TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61K photos
1.55K videos
215 files
4.24K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሲዳማ ክልል ፣ በትግራይ ክልል ፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ በኦሮሚያ ክልል እና አማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በቫይረሱ ስለተያዙት ሰዎች ከላይ ባሉት ምስሎች ተመልከቱ።

የጋምቤላ ክልል እንዲሁም የሱማሌ ክልል የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት እስካሁን በክልሎቹ ጤና ቢሮዎች ይፋ አልተደረገም።

በሲዳማ ክልል ተብሎ የተገለፀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ናሙና ምርመራው የተደረገው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ነው።

ሌላው በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሁሉም (14 ሰዎች) ከማህበረሰቡ ከተወሰዱ ናሙናዎች የተገኙ ናቸው። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዴክሳሜታሶንን በሚመለከት የተሰጠ ማሳሰቢያ!

(ዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር)

በቅርቡ የዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) መድሃኒት ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ቢያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን ዘንድ ሊከሰት የሚችለውን የሞት አደጋ መቀነስ እንዳስቻለ መገለፁ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር በሀገራችን ኦክሲጅን ወይም መተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሞያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታሶን እንደ ድንገተኛ ህክምና ጥቅም ላይ እንዲውል ተወስኗል።

ነገር ግን ዴክሳሜታሶን የኮቪድ-19 መድሃኒት ያለሆን እና ለመከላከል የማይጠቅም ሲሆን የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለው ግንዛቤ እንዲወሰድ እና ያልታመሙ ሰዎች ያለ ህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ከወሰዱት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ሕብረተሰቡ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መድሃኒቱን እንዳይወስድ እንዲሁም የፋርማሲ እና ሌሎች የጤና ባለሞያዎችም የዴክሳሜታሶን መድሃኒትን ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ለደንበኞቻቸው መሸጥ እንደሌለባቸው በአፅንኦት እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጸሃይ ግርዶሽ ምንድነው ?

ፀሐይ ግርዶሽ ጨረቃ በፀሐይ እና መሬት መሃከል ስትገባና ፀሐይን እንዳናያት ስትጋርድብን የሚከሰት ክስተት ነው።

የጸሃይ ግርዶሽ አይነቶች ስንት ናቸው ?

'ሙሉ የፀሐይ ግርዶች' የምንለው ጨረቃ ጸሃይን ሙሉ ለሙሉ የምትጋርድ ከሆነ ሲሆን ጨረቃ ከፊሉን የፀሐይ ክፍል ብቻ የምትጋርድብን ከሆነ 'ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ' (Partial Solar Eclipse) ይባላልም

ጨረቃ ፀሐይን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ሳትችል ስትቀርና በጨረቃ ጠርዝ ዙሪያ ቀለበት ሠርታ ፀሐይ የምትታየን ከሆነ 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ (annular solar eclipse)' ይባላል።

ነገ በሀገራችን የምናየው ግርዶሽ ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ የሚባለውን ነው - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የነገው ግርዶሽ የትና ስንት ሰዓት ?

ነገ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡

ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለው ዋናው ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ግርዶሹ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላልይበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ ባህር ዳር በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

ከላይ ባለው ምስል ግርዶሹ የሚጀምርበትን ሰዓት ፣ ቀለበት ካለ ቀለበት የሚታይበትን ሰዓት ፣ ግርዶሹ የሚያልቅበት ሰዓት እንዲሁም ጸሃይ የምትሸፈንበትን መጠን መመልከት ትችላላችሁ - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIGRAI TV LIVE!

'በአላማጣ ከተማ' ያለውን የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን በቀጥታ መመልከት ትችላላችሁ።

በአላማጣ ቀለበታማ ግርዶሽ የሚሆንበት ሰዓት 2:00:27 - 2:01:27 ሲሆን ከፍተኛው የመጨለም መጠን 97 በመቶ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ!

ከጥቂት ደቂቃ በኃላ 'አላማጣ' ላይ የሚከሰተውን ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ከቤትዎ ሆነው በቀጥታ በትግራይ ቴሌቪዥን በመመልከት የዚህ ታሪካዊ ክስተት አካል ይሁኑ። በሚፈጠረው ሁኔታ ልንደናገጥ እንደማይገባ ባለሞያዎች መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተለያየ አጋጣሚ ውስጥ ሆናችሁ ቴሌቪዥን ለማየት እድል ያላገኛችሁ አሁን በአላማጣ ከተማ ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ - በአላማጣ!

በአላማጣ ከተማ የተከሰተውን 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ' ከትግራይ ቴሌቪዥን በወሰድነው ቪድዮ (33 MB) መመልከት ትችላላችሁ። ግርዶሹ ሲከሰት በአላማጣ ከተማ የነበረውን ክስተት በቪድዮው ላይ ተመልከቱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ' በአላማጣ ከተማ ሲከሰት በከተማው የነበረው ገፅታ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር፤ 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሹ ከ2:00:27 - 2:01:27 ድረስ ነው የቆየው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 63 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,457 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

ቫይረስ የተገኘባቸው 42 ወንድ እና 21 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ14-76 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

31 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣1 ሰው ከትግራይ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

ከዚህ በተጨማሪ በለይቶ በህክምና ማዕክል ውስጠ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አራት (74) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አንድ (91) ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ፣ 16 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1213 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ዕለታዊ መግለጫ በቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) እና በCARD ትብብር የተዘጋጀ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia