በአወዳይ ከተማ የቤት ለቤት ልየታ ስራ ተጀምሯል!
(ሕይወት ፋና ሆስፒታል)
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል አስተባባሪነት 40 የሚሆኑ ጠቅላላ እና ስፔሻሊስት ሐኪሞች በአወዳይ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ (Screening) ስራ ተጀምሯል።
አወዳይ ከተማን ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እና በሁሉም አቅጣጫ ሞዴል ዲስትሪክት ለማድረግ በማሰብ ነው የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ (Screening) ስራው የተጀመረው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#HARGEISA
በሶማሊላንድ ሁለተኛ (2) ሰው በኮቪድ-19 መሞቱ ሪፖርት ተደረገ ፤ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው ግለሰብ የሀርጌሳ ነዋሪ ሲሆኑ ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,382 ላቦራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,382 ላቦራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአ/አ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 4 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 5 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 6 - የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 7 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።
ታማሚ 8 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታ አፋር (የተገኘው አ/አ) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 9 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 10 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 11 - የ53 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአ/አ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።
ታማሚ 12 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 13 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 14 - የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 15 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 16 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 17 - የ41 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከሱማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ሶስት (93) ደርሷል።

#COVID19
በአዲስ አበባ ከመጭው ዓርብ (ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም) ጀምሮ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን #በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ሊደረግ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳለው ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠቀም ሲንቀሳቀሱ ጭምብሎችን መጠቀም ይኖርባቸዋል ብሏል። ባለስልጣኑ ተሳፋሪዎች ያለ አፍ መሸፈኛ ጭምብል ታክሲ መጠቀም አይችሉም ሲል ገልጿል - #FBC

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 26,517
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,382
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 17
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 63
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 2
• አጠቃላይ ያገገሙ - 93
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 162
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 26,517
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,382
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 17
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 63
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 2
• አጠቃላይ ያገገሙ - 93
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 162
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለግብር ከፋዮች የግብር ዕዳ ስረዛ ተደረገ!
(ኤፍ ቢ ሲ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያመጣውን ተጽዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት ለግብር ከፋዮች የግብር ዕዳ ስረዛ አደረገ።
እዳው የተሰረዘላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዚያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምህረት እንዲደረግላቸው መወሰኑን ተከትሎ ነው።
በዚህ መሰረት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ እዳ ያለባቸው እንዲሁም ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም ሂሳባቸውን የሚዘጉ የውሳኔው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ፍሬ ግብር ፣ መቀጫ እና ወለድ ያለባቸው ተቋማት ዕዳ ሙሉ ለሙሉ መሰረዙም ነው የተገለጸው።
ከዚህ ባለፈም ከ 2008 እስከ 2011 ዓ.ም ዕዳ ያለባቸው ተቋማት 25 በመቶ በአንድ ወር ለሚከፍሉ ወለድ እና እንደሚነሠሳላቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በአንድ ወር ሙሉ በሙሉ እዳቸውን ለሚከፍሉ ደግሞ 10 በመቶ ከፍሬ ግብሩ ተቀናሽ የሚደረግላቸው ሲሆን ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው የተባለው።

የኮቪድ-19 ተማራማሪው አሜሪካ ውስጥ ተገደሉ!
(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)
በኮሮና ቫይረስ ላይ ምርምር ሲያደርጉ የነበሩት እና አዲስ ግኝቶችን ለማውጣት ጫፍ ላይ ደርሰው የነበሩት ተመራማሪ መገደላቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ተመራማሪ የነበሩት ዶ/ር ቢንግ ሊኡ፤ በፔንሲልቫኒያ በሰሜን ፒትስበርግ ሮስ ታውንሽፕ ሕይወታቸው አልፎ እንደተገኙ ባለፈው ቅዳሜ የአካባቢው የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
ፖሊስ የተማራማሪው አስክሬን ከተገኘበት ቦታ አንድ ማይል ርቀት ላይ ወዲያውኑ የሁለተኛውን ሟች ሃኦ ጉ አስክሬን መኪና ውስጥ ማግኘቱን ገልጿል፡፡
መርማሪዎች ለኤንቢሲ እንዳሉት ሃኦ ጉ ፣ ዶክተር ሊውን ገድለው ከዚያም ራሳቸው ላይ በመተኮስ ሕይወታቸው ሳይልፍ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
የህክምና ትምህርት ቤቱ በድረገጹ ላይ ባስነበበው መግለጫ ዶ/ር ሊኡ በሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው የተከታታሉ ሲሆን ለሳይንሱ ዘርፍ የተለየ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጎበዝ ተመራማሪ ነበሩ ሲል ገልጿቸዋል፡፡
አክሎም ዶክተር ሊኡ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጀርባ ያለውን ዑደት ለመረዳት የሚያስችል ወሳኝ የሆነ የምርምር ውጤት ለማግኘት #ጫፍ ላይ ደርሰው ነበር ብሏል፡፡

#DrLaiTadesse
ኅብረተሰቡ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር #እየጨመረ መምጣቱን ከግምት በማስገባት አሁንም የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ።
ባለፉት 24 ሠዓታት ብቻ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ያሳዘናቸው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ፤ ''በዚህም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግባለች'' ብለዋል።
እስከሁን የተመዘገቡትና የተገለጹት ቁጥሮች ትክክለኛ አሃዝ እንደማያሳይ ገልጸው ፤ "የምናውቀው የመረመርነውን ብቻ ነው፣ የመረመርነው ደግሞ ትንሽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ስለዚህ ወረርሽኙን መርሳትና መዘናጋት እንደማይገባ እና ኅብረተሰቡም ቁጥሩ "ያነሰው በሽታው እኛ ጋር ስላልመጣ ወይንም ስለማይመጣ" እንዳልሆነ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በኬንያ እና በሱዳን በመጀመሪያዎቹ ቀናት ትንሽ ቁጥር ማስመዝገባቸውን ተከትሎ መዘነጋት መታየቱን አስታውሰው ፤ ''ዋጋ አስከፍሏቸዋል'' ብለዋል።
ሕዝቡም ከጎረቤት አገሮች መዘናጋት ትልቅ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል በመማር የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።
"ትክክልኛ ትምህርትና እርምጃ ለመውሰድ ፣ በብዙ ቁጥር መያዝ ፣ በብዙ ቁጥር መሞት የለብንም" ያሉት ሚኒስትሯ ፤ ያለው #ብቸኛ አማራጭ #መጠንቀቅ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#MutahiKagwe
በኬንያ በአንድ ቀን 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት አርባ ሰባት (47) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 581 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 8 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 190 ደርሷል።
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26 ደርሷል።

TIKVAH-ETHIOPIA
አሳዛኝ ዜና! የአዳማ ጀነራል ሆስፒታል እና የህክምና ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ባለቤት የሆኑት አቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል፡፡ አቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ ብዙዎች በማይደፍሩት የጤና ዘርፍ ላይ ኃብታቸውን አውጥተው በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሚባለውን ሆስፒታል ሰርተው ለህብረተሰቡ እስካሁን ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!
(በጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
የአዳማ ጄኔራል ሜዲካል ኮሌጅ እና ሆስፒታል ባለቤት አቶ ከቢር ሁሴን ዋቆ የቀብር ስነ ስረዓት በዛሬው ዕለት ተፈፀመ።
አቶ ከቢር ሁሴን ባጋጠማቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ትናንት ነው በ73 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቀብር ሥነ ሥረዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
አቶ ከቢር ሁሴን በኦሮሚያ ክልል ስማቸው ጎልቶ ከሚነሳ ባለሃብቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ።

ስፔን ?
በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር አሳይቷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት 244 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር 25,857 ደርሷል።
በሌላ በኩል በአንድ ቀን 3,121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 253,652 ከፍ ብሏል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ነገ እንዲህ ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይገመት ፤ የስርጭትና የመስፋፋት ፍጥነቱ እጅግ አደገኛ ነውና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!

በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!
በደቡብ ሱዳን 162 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 58 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን 162 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 58 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 74 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!
የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 74 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት አድርጓል። 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 10 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 852 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 49 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 80 ሰዎች ማገገማቸዉ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 74 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት አድርጓል። 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 10 ሰዎች ደግሞ በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 852 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 49 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 80 ሰዎች ማገገማቸዉ ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ተጨማሪ 38 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!
ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 38 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 873 ደርሷል።
በሌላ በኩል አስራ ሁለት (12) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 87 ደርሷል።
በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 39 ከፍ ብሏል ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 38 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 873 ደርሷል።
በሌላ በኩል አስራ ሁለት (12) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 87 ደርሷል።
በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 39 ከፍ ብሏል ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል!
በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። በተጨማሪ 160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,124 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት ተጨማሪ 10 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 755 መድረሳቸው ተገልጿል።

በማዳጋስካር 7 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር ዛሬው ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 158 ደርሷል።
በማዳጋስካር እስካሁን ድረስ ምንም ሞት ያልተመዘገበ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 158 ሰዎች መካከል 101 የመሆኑት ማገገማቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር ዛሬው ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 158 ደርሷል።
በማዳጋስካር እስካሁን ድረስ ምንም ሞት ያልተመዘገበ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 158 ሰዎች መካከል 101 የመሆኑት ማገገማቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ! በደቡብ ሱዳን 162 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ስድስት (6) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 58 ደርሷል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አይ ሬድዮ በሰበር ዜናው አሳውቋል።
ከአስራ ስድስቱም (16) የደቡብ ሱዳን ዜጎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አንዳንዶቹ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው እንደሆነም ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል ፤ ሁለት (2) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አይ ሬድዮ በሰበር ዜናው አሳውቋል።
ከአስራ ስድስቱም (16) የደቡብ ሱዳን ዜጎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አንዳንዶቹ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው እንደሆነም ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል ፤ ሁለት (2) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVIDO_ORGANICS
ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት ሰዎች ለኮቪድ-19 ህክምና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ ባህላዊ መድሃኒቶችን እንዳይጠቀሙ ቢያስጠነቅቅም የማዳጋስካርን መድሃኒት ፈላጊ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው።
ደቡብ ሱዳን በማዳጋስካር ፕሬዘዳንት አንድሪ ራጆሊና የተዋወቀውን የኮሮና ቫይረስ ባህላዊ መድሃኒትን ወደ ሀገሯ ለማስገባት ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል።
በሌላ በኩል ማዳጋስካር ከሳምንታት በፊት አገኘሁት ብላ ባሳወቀችው የኮቪድ-19 መድሃኒት ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ንግግር መጀመሩም ተሰምቷል።