TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MinistryOfPeace

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ስርዓት አካል የሆነው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ አብስሯል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የቅድመ ማስጠንቀቂያው ስርዓት ማህበረሰቡን ከተለያዩ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ስርዓቱ የሙከራ ጊዜዉን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናቶች ውስጥ አገባዶ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
"ሃጫሉ ሁንዴሳ የተገደለው በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አይደለም ፤ የኦ.ነ.ሰ ሃጫሉን አይገድለውም!' - ኩምሳ ድሪባ /ጃል መሮ/

በቅፅል ስሙ ጃል መሮ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አዛዥ ኩምሳ ድሪባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ተጠያቂ አይደለሁም ብሏል።

ጃል መሮ ከአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ፅዮን ግርማ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ድምፃዊ ሃጫሉ ስልጣን ላይ ካሉት መሪዎች ይልቅ ለኦሮሞ ነፃነት ጦር የቀረበ ነበር ፤ ተቃውሞ ቢኖረው እንኳን እርሱን ልንገድል የምንችልበት ምክንያት የለም ብሏል።

ጃል መሮ አያይዞ መሳሪያ ከታጠቀው ኃይል ጋር ጦርነት ላይ ብንሆንም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግን በፍፁም ጥቃት አናደርስም ብላል። ሰላማዊ ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ተግባር የመንግስት ነው ሲልም ገልጿል።

ኩምሳ ድሪባ /ጃል መሮ/ ከአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጋዜጠኛ ፅዮን ግርማ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ማድመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ310 ሺህ አለፉ!

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 311,049 ደርሷል። በሀገሪቱ ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ የ4,453 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 160,693 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጎጂዎችን የማቋቋም ስራ በጎባ ከተማ!

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት ተከትሎ በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተፈጠረ አለመረጋጋት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በማጽናናት የጠፋባቸውን ንብረት መልሶ የማቋቋም ስራ መጀመራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች መግለፃቸውን ኢዜአ አስነብቧል።

በጎባ 46 የመኖሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን የጠፋው ንብረት 3 ሚሊዮን 700 ሺህ ብር ይገመታል ተብሏል።

በከተማው ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሃምሳ አራት (54) ግለሰቦች ተይዘው ጉዳያቸው ለፍርድ ቤት መቅረቡን የኢዜአ መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ሙሉ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር መሆኑን የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልጿል።

የትምህርት ፣ የጤና ፣ የስራና የሌሎች አስገዳጅ ጉዞዎች ብቻ የፓስፓርት አገልግሎትን በመስጠት ላይ የሚገኘው ተቋሙ በቀጣይ ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን መስጠት የሚያስፈልግበት ሁኔታ በመፈጠሩ በቅርቡ በሙሉ አቅም ወደ ሰራ ለመግባት መታቀዱን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 8,803 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6,911 የላብራቶሪ ምርመራ 328 ሠዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ2 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ሠዎች 250 ከአዲስ አበባ ፣ 27 ከጋምቤላ ፣ 15 ከኦሮሚያ፣ 13 ከትግራይ፣ 8 ከአፋር፣ 5 ከድሬደዋ ፣ 5 ከሱማሌ፣ 3 ከሲዳማ ፣ 1 ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ 1 ከአማራ ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሠዎች ቁጥር 8,803 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ቁጥር ደግሞ 150 ደርሷል፡፡

ትላንት አርባ ስድስት (46) ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4,814 መድረሱ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊ መግለጫው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ መንገደኛ በሰባ ሁለት ሰዓት (72) ውስጥ ተመርምሮ ከኮቪድ ነፃ የሚል ማረጋገጫ እንዲያመጣ የሚያስገድደው መመሪያ ወደ አምስት ቀናት ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት በበርካታ አገራት ምርመራው ጊዜ የሚወስድ እና መንገደኞችም በቶሎ ምርመራውን አድርገው ውጤቱን ይዘው መምጣት እንዲችሉና መንገዱ የሚፈጀው ጊዜ ታሳቢ ተደርጎ መሻሻል እንደነበረበት አንስተዋል።

ባሉበት አገር ተመርምረው ኢትዮጵያ እስከሚገቡ ከሶስት (3) ቀናት በላይ ይወስድብናል የሚል ቅሬታ ከተለያዩ መንገደኞች በመምጣቱ ነው ማሻሻያው የተደረገው ሲሉ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩት በተለያየ መደብ ተከፍለዉ እንደሚሆን የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢሲ አስነብቧል።

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም በሰጡት መግለጫ የ2012 የትምህርት ዘመን ማካካሻና ማሟያ ትምህርትን ለመስጠት ተቋማት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የትምህርት አሰጣጡን በተመለከተ ሳምንቱን በሙሉ እስከ ምሽት የሚከናወን ሲሆን ከ4ተኛ አመት በላይ ያሉና ተመራቂ ተማሪዎች በቅድሚያ እንዲገቡና ትምህርታቸዉን በኦንላይንና በገፅ ለገፅ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ቀድመዉ የገቡት መርሀ ግብራቸውን እንዳጠናቀቁ ከ3ተኛ አመትና ከዚያ በታች ያሉት ተማሪዎች በተመሳሳይ መንግድ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርትም ይሁን አጠቃላይ ትምህርቱ የገፅ ለገፅ ተግባራዊ የሚደረገዉ የኮሮና ቫይረስ በጤና ሚኒስቴር እንዲሁም በሚመለከታቸዉ አካላት ስጋትነቱ መቀነሱ ሲረጋገጥ መሆኑን ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፍርድ ቤት ውሎ!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት የአቶ ጃዋር መሐመድና በ9 ግለሰቦች እንዲሁም የአቶ በቀለ ገርባና የአቶ እስክንድር ነጋ አራት የምርመራ መዝገቦችን ተመልክቷል፡፡

በዚህም በአቶ ጃዋር መዝገብ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን ሲፈቅድ በ9ኙ ተጠርጣሪዎች ላይ የ12 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም በአቶ በቀለ ገርባ ላይ 11 ቀን፣ እንዲሁም በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ 13 ቀን ተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

@tikvahmagBot @tikvahethmagazine
ከለይቶ ማቆያ የሚያመልጡ የኮቪድ-19 ተጠርጣሪዎች!

በጋምቤላ ክልል በኮሮና የተጠረጠሩ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ እየጠፉ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኡጁሉ እንደተናገሩት በለይቶ ማቆያነት ከሚያገለግለው ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜያት ያመለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ደርሷል።

ሰዎቹን ፈልጎ ማግኘቱ አስቸጋሪ እንደሆነ የጠቀሱት ሃላፊው ከመካከላቸው እስካሁን የተገኘ አለመኖሩን አስረድተዋል።

የክልሉ ነዋሪዎች በሽታው የለም መመርመሪያውም በትክክል አይመረምርም የሚሉና ሌሎች የተሳሳቱ አመለካከቶችን እንደሚያንጸባርቁ የገለጹት ዶ/ር ኡጁሉ ህዝቡ ስለ በሽታው ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን #አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

አብዛኛዎቹ የኮሮና ታማሚዎች ምልክት ስለማያሳዩ ብዙዎች በሽታው የለም የሚል እምነት እንዳደረባቸው ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

በጋምቤላ ክልል እስካሁን በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር 180 የደረሰ ሲሆን 54 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የዶቼ ቨለ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 9‚147 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7‚407 የላብራቶሪ ምርመራ 344 ሠዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ13 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል አራቱ የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ዘጠኙ በአስከሬን ምርመራ የተለዩ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሠዎች ቁጥር 9,147 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ቁጥር ደግሞ 163 ደርሷል፡፡

በትላንትናው ዕለት ሰማንያ ስድስት (86) ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4,900 መድረሱ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊ መግለጫው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከፍተኛ ጥንቃቄ!

#SHARE #ሼር

በኢትዮጵያ የምትኖሩ የቲክቫህ አባላት ፣ ይህን መልዕክት የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችሁ ማንበብ የቻላችሁ በሙሉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ በሀገሪቱ እየተሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ አድርጉ።

ኢትዮጵያ የመመርመር አቅሟን እያሣደገች መጥቱን ተከትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።

በሀገሪቱ በሁለት ቀናት #ብቻ (ሀምሌ 9/2012 እና ሀምሌ 10/2012) 672 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል በትላንት እንዲሁም በዛሬ ሪፖርት መሰረት 15 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህንን መልዕክት በስልካችሁ ያገኛቹ ወገኖቻችን እራሳችሁ እና ቤተሰባችሁን በሙሉ ከዚህ አስፈሪ ወረርሽኝ ሳትዘናጉ እንድትጠብቁ ጥሪ እናቀርባለን ፤ ኢንተርኔት ማግኘት ላልቻሉ ወዳጆቻችሁ በSMSና በመደወል አሳሳቢውን ሁኔታ አሳውቋቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ ጉዮን ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት ሄደዋል" - የጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ቤተሰብ አባል

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ ከአንድ (1) ሳምንት በፊት በOMN ቃለመጠይቅ ያደረገለት ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ከጋዜጠኛው ቤተሰብ አባላት አንዱ ለBBC እንደተናገሩት ዛሬ እኩለ ቀን ላይ "የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ" ጉዮን ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት ሄደዋል፤ የጸጥታ አባላቱ ጉዮን ወደየት ይዘውት እንደሚሄዱ ለመናገር ፍቃደኛ አልነበሩም ሲል ገልጿል።

ከፀጥታ አባላቱ መካከል አምስቱ (5) የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ የደንብ ልብስን የለበሱ ሲሆን አንዱ (1) ደግሞ መደበኛ ልብስ መልበሳቸውን የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።

አክለውም ከሃጫሉ ግድያ እና የOMN ቢሮ መዘጋት በኋላ ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው ራቅ ያለ ስፍራ ተሸሽገው እንደነበር ተናግረው ፖሊሶቹ ያሉበትን ፈልገው እንዳገኟቸው ገልጿል።

እኚሁ የጋዜጠኛ ጉዮ ቤተሰብ አባል ለBBC እንደገለፁት "የጸጥታ ኃይሎቹ በመሳሪያ ስላስፈራሯቸው" ተከትለውት መሄድ አልቻሉም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡ ነው!

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሐምሌ 13/2012 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡ መሆኑ ኢቢሲ ዘግቧል።

ከመጪው ሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዳኞች በመደበኛ የስራ ሰዓት ቢሮ ገብተው አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ክስ መስማት ፤ ምርመራቸው በተገባደደ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት እና የመሳሰሉ ስራዎችን ያከናውናሉ ተብሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ14 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 14,061,849 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 595,029 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 8,360,841 ሰዎች አገግመዋል።

በዓለም ከፍተኛ ሰዎች በቫይረሱ የተያዘባቸው ሦስት ሀገራት አሜሪካ (ከ 3.7 ሚሊዮን በላይ) ፣ ብራዚል (ከ 2 ሚሊዮን በላይ) ፣ እንዲሁም ህንድ (ከ 1 ሚሊዮን በላይ) ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ የሰዎች ሞት የተመዘገበባቸው 3 ሀገራት አሜሪካ (141,479) ፣ ብራዚል (76,997) እንዲሁም UK (45,223) ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በእስራኤል!

በእስራኤል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ የመገበያ ግዙፍ መደብሮች ፤ ክፍት የገበያ ቦታዎች ፤ የፀጉር ማስተካከያ ቤቶች፤ የመጽሐፍ መደብሮች እና ሙዚየሞች ዝግ እንዲሆኑ መደረጉ ተሰማ።

በሚቀጥለዉ ሳምንት በሃገሪቱ የመዝናኛ የባህር ዳርቻዎች ዝግ ሆነዉ እንደሚቆዩም የፈረንሳይ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

በእስራኤል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑ የሃገሪቱን መንግሥት ስጋት ላይ እንደጣለው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ በቀለ ገርባ ልጆች ከእስር ተፈተዋል!

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተነሳው ግርግር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሰዎች መካከል የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ቦንቱ በቀለ፣ ወንድሟ እና የእክስቷ ልጅ ትላንት ከእስር መፈታታቸውን ቢቢሲ በሬድዮ ስርጭቱ ዘግቧል።

ቦንቱ በቀለ ዛሬ ከቢቢሲ የሬድዮ ስርጭት ጋር በነበራት ቆይታ ተከታዩን ብላለች ፦

"ያለ ጥፋታችን ነው የታሰርነው ፣ የተንገላተነው። እኔ እና ወንድሞቼ ከአባቴ ጋር ስለነበርን ነው እንጂ ምንም የሰራነው ወንጀል የለም። አባታችን ፖለቲከኛ ነው፣ ለሰብዓዊ መብት የሚታገል፣ ለዴሞክራሲ የሚታገል፣ ለብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የሚታገል ሰላማዊ ታጋይ ነው።

ከዚህ በፊትም እስር ቤት ነበር አሁንም እስር ቤት ነው በእግዚያብሔር ፍቃድ አንድ ቀን ይወጣል ፤ ሰላማዊ ትግልን ይቀጥላል።

እኛም እንደ ቤተሰብ እሱን ከመደገፍ ወደኃላ አንልም። አባቴ የተቃዋሚ አመራር ስለሆነ እኔ ወይም ወንድሞቼ ለእደዚህ አይነት እንግልት በመዳረጋችን በጣም ነው የምናዝነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ670 ሺህ አለፉ!

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 670,741 ደርሰዋል ከነዚህ መካከል 14,492 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 348,236 ሰዎች አገግመዋል።

ከፍተኛ የሰዎች ቁጥር በቫይረሱ የተያዘባቸው ሦስት ሀገራት ደቡብ አፍሪካ (324,221)፣ ግብፅ (85,771) እንዲሁም ናይጄሪያ (34,854) ናቸው።

እንደ #worldometers መረጃ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ባላት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር አስራ ሁለተኛ (12) ላይ ትገኛለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀላፊነት የጎደላቸው የአዲስ አበባ መጠጥ ቤቶች!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሽታ በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ ጨመሯል የሟቾችም ቁጥር ከዕለት ወደዕለት ቁጥሩ እያሻቀበ ይገኛል።

በርካቶች በኮቪድ-19ኝን ለመከላከል የሚወስዱት ጥንቃቄ በእጅጉን አናሳ ሲሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኾላ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች ፍፁም ሀላፊነት በጎደለው መልኩ የመጠጥ ሽያጭን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ይባስ ተብሎም አንዳንድ ቤቶች በአንድ ጠረጴዛ ላይ በርከት በማለት ይጠጣል ፣ ይበላል ፣ ይደንሳል፣ ተሰክሮም ይጨፍራል።

ይህ ሁሉ ሲሆን የፀጥታ ሀይሎች ምንም አይነት እርምጃ ሲወስዱ አይታይም።

ጭራሽ 20/80 የሚባል የመጠጥ ቤቶች ሀሜት ይወራል 20%ቱ በአከባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አስከባሪዎች ጉርሻ መሆኑ ነው።

ስለዚህ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እየገደለ ስለሆነ ሁላችንም የሀላፊነት ስሜት ካልተሰማን ኮቪድ-19 ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

ጉዳዩ ይመለከተናል ፣ የህዝብ ደህንነትና ጤና ያሳስበናል የሚሉ አካላት ሁሉ ከወዲሁ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እና እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር ከ600 ሺህ አለፈ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) መያዛቸው ከተረጋገጠው 14,214,771 ሰዎች መካከል 600,0037 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሳይሪል ራማፎዛ የኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን መሪዎችን በመጪው ማክሰኞ በድጋሜ ለማገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia