TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19Ethiopia

- በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1 ሰው ከሸበዲኖ፣ 1 ሰው ከዳሌ፣ 1 ሰው ለዳራራ ፣ 1 ሰው ከአርቤጎና ነው።

- በኦሮሚያ ክልል 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ከሰበታ ፣ 1 ሰው ከሰንዳፋና 1 ሰው ከጉጂ ናቸው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ንክኪ ያላቸው ናቸው።

- በትግራይ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው።

- በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ከባህር ዳር ናቸው ፤ ሁለቱም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

- በአፋር ክልል 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 72 ደረሰዋል።

- በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- በሐረሪ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ግለሰቡ የሱማሌ ክልል ነዋሪ ሲሆን ለህክምና ሐረር መጥቶ ናሙና የተወሰደለት ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ባሉት ምስሎች ታገኛላችሁ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በስፔን ተጥለው የነበሩ ዕገዳዎች ተነስተዋል!

በስፔን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የድንበር መተላለፊያዎች ተዘግተው የከረሙ ሲሆን ዕገዳዎች ተነስተው ወዳጅ፣ ዘመድ ቤተሰብ እየተገናኘ ነው።

ወደ ስፔን የሚገቡ መንገደኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፤ የሰውነት የሙቀት መጠን ምርመራ፣ የሚያርፉበትንም ቦታ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው - #VOA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዱባይ!

ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዝ እንደሚችሉ በመፍቀድ አንስተዋለች።

ከዚህ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩና ወደ ዱባይ መግባት ለሚችሉ ሰዎች ከሐምሌ ሰባት ጀምሮ ወደ ዱባይ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዱባይን ለመጎብኘት የሚመጡ የውጭ ዜጎች በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዱባይ አየር መንገድ ውስጥ እንደገና ለመመርመር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Ethiopia_COVID-19-Response_Directives_62012_Amh.pdf
4.3 MB
#COVID19Ethiopia

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭትን ለመከላከል ፤ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አዋጁን ለማስፈፀም በሚኒስቴሮች ኮሚቴ የወጣ መመሪያ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SHARE #ሼር

በተሻሻለው መመሪያ መሰረት በቤት ውስጥ ሆነን የኮሮና ቫይረስ ሕክምና የምንከታተል ሰዎች በሽታው ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንዳይሰራጭ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ አለብን - #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በቤት ሆኖ የኮቪድ-19 ህክምና ለማግኘት ፍቃደኛ የሆነ፣

2. ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት፣

3. በቤት ውስጥ የቆይታ ጊዜ አጋዥ ወይም ረዳት ያለው እንዲሁም እራሱን መርዳት የሚችል፣

4. የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘት ወይም ማሟላት የሚችል፣

5. በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሌላ ሰው የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ ማሸፈኛ ጭንብሎችን ማግኘት የሚችል እንደሆነ፣

6. ኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከሌሎች ተዷጋኝ በሽታዎች ማለትም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ፣ አስም፣ ኤች አይቪ፣ ቲቢ፣ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የማይኖር ከሆነ፣

7. የኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከቤት ላለመውጣት ወይም ማናቸውም ጠያቂ ወደቤት እንዳይመጣ ለማድረግ ማረጋገጫ የሚሰጥ ከሆነ፣

8. እራሱን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ለይቶ ማቆየት የሚያስችል ክፍል ወይም ከቤተሰብ አባላት በ2 ሜትር ርቀት ላይ መቆየት የሚያስችል ክፍል ያለው እንደሆነ፣

9. በጤና ቡድን በቋሚነት ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆነ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቀብር አፈፃፀም ወቅት ከ50 በላይ ሰዎች እንዳይገኙ እድሮች ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል በቀብር አፈፃፀም ወቅት ከ50 በላይ ሰዎች እንዳይገኙ እድሮች ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ሞት ሲከሰት የአስክሬን አያያዝና የቀብር አፈፃፀሙ ምን መምሰል እንዳለበት ለእድር አመራሮች ትላንት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከጤና ተቋማት ውጭ ሞት ሲከሰት ሟች የኮቪድ-19 ቫይረስ ይኑርበትም አይኑርበትም ናሙና ከተወሰደ በኋላ አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ስርአተ ቀብሩ መፈጸም አለበት ተብሏል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሳዑዲ አረቢያ!

የዚህ ዓመት 'የሃጅ የጸሎት ስነ ስርዓት' አስፈላጊ የጥንቃቄ መርሆዎችን በመከተል በውስን ነዋሪዎች እንደሚካሄድ ሳዑዲ አረቢያ ማስታወቋን አል አይን /AlAin/ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በማላዊ ምርጫ ተካሄደ!

ትላንት በማላዊ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አድርገዋል።

የትላንቱ ምርጫ የተካሄደው ባለፈው አመት የተደረገውና ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ አሸነፉ የተባለበት ምርጫ የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በስፋት የማጭበርበር ተግባር ተፈፅሞበታል ብሎ ከሰረዘው በኃላ ነው።

በትላንቱ የምርጫ ሂደት የተወሰኑ እክሎች ቢታዩም የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚሽን ይሄኛው ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ ይጠናቀቃል ብለን እንጠብቃለን ብሏል።

የትላንትናው ምርጫ የተካሄደው በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ባለበት ወቅት ሲሆን እስካሁን 803 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አንድ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በጠቅላላ አስፈላጊው የሆነ የመከላከል እርምጃ ተግባራዊ መደረጉን መናገራቸውን ቪኦኤ /VOA/ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ480 ሺህ አለፈ!

በዓለም በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ 9,377,608 ሰዎች መካከል ከ480,000 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ከተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል አሜሪካ [123,476] ፣ ብራዚል [52,771] እና ዩናይትድ ኪንግደም [42,927] ይጠቀሳሉ።

በአፍሪካ ደረጃ ግብፅ [2,365] ፣ ደቡብ አፍሪካ [2,102] እንዲሁም አልጄሪያ [861] ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ ሀገራት ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ከተያዙት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው 1 ሚሊዮን የተመዘገበው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን የኃለኛው 1 ሚሊዮን ግን በ8 ቀን ጊዜ ውስጥ ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውጭ ጫማዎን ቤት ውስጥ ባለመጠቀም የኮሮና ቫይረስ በሽታን ይከላከሉ!

(ጤና ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ)

- ውጪ ያደረጉትን ጫማ በቤትዎ በር በማውለቅ የቤት ጫማ ይቀይሩ፤

- ያወለቁትን ጫማ በፌስታል ወይም ለጫማ በተዘጋጀ ቦታ ያስቀምጡ፤

- ልብስዎን ይቀይሩ ከዚያም በውሃ እና በሳሙና እጅዎን ይታጠቡ ፤

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኮቪድ-19 ውጭ ያሉ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethmagazine በኩል ተከታተሉ ፦

- የሀላባ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የ2012 3ኛ አስቸካይ ጉባኤ ሰኔ 19-2012 ዓ.ም የፊታችን አርብ በሀላባ ያካሃዳል።

- ምዕራብ ሐረርጌ ቱሎ ወረዳ የአንበጣ መንጋ መታየቱን የምዕራብ ሐረርጌ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ጥቆማ አድርሰዋል።

- በባብሌ የዝሆኖች መጠለያ የአንበጣ መንጋ በተፈጥሮ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን መ/ቤት አስታውቋል።

- የደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 5ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሂድ ጀምሯል።

- 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

- በፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን ዛሬም ቀጥለው እየተገመገሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

- ግብጽ የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገዉ ጥረት የማይሳካ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል።

ትክክለኛው (@tikvahethmagazine) ገፅ ከ 229,000 በላይ የቲክቫህ አባላት ያሉበት ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳይ!

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ የሚገታበት ጊዜ ባለመታወቁ የሚጀምራቸውን ትምህርቶች ለመለየት መቸገሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

በቫይረሱ ምክንያት በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጡ የነበሩ መደበኛ ትምህርቶች ተቋርጠው የተወሰኑትን በመለየት በበይነ መረብ አማካኝነት የመማመር ማስተማሩ ሂደት መቀጠሉ ይታወቃል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ለመደበኛ ተማሪዎች በበይነ መረብ አማካኝነት እየሰጡት ያለውን ትምህርት በክረምቱ እንደማይቀጥሉ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ግን በመደበኛው ትምህርት የተጀመረው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ነው ብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ መቼ እንደሚቆም አለመታወቁ መደበኛውን ወይስ ደግሞ የክረምቱንና የርቀቱን ለመጀመር ቁርጥ ውሳኔ ማሳለፍ አልተቻለም - #AhaduRadio

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 186 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ5,000 አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,034 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5,034 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንድ እና 113 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ6 ወር - 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 181 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5 የውጭ ዜጋ ናቸው።

147 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 10 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 8 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከደቡብ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 (15 ከጤና ተቋም እና 20 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል።

በተጨማሪ አንድ (1) በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ስምንት (78) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,486 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ38 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

2. የ19 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

3. የ40 ዓመት ሴት የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ በሱማሌ ክልል ፣ በአፋር ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል እና በደቡብ ክልል በድምሩ 39 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

በአፋር ክልል ከተደረገው 91 የላብራቶሪ ምርመራ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ደርሷል።

በኦሮሚያ ክልል ከ704 የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 2 ሰዎች (1 ወንድና 1 ሴት) ከቦረና ናቸው ፤ ወንዱ ከማህበረሰቡ የተገኘ ፣ ሴቷ ወደ ኬንያ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላት ናት። 12 ዓመት ታዳጊ ከምስራቅ ሐረርጌ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት፤ አንድ የ22 ዓመት ሴት ከቡራዩ ከማህበረሰቡ የተገኘች ናት።

በደቡብ ክልል 362 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፤ ግለሰቡ የ44 ዓመት ወንድ የጋሞ ዞን ጨንቻ ወረዳ ነዋሪ ሲሆን፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አለው።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተደረገው 146 የላብራቶሪ ምርመራ 8 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 5ቱ ወንዶች ሲሆኑ 3ቱ ሴቶች ናቸው። ሁሉም ከማህበረሰብ ክፍሎችና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ግለሰቦች የተወሰዱ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia