TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በሶሪያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 58 ደርሰዋል፤ በዛሬው ዕለት 7 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት የ145 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። ይህ የሟቾች ቁጥር ከየካቲት 30/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- በደቡብ ኮሪያ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ሰባቱ (7) ከውጭ የገቡ ናቸው፤ አምስቱ (5) ከምሽት መዝናኛ ቤቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኬዞች ናቸው።

- በዩናትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት የ170 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከመጋቢት 15 በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- ኳታር ውስጥ በአንድ ቀን 1,632 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 32,604 ደርሷል።

- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 510 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ5 አፍሪካ ሀገራት የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 14,355 ፣ ሞት 261 ፣ ያገገሙ 6,478

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 12,229 ፣ ሞት 630 ፣ ያገገሙ 3,172

- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 7,019 ፣ ሞት 548 ፣ ያገገሙ 3,507

- ሞሮኮ በቫይረሱ የተያዙ 6,870 ፣ ሞት 192፣ ያገገሙ 3,660

- ጋና በቫይረሱ የተያዙ 5,735 ፣ ሞት 29 ፣ ያገገሙ 1,754

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 2,289፣ ሞት 97፣ ያገገሙ 222

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,421፣ ሞት 56 ፣ ያገገሙ 152

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,401 ፣ ሞት 4 ፣ ያገገሙ 972

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 887 ፣ ሞት 50 ፣ ያገገሙ 313

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 317፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 113

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 290 ፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 4

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 39

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 302 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤ/ሚ/ር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 302 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ8 ሰዎች (3 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 25 ሰዎች (22 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች ፦

1. ካርቱም ግዛት 235
2. ጀዚራ 11
3. ሰሜን ኮርዶፋን 11
4. ገዳሪፍ 7
5. ስናር 10
6. ምዕራብ ዳርፉር 10
7. ሰሜን ዳርፉር 5
8. ደቡብ ዳርፉር 5
9. ኒል አዘርገ 3
10. ኒል አብያድ 4
11. ምዕራብ ኮርዶፋን 1

በዚህ መሰረት ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,591 (ካርቱም ግዛት 2,109) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 105 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 247 ሰዎች ማገገማቸዉን ታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 4,801,517 ሰዎች መካከል 316,659 ሰዎች መሞታቸውንና 1,858,090 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ማገገማቸውን የዎርልዶሜትርስ ድረገፅ መረጃ ያሳያል።

ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው 5 ሀገራት ፦

- አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ 1,527,664 ፣ ሞት 90,978 ፣ ያገገሙ 346,389

- ዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ የተያዙ 243,695 ፣ ሞት 34,636 ፣ ያገገሙ N/A

- ጣልያን በቫይረሱ የተያዙ 225, 435፣ ሞት 31,908፣ ያገገሙ 125,176

- ፈረንሳይ በቫይረሱ የተያዙ 179,569፣ ሞት 28,108 ፣ ያገገሙ 61,213

- ስፔን በቫይረሱ የተያዙ 277,719 ፣ ሞት 27,650 ፣ ያገገሙ 195,945

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኒውዚላንድ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ!

ኒውዚላንድ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በማሰብ ከመጋቢት 15 ጀምሮ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተከፍተዋል።

እንደ RNZ መረጃ ከሆነ ወደ 800,000 የሚጠጉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።

ከሳምንታት በፊት የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን በኮሮና ቫይረስ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

ኒውዚላንድ ውስጥ ባለፉት 9 ተከታታይ ቀናት የተመዘገቡት የኮቪድ-19 ኬዞች ከአምስት (5) በታች ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ደግሞ 2,570 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ ሁሉም ከቫይረሱ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 1,499 ሰዎች መካከል የሃያ አንድ (21) ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1,433 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ ስራ ጀመረ። መሳሪያው በአንድ ጊዜ 92 ሰው የመመርመር አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

ቀደም ሲል በክልሉ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማሽን #ባለመኖሩ የተጠርጣሪ ማህበረሰብ ክፍሎችን ናሙና አዲስ አበባና ባህርዳር ሲላክ ቆይቷል።

ይህንን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት እና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመነጋገር ፒሲአር ማሽኑን ክልሉ አግኝቷል።

ትናንት በሙከራ ደረጃ 9 ሰዎችን መርምሮ ውጤታማ በመሆኑ ዛሬ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰንና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

(የክልሉ ጤና ቢሮ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1775 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ አምስት (35) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ምሳ ሁለት (352) ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 17 ወንድ እና 18 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ (አንድ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ 23 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለቸው ፣ 5 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) ፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እንዲሁም 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

ሚያዚያ 27 በተሰጠው መግለጫ በኮቪድ-19 ምክንያት የ75 ዓመት ሴት ህይወታቸው ማለፉ መገለፁ ይታወሳል።

በመሆኑም ከግለሰቧ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 25 ሰዎች ተለይተው ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች ቫይረስ አደተገኘባቸው ተረጋግጦ በግንቦት 1 ቀን በተሰጠው መግለጫ የተካተቱ ነበሩ።

በዛሬው ዕለት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ውስጥ 22 ሰዎች ግንቦት 1 ቀን ከተገለፁት 5 ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው እና ክትትል ላይ ከነበሩ 94 ግለሰቦች ውስጥ ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 6

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 24

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 5

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 3 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 10 በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ፦

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - አስራ ሶስት (13) ሰዎች
• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ግንቦት 3/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 6/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 7/2012 ዓ/ም - ስምንት (8) ሰዎች
• ግንቦት 8/2012 ዓ/ም - ሁለት (2) ሰዎች
• ግንቦት 9/2012 ዓ/ም - አራት (4) ሰዎች
• ግንቦት 10/2012 ዓ/ም - ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች

በድምሩ 111 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሁንም #በድጋሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ፤ መዘናጋት እና መሰላቸት የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

ኬንያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,139 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 912 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ሃያ ሶስት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 336 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WHA73

የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል።

አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚውል 2 ቢሊየን ዶላር እንደምትለግስ ቃል ገብተዋል።

የWHO ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ዓለም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነርሶች እና አዋላጆች ያስፈልጓታል ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ የጤና ባለሙያዎች ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራና ቢቢሲ (በኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Italy

በሮም የኢፌዴሪ ሚሲዮን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከ03/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በሳምንት ሁለት (2) ቀን ብቻ ተወስኖ የቆየው የቆንስላ አገልግሎት ከ10/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ #መደበኛ ስራውን የሚጀምር መሆኑን ገልጿል። የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከአስፈላጊ ጥንቃቄ ጋር እንዲሆንም #ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች!

በዚህ ፈታኝ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ሆነው በተለያዩ ሀገራት ህዝብና ወገንን እያገለገሉ የሚገኙ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች እንዲሁም ረዳቶቻቸው ናቸው።

በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በየዕለቱ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን እየሰማን ነው።

ዛሬ እንኳን ሀገራችን ሪፖርት ካደረገቻቸው ኬዞች መካከል 2 የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መረጃ ደግሞ በታንዛኒያ ድንበር 53 (51 የታንዛኒያና 2 የቡሩንዲ ዜጎች) የድንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ሁሉም ወደየመጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ባለፉት 24 ሰዓት በዩጋንዳ 1,071 የላብራቶሪ ምርመራ (በድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች) ላይ ተደርጎ ሃያ አንዱ (21) ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

የደንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ክትትል ማድረግ ካልተቻለ ፤ የጤናቸውን ሁኔታ መከታተል ካልተቻል፣ እራሳቸውን ከቫይረሱ የሚጠብቁበትን መንገድ ማመቻቸት ካልተቻለ ፤ በሁሉም ሀገራት ከፍተኛ የሆነ አደጋ መፈጠሩ የማይቀር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,455 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ አንድ (11) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 163 ደርሷል።

በተጨማሪ የ1 ሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ሰባት (57) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በአንድ ቀን 117 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት 813 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 117 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,518 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አርባ ስድስት (46) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,018 መድረሳቸው ገልጿል።

በተጨማሪ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰባት (7) ደርሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዘገበ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያን የዘጠና ዘጠኝ (99) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከየካቲት 30/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 451 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ይህ ደግሞ ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ኬዝ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቡሩንዲ ምርጫ ከፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል!

(በጋዜጠኛ እሸት በቀለ)

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ይሰሩ የነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎችን ባለፈው ሳምንት ያባረረችው ቡሩንዲ ረቡዕ አዲስ ፕሬዝዳንት ትመርጣለች።

አገሪቱ እስካሁን አርባ ሁለት (42) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አረጋግጣለች።

ቡሩንዲን እንደ ብረት ቀጥቅጠው ላለፉት 15 አመታት የገዙትን ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛን ለመተካት 7 እጩዎች ቀርበዋል።

የገዢው CNDD-FDD ፓርቲ እጩ 'እግዜር ቡሩንዲን ስለሚያፈቅር የአገሪቱ ዜጎች ኮሮናን መፍራት የለባቸውም' ብለዋል።

የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ባለፈው ወር ቡሩንዲ "ከፈጣሪ ልዩ ቃል ኪዳን ተፈራርማለች" ሲሉ የኮሮና ሥጋትን አጣጥለው ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀ በተንቀሳቃሽ ሰልክ የሚሰጥ ስልጠናን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia