TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,552 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5,570 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 86 ወንድ እና 59 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2 ወር - 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት/ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

94 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 22 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 10 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 6 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ እና 3 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 8 (1 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 2 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ 3 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 94 ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ህይወታቸው ያለፈ 5 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ64 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

3. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

4. የ90 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ።

5. የ40 ዓመት ሴር የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 327 ሰዎች አገገሙ!

በትላንትናው ዕለት 327 ሰዎች (317 ከአዲስ አበባ ፣ 8 ከአማራ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2,015 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በኢትዮጵያ የተመዘገበው 'አዲስ ያገገሙ' ሰዎች ቁጥር (327) ወረርሽኙ ሀገሪቱ ውስጥ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሁለት (2) በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችንና ሰላሳ አምስት (35) አዲስ ያገገሙ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋል!

በፌደራል ደረጃ ይፋ በተደረገው ሪፖርት በትግራይ ክልል አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ አይገልፅም።

በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ይፋ በተደረገው ሪፖርት ከ370 የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች (በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው) በቫይረሱ መያዛቸውን ይገልጻል።

በሌላ በኩል በጤና ሚኒስቴር ሪፖርት በትግራይ ክልል አዲስ ያገገሙ ሰዎች 1 ተብሎ ይተገለፀ ቢሆንም በክልል ደረጃ በወጣው ሪፖርት አዲስ ያገገሙ ሰዎች 35 መሆናቸውን ያሳያል።

በትግራይ ክልል ደረጃ (እንደ ክልሉ ጤና ቢሮ መረጀ መሰረት) በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 206 ሲሆን 77 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Oromia

ባለፉት 24 ሰዓት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀጥሎ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ኬዝ የተመዘገበው በኦሮሚያ ክልል ነው።

በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 22 ሰዎች ፦

- 3 ሰዎች ሱሉልታ
- 1 ሰው አ/አ (ነቀምቴ ላብራቶሪ በተደረገ ምርመራ)
- 5 ሰዎች ምስራቅ ሐረርጌ
- 2 ሰዎች ምዕራብ ሐረርጌ
- 5 ሰዎች ቡራዩ
- 1 ሰው ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 2 ሰዎች ቦረና
- 1 ሰው ሰበታ
- 1 ሰው አርሲ
- 1 ሰው ሱሉልታ

የእድሜ ክልላቸው ከ1-64 ዓመት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በፆታ አኳያ ደግሞ አምስቱ (5) ሴቶች ሲሆኑ 17 ወንዶች ናቸው።

ከሃያ ሁለቱ መካከል 10 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ናቸው፤ 5 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ አላቸው (ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱማሊላንድ -ሃርጌሳ) ፣ 7 ሰዎች ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 898 ሲሆን 10 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

- 9 ሰዎች ከምዕራብ ጎንደር ዞን (3 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ፣ 4 ሰዎች በቤት ውስጥ ለይቶ ማቆያ Home Quarantine ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ) ናቸው። 3 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 6 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

- 1 ሴት ከደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ፤ ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላት የነበረች ፥ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም።

በፆታ አኳያ 6 ወንድና 4 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2-52 ውስጥ ነው።

#COVID19Diredawa

በድሬዳዋ ከተማ ከተደረገው 110 የላብራቶሪ ምርመራ 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

#COVID19BenishangulGumuz

ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው 186 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ሶስት (3) ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በዛሬዉ እለት ቫይረሱ እንደተገኘባቸዉ ከተገለጹ ግለሰቦች ሁለቱ (2) ከጉባ ወረዳ ለይቶ ማቆያ የነበሩ የ25 እና 32 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ወንዶች ናቸው።

ለላኛው በቫይረሱ የተገኘበት የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን ደግሞ ሰኔ-19-2012 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በመጣበት ወቅት ከዳቡስ ኬላ ለይ ከተሳፋሪዎች በተወሰደዉ የናሙና ምርመራ ነዉ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ስድስት (3,636) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ሰዎች ናቸው። ዘጠና አንዱ (91) አድራሻቸው አዲስ አበባ ሲሆን የቀሩት 3 ሰዎች በአ/አ ከሚገኙ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ የስደት ተመላሾች ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው 3 ፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው 5 ሲሆኑ የቀሩት 86 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሃይድሮክሲክሎሮከዊን እጥረት እያጋጠመ ነው!

ሃይድሮክሲክሎሮከዊን የተባለው መድኃኒትን ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮ እና የአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ሲቀሰቅሱ እንደነበረ አይዘነጋም።

በዚህም ሳቢያ ሃይድሮክሲክሎሮከዊን መድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ በአቅርቦት ላይ እጥረት ማስከተሉንና የዋጋ ጭማሪ መፈጠሩን #BBC ዘግቧል።

ይህ ሁኔታ ሃይድሮክሲክሎሮከዊን ለተለያዩ ህክምናዎች በሚወስዱ ህሙማን ላይ ቀጥተኛ ጫናን ማስከተሉ BBC አስነብቧል።

በቅርቡ የተደረገ ሙከራ መድኃኒቱ ኮቪድ-19 ለማከም አስተዋጽኦ እንደሌለው ቢያመለክትም ፤ አንዳንድ አገራት ግን መድኃኒቱ ጥቅም እንዳለው ማስተዋወቃቸውን ቀጥለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅትም ሃይድሮክሲክሎሮከዊን ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚፈይደው ነገር የለም በማለት በመድኃኒቱ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ ማቆሙን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ10 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ቁጥር ከ10 ሚሊዮን መብለጡን የworldometers ድረገፅ መረጃ ያሳያል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሟቾች ቁጥር 498,952 የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 5,414,648 ደርሰዋል።

ከፍተኛ የሰው ቁጥር በቫይረሱ ከተያዘባቸው የዓለም ሀገራት መካከል አሜሪካ (2.5 ሚሊዮን ሰዎች) ፣ ብራዚል (1.2 ሚሊዮን ሰዎች) እና ሩሲያ (627,627 ሰዎች) በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የህዳሴ ግድቡ ደህንነት እንዴት እየተጠበቀ ነው ?

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ (የጦር ኃይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ፦

...ከደህንነት አንፃር በኃይል የሚሆን ነገር የለም ፤ ጦርነት ጥፋት ነው እንጂ ውሃም አያስገኝም ፣ ልማትም አያስገኝም ቀጠናውን በሙሉ ነው የሚጎዳው የበለጠ ደግሞ የምትጎዳው ግብፅ ልትሆን ትችላለች።

እኛ ባለመልማታችን ችግር ላይ ነው ያለነው ለመልማት ነው እየሞከርን ያለነው፣ ለመልማት የሚሞክርን ሀገር መደገፍ ነው እንጂ ማደናቀፍ ተገቢ አይደለም።

በዚህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ኢትዮጵያን እየደገፈ ነው ፤ ከኢትዮጵያ ጎን ነው። ያ የመጀመሪያው ሞቅታ ልክ አይደለም!

ግድቡ እየተሰራ ነው ፤ ስራውም ይቀጥላል። ግድቡን የሚያጠቃ ነገር ይመጣል ብለን አንጠብቅም ፤ ከመጣም እንመክታለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ምንድነው ?

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምከንያት በተቋረጠው ትምህርት ዙሪያ የተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ አገር አቀፉ ኮማንድ ፖስት በሚያስተላልፈውና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚወሰን መሆኑን ኢ.ፕ.ድ. (EPA) ዘግቧል : https://telegra.ph/EPA-06-28

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ2 ሳምንት ስምምነት ላይ ባይደረስስ ?

የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ቡድን አባል ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው በትላንትናው ዕለት ከአልጀዚራ የአረብኛው ክፍል ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። ይህን ቆይታቸውን ኡስታዝ ጀማል በሽር አህመድ ተርጉሞ ለህዝብ አሰራጭቷል።

በአልጀዚራ አረብኛው ክፍል ከተነሳላቸው ወሳኝ ጥያቄዎች አንዱና የብዙ ሰዎች ጥያቄ የሆነው እንደው አይበለውና በሁለት ሳምንት ውስጥ በሀገራቱ መካከል ስምምነት ላይ ባይደረስ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ትችጀምራለች ? የሚለው ነበር።

የአልጀዚራ ጋዜጠኛ : በሁለት ሳምንት ውስጥ ስምምነት ላይ ባይደረስ ኢትዮጵያ ውሃውን መሙላት ትጀምራለች ? በአጭሩ ይመልሱልኝ።

ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው : አዎን/نعم/na'am/yes

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3895 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5689 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 87 (52 ከጤና ተቋም እና 35 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ህይወታቸው ያለፈ 4 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ20 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በሕክምና ላይ የነበረ።

2. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በሕክምና ላይ የነበሩ።

3. የ80 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

4. የ21 ዓመት ወንድ የሐረሪ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35 ከትግራይ ክልል እና 4 ከድሬደዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2132 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#COVID19Harari

ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ከፍተኛው የ24 ሰዓት ኬዝ የተመዘገበው በሐረሪ ነው። 100 የላብራቶሪ ምርመራ 7 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

6 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ ሁለቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ፤ አምስቱ ለህክምና ወደ ሐረር መጥተው ናሙና የተወሰደላቸውና ነዋሪነታቸው 1 ሰው ሱማሌ ክልልና 6 ሰዎች ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሆኑ ናቸው።

#COVID19Tigray

በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች 96 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 19 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል (የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ላይ አልተገለፀም)።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 195 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል (2 ሰዎች የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸውና 1 ሰው ንክኪ ያለው ነው)፤ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 209 ደርሰዋል።

#COVID19Oromia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 215 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ከተገኝቶባቸዋል። የ24 ዓመት እድሜ ያለው የምሥራቅ ሐረርጌ ነዋሪ ከማህበረሰቡ የተገኘ ፣ የ55 ዓመት እድሜ ያላቸው የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ነዋሪ ከማህበረሰቡ የተገኙ እንዲሁም 20 ዓመት ሴት ከምዕራብ ሐረርጌ ናት።

#COVID19Amhara

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 451 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ቫይረሱ የተገኘበት የ23 ዓመት ወጣት ሲሆን በወረይሉ አውቶብስ መናኸሪያ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ነው ቫይረሱ ሊገኝበት የቻለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia