TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከኮቪድ-19 ውጭ ያሉ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethmagazine በኩል ተከታተሉ ፦

- የሀላባ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የ2012 3ኛ አስቸካይ ጉባኤ ሰኔ 19-2012 ዓ.ም የፊታችን አርብ በሀላባ ያካሃዳል።

- ምዕራብ ሐረርጌ ቱሎ ወረዳ የአንበጣ መንጋ መታየቱን የምዕራብ ሐረርጌ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ጥቆማ አድርሰዋል።

- በባብሌ የዝሆኖች መጠለያ የአንበጣ መንጋ በተፈጥሮ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን መ/ቤት አስታውቋል።

- የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሂድ ጀምሯል።

- 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

- በፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን ዛሬም ቀጥለው እየተገመገሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

- ግብጽ የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገዉ ጥረት የማይሳካ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል።

ትክክለኛው (@tikvahethmagazine) ገፅ ከ 229,000 በላይ የቲክቫህ አባላት ያሉበት ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳይ!

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ የሚገታበት ጊዜ ባለመታወቁ የሚጀምራቸውን ትምህርቶች ለመለየት መቸገሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

በቫይረሱ ምክንያት በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጡ የነበሩ መደበኛ ትምህርቶች ተቋርጠው የተወሰኑትን በመለየት በበይነ መረብ አማካኝነት የመማመር ማስተማሩ ሂደት መቀጠሉ ይታወቃል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ለመደበኛ ተማሪዎች በበይነ መረብ አማካኝነት እየሰጡት ያለውን ትምህርት በክረምቱ እንደማይቀጥሉ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ግን በመደበኛው ትምህርት የተጀመረው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ነው ብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ መቼ እንደሚቆም አለመታወቁ መደበኛውን ወይስ ደግሞ የክረምቱንና የርቀቱን ለመጀመር ቁርጥ ውሳኔ ማሳለፍ አልተቻለም - #AhaduRadio

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 186 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ5,000 አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,034 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5,034 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንድ እና 113 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ6 ወር - 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 181 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5 የውጭ ዜጋ ናቸው።

147 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 10 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 8 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከደቡብ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 (15 ከጤና ተቋም እና 20 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል።

በተጨማሪ አንድ (1) በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ስምንት (78) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ38 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

2. የ19 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

3. የ40 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ በሱማሌ ክልል ፣ በአፋር ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል እና በደቡብ ክልል በድምሩ 39 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

በአፋር ክልል ከተደረገው 91 የላብራቶሪ ምርመራ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ደርሷል።

በኦሮሚያ ክልል ከ704 የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 2 ሰዎች (1 ወንድና 1 ሴት) ከቦረና ናቸው ፤ ወንዱ ከማህበረሰቡ የተገኘ ፣ ሴቷ ወደ ኬንያ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላት ናት። 12 ዓመት ታዳጊ ከምስራቅ ሐረርጌ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት፤ አንድ የ22 ዓመት ሴት ከቡራዩ ከማህበረሰቡ የተገኘች ናት።

በደቡብ ክልል 362 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፤ ግለሰቡ የ44 ዓመት ወንድ የጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ነዋሪ ሲሆን፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አለው።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተደረገው 146 የላብራቶሪ ምርመራ 8 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 5ቱ ወንዶች ሲሆኑ 3ቱ ሴቶች ናቸው። ሁሉም ከማህበረሰብ ክፍሎችና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ግለሰቦች የተወሰዱ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያውቅለትና ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ እንዳልተቀበለው አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የምሰጥበት የህግ አግባብ የለም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል - @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኮቪድ-19 ያገገሙ ታካሚዎች ወደቤታቸው ተሸኙ!

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል የኮቪድ 19 ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

በኮቪድ-19 ፓዘቲቭ ሆነው ወደ ሆስፒታሉ የገቡት በአጠቃላይ 178 ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሁለቱ ዙር አጠቃላይ 81 ሰዎች አገግመው ወጥተዋል።

በሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ሰዎች 205 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 144 ሰዎች ነጻ ተብለው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ሆስፒታሉ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ114 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ከኮቪድ-19 አገገሙ!

የ114 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው መውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ አግደው አሳውቀዋል።

ከኮቪድ-19 ያገገሙት አዛውንት ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ዶ/ር ያሬድ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንሱ ሶኒ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ!

የላይቤሪያው ትምህርት ሚኒስትር በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

የላይቤሪያ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ሳምንት ትምህር ቤቶች እንዲከፈቱ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት ሚኒስትሩ ሆስፒታል የገቡት።

ሚኒስትር አንሱ ሶኒ ብቻ ሳይሆን ምክትላቸው ላቲም ዳ - ቶንግም ሆስፒታል ገብተዋል። ፍሮንት ፔጅ አፍሪካ የተሰኘው የላይቤሪያ ጋዜጣ ሚኒስትር ዴኤታው ሕመማቸው ሲፀና ወደ ጋና ሄደው እንዲታከሙ መደረጋቸውን ዘግቧል።

የላይቤሪያ መረጃ ሚኒስትር ሌን ዩጂን ናግቤ ለጋዜጣው እንደተናገሩት ዴኤታው ጤናቸው ሰላም ነው ፤ ዋና ሚኒስትሩም ወደ ጋና ለሕክምና ሄደዋል የሚባለው ውሸት ነው ሲሉ አስተባብለዋል።

በላይቤሪያ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ይዘጋጁ ዘንድ በሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኒው ዮርክ ማራቶን በኮቪድ-19 ምክንያት ተሰረዘ!

በኮቪድ-19 ስጋት ምክንያት የኒው ዮርክ ከተማ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ዛሬ አዘጋጆቹ ይፋ ማድረጋቸውን #ቪኦኤ ዘግቧል።

የኒው ዮርክ ማራቶን በመጪው ኅዳር ወር 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ዝግጅት ላይ ሃምሳ ሺህ ሯጮች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች እና 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰባል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ በአሳሳቢ ደረጃ እየተዛመተ መሆኑንና ከበጋው በኋላ በሚመጡት ወራት 2ኛ ዙር ወረርሽኝ ይከተላል የሚል ሥጋት በመኖሩ ነው ውድድሩ የተሰረዘው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsigeredaKifle

በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ድንበር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው የደወሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያና የህክምና መከታተያ ማዕከል ለአገልግሎቶ ብቁ ባለመሆኑ #መዘጋቱን የፌደራል መንግስት አስታውቋል።

ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጥ የማቆያ እና ህክምና ማዕከል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና በፌደራል ጉምሩክ በተገነባው አዲስ ጣቢያ መዘጋጀቱን በጤና ሚንስቴር የተቋቋመው የክልሎች የኮቪድ መከላከልና ዝግጁነት ምላሽ አስተባባሪ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ ለDW ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ማንንም እንዳልጠየቅን ሁሉ ለመሙላትም የማንንም ፈቃድ #አንጠይቅም ፤ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ኃላፊነት እንደሚሰማት ታላቅ ሀገር በእውነትና በእውቀት ላይ ተመስርታ እንደምትሰራ ለዓለም እናስረዳለን" - ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢንቨስትመንት ላይ ያለው ተጽዕኖ እና የመንግስት ምላሽ - #PMO

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia