TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በርካታ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም አካባቢ ዘረፋ እየተፈፀመ መሆኑን በተደጋጋሚ እየጠቆሙ ነው ከተላኩት መልዕክቶች መካከል አንዱን እንሆ...

"ሀይ ፀግሽ እንደት ነህ? እኔ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ። በአርባምንጭ ላይ እየተካሄድ ያሉ ስርቆቶች በጣም ለህይወታችን እያስፈሩን ነው እኛን ከቀሙም ቡሀላ በሞተር ያመልጣሉ በተለይ ነጭ ሳር ካንፓስ አካባቢ ሞባይሎቻችንን ኮንፒተሮቻችንን እየተቀማን ነው ከዛም አልፎ ከኛ የሚወስድት ካጡ ጫማችንን ያስወልቃሉ ወይም ወግተው ይሄዳሉ። እባክህን ለሚመለከተው አካል ይህንን መልእክት አድርስልን ለህይወታችን በጣም ፈርተናል። ስም አይጠቀስ።"

ተማሪዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ መማር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። መንግስትም ለአፍታም ቢሆን የሰዎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ወደ ኋላ ማለት እንደሌለበት ግልፀው የዘረፋ ወንጀል እየፈፀሙ ያሉትን ግለሰቦች ለህግ ማቅረብ እንዳለበት አሳውቀዋል።

@tsegabwode @tikvahethiopia
ክቡር ኦቦ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት የተናገሩት..

1/ ዲሞክራሲ በወሬ ብቻ አይመጣም፡፡ የሚሰባበረውን መሰባበር የሚነቀለውን መንቀል ያስፈልጋል፡፡

2/ ባህላችንም ዲሞክራሲን እንዲሰፋ የሚያግዝ ሳይሆን በተቃራኒው እንዲቀጭጭ የሚያደረግ ስለሆነ እሱ ላይም መስራት አለብን፡፡

3/ እስረኛውን እንደወራጅ ወንዝ እየለቀቅን ያለነው እስርቤት ለመዝጋት እቅድ ስላለን ሳይሆን አዲስ የፓለቲካ አየር ለመፍጠር ስለምንፈልግ ነው፡፡

4/ በኦሮሚያ በአንድ አመት ውስጥ 40ሺ እስረኛ በላይ የለቀቅነው ግለሰብን ብቻ ነፃ ለማውጣት ስለምንፈልግ እንዲሁም ለመወደድ ወይም እንዲጨበጨብልን ስለፈለግን ሳይሆን የመጠላለፍ እና የመጠፋፋት ባህላችንን ለመቀየር ነው ፡፡

5/ ሰዎችን ከእስርቤት አይደለም ነጻ ያወጣነው..ተሰደው የዜግነት መብታቸውንም ካጡት የስደት ኑሮ ነው..ከባዕድ ሀገር እስር ቤት ጭምርም ነው ፡፡

6/ ታሪክ እየቀየርን ነው.. ሁሉንም የፓለቲካ ፓርቲ ከያሉበት ግቡና አብረን እንስራ የምንለው የፓለቲካ ገበያ ለመክፈት ሳይሆን በእውነት እና በሀቅ የሀገሪቱን ታሪክ ለመቀየር ስለምንፈልግ ነው፡፡ በስደት በባረና በኩል ተሰደደው ኃይል ቦሌ በኩል እንዲገባ ያደረግነው ሞተው እሬሳቸው ተጭኖ ከሚመጣልን ይልቅ በህይወት መጥተው ለህዝባቸው እንዲሰሩ እና እንዲያገለግሉ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜጋ መሆናቸው እንዲረጋገጥላቸውት ነው፡፡ እነዚህ አካላት ሀገር ውስጥ ሆነው በህዝባቸው መሀከል ሆነው ሲሰሩ ነው ሚያወሩትን ለውጥ በተግባር ሊያመጡ ሚችሉት፡፡

7/ ኦፒዲዬ ስለሆን ለዘመናት ይጠየፍን እና ይንቁን የነበሩትን እና ከእናንተ በላይ ነን የሚሉትንም ነፃ አውጥተን ለሀገራቸው አብቅተናቸዋል፡፡

8/ እኔ ምኞቴን ነግራችሁለው..እዚህ ወንበር ላይ ለመቆየት አይደለም ዕቅዴ ለዚህ ህዝብ ነፃነት ማምጣት ከቻልን ድላችን ወደሃላ የማይመለስበት ደራጃ መድረሱን ካረጋገጥን ለመልቀቅ ደስተኞች ነን፡፡

9/ ከአሁን ወዲህ ተገቢውን የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ እዚህ ወንበር ላይ መቀመጥ አይቻልም፡፡

10/ 3 ሰዓት አንብቤ 30 ደቂቃ ድንቅ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው……፡፡ መስራት ነው የሚከብደው.. ጥሮ ግሮ ትንሽም ሆን ትልቅ ውጤት ማምጣት ነው ከባዱ..ማውራትም ሺ ዋች አሳምረው ያወራሉ….

11/ እኛ የተሰደደውን ብቻ ነፃ ማውጣት ሳይሆን ሀገሩቱንም ከመበተን አድነናታል.. እኛ ወደ ስልጣን ስንመጣ ብዙዎቹ አሳንሰው እንዳዩን ሳይሆን ከኦሮሞ ህዝብ የወጣን ቢሆንም ለመላው ኢትዬጵያ የምንተርፍ መሆናችንን አረጋግጠናል፡፡ በዳቦ ከሆነ ወደስልጣ በመምጣታችን አንድ ዳቦ እንኳን ለኦሮሞ የጨመርነው የለም፣ ሀገራችን እንድትከበር ግን ማድረግ ችለናል፡፡ ክብር ደግሞ ከዳቦ ይበጣል፡፡በቀጣይ ዳቦውን በላባችን ሰርተን እናገኘዋለን፡፡

12/ አሁን ተንሰንሰፍስፈው የሚያናግሩን እና በአጀብ አቀባበል ሚያደርጉልን የአለም ሀገራት ከወራት በፊት በአማላጅ አንኳን ለማናገርም ተጠይፈውን እና እንቢ ብለውን ነበር… በአንድነታችን ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን ኢትዬጵያንም ነው ያስከበርነው በቀጣይም አፍሪካንም ጭምር ለማስከበር ነው የምንሰራው አሁንም ህዝባችን ብዙ መካራ አለበት፡፡ ዋናው ሰንሰለት ግን ከላያችን ላይ መበጣጠስ ችለናል፡፡

13/ ዛሬም በሀሳብ ልዩነትን ተቻችለን አብረን ለህዝባችን መስራት የማንችል እና ልክ እንደትናንቱ በመሳሪያ የምንጫረስ ከሆን ምንም ያልተማርን መሀይሞች ነን ማለት ነው፡፡

14/ ወንበርን ሀብትን ለማፍሪያነት ፈልገነው የተቀመጥንበት ሲሆን ብቻ ነው ለመልቀቅ የምናንገራግረው..ለመቆየትም ስንል ሌላውን የምናጠፋው… ፍላጎታችን የህዝባችንን ኑሮ ለመቀየር ከሆነ ግን ወንበር ላይ ውሎ ለማደር የምንጫረስበት ምክንያት አይኖርም፡፡

15/ በየፌስብኩ እከሌን ያስፈታነው እኛ ነን ብለው የሚፎክሩ አሉ.. ይፎክሩ ለህዝብ እስከጠቀመ ድረስ ይሁን ክሬዲቱን ለመውሰድ ሚሰጠው ሰርተፍኬቱ አያልቅም.. ግን የዛሬ ሶስት አመት ለምን አላሰፈቱም …? የዛሬ አራት አመትስ..? ዛሬም ሁኑ ነገር አልተፈታም ..ብዙ ችግሮቻችን ገና በሂደት ላይ ናቸው፡፡ ግን በመደማመጥ መስራት አለብን… ነገም ተነስተን በገጀራ ምንጨፋጨፍ ከሆነ እና በዱላ ምንደባደብ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ በቅርብ ህዝባችንን መልሰን ወደባርነት እንመልሰወለን ማለት ነው፡፡ በንግግር የምንስማማበት የመቻቻልና የአንድነት ዘመን ይሁንን፡፡

©ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበታ! በሰበታ ከተማ በቀበሌ 04 የሚገኙ ሙስሊሞች እምነትን የሚተገብሩበትን የአምልኮ ቦታ እንዲያፈርሱ ማስጠንቀቂያ እንደ ተሰጣቸው ተናገሩ። በወርሃ ርመዳን ተሰባስበን ስርአተ ጸሎትን የምናከናውንበት ቦታን እንድናፈርስ መደረጋችን አስተዳደራዊ በደል ነው በማለት የሚገልጹት የሰበታ ነዋሪዎች ጉዳዩን አስመልክቶ መጅሊስ የትብብር ደብዳቤ ቢጽፍልንም ተቀባይነት አላገኘንም ሲሉ ያማርራሉ።

እንደ አገሪቱ ዜጋ በህገመንግስት የተረጋገጠልን መብት መከበር አለበት ብለዋል የሰበታ ነዋሪዎች።

ምንጭ፦ BBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ESFNA! በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አመራር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመገናኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የህዝብ አስተያየት ሰብስቦ 65% የህዝብ ድጋፍ ቢያገኝም ውጤቱን በመተው የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

*ጠቅላይ ሚንስትሩ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚያገኙባቸው ሌሎች መድረኮች እንደሚኖሯቸው ይጠበቃል፡፡

እናተስ ስለ ESFNA ውሳኔ ምን ትላላችሁ?

ውሳኔው ትክክል ነው
ውሳኔው ትክክል አይደልም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ! የኢፌድሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች በንድፈ-ሃሳብ የታገዘ ገለጻና ከሃላፊዎቹ ጋር በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ሀገራችን ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ፣ ዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ሀገራዊ ክብርና ልዕልናዋን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የመከላከያ ሰራዊት የማይተካ ሚና እንዳለው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡

ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም በሌላ ቋንቋ የህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ማለት በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊትከ ከህገ-መንግስቱ የሚመነጩ ግልጽ ተልዕኮዎችን አንግቦ ለህዝብ ፍላጎት የሚገዛና ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በወደቀ አገር ውስጥ የተከበረ ጀነራል መኖር አይችልም የወደቀ አገር የሚያከብረው ጀነራል የለውም። ጠንካራ አገር ያለው አስር አለቃ ይሻላል ከወደቀ አገር ጀነራል።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለሀገር መከላከያ ሀላፊዎች የተናገሩት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር!

ከሀገር ውስጥ

🗞ከሰሞኑ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወደ እንግሊዝ በማምራት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ።

🗞በቤተመንግስት ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ እንዲሁም ጠ/ሚኒስትሩን የሚያጅቡ ሰዎች እየተቀየሩ ሲሆን ከ 20 አመታት በላይ የቤተመንግስት ዋና ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ገብረትንሳኤ ገብረሚካኤል ከስልጣናቸው ተወግደው በምትካቸው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወርቅነሽ ብሩ ሲተኩ ገብረትንሳይ ከስልጣን እንደተነሱ በእርሳቸው ስር የነበሩ ጠባቂዎችና አጃቢዎችም እንዲቀየሩ ተደረገ።

🗞በአዲ ረመጥ ከተማ ፌስቡክ ላይ ጽፋችሁዋል የተባሉ ወጣቶች ታሰሩ።

🗞ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በምዕራብ አርሲ ዞን የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ 22 ሰዎች ሲሞቱ ሰባት ሰዎች ቆሰሉ፡፡ በአደጋው 45 የቤት እንስሳት ያለቁ ሲሆን በንብረት ላይ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት መድረሱ ታወቀ፡፡

🗞የግንቦት ሰባት ሊቀርመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሀመድ እንደዚሁም ደግሞ ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥንን ጨምሮ የ 137 አካላት ክስ ተቋረጠ፡፡

🗞በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ እና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

🗞ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዘንድሮ በዳላስ ከተማ በሚካሄደው 35ኛው የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ መገኘት አይችሉም ሲል የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ወሰነ፡፡

🗞የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ 1 ሚሊዮን ብር ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት ወጪ እንዲሆን ወሰነ።

🗞በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተ መንግስት በመሄድ ተቃውሞ ቢያሰሙም መልስ የሚሰጣቸው አካል አለማግኘታቸውን ተከትሎ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ሲያመሩ በፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ እንዲታገዱ መደረጉ ተነገረ።

🗞ሁለት ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች "ጎ ፈንድሚ" በተባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ድረ-ገፅ በኩል ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የሕክምና ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ።

🗞መንግሥት በፖለቲካ ምክንያት የታሠሩ ዜጎችን መፍታት ያለበት በአንድ ጊዜና በአጠቃላይ ምህረት እንጂ ተራ በተራ አይደለም ሲሉ ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።

🗞የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የዘገየው ማረሚያ ቤቱ “ሰነድ አልደረሰኝም” በማለቱ እንደነበር ተገለፀ፡፡

🗞በቅርቡ በምህረት የተፈቱት የልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የእሳቸው ሕክምና ክትትል ያስፈልጋቸው የነበሩ ከ 20 የሚልቁ ሕሙማን በእስር ማረሚያ ቤት በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ መሞታቸውን ገልፀው ከመታሰራቸው በፊት የልብ ባትሪ የገጠሙላቸውን እነዚህኑ ሕሙማን በፖሊስ እየተጠበቁም ቢሆን ለማከም ቢጠይቁም ውድቅ እንደተደረገባቸው ተናገሩ።

🗞"መታሠሬ በሕይወቴ ልጽፈው የማልችለውን መጽሐፍ እንድጽፍ ረድቶኛል። የሕዝቡ መልካም እና ደማቅ አቀባበልም አኩርቶኛል።" ሲሉ ከእስር ቤት የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገልፀዋል።

ከውጭ

🗞ኡጋንዳ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ቀረጥ ልታስከፍል ነው፡፡

🗞በአልጄሪያ መርከብ ሙሉ ኮኬይን የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ።

🗞በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው የሠራተኞች ወርሃዊ ክፍያ 7ሺ ብር እንዲሆን የሀገሪቱ ፓርላማ ረቂቅ ህገ ደንብ አፀደቀ፡፡

🗞ፓፓዋ ኒው ጊኒ ሐሰተኛ የፌስ ቡክ ገጾችን ለመለየት እና ማህበራዊ ገፁ በሀገሪቱ ላይ ያለውን ተፅእኖ ለመለየት በሚል ፌስ ቡክን ለአንድ ወር ልታግድ ነው።

🗞በፈረንሳይ የአጫሾች ቁጥር በ 1 ሚሊዮን መቀነሱ ይፋ ተደረገ።

🗞የ22 አመቱ ማሊያዊው ፍልሰተኛ ማማዱ ጋሳማ አንድ የአራት ዓመት ሕፃን ልጅ ከአራተኛ ፎቅ ላይ ሊወድቅ ሲል በድንገት በመድረስ ከሞት በመታደጉ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው፡፡

🗞የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በጋዛ ሰርጥ እስላማዊ ጂሃድ የተባለው አማፂ ቡድን ይዞታዎችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት አካሄዱ።

🗞የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ሊያደርጉት ስለታቀደው ጉባዔ የሚወያዩት ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣን ኒውዮርክ የደረሱ ሲሆን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋርም ተገናኝተዋል።

ስፖርት

🗞የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከስፔኑ ክለብ ጋር ተለያየ።

🗞የቀድሞው የቼልሲ አማካኝ ፍራንክ ላምፓርድ የደርቢ ካውንቲ አዲስ አሰልጣኝ ተደርጎ ተሾመ።

🗞የቀድሞው የሁል ሲቲና ዋትፎርድ አለቃ ማርኮ ሲልቫ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሆኑ።
****************
አንኳር ዘገባዎቹ የተጠናቀሩት ከቢቢሲ አማርኛ፣ ከቪቮኤ አማርኛ፣ ከዶቼዌሌ አማርኛ እና ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እና ዘጋርዲያን ጋዜጣ ነው፡፡

# EthioNews
# Wekly News Brief
# VOA Amharic
# DWAmharic
# ESAT

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ለፍርድ ቀረበ! በጋሞ ጎፋ ዞን ጨንቻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለጓደኛው ሲፈተን የተገኘው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለፍርድ ቀረበ፡፡

ግለሰቡ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሶስተኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪ መሆኑ እንደተረጋገጠም የዞኑ የብሔራዊ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተጠርጣሪው ሀሰተኛ የመፈተኛ መታወቂያ ይዞ በመግባት ለጓኛው የሂሳብ ፈተና ሲፈተን እንደተደረሰበትም ነው የተገለጸው፡፡

የራሱን ፈተና ለሌላ ሰው አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠረው የትምህርት ቤቱ ተማሪም አብሮ ተይዟል።

ሁለቱም ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ለፍርድ ቀርበው ውሳኔያቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰኗል። ምክር ቤቱ ዛሬ መደነኛ ስብሰባውን አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋጁ እንዲነሳ ተወሰነ! ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል።

አሁን ላይም በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።

ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ በምክር ቤቱ ሲፀድቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 23 2010 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 9 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ለስድስት ወራት
ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል።

ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በምክር ቤቱ ያፀደቀው።

በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የተጋረጠውን ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት በማስፈለጉ ነበር የታወጀው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ አሁን ላይ በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈታ! ፍቅረማርያም አስማማው ዛሬ ከእስር መፈታቱ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️የዋልድባ አባቶች ወደ ገዳም ተመልሰዋል! በመጀመሪያ በማዕከላዊ በመቀጠል በቂሊንጦ እስር ላይ የነበሩት እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሁለቱ የዋልድባ አባቶች ወደገዳማቸው መመለሳቸው ተነግሯል። መነኮሳቱ የ14 ሰዓታት የበረሃ የእግር ጉዞ በማድረግ ዋልድባ ከገዳማቸው መድረሳቸው ነው የተነገረው።

አባቶቹ ዋልድባ ሲደርሱ ማኅበረ መነኮሳቱ ከየ በአታቸው በመውጣት ተቀብለዋቸዋል። እነሱም በአበው እግር ስር ተደፍተው በግምባራቸው በመውደቅ ጸሎት ቡራኬ ተቀብለዋል። በአታቸውን የዘጉና በአርምሞ የሚኖሩ አባቶች ጭምር መነኮሳቱን ከበአታቸው እንደተቀበሏቸው ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ፦ ዘመድኩን በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዘን! የደ/ብርሀን ዩኒቨርሲቲ በያዝነው ሳምንት በነበረው አሰቃቂ የመኪና አደጋ 3 ተማሪዎቹን አጥቷል።

በአጠቃላይ በአደጋው ህይወታቸው ላለፉ ወገኖች ነብስ ይማር እያልን ለቤተሰብ እና ወዳጆች መፅናናትን እንመኛለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውሸት ነው! የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል በዚህም ፈተናው ተራዝሟል በማለት የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው። ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ሰኞ ፈተናችሁን እንድትፈተኑ ቻናላችን መልዕክቱን ያስተላልፋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሌንጮ በደኖ የሚባል ቦታ ረግጬ አላውቀውም አሉ። ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከአፍታ በኋላ ለጥፋላችኋለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC: ''በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም'' አቶ ሌንጮ ለታ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለአስርት ዓመታት የቆዩትና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር መስራች የሆኑት ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ጥያቄዎችን ወደፊት በማስቀደም ፈር ቀዳጅ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።

ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠርም በሽግግር መንግሥት ምስረታው ተሳታፊ ነበሩ። ለረጅም ዓመታት በስደት የቆዩት አቶ ሌንጮ ከሦስት ዓመት በፊትም የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የተሰኘ ፖርቲንም አቋቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ አገር ቤት ባለው ፓለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ተመልሰዋል። በመጪው ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውና ከኦነግ ጋር ተያይዞ በሚቀርብባቸው አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

*⃣ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እያደረጋችሁት ያለው ድርድር በምን መንገድ እየሄደ ነው?

▪️አቶ ሌንጮ፡ ድርድር ልለው አልችልም። ውይይት ነው እያካሄድን ያለነው። አሁን እየተፈጠረ ያለው ለውጥ ደካማና ጠንካራ ጎኑን እንዲሁም እኛ ልናበረክተው የምንችለው አስተዋፅኦ ምን ሊሆን ይችላል? በሚለው እየተወያየን ነው። ውይይቱ ጅማሮ ላይ ነው ሰፊ ጉዳዮችም አልተነሱም። እኛ ለብዙ ዓመታት ከዚህ አገር ተገልለን ባዕድ አገር ከመኖራችን አንፃር፤ እንዲሁም በስደት በነበርንበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ለውጥ በመከሰቱ ይህንን ለመረዳት እየሞከርን ነው። ያንን ሳንረዳ የሚረባ አስተዋፅኦ ልናበረክት አንችልም።

*⃣ከመንግሥት ጋር እያደረጋችሁት ያለው ውይይት በጥሩ መንገድ ከሄደ ምን ለማድረግ ታስባላችሁ?

▪️አቶ ሌንጮ፡ እንደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ እንፈልጋለን። በአሰራሩ መሰረት መመዝገብ እንዲሁም ቢሮ መክፈት እንፈልጋለን። በእነዚህም ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደናል። የተፈጠረው ሁኔታ አበረታች ነው። ለመሰማራት ዝግጁ ነን።

*⃣ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሳተፍዎ አንፃር የእርስዎ አስተዋፅኦ ምንድን ነው?

▪️አቶ ሌንጮ፡ይሄን ያህል አይደለም። ትልቁ አስተዋፅኦ የምለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በማቋቋም ተሳትፌያለሁ። ደርጅቱም የኦሮሞን ሁኔታ በመለወጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። በኋላ ሁኔታዎች እንደፈለግነው አልሆኑም እንጂ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ነበር። ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለመሸጋገር ምን ያስፈልጋል በሚለው ላይ እናተኩራለን። ስላለፈው የኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ እንነታረካለን፤ ጥቅሙ የረባ አይደለም።

*⃣ወደኋላ ዞር ብለው ሲመለከቱ ባደረጉት ነገር የሚፀፅትዎት ነገር አለ?

▪️አቶ ሌንጮ፡ ከአፄ ኃይለሥላሴ ወደ ደርግ ሥርዓተ- መንግሥት በነበረው ሽግግር ወጣቶች ነበርን። እኔም ሆንኩ እኩዮቼ የፈፀምናቸው ስህተቶች ነበሩ። ከደርግ ወደ ኢህአዴግም ስንሸጋገር ብልህነትንና ጥበብን የተካነ እርምጃዎች መውሰድ ሲኖርብን ያው በስሜታዊነት ተነድነተን ያደረግናቸው ነገሮች አሉ። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በፖለቲካ ዕውቀት ደሀ መሆኗን ነው። እኔ ተማሪ በነበርኩበት ወቅትም ሆነ በደርግ ወቅት ፖለቲካ ወንጀል ነበር። ፖለቲካ ህጋዊ የሆነው ባለፉት 27 ዓመታት ነው። ይህም ቢሆን ዲሞክራሲያዊ የሆነ የፖለቲካ ባህል እንድናዳብር ይሄን ያህል የረዳ አይመስለኝም። ይሄ እንዳይደገም ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል መገንባት ላይ መሰማራት አለብን። ብቻችንን የምንሰራው ሳይሆን ሌሎች ድርጅቶችንም ጨምሮ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሊሆን ይገባል። አምባገነንነት ፈፅሞ እንዳይከሰት መረባረብ ያስፈልጋል።

*⃣ኦነግ በደኖ ላይ ከተከሰተው ግድያ ጋር ተያይዞ ስሙ ይነሳል። ጭፍጨፋውን ፈፅሟል እያሉ የሚያነሱት አካላት አሉ። የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው?

▪️አቶ ሌንጮ፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ከሚያሳዝነው አንደኛው ጉዳይ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚነሳ ነገርና የፍትህ ጥያቄን ለመመለስ ተጠንቶ የሚቀርብ ሁኔታ የለም። ፕሮፓጋንዳ ነው? ወይስ የፍትህ ጥያቄ የሚለውን መለየት አይቻልም። በመጀመሪያ ነገር እኔ በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም። ቦታው ላይ የነበረውንም ሰራዊት አላዘዝኩም። ሁለተኛ ገለልተኛ በሆነ አካል የተጠና ጥናት የለም። እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን ዝም ብለን ከማራገብ ጥናት ተደርጎ እልባት ቢደረግላቸው ይሻላል። በእንዲህ አይነት ጉዳይ ከመወነጃጀል እንዳይደገም ማተኮሩ ነው የሚበጀው።

*⃣ተጠንቶ ጭፍጨፋው ከኦነግ ጋር የሚገናኝ ቢሆን ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነዎት?

▪️አቶ ሌንጮ፡ በእኛ ላይ በትክክለኛ መንገድ ተጠንቶ ማስረጃ ከቀረበ ያን ጊዜ ከኦነግ መሪዎች አንዱ ስለነበርኩ ማንኛውንም ህጋዊ ውሳኔ እቀበላለሁ።

*⃣በባለፉት ሦስት ዓመታት እንዲሁም የባለፉትን ሁለት ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዴት ገመገሙት?

▪️አቶ ሌንጮ፡ በእድሜዬ ይህ ሦስተኛው እድል ነው። ከአፄ ኃይለሥላሴ ወደ ደርግ የነበረው የሽግግር ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ መልክ አልነበረውም። ለተፈጠረው ዴሞክራሲያዊ ጅምር መጨናገፍ ብዙ ኃይሎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ አለ። ከደርግ ወደ ኢህአዴግ ሽግግር ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በፅሁፍ ቃልኪዳን ገብተን ነበር። በተለያዩ ምክንያቶች እንደፈለግነው ሳይሆን ቀረ። እውነተኛ ዴሞክራሲም እውን ሳይሆነ ተጨናገፈ። በዚህ ወቅት ስህተት መፈፀም የለብንም። ይህ የመጨረሻ ሊሆን ይችላል። ሁሉም የሚመለከታቸው ኃይሎች እንዲሁም ህብረተሰቡን ጨምሮ ተረባርበን ዴሞክራሲን እውን ልናደርግ ይገባል።

*⃣ባለፉት ዓመታት ብሔርተኝነት በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህም በተለያዩ አካባቢዎች ላሉት መፈናቀሎች አስተዋፅኦ እንዳደረገ አስተያየታቸውን የሚሰጡ እንዳሉ ሁሉ ጥሩ ነው የሚሉ አሉ። ይህንን የብሔርተኝነት ጉዳይ እንዴት ያዩታል?

▪️አቶ ሌንጮ፡ ብሔርተኝነት ማንም ግለሰብ ከመሬት ተነስቶ ሊፈጥረው የሚችለው ነገር አይደለም። ብሔርተኝነት የሚነሳው በምክንያት ነው። ብሔርተኝነትን ከመቃወም በፊት ምክንያቱ ምንድን ነው የሚለው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። በግሌ ብሔርተኝነትን በፍራቻ መነፅር የሚያዩ ሰዎች ችግራቸው ይገባኛል፤ ነገር ግን የነሱን ያህል አልሰጋም። መረዳት ያለብን ኦሮሞም ሆነ፣ አፋርም፣ ጉራጌም ሆነ የተለያየ ብሔር ያለው ግለሰብ ሆኖ ኢትዮጵያዊ መሆን ከተቻለ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ የብሔርን ማንነት በሚያንፀባርቅ መልኩ ከተዋቀረ ሁሉም ሰው ኢትዮጵያን ሲያያት ራሱን ለማየት ከቻለ ኢትዮጵያ ኃያል ሀገር ትሆናለች። ብሔርተኝነት እንደማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም አደጋ ሊኖረው ይችላል፤ ሊጠቅምም ይችላል።

©BBC
@tseagabwolde @tikvahethiopia
የዚህን ሳምንት የግዕዝ ትምህርት ወደ @TIKVAHETHEDU ገብታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።

በወጣት ዮርዳኖስ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ!
@tseagbwolde @tikvahethiopia
STOP EVICTION NOW! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉም የሀገራችን ክፍል የሱ ነው። ዜጎችን ማፈናቀል ሊቆም ይገባል።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia