በትግራይ ክልል ከነገ ሚያዚያ 17/2012 ዓ/ም ጀምሮ የተነሱት ክልከላዎችን በሚመለከት የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ለትግራይ ቴሌቪዥን ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ፦
- በአንድ ወረዳ ውስጥ የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ተፈቅዷል። በአንድ ወረዳ ውስጥ የገበያ እንቅስቃሴ ተፈቅዷል።
- በአንድ ወረዳ ውስጥ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተፈቅዷል። ሹፎሮች እና ረዳቶች አስፈላጊውን ጥንቀቄ ማድረግ አለባቸው፣ ማስክ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ የመቀመጫ ወንበሮችን ማፅዳት አለባቸው፤ መኪናው መጫን ከሚቻለው ግማሽ ሰው ብቻ መሆን አለበት ፣ ለተሳፋሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ማቅረብ አለባቸው።
- ትንንሽ ጠላ ቤቶች፣ ጠጅ ቤቶች በተዘጋጁ እቃዎች (takeaway) #ብቻ መሸጥ ይችላሉ።
- ኮፊ ሀውስ፣ ካፌ፣ ሻይ ቤቶች፣ ጭማቂ ቤቶች፣ የወንድና የሴት ፀጉር ቤቶች በጥንቃቄ እንዲከፈቱ። ከጥንቃቄዎች መካከል ፦ ተጠቃሚዎች በአንድ ወንበር እና ጠረጴዛ እንዲገለገሉ ማድረግ ፣ በተጠቃሚዎች መካከል የ2 ሜትር ርቀት እንዲኖር፣ የእጅ መታጠቢያዎች፣ ሳኒታይዘሮችን እንዲያቀርቡ፣ አገልግሎት ሰጪዎች የፊት ማስክና ጓንት እንዲጠቀሙ...የሚሉት ይገኙበታል።
- አልኮል ማከፋፈያዎች ለሆቴሎች ፣ ለምግብ ቤቶች ፣ ለግሮሰሪዎች፣ ለሱፐር ማርኬቶች እና በግል ገዝተው ወደቤት ለሚሄዱ ሰዎች መሸጥ ይችላሉ።
- የመንግስት ተቋማት ተከፍተው ሰራተኞች አገልግሎት እዲሰጡ፤ ስራዎች ሲሰሩ ግን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በተጠበቀ መልኩ እንዲሆን ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኑሮ መመሪያችሁ እንደሚከተለው ይሁን:-
(በዶክተር ኤፍሬም ሓጎስ)
- በዙርያዮ ያለው ሰው በሙሉ ፣ በመንገዴ የማገኘው ሰው በሙሉ ፣ ምልክት ኖረውም አልኖረውም በደሙ ቫይረሱ ሊኖርበት ይችላልና ፣ እንዳያስተላልፍብኝ ፣ እራሴንም በዙርያዮ ያሉ ሰዎችንም እንዳልጎዳ በምችለው ሁሉ እጠነቀቃለሁ፣
- እኔም ስኖር በማንኛውም ሰዐት ቫይረሱ ሊጋባብኝ ስለሚችል፣ ምልክት ኖረኝም አልኖረኝም ቫይረሱ በደሜ ሊገኝ የሚችልበት ዕድል ስላለ፣ በዚሁም ወደ ሌሎች ላስተላልፍና ሌሎችን ልጎዳ ስለምችል እጠነቀቃለሁ።
አኗኗሬ፣ መረዳቴ ማንኛውም በመንገዴ የማገኘው ሰው ሁሉ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆን እንደሚችል፣ እኔም እራሱ የቫይረሱ ተሸካሚ ልሆን እንደምችል ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፣ ከዚሁ እሳቤ የሚቀደዳ፣ በዚሁ እሳቤ የሚከወን ነው።
እኛ የጤና ባለሞያዎች ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ደህንነት ሁሌም በሆስፒታል እንገኛለን። እርስዎ ደሞ ከቤት ባለመውጣት የእኛን ደህንነት ይጠብቁ።

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል!
ካፒቴን ተሾመ መለሰ ይባላሉ ፤ ካፒቴኑ ተወልደው ያደጉት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ጨለንቆ ከተማ ሲሆን የጨለንቆና አካባቢዋ ተወላጆች ከዚህ ቀደም Chelenko Development Alliance (CDA) በሚል ተሰባስበው የተለያዪ ድጋፎችን ለከተማቸው እንዲሁም ለአካባቢያቸው ሲያደርጉ መቆየታቸውን ነግረውናል፡፡
በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኮሮና ቫይረስ [ካቪድ-19] ወረርሺኝ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እንዳያደርስ ህዝብና መንግስት የሚያደርጉትን መጠነ-ሰፊ ርብርብ ከማገዝ አኳያ እነሱም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት የጨለንቆና አካባቢዋን ተወላጆች በማስተባበር የኮሮናን ወረርሺኝ ለመከላከል የሚያገለግሉ የተለያዪ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጨለንቆ መጀመሪያ ደረጃ ሆሰፒታል አስረክበዋል።
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አብዱልቃድር ፣ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና የሜታ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የተወሰኑ የማህበረሰቡ አካላት በተገኙበት በዋነኝነት ይህን በሽታ ለመከላከል በፊት መስመር ተሰልፈዉ ለሚዋደቁት የህክምና ባለሞያዎችን ለማገዝ የሚውሉትን የህክምና ቁሳቁሶች የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርና የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተረክበዋል።
(ካፕቴን ተሾመ መለሰ)

#WeyzeroLemlemBezabeh
ከድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ፦
- ከጅቡቲ ተመላሾችን ከድንበር ጀምሮ በተደራጀ መልኩ እንዲሰባሰቡና ወደለይቶ ማቆያ ማዕከላት ገብተው የጤንነታቸው ሁኔታ ተረጋግጦ ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ ለመስቻል ስራዎች እየትሰሩ ነው።
- በአሁን ሰዓት ከ700 በላይ ከጅቡቲ ተመላሾች በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ገብተው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።
- ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተገለፀውና በለይቶ ህክምና ተቋም ያሉ 6 ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
- መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ፦ የእናቶችና ህፃናት ጤና፣ ክትባት፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቋሚ የጤና ክትትል የሚደልጉ እንደ ስኳር፣ ደምግፊት ፣ ኤች አይቪና የመሳሰሉት ለኮሮና ለይቶ ማቆያና ህክምና ከተመረጡ ተቋማት ውጭ በሌሎች ተቋማት በመደበኛነት የሚሰጡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ተጠይቋል።
- የደም እጥረትን ለመቅረፍ የደም ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1019 የላብራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 122 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 2 - የ39 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታ ሰበታ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።
ታማሚ 3 - የ49 ዓመት ቻይናዊት የመኖሪያ ቦታ ሰበታ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።
ታማሚ 4 - የ59 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታ ሰበታ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።
ታማሚ 5 - የ28 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታ ሰበታ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች 29 ደርሰዋል!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ አራት ሰዎች (ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ሀያ ዘጠኝ (29) ደርሰዋል።

#UhuruKenyatta
በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 343 ደረሱ!
ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፤ በኬንያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 343 መድረሱን አሳውቀዋል። ትላንት 336 እንደነበር ይታወሳል።
በሌላ በኩል ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ዘጠና ስምንት (98) መድረሳቸውን ፕሬዘዳንቱ በመግለጫቸው ተናግረዋል፤ በትላንትናው ሪፖርት ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 94 እንደነበሩ አይዘነጋም።

በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,008 ደረሱ!
ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል 43 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 373 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል 43 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 373 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
- በኳታር ተጨማሪ 833 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋግጧል (ይህ እስካሁን በሀገሪቱ ውስጥ ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች ከፍተኛው ነው) ፤በኳታር አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 9,358 ደርሷል።
- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1,134 በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 76 ተጨማሪ ሰዎች ሞተዋል።
- በቤልጂየም ባለፉት 24 ሰዓት 1,032 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 241 ሰዎች ሞተዋል።
- የዓለም ጤና ድርጅት ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያገገሙ ሰዎች ድጋሚ በቫይረሱ ስላለመያዛቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንደሌለ አሳውቋል።
- በሲንጋፖር በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 618 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- ደቡብ ኮሪያ ለ7ኛ ተከታታይ ቀን ከ15 በታች ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች፤ ባለፈት 24 ሰዓት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 10 ናቸው፤ አራቱ ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ተሰምቷል።
- ቻይና 12 ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች፤ 11 ከውጭ የገቡ ናቸው።
- በሳዑዲ አረቢያ ተጨማሪ 9 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 136 ደርሷል።
- በስፔን የሟቾች ቁጥር 22,905 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 381 ሰዎች ሞተዋል።
- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ925,000 በልጧል፤ ከ52,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ በ110,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።
- በማዳጋስካር አንድ ተጨማሪ ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 123 ደርሰዋል። በሌላ በኩል አንድ ተጨማሪ ሰው አገግሟል።
- ኬንያ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ጥላ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ለቀጣዮቹ 3 ሳምንታት አራዝማለች።
- በመላው ዓለም ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ810,000 በልጠዋል።
@tikvahethiopia

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 12,688
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,019
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 88
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 4
• አጠቃላይ ያገገሙ - 29
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 122
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 12,688
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,019
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 5
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 88
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 4
• አጠቃላይ ያገገሙ - 29
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 122
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump #DrAbiyAhemed
“ከኢትዮጵያው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ተወያይተናል ፤ ኢትዮጵያ #ቬንቲሌተሮች (የመተንፈሻ መሳሪያ) ያስፈልጓታል አሜሪካም ድጋፍ ለማድረግ በጥሩ አቋም ላይ ትገኛለች፤ ይህንንም እናደርጋለን!” - ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ
.
.
"ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኢትዮ - አሜሪካንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ አበረታች የስልክ ውይይት አድርገናል፡፡ የCOVID-19 መከላከል እና ቅነሳ ጥረቶች እንዲሁም በበረሃ አንበጣ ቁጥጥር ላይ የሚደረገውን ድጋፍ ለማድነቅ እወዳለሁ፡፡" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

በሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 213 ደረሱ!
በሱዳን ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 213 ደርሷል። በተጨማሪ አንድ ሰው መሞቱን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 213 ደርሷል። በተጨማሪ አንድ ሰው መሞቱን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 390 ደረሱ!
በሱማሊያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 62 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 390 ደርሷል።
በተጨማሪ ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18 ደርሷል። በሌላ በኩል ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ብዛት 10 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 62 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 390 ደርሷል።
በተጨማሪ ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18 ደርሷል። በሌላ በኩል ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ብዛት 10 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦
- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ቀንሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 415 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በተጨማሪ 2,357 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- ባለፉት 24 ሰዓት በፈረንሳይ 369 ሰዎች ሲሞቱ 1,660 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 813 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 20,319 ደርሷል።
- በግብፅ የሟቾች ቁጥር 307 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ13 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል፤ ከዚህ በተጨማሪ 227 ሰዎች በቫይሩ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 4,319 ደርሷል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ201,501 ደርሷል፤ 824,905 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 2,891,073 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

#BGIEthiopia #FightCOVID19
የፌዴራል ስፓርት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደረሽን እና እግር ኳስ ፌደረሽን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚደግፍ የአንድ (1) ወር የምገባ ፕሮግራም ዛሬ አስጀምረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌዴራል ስፓርት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደረሽን እና እግር ኳስ ፌደረሽን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚደግፍ የአንድ (1) ወር የምገባ ፕሮግራም ዛሬ አስጀምረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በክትባት ፍለጋው ላይ ዓለም አቀፍ ርብርብ ሊደረግ ይገባል" - አንቶኒዮ ጉተሬዝ (የተመድ ዋና ፀሃፊ)
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ክትባት ፍለጋው ላይ በሚደረግ ጥረት አለማቀፍ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
«በመላው ዓለም መንግሥታት በአንድ በኩል ኢኮኖሚያቸውን ከውድቀት ለመታደግ ብርቱ ትግል ያደርጋሉ ፤ በሌላ በኩል በወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ከ2,8 ሚሊዮን በላይ ሆነው ብርቱ ፈተና ከፊት ተጋርጧል» ብሏል ድርጅቱ።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት መዛመት ክትባት ፍለጋው ላይ የሚደረገው ጥረትም የዚያኑ ያህል ፈጣን ካልሆነ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አስጠንቅቀዋል። በክትባት ፍለጋው ላይ ዓለም አቀፍ ርብርብ ሊደረግበት ይገባልም ብለዋል።
እስካሁን እየተደረጉ የነበሩ ጥረቶች ከተስፋ የዘለለ ተጨባጭ ውጤት አልተገኘም ያሉት ዋና ጸሐፊው ምናልባትም ረዘም ያለ ጊዜ ሊጠይቅ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
'ከእስከ ዛሬው ሁሉ የሰው ልጅ የተለየ ጠላት ነው የገጠመው' ያሉት አንቶኒዮ ጉተሬዝ ክትባቱን ለማግኘት በሚደረግ ጥረት የአለም መሪዎች ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት መስራት ይጠበቅባቸዋል በማለት አሳስበዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

በሩዋንዳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 183 ደርሱ!
በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 1,275 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባት (7) ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሌላ በኩል አንድ ተጨማሪ ሰው ማገገሙን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 88 ደርሰዋል። በሩዋንዳ እስካሁን ሞት አልተመዘገበም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 1,275 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባት (7) ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሌላ በኩል አንድ ተጨማሪ ሰው ማገገሙን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 88 ደርሰዋል። በሩዋንዳ እስካሁን ሞት አልተመዘገበም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ምንም ነገር #እናቶችን ከሞት ለመታደግ የሚያቆመን የለም!" - ባህር ዳር ደም ባንክ
በባህር ዳር ከተማ የደም ልገሳ እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ ብቻ 255 የባህር ዳር ነዋሪዎች ደማቸውን ለወገናቸው ለግሰዋል።
ደም ከለገሱ መካከል ፦
- የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዋች
- ጥበበ ግዮን ሆስፒታል የጤና ባለሙያዋች
- አፊላስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዋች
- ኢዜማ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች
- ሮትራክት ባህር ዳር
- የባህር ዳር lion security አባላት
- ዶ/ር ሙሉነሽ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ
- ዶ/ር ፍሬው የባህር ዳር ዮንቨርስቲ ፕሬዘዳንት ከእነ ሴት ልጃቸው
- አቶ ክንድይሁን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ይገኙበታል።
ከባህር ዳር ደም ባንክ በተላከልን መልዕክት ይህ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ነገም ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ይቀጥላል። ይህን መልዕክት የምታነቡ የባህር ዳር ነዋሪዎች ደም በመለገስ የወገናችሁን ህይወት እንድትታደጉ ጥሪ ቀርቦላችኃል።

"ከቁጥር እዳንጎድል ቁጥሩን ሳይሆን ቫይረሱን በእውቀት እንቆጣጠረው"
(በዶክተር ያቤፅ ከበደ-የህብረተሰብ ጤና ተመራማሪ)
ከሠሞኑን እየታየ ያለው አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው ግምት ምንድን ነው ?
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቫይረሱን የመመርመር አቅሟን እየጨመረች ሲሆን ሠሞኑን እየታየ ካለው በቫይረሱ የተያዙ ሰዋች ቁጥር መቀነስ ህዝቡን እንዳያዘናጋ የሚያሰጋ ነው።
የቫይረሱ አሰራር ገና እርግጠኛ ባልሆንበት ጊዜ፣ ባህሪውን በሚለዋውጥበት ወቅት፤ ህዝባችን የተያዘውን ሰው ቁጥር ሳይሆን ገና እርግጠኛ የሆነ ክትባትም ሆነ መድኃኒት ያልተገኘለትን የኮሮና ቫይረስን በአግባቡ መጠንቀቅና እዲሁም በትጋት ሲያደርገው የነበረውን መከላከል እዳያቆም እላለሁ።