓት የኦሮሚያ ክልል ወደ ቀደመ ሰላም ተመልሷል ፤ ንብረት የወደመባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
በ2 ቀን ብቻ 1,008 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

በኢትዮጵያ ከትላንት በስቲያ እንዲሁም ትላንት በድምሩ 1,008 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ለወረርሽኙ መጨመር ከምክንያቶቹ ዋነኛው የህብረተሰቡ መዘናጋት እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

በትላንትናው ዕለት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችሁ ይህ ፅሁፍ ማንበብ የቻላችሁ የቲክቫህ አባላት በየአካባቢያችሁ ያለውን ሁኔታ እንዴት እየገመገማችሁት ነው ?

እየታየ ያለውን ከፍተኛ መዘናጋት ለመቅረፍ መፍትሄ የምትሉት ሃሳብ ምን ይሆን ? በ @tikvahethiopiaBot መጠቆም ይቻላል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
የኢንተርኔት መቋረጥና የትራንስፖርት አገልግሎት!

'ዛይራይድ' የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በሀገሪቱ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ኢንተርኔት በመቋረጡ በ2 ሳምንት ግማሽ ሚሊዮን ብር (500,000 ብር) ገቢ ማጣቱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde