TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በደቡብ ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 90 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,133 ፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 799

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 607 ፣ ሞት 29 ፣ ያገገሙ 197

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 928፣ ሞት 44 ፣ ያገገሙ 106

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 930 ፣ ሞት 52 ፣ ያገገሙ 92

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 191 ፣ ሞት 4 ፣ ያገገሙ 93

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 90 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 30

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

የአራቱ ወጣቶች ኬዝ የማንቂያ ደውል ይሁነን!

ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ለኢትዮጵያውያን መልዕክት አላቸው ፦

"ሁሉም ሰው ሊነቃ ይገባል ፤ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችም ቫይረሱን (COVID-19) ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ መረዳት ያስፈልጋል። ወጣቶች ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሊይዛቸው እንደሚችል በማወቅ እራሳቸውን ሊጠብቁ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ምክር ሊያዳምጡ ይገባቸዋል።"

ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ይህ መልዕክት ያስተላለፉት በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ ስለተያዙት 4 ወጣቶች አጠር ያለ ማብራሪያ በሰጡን ወቅት ነው።

በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ወጣቶች ምንም አይነት 'ምልክት የሌላቸው' ሲሆኑ በክልሉ በተሰራው ጠንካራ የክትትል ስራ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች (Face Masks) !

(በዶክተር መክብብ ካሳ - ከCOVID-19 RRT)

የኮቪድ-19 ቫይረስ በምናወራበት ፣ በምንስልበት እና በምናስነጥስበት ጊዜ ከአፍና አፍንጫችን በሚወጡ ጥቃቅን ጠብታዎች (droplets)አማካኝነት እንደሚተላለፍ ይታወቃል፡፡

በርካታ ጥናቶች አንደሚያሳዩት ጭንብሎችን መጠቀም በቫይረሱ እንዳንያዝ አንዲሁም እኛም ወደ ሌሎች እንዳናሰተላልፍ በተለይም በማህበረሰብ ውስጥ ሊፈጠር የሚችልን ስርጭት (community spread)ለመቀነስ ያግዛል::

በተለይ እንደኛ አብዛኛው ህዝብ ቤት መቀመጥ ባልቻለበት ሁኔታ ጭንብሎችን መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምልክት ባይኖራቸውም ቫይረሱን ማስተላለፍ ይችላሉ ስለዚህ መጠንቀቅ ያለብን የሚያስሉ ወይም የሚያስነጥሱትን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ግለሰብ ነው፡፡

ሌሎች በተደጋጋሚ የተነገሩ የመከላከያ ዘዴዎችን ጭንብሎችን ከመጠቀም ጋር አብረው መከወን ይኖርባቸዋል እንጂ የተወሰኑትን ብቻ ተግባራዊ ማድረግ በቫይረሱ እንዳንያዝ አያደርገንም፡፡

ጭንብሎችን ከማድረጋችን በፊት እጃችንን በአግባቡ ማፅዳት፣ አፍና አፍንጫችንን በደንብ መሸፈኑን ማረጋገጥ፤ ከማውለቃችን በፊት በድጋሚ እጃችንን ማፅዳትና የጭንብሉን መያዣ ክሮች ብቻ በመጠቀም ማውለቅና አካባቢን በማይበክል መንገድ ማስወገድ፡፡

የህክምና ባለሙያዎች የሚጠቀሙባቸውን ጭንብሎች ባለመጠቀም እጥረት እንዳይፈጠር የበኩላችንን እንወጣ፡፡

በምንጠቀምበት ጊዜ ምቾት ላይሰማን ይችላል ነገር ግን ለጋራ ደህንነታችን ሲባል ለተወሰነ ጊዜ እንቸገር::

የአንድ ሰው ጥንቃቄ ጉድለት መዘዙ ለብዙኀን ይተርፋል፤ እንተሳሰብ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኮቪድ-19 ውጭ መረጃዎች የሚሰባሰቡበት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁለተኛው ገፅ 👉 @tikvahethmagazine ነው! (ከ 192,000 በላይ አባላት ያሉበት)
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ጤና ቢሮ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል መረጃና ጥቆማ አገልግሎት እንዲውል ነጻ የጥሪ ማዕከል አዘጋጅቷል። 6406 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

ለሚፈለገው ዓላማ ብቻ ደውሉ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ የተሰራው የመተንፈሻ መሳሪያ!

(በአል ዓይን የተዘጋጀ)

ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ህክምና የሚረዳ መተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ተሰርቷል፡፡ በ3 ወራት ውስጥ መሳሪያውን በብዛት ለማምረት ታቅዷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalSupremeCourt

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ቀጣይ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ በማስፈለጉ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩበትን ጊዜ ለተጨማሪ 22 የስራ ቀናት አራዝሟል፡፡

ምንጭ፦ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,861 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ዘጠና አራት (194) ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የሁሉም ታማሚዎች የመኖሪያ ቦታ አዲስ አበባ ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 0

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው- 2

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ያለ - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሁለት ሰዎች (1 ከአዲስ አበባ እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አምስት (95) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በኢትዮጵያ ተጨማሪ 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,847 ላቦራቶሪ ምርመራ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ሰማንያ ሰባት (187) ደርሷል። ዛሬ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 24 ወንድ 1 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው…
አስራ ዘጠኙ (19) የኮቪድ-19 ታማሚዎች እንዴት በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ ?

(በሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

በትላንትናው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ አዳዲስ ሰዎች መካከል አስራ ዘጠኙ (19) በአዲስ አበባ ከተማ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ የተገኙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጿል።

ይህ ሁኔታ ኮቪድ-19 በህብረተሰቡ ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገኝ የሚጠቁም በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት ተላልፏል።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጅት እና ምላሽ አስተባባሪው አቶ ዘውዱ አሰፋ እነዚህ አስራ ዘጠኙ (19) ሰዎች (የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው) በቤት ለቤት አሰሳና ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ወገኖችን በመመርመር በሽታው እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።

አቶ ዘውዱ ከዚህ ቀደምም ከአዲስ አበባ ውጭ በአፋር ፣ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያልነበራቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው እንደተገኙ አስታውሰዋል።

በበሽታው ከተያዙት መካከል ሰማንያ በመቶዎቹ (80%) ምልክት እንደማያሳዩ ገልፀው በቫይረሱ መያዛቸውን እራሳቸውም ሳያውቁ ሌላውም ሰው ሳያውቅ ቫይረሱን የሚያስተላልፉ ብዙ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄው ላይ እንዲበረታ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 824 ደረሱ!

ጅቡቲ ውስጥ በየዕለቱ በኮቪድ-19 ከሚያዙ ሰዎች ይልቅ ከበሽታው የሚያገግሙት ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመሩ ናቸው።

የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ውስጥ 25 ሰዎች ማገገማቸውን ሪፖርት አድርጓል።

በሌላ በኩል 106 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አሳውቋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,135 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 922 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አስራ አራት (14) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 621 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 5 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 202 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንዘናጋ!

ከምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የተላለፈ መልዕክት ፦

ዛሬ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚያግዙ እና ተጨማሪ የአሰራር ማሻሻያ የሚጠይቁ ሁለት መመሪያዎችን ተወያይተን አፅድቀናል።

ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 49 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ውጤታቸው የተለየ ሲሆን ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሽታው በፍጥነት የመዛመት ዕድል እንዳለው በግልፅ ያሳያል።

የወረርሽኙ አዝማሚያ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት በወቅታዊ ጉዳዮች #ሳንዘነጋ የጥንቃቄ መመሪያዎችን አጥብቀን ተግባራዊ እንድናደርግ በአፅንዖት አደራ ለማለት እወዳለሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFRICA

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በቀጣዮቹ 12 ወራት 190 ሺ ሰዎችን በአፍሪካ ሊገድል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ አስጠንቅቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የ47 ሃገራት ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አስጠናሁ ባለው ጥናት ለወረርሽኙ አፋጣኝ ምላሽ እና ተገቢው ትኩረት ካልተሰጠ ስርጭቱ ሙሉ በሙሉ ሳይጠፋ ረጅም አመታትን ሊቆይ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡

ከአሁን ቀደምም እንደ መንግስታት የዝግጁነት እና የምላሽ ሁኔታ ቢለያይም እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

በያዝነው ሳምንት ይፋ የሆነው የድርጅቱ ጥናት የቁጥጥር ስራዎች በታሰበው ልክ ውጤት የማያመጡ ከሆነ ወረርሽኙ በተከሰተበት በዚህ ዓመት ብቻ ከ29 እስከ 44 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኳታር በአንድ ቀን ብቻ 1,311 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ (እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው) ፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20,000 በልጧል።

- ሩስያ በኮቪድ-19 እየታመሰች ነው። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 10,699 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 98 ሰዎች ሞተዋል።

- በUAE በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 16,793 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 553 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በኢራን በአንድ ቀን 1,556 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 55 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በሳዑዲ አረቢያ 1,701 ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት ቻይና 1 ደቡብ ኮሪያ ደግሞ 12 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ማገኘታቸውን ሪፖርት አድርጓል።

- በስፔን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 3,726 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 229 ሰዎች ሞተዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ77,000 በልጧል።

- በአሜሪካ የሥራ አጦች ቁጥር በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ከነበረው 4.4 በመቶ አሁን ወደ 14.7 በመቶ ከፍ ብሏል።በ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተፈጠረው የኢኮኖሚ ውድቀት 20.5 ሚሊየን የሥራ እድሎችን አጥፍቷል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በህክምና ላይ ለተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የአደጋና የህይወት መድን ሊገባላቸው ነው!

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ለመከለካል ድጋፍ ለሚሰጡ የጤናና ሌሎች ባለሙያዎች የህይወት መድን ሽፋን ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ።

የመግባቢያ ሥምምነቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳ ፈርመውታል።

በሥምምነቱ መሰረት የኮሮናቫይረስ ለመከላከል በተለያዩ የጤና ተቋማት ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የህይወት መድን ሽፋን ይደረግላቸዋል።

በለይቶ ማቆያ፣ በኳራንቲን፣ በላብራቶሪ ምርመራ ማዕከል፣ በፈጥኖ ምላሽ ቡድን፣ በድንገተኛና በሌሎች ክፍል የሚሰሩ ባለሙያዎችን ይሸፍናል ተብሏል።

ጎን ለጎንም ጽዳቶች ፣ የአንቡላንስ ሹፌሮች እና ሌሎችም ፊት ለፊት የሚሰሩ ባለሙያዎች በዚሁ የህይወት መድን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የተገለጸው - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን በአንድ ቀን 30 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በደቡብ ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ ሰላሳ (30) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 120 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች 37 ደረሱ!

ኤርትራ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 39 ሰዎች መካከል ሰላሳ ሰባቱ (37) ከበሽታው ማገገማቸውን የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር አሳወቀ። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ ሰባት (7) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በሱዳን በአንድ ቀን 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 181 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 10 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,111 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 59 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 102 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ከበሽታው ማገገማቸዉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia