TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BREAKING

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1775 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ አምስት (35) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ምሳ ሁለት (352) ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 17 ወንድ እና 18 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ (አንድ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ 23 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለቸው ፣ 5 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) ፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እንዲሁም 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

ሚያዚያ 27 በተሰጠው መግለጫ በኮቪድ-19 ምክንያት የ75 ዓመት ሴት ህይወታቸው ማለፉ መገለፁ ይታወሳል።

በመሆኑም ከግለሰቧ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 25 ሰዎች ተለይተው ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች ቫይረስ አደተገኘባቸው ተረጋግጦ በግንቦት 1 ቀን በተሰጠው መግለጫ የተካተቱ ነበሩ።

በዛሬው ዕለት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ውስጥ 22 ሰዎች ግንቦት 1 ቀን ከተገለፁት 5 ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው እና ክትትል ላይ ከነበሩ 94 ግለሰቦች ውስጥ ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 6

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 24

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 5

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 3 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 10 በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ፦

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - አስራ ሶስት (13) ሰዎች
• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ግንቦት 3/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 6/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 7/2012 ዓ/ም - ስምንት (8) ሰዎች
• ግንቦት 8/2012 ዓ/ም - ሁለት (2) ሰዎች
• ግንቦት 9/2012 ዓ/ም - አራት (4) ሰዎች
• ግንቦት 10/2012 ዓ/ም - ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች

በድምሩ 111 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሁንም #በድጋሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ፤ መዘናጋት እና መሰላቸት የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

ኬንያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,139 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 912 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ሃያ ሶስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 336 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WHA73

የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል።

አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚውል 2 ቢሊየን ዶላር እንደምትለግስ ቃል ገብተዋል።

የWHO ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዓለም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነርሶች እና አዋላጆች ያስፈልጓታል ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ የጤና ባለሙያዎች ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራና ቢቢሲ (በኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Italy

በሮም የኢፌዴሪ ሚሲዮን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከ03/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በሳምንት ሁለት (2) ቀን ብቻ ተወስኖ የቆየው የቆንስላ አገልግሎት ከ10/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ #መደበኛ ስራውን የሚጀምር መሆኑን ገልጿል። የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከአስፈላጊ ጥንቃቄ ጋር እንዲሆንም #ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች!

በዚህ ፈታኝ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ሆነው በተለያዩ ሀገራት ህዝብና ወገንን እያገለገሉ የሚገኙ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች እንዲሁም ረዳቶቻቸው ናቸው።

በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በየዕለቱ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን እየሰማን ነው።

ዛሬ እንኳን ሀገራችን ሪፖርት ካደረገቻቸው ኬዞች መካከል 2 የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መረጃ ደግሞ በታንዛኒያ ድንበር 53 (51 የታንዛኒያና 2 የቡሩንዲ ዜጎች) የድንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ሁሉም ወደየመጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ባለፉት 24 ሰዓት በዩጋንዳ 1,071 የላብራቶሪ ምርመራ (በድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች) ላይ ተደርጎ ሃያ አንዱ (21) ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

የደንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ክትትል ማድረግ ካልተቻለ ፤ የጤናቸውን ሁኔታ መከታተል ካልተቻል፣ እራሳቸውን ከቫይረሱ የሚጠብቁበትን መንገድ ማመቻቸት ካልተቻለ ፤ በሁሉም ሀገራት ከፍተኛ የሆነ አደጋ መፈጠሩ የማይቀር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,455 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ አንድ (11) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 163 ደርሷል።

በተጨማሪ የ1 ሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ሰባት (57) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በአንድ ቀን 117 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት 813 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 117 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,518 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አርባ ስድስት (46) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,018 መድረሳቸው ገልጿል።

በተጨማሪ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰባት (7) ደርሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዘገበ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያን የዘጠና ዘጠኝ (99) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከየካቲት 30/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 451 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ይህ ደግሞ ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ኬዝ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቡሩንዲ ምርጫ ከፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል!

(በጋዜጠኛ እሸት በቀለ)

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ይሰሩ የነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎችን ባለፈው ሳምንት ያባረረችው ቡሩንዲ ረቡዕ አዲስ ፕሬዝዳንት ትመርጣለች።

አገሪቱ እስካሁን አርባ ሁለት (42) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አረጋግጣለች።

ቡሩንዲን እንደ ብረት ቀጥቅጠው ላለፉት 15 አመታት የገዙትን ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛን ለመተካት 7 እጩዎች ቀርበዋል።

የገዢው CNDD-FDD ፓርቲ እጩ 'እግዜር ቡሩንዲን ስለሚያፈቅር የአገሪቱ ዜጎች ኮሮናን መፍራት የለባቸውም' ብለዋል።

የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ባለፈው ወር ቡሩንዲ "ከፈጣሪ ልዩ ቃል ኪዳን ተፈራርማለች" ሲሉ የኮሮና ሥጋትን አጣጥለው ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀ በተንቀሳቃሽ ሰልክ የሚሰጥ ስልጠናን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 57 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ ሃምሳ ሰባት (57) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 347 ደርሰዋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አራት (4) ሲሆኑ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ደግሞ ስድስት (6) ደርሰዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በስፔን ለሁለተኛ ቀን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዝግቧል!

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሃምሳ ዘጠኝ (59) ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ ከመጋቢት 7/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሰበር ዜና!

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሬክ ማቻር እና ባለቤታቸው አንጀሊና ቴኒ (የመከላከያ ሚኒስትር) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በተጨማሪም የተቀዳሚ ም/ፕሬዘዳንቱ የቢሮ ሰራተኞች እና ጠባቂዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ፦

- ዶክተር ሬክ ማቻርን ጨምሮ ሌሎች 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባላት ምርመራ የተደረገላቸው ግንቦት 5/2012 ዓ/ም ነው።

- ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንቱና ከባለቤታቸው (አንጀሊና ቴኒ) ፣ ከቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም ከጠባቂዎቻቸው በተጨማሪ ቁጥራቸው ያልተገለፀ የቀድሞ ታስክ ፎርስ አባላት በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ከዚህ ቀደም ዶክተር ሬክ ማቻር ሚያዚያ 19/2012 ዓ/ም ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጦ ነበር። ሌላኛው ምርመራ የተደረገው ከታስክ ፎርሱ አባላት በአንዱ ላይ ቫይረሱ ስለተገኘ ነው።

- ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሬክ ማቻር እና ሌሎች በቫይረሱ የተያዙ ከፍተኛ አመራሮች ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ 14 ቀናት ራሳቸውን አግልለው ክትትል ይደረግላቸዋል።

- ዶክተር ሬክ ማቻር እስካሁን ምንም ምልክት የለባቸውም።

#JamesGatdetDak #FVPDrRiekMachar
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በሱዳን ካርቱም ግዛት ከዛሬ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት (2) ሣምንታት ከዚህ በፊት የታወጀዉ የእንቅስቃሴ ዕገዳና ከቤት ያለ መዉጣት ገደብ መቀጠሉን የሱዳን መንግስት አስታዉቋል።

ስለዚህ ሱዳን ካርቱም ግዛት የምትኖሩ ዜጎቻችን ይህን ዉሳኔ በማክበር እራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከቫይረሱ እንድትጠብቁ በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን!

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዶሃ)

የኳታር የሚኒስትሮች ም/ቤት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ያስችላሉ ያላቸውን ተጨማሪ ውሳኔዎች አሳልፏል። በዚህም መሰረት፦

- ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች እና ሁሉም ነዋሪዎች ከግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም (22 May 2020) ጀምሮ ከቤታቸው ሲወጡ የቫይረስ ተጋላጭነት ደረጃን የሚያሳየውን EHTERAZ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በስልኮቻቸው ማውረድ ይጠበቅባቸዋል።

- በግል መኪናዎች ውስጥ ከ2 ሰው በላይ ሆኖ መጓዝ አይፈቀድም። በታክሲዎች፣ በሊሞዚኖች እና በቤተሰብ ሹፌሮች በሚሽከረከሩ መኪናዎች ውስጥ ከ3 ሰው በላይ ሆኖ መጓዝ አይቻልም። አምቡላንሶችና የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መኪኖች፣ የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የደህንነት ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውሳኔው አይመለከታቸውም።

- ከግንቦት 11 - 22 ቀን 2012 ዓ.ም (19 -30 May 2020) ሁሉም ሱቆች ዝግ ሆነው ይቆያሉ፤ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይቆማሉ። ምግብ ቤቶች፣ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶች እና ፋርማሲዎች ውሳኔው አይመለከታቸውም።

- ከግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም (19 May 2020) ጀምሮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ (የፊት መሸፈኛ በመጠቀም፣ ርቀትን በመጠበቅ) በማድረግ መከናወን ይኖርባቸዋል።

- ውሳኔዎቹን ተላልፎ የተገኘ ግለሰብ እስከ ሶስት ዓመት እስር እና እስከ 200,000 የኳታር ሪያል የሚቀጣ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WHA73 የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል። በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል። አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን…
#WHA73 #DrTedrosAdhanom

በትንሹ 320 ነርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተዋል!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሚሞቱ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከፍተኛ አደጋን ደቅኗል ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገረዋል።

ዓለም አቀፉ የነርሶች ምክርቤት በስሩ ካሉት ማህበራት ባሰባሰበድ መረጃ መሰረት በአንዳንድ ሃገራት የሚስተዋለው የነርሶቹ የተጠቂነት ቁጥር በ20 በመቶ አሻቅቧል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም በትንሹ 320 ነርሶች ሞተዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ መረጃዎች በወጉ ሊሰበሰቡ ቢችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የድርጅቱ አባል ሃገራት የጤና ባለሙያዎቻቸውን ከወረርሽኙ #ሊጠብቁ ፣ አስፈላጊውን የህክምና ግብዓቶች ሊያሟሉላቸው እና መረጃዎችን ስርዓት ባለው መልኩ ሊሰበስቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia