This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት እንዳሳወቀው ተጨማሪ አንድ መቶ ሰላሳ አራት (134) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 481 ደርሰዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ!
በመላው ዓለም በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ከ5 ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ከነዚህ ውስጥ ከ327,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ 1.9 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች አገግመዋል።
በአፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት እጅግ በፍጥነት እየተስፋፋ ሲሆን እስካሁን ከ96,000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ2,900 በላይ ሰዎች ሞተዋል ፤ ከ39,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።
3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦
- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 18,003 ፣ ሞት 339 ፣ ያገገሙ 8,950
- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 14,229 ፣ ሞት 680 ፣ ያገገሙ 3,994
- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 7,542 ፣ ሞት 568 ፣ ያገገሙ 3,968
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የዕርቅ ሀሳብ አለኝ!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Eth) ከእርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በጋራ በመተባበር ወጣቶች ከያሉበት ሆነው የሚሳተፉበትና የሚወዳደሩበት እንዲሁም ማኅበራዊ አስተዋጿቸውን የሚያበረክቱበት 'የእርቅ ሀሳብ አለኝ' የተሰኘ ንቅናቄ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡
ይህንን ፕሮጀክት በይፋ ያስጀመሩት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በሀገር በቀል የእርቅ ሥርዓት ውስጥ የወጣቱ ተሳትፎ አነስተኛ ነው ያሉ ሲሆን ምንም እንኳን በሚፈጠሩ ግጭቶች ቀዳሚ ተጎጂና ተሳታፊ ወጣቱ ቢሆንም ሰላም ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ አነስተኛ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ አክለውም ይህ የ'እርቅ ሀሳብ አለኝ' የተሰኘው ፕሮጀክት ወጣቱ የእርቅ እሴቱን እንዲያውቅ፣ እንዲመረምርና በመረጃ የተደገፈ ጥናት እንዲያቀርብ ያስችላል ብለዋል፡፡
በተለይ አሁን ከተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በቤታቸው የሚገኙ ተማሪዎች እንዲሁም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች በዚህ በጎ ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ፕሮጀክት ከኮሚሽኑ ጋር ሲጀምር ወጣቶች ጋር ያለውን የእውቀትና የክህሎት አቅም ለሰላም ፣ ለበጎነትና ለፍቅር መጠቀም እንደሚቻል ለማሳየት በማለም ነው፡፡
ከዚህም ባሻገር ወጣቶች በአከባቢያቸው ያለ የእርቅ ሥርዓቶችን በማጥናት ፣ በመጠየቅ ፣ በማንበብ በሚያቀርቡት ዳሰሳዊ ጹሑፍ በባለሞያዎች አወዳድሮ ለተሳታፊዎች ሰርተፊኬት ለአሸናፊዎች ልዩ ሽልማት የሚያስገኝ ይሆናል፡፡

የዕርቅ ሃሳብ አለኝ!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Ethiopia) ትላንት ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር በይፋ ያስጀመርነው ንቅናቄ ወጣቶች ከያሉበት ሆነው በአከባቢያቸው ስላለ የዕርቅ ሥርዓት ጥናት በማድረግና በመጠየቅ ከ5-10 ገጽ በሚሆን አጭር የገለጻ ጹሑፍ ውድድር ነው፡፡
በውድድሩ የሚሳተፉ ወጣቶች በቅድሚያ የሚመዘገቡ ሲሆን ከ15-20 ቀናት የመዘጋጃ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች ፅሁፋቸውን የሚያቀርቡት #በመረጡት ሀገራዊ ቋንቋ ነው።
በሚያስገቡት ጹሑፍ ስለ አከባቢያቸው አጠቃላይ ገለጻ፣ ማስተዋወቅ ስለሚፈልጉት ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ሥርዓቱ በአሁኑ ወቅት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት በተጨማሪም በሥራው ወቅት የተገነዘቡት እና የታዘቡትን ምልከታ ማካተት የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡
በመቀጠልም ያስገቡት #ጹሑፍ 'የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን' በሚያዋቅረው ቡድን #ከተገመገመ በኃላ የጹሑፋቸው ይዘት እና አቀራረባቸው በተለያዩ የማወዳደሪያ መስፈርቶች ከተገመገመ በኃላ አሸናፊዎች የሚለዩ ይሆናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በውድድሩ የሚሳተፉ እንዲሁም ዋና ዋና መስፈርቶችን ያሟሉ ተሳታፊዎች በሙሉ ሰርተፍኬት ይዘጋጅላቸዋል ፤ #ለአሸናፊዎች ደግሞ 'ልዩ ሽልማት' የሚበረከት ይሆናል።
የምዝገባ ሂደቶችን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል!

በሱዳን ተጨማሪ 410 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)
የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ተጨማሪ 410 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ10 ሰዎች (5 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች (13 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።
ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች፦
1. ካርቱም ግዛት 345
2 .ከሰላ 3
3. ጀዚራ 27
4. ገዳሪፍ 10
5. ቀይ ባህር 2
6. ምዕራብ ዳርፉር 3
7. ሰሜን ዳርፉር 4
8. ሰሜን ኮርዶፋን 7
9. ስናር 1
10. ኒል አብያድ 2
11. ናህርኒል 6
ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3138 (ካርቱም ግዛት 2553) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 121 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 309 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ታውቋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን ተጨማሪ 410 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! (በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ) የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ተጨማሪ 410 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ10 ሰዎች (5 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች (13 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል። ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች፦ 1. ካርቱም ግዛት 345 2 .ከሰላ 3 3. ጀዚራ 27 4. ገዳሪፍ 10…
#SUDAN
'በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የቀረበው መረጃ ክፍተት አለው ፤ ሪፖርት የተደረገበትን ቀን እንጂ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገባቸውን ቀናት የሚገልፅ አይደለም።
ከሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ ዛሬ የወጣው ሪፖርት የግንቦት 10፣ 11 እና 12 ድምር ነው።
በአጠቃላይ በሶስቱ ቀናት 410 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 3,138 ከፍ አድርጎታል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የቀረበው መረጃ ክፍተት አለው ፤ ሪፖርት የተደረገበትን ቀን እንጂ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገባቸውን ቀናት የሚገልፅ አይደለም።
ከሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ ዛሬ የወጣው ሪፖርት የግንቦት 10፣ 11 እና 12 ድምር ነው።
በአጠቃላይ በሶስቱ ቀናት 410 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 3,138 ከፍ አድርጎታል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
ከስሐራ በታች ባሉ ሀገራት በኮቪድ-19 ምክንያት ከፍተኛ አድሎና መገለል እየደረሰ ነው ተብሏል።
በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ነው፣ የህክምና ባለሙያዎችም ከፍተኛ መገለል ደርሶባቸዋል፡፡
ሴት ነርሶችም በትዳር አጋሮቻቸው እየተካዱ ፤ ትዳርም እየተበተነ ነው ይላል የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ፡፡
ቫይረሱ እንዳለባቸው የተጠረጠሩ ሰዎችም ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ነው ጥናቶች የጠቆሙት፡፡ ጥናቶቹን ያካሄደው የድንበር የለሽ ሀኪሞች የምርመራ ማዕከል ነው።
በመገለል ምክንያትም በርካቶች ለበሽታው ከመጋለጣቸው ባለፈም ተገቢውን የጤና ክትትል እያገኙ አይደለም፤ ይህም ከፍተኛ ስጋትን ጭሯል ብሏል ማዕከሉ፡፡
ምንጭ፦ አሐዱ ሬድዮ ጣቢያ (AFP)

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,747 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 398 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 8 ወንድ እና 1 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ20 እስከ 49 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 3 ሰዎች ከአዲስ አበባ (2 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 1 ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው) ፣ 2 ሰዎች ከአፋር ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 1 ሰው ከሶማሌ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለውና በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ፣1 ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው እና በማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያለ)፣ እንዲሁም 2 ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 5
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 2
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 2
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላትናው ዕለት 1 ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ሶስት (123) ደርሷል።

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦
- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 3,138፣ ሞት 121፣ ያገገሙ 309
- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,828 ፣ ሞት 9 ፣ ያገገሙ 1,052
- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,573፣ ሞት 61 ፣ ያገገሙ 188
- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 1,029 ፣ ሞት 50 ፣ ያገገሙ 366
- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 481 ፣ ሞት 6፣ ያገገሙ 6
- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 398 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 123
- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 39
(በዚህ መረጃ የጅቡቲ ፣ የኬንያ ፣ የደቡብ ሱዳን ፣ ሱማሊያ የ24 ሰዓት ሪፖርት አልተካተተም፤ የአራቱም (4) ሀገራት ሪፖርት #እየተጠበቀ ነው። በሌላ በኩል ኤርትራ ከሚያዚያ 10/2012 ዓ/ም በኃላ አዲስ ኬዝ ሪፖርት አላደረገችም ፤ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሁሉም ታማሚዎች ማገገማቸው ይታወቃል)

ኬንያ ውስጥ በአንድ ቀን 80 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋገጠ!
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,102 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ (80) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,109 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 375 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,102 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ (80) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,109 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 375 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA
ባለፉት 24 ሰዓት በኬንያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ሰማንያ (80) ሰዎች መካከል የስድስት (6) ወር ህፃን ይገኝበታል።

ጅቡቲ ውስጥ በአንድ ቀን 219 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ጅቡቲ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,100 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ (219) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,047 ደርሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል ፤ በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር አስር (10) ደርሷል።
በሌላ በኩል ትላንት ሶስት (3) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,055 ደርሰዋል።

"ኮቪድ-19 በአውሮፓ ድጋሚ ሊያገረሽ ስለሚችል ሀገራት ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው" - ዶክተር አንደሪያ አሞን
የአውሮፓ ሀገራት ለኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባትም ሆነ መድኃኒት እስካልተገኘ ድረስ ለሁለተኛው ዙር የቫይረሱ ጥቃት ራሳቸውን ማዘጋጅ እንደለባቸው የህብረቱ የበሽታዎች ቁጥጥር ኃላፊ ዶክተር አንደሪያ አሞን አሳሰቡ።
እስከ አሁን ጥቂት ሰዎች ብቻ ቫይረሱን የመከላከል አቅም ያጎለበቱት የሚሉት ኃላፊዋ፤ እስከ አሁን ቫይረሱን ማሸነፍ አልቻልንም ማለታቸውን ዴሊ ሜል ዘግቧል።
እስካሁን 15 ከመቶ የህብረቱ አባል ሀገራት በኮቪድ-19 መጠቃታቸውን የሚናገሩት ዶክተር አንድሪያ ፤ አብዛኛው ሕዝብ የቫይረሱ ተጋላጭ የሚሆነው ወደፊት ነው ብለዋል።
በሳይንሳዊ ስሙ ሳርስ ኮቪድ 2 (SARS-COV-2) እየተባለ የሚጠራው ቫይረሱ መቼና በምን ሁኔታ ከኅብረተሰቡ ሊጠፋ እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ መሆኑንም ተናግረዋል።
#ENA

በደቡብ ሱዳን የቲክቫህ አባላት!
ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በሀገሪቱ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ እየተሰራጨ እንደሆነ ገልፀውልናል።
ሀገሪቱ የምታደርገው ምርመራ ትንሽ ቢሆንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ግን ከፍጥነት እየጨመረ ነው ሲሉ አሳውቀውናል።
አንዳንድ የሀገሪቱ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የሚባለው #ውሸት ነው፣ አሉባልታ ነው፣ እንዲህ የሚባል በሽታ የለም ፤ ጥቁሮችን አይዝም የሚል አመለካከት አላቸው ብለዋል።
በሀገሪቱ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚሰራው ስራ ደካማ ነው ፤ ቁጥራቸው በርካታ ባለስልጣናት ሳይቀሩ በቫይረሱ ተይዘዋል።
በሀገሪቱ ባለፉት ሳምንታት ብቻ በርካታ ሰዎች (የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሳይቀሩ) ሞተዋል ግን በምን ምክንያት እንደሆን አይገለፅም ሲሉ ያለውን ሁኔታ አስረድተውናል።
አካላዊ ርቀት፣ እጅን አዘውትሮ በሳሙና መታጠብ፣ በአንድ ቦታ አለመሰባሰብ፣ ሌሎችም ቫይረሱን የመከላከያ መንገዶች ተግባራዊ አይደረጉም ይህ ሁኔታ የጤና ስርዓቷ እጅግ ደካማ በሆነው ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም ሲሉ ያደረባቸውን ስጋት ገልፀዋል።

በሱማሊያ ተጨማሪ 21 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 21 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,594 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 204 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 21 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,594 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 204 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ዕጣ ፈንታ!
(በአሃዱ ቴሌቪዥን)
የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዕጣ ፈንታ ምን ይሁን፣ ፈተናው በተያዘው ዓመት ይሰጥ ወይስ ይተላለፍ የሚለው ውሳኔ ከፌደራሉ መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጹን አሐዱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።
እንደሥራ ኃላፊዎቹ መረጃ ውሳኔው በ15 ቀናት ውስጥ ይታወቃልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን እንደቴሌግራም ባሉ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ማስተማር እንዲቀጥሉ ቢልም ስኬታማ ሆኖ አልቀጠለም፡፡
ከዚህም አልፎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰዎች መሰብሰብ መከልከልም ተማሪዎች ቢዘጋጁ እንኳን ፈተናው በምን አግባብ ይሰጣል የሚለውን ምላሽ አልባ አድርጎታል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethmagazine

<unknown> – Professor_Tasew__TIKVAH
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!
(አሐዱ ቴሌቪዥን - ኬላ ፕሮግራም)
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በዚህ ዓመት #እንደማያስመርቅ አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና በአሐዱ ቴሌቪዥን ከሚተላለፍ 'ኬላ' ከተሰኘ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ሐምሌ 4/2012 ዓ/ም በሚካሔደው የተማሪዎች ምርቃት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የማታ የመጀመሪያ ዲግሪ ፣ የ2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች ብቻ ይካተታሉ።
በተያያዘ ዜና የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ እንዳበቃ የገጽ ለገጽ ትምህርታቸውን እንደሚቀጥሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ይፋ አድርጓል።
የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ግን በበይነ መረብ ወይም ኦንላይን ተፈትነው ትምህርታቸውን የሚያጠናቀቁበት ሁኔታ ተቀምጧል ብሏል።

#UPDATE
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 39 ሚሊዮን መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 39 ሚሊዮን መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ወጣቶች 'በባህላዊ የዕርቅ ሥርዓቶች' ላይ የሚያደርጉት አጭር ገለጭ ፅሁፍ ውድድርን በማስመልከት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ያስተላለፉት መልዕክት!