TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መድሃኒት ለማግኘት ሲጠቀምበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ፣ ሃይድሮክሲክሎሮክዊን ለጊዜው #አቋረጠ

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአምስት ቀን በፊት በታተመው ላንሰት የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት መሰረት አድርጎ ነው። በዚህ ጥናት መሰረት መድሃኒቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ሞት #ያፋጥናል ይላል።

የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "የከፍተኛ አመራሮቹ ቡድን አባላቱ #የሃይድሮክሲክሎሮክዊን ሙከራ ደህንነቱ ዳግም በደህንነት ቁጥጥር ቦርዱ እስኪመረመር ድረስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ወስነዋል" ብለዋል። ሌሎቹ የምርምር ስራዎች ግን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

'ሃይድሮክሲክሎሮክዊን' (የፀረ ወባ መድሃኒት) በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች መሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ቢሰጥ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል በሚል ሲወደስ ቆይቶ ነበር።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 156 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በሱዳን ተጨማሪ 156 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሲያዙ አምስት (5) ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል 45 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ተገልጿል።

ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,976 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 170 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 503 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብራዚል!

በብራዚል በአንድ ቀን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአሜሪካ በለጠ። ባለፉት 24 ሰዓት በአሜሪካ የ620 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በብራዚል 807 ሰዎች ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከ376,000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መኃል ከ23,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።

ብራዚል ውስጥ መጀመሪያ ሰሞን የነበረው መዘናጋት ፣ ቸልተኝነት ፣ መመሪያን አለማክበር፣ በሽታው አይገልም ብሎ ማሰብ፣ ወጣቶትችን ሊያጠቃ አይችልም ብሎም ማሰብ ዛሬ ዋጋ እያስከፈለ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ክትባት!

በአሁን ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ኮቪድ-19 #ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ደግሞ በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው በሰዎች ላይ የሚደረግ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በሜልቦርን ተጀምሯል።

ሙከራ እየተደረገበት ያለው ክትባት 'NVX-CoV2373' የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ክትባቱ 'ኖቫቫክስ' በተባለው የአሜሪካ ኩባንያ የተመረተ ነው።

ተመራማሪዎች የሚሞክሩት በ130 አዋቂ ጤነኛ ሰዎች ላይ ነው። እንደ #BBC መረጃ የክትባቱ ሙከራ ውጤት #ሐምሌ ወር ላይ ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ወንድ እና 17 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ12 እስከ 79 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 45 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ የእስራኤል ዜጋ ናት።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 13 ሰዎች ከአዲስ አበባ (4 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው እና 8 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ)፣ 15 ሰዎች ከአማራ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ)፣ 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ) እንዲሁም 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 34

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 4

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 8

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት 8 ሰዎች (2 ሰዎች ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ፣ 6 ሰዎች ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 167 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 6 ደረሰ!

በተጓዳኝ ህመም ምክንያት በፅኑ ህክምና ላይ የነበረች እና በትናንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባት የ32 ዓመት 'የአዲስ አበባ ነዋሪ' የሆነች ኢትዮጵያዊት ትላንት ለሊት ህይወቷ አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት (6) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሞንቴኔግሮ ከኮቪድ-19 ነፃ መሆኗን አሳውቃለች!

ሞንቴኔግሮ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) #ነፃ መሆኗን በትላንትናው ዕለት አሳውቃለች። በአጠቃላይ 324 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 315 ሰዎች አገግመዋል።

ምንም እንኳን ሞንቴኔግሮ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ነፃ ብትሆንም የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እንዳያገረሽ የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደሚቀጥሉ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱ ከግንቦት 24 ጀምሮ ያወጣችውን መስፈርት ለሚያሟሉ የአውሮፓ ሀገራት ዜጎች #ድንበሯን ለመክፈት እየተዘጋጀች እንደሆነ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባትና መድሃኒት ማምረቻ ድጋፍ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ክትባት ለማግኘትና መድሃኒት ለማምረት የሚያግዝ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማስታወቃቸውን #BBC ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ ተጨማሪ 62 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ስልሳ ሁለት (62) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,348 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላትናው ዕለት ሶስት (3) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 405 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ወንድ እና 17 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ12 እስከ 79 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 45 ሰዎች ኢትዮጵያውያን…
#AtoAknawKawza

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰባት (7) ሰዎች መካከል ስድስቱ (6) በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

ዛሬ በፌደራል ደረጃ በተሰጠው መግለጫ በደቡብ ክልል ሁለት (2) ሰዎች ማገገማቸው መገለፁ ይታወሳል።

እኚህ ያገገሙት ታማሚዎች ከጉራጌ ዞን (ቡታጅራ ወረዳ) እና ከሃዲያ ዞን (ሻሸጎ ወረዳ) መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
 #DrYohannesChala 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 436 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንድ መቶ ሰባ አራት (174) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 69 ሰዎች
• አራዳ - 21 ሰዎች
• ቦሌ - 54 ሰዎች
• ገለሌ - 38 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራንዮ - 38 ሰዎች
• ልደታ - 122 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 27 ሰዎች
• ቂርቆስ - 16 ሰዎች
• የካ - 25 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 8 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 18 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አማራ ክልል!

በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠውን 15 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በአማራ ክልል 44 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ፦

• ምዕ/ጎንደር - 29 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 3 ሰዎች
• ጎንደር ከተማ - 1 ሰው
• ደሴ ከተማ - 1 ሰው
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ - 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 1 ሰው

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,711 ደርሷል።

በተጨማሪ አንድ ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 67 ከፍ ብሏል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ ስምንት (18) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 253 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMikeRyan

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰባቸው ባሉ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ እገዳዎች በቶሎ የሚነሱ ከሆነ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል ሲል #አስጠንቅቋል፡፡

የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ርያን አለም በመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሞገድ ውስጥ ነች፤ ምንም እንኳን በብዙ ሀገራት በቫይረሱ የመያዝ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በማእከላዊና በደቡብ አሜሪካ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ማይክ ርያን ከሆነ ወረርሽኞች ሁሌም ወቅታዊ ናቸው ፤ በዚህ አመት የመጀመሪያው ሞገድ ያቆመባቸው ሀገራት እንደገና ይመለሳል ብለዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ ክልከላዎች ቶሎ የሚነሱ ከሆነ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጸዋል - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ100,000 አለፈ!

እንደ #worldometers መረጃ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት የሞቱ ሰዎች 100,103 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል ሪፖርት ያደረገው 2 ኬዝ!

በፌደራል እና በክልል ጤና ቢሮዎች የሚሰጡ መረጃዎች ሊናበቡና በግልፅ ማብራሪያ ሊሰጥባቸው ይገባል!

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

ዛሬ ግንቦት 18/2012 ዓ/ም የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሚገልፅ መረጃ እንዳልነበር ይታወሳል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 648 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት(2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቋል።

እነዚህ ሰዎች በቀትር መረጃው ላይ የተካተቱ ቢሆን በግልፅ የተገኙበት ክልል እና ከተማቸው ሊገለፅ ይገባ ነበር።

መረጀው ከክልል ቢሮ ዘግይቶ ደርሶ ከሆነም ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው ዘግይቶ የመጣ መረጃ በሚል ሊቀርብ ይገባ ነበር ፤ እስካሁን ስንጠብቅ ነበር ምንም ነገር የለም!

ምናልባት 4 ደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ተብሎ የተገለፀው ውስጥ ይገኙበት ይሆን በሚል አስበን ነበር በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በወጣው መረጃ እንዲህ የሚል ነገር አላገኘንም።

ከዚህ ቀደም በጤና ሚኒስቴር በሚወጣው መረጃ 'በቫይረሱ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ተይዙ' ተብሎ ከመግለፅ ውጭ ዝርዝር መረጃ አይሰጥም።

ለማንኛውም ዛሬ ግንቦት 18/2012 የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ያላቸው ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔት ይህን ይመስላል፦

ታማሚ 1 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ (ወንድ) #የጅማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው።

ታማሚ 2 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊት (ሴት) #የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላት።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የለቅሶዉ መዘዝ በአዲስ አበባ!

(ዶቼ ቨለ/DW/ - በጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ)

አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ፣ በወረዳ 3 ፣ ቀጠና 5 ፣ መንደር 3 (በተለምዶ አብነት የሚባለው አካባቢ) የኮሮና ቫይረስ በርካታ ሰዎችን በመያዙ ምክንያት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በሙሉ ከሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች ጋር እንዳይገናኙ ታግደዋል።

የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (DW) ያነጋገራቸው ወጣቶች እርምጃዉ የተወሰደዉ በነዋሪዎቹ ፈቃድ እና ይሁንታ ነዉ ብለዋል።

የመንደሩ ነዋሪዎች ከወትሮ እንቅስቃሴቸዉ እንዲታቀቡ ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ ነዉ። በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ይህንን ስራ እያስተባበሩ ነው።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት የአራተኛው (4) ሰው ቤተሰቦችን ለማስተዛዘን ለቅሶ ተቀምጠው የነበሩ ከ30 በላይ የመንደሩ ነዋሪዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉን እርምጃዉን ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ ገልጿል። መንደር 3 አንድ መቶ ያህል መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AshleyBloomfield

በኒውዚላንድ እስከ ትናንት ድረስ ሆስፒታል ይዞ ይታከም የነበረ አንድ ታማሚ ብቻ ነበር። እሱም ዛሬ ጠዋት ድኖ ወደ ቤቱ መሄዱን #BBC አስነብቧል።

በአሁን ሰዓት በኒው ዚላንድ አልጋ የያዘ የኮቪድ-19 ታማሚ የለም። ከዚህም ባሻገር ለተከታታይ 5 ቀናት በቫይረሱ የተያዘ አንድም ሰው አለመመዝገቡ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ተገልጿል።

የአገሪቱ ባለሥልጣናት በኒው ዚላንድ የኮቪድ-19 ሥርጭት በማኅበረሰብ ደረጃ ስርጭቱ ሙሉ በሙሉ #እንደተገታ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ በኋላ የሚፈራው በድንበር የሚገቡ ሰዎች ቫይረሱን እንዳያዛምቱት ብቻ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሳቢያ ህይወታቸው እንዳለፈ የሚነገርላቸውን ታማሚ ሲያክሙ የነበሩ በርካታ 'የጤና ባለሞያዎች' የመገለል አገልግሎት እየጠየቁ መሆናቸው የVOA ዘገበ።

በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ራሳቸውን አግልለው እንደሚገኙ የሚናገሩት ባለሞያዎቹ በቂ ምላሽ #እንዳለገኙም ገልጸዋል።

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት በአንድ ወይም በሌላ ሆስፒታል ሊፈጠሩ የሚችሉ ከባድ ችግሮች እንዳሉ አስገንዝበዋል።

ይሁንና በመላው የሀገሪቱ የህክምና አገልግሎት ስርዓት በዚህ ረገድ ሀገሪቱ ካላት የሰውና የቁሳቁስ ሃብት አኳያ ያለውን ሁኔታ ማጤን ያስፈልጋል ብለዋል።

ዶክተር ዳዊት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተከሰተውን ችግር ያላስተባበሉ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አስረድተዋል።

🎧 5 MB
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia