#FightCOVID19
- የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሜድሮክ ኢትዮዽያ ኢትዮ አግሪሴፍ የተረከባቸውን 45 የደለቡ በሬዎች 'ማዕድ ማጋራት' በሚል ለአርባ ሰፈሮች በቄራዎች ድርጅት ጤናማነቱን ያረጋገጥ እርድ ተከናውኖ እንድሰራጭ በቄራዎች ድርጅት ግቢ ርክክብ ተደርጎል። የስጋ ስርጭቱን የአ.አ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይድ እንድሪስ እና ከአርባ ሰፈር በጎ ፈቃደኞች ወጣቶች ጋር በመተባበር ለመስራት ቃል ገብተዋል።
- አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል አስረክባለች።
- ራይድ #RIDE የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት በተለያዩ የህክምና ተቋማት እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እንዲሆን 50,000 የአፍ መሸፈኛ ማስኮችን ለኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር አስረክቧል።
- ጋስት ሶላር መካኒክስ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የያዛቸው ታካሚዎች አተነፋፈሳቸውን የሚያግዝ ቱቦ ወደ አየር ቧንቧቸው ሲገባ እንደ መከላከያ የሚያግዝ መሳሪያ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እገዛ አድርጓል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

አጫጭር መረጃዎች ፦
- ሳዑዲ አረቢያ ባለፉት 24 ሰዓት 1,132 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ኬዞች ከፍተኛው ነው። በሳዑዲ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 8,274 ናቸው።
- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1,374 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ በ26 ቀን የተመዘገበ ዝቅተኛው ኬዝ ነው። እንዲሁም 73 ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል፤ በ38 ቀናት የተመዘገበ ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።
- በስፔን የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ May 9 ተራዝሟል።
- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት የ642 ሰዎች ሞት ተምዝግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 19,323 ደርሷል።
- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ38,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ728,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
- በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 712 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 144 ደርሰዋል። በሌላ በኩል ተጨማሪ 4 ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 69 ደርሰዋል።
- ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ 25 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 19 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 135 ደርሰዋል። በተጨማሪ ሁለት (2) ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓት ሞተዋል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች 2,313,897 ደርሷል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ590,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ159,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሱማሊያ ?
የመመርመር አቅሟ ትንሽ በሆነው በጎረቤታችን ሱማሊያ ከትላንት በስቲያ 47 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት በተደረገ 25 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። አሁን አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 135 ደርሰዋል።

#ETHIOPIA
ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባት የተረጋገጠው የጅማ ዞን ሊሙኮሳ ወረዳ ነዋሪ ከሆነችው ግለሰብ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እያሰባሰበ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።
እስካሁን 39 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን እና የቅርብ ግንኙነት ያላቸው የ12 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጣሂር ኢብራሂም ተናግረዋል።
በሊሙ ኮሳ ወረዳ የወለኬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው የ20 ዓመት ወጣት የህመሙን ምልክት ካየች ከአንድ ወር ያላነሰ ጊዜ እንደሆነ እና ለህክምና እና ለጠበል ወደተለያዩ አካባቢዎች መንቀሳቀሷን አቶ ጣሂር ተናግረዋል።
ከእነዚህ ውስጥም ለ19 ቀናት ያህል በጢስ አባይ ጠበል ላይ መቆየቷን ይናገራሉ። በቫይረሱ መያዟ ከተረጋገጠባት ወጣት መኖሪያ ቀበሌና አካባቢው እንቅስቃሴዎች መገደባቸውን አቶ ጣሂር ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Baga ayyaana Du'aa Ka'u Kiristosin nagaan gessan!
እንኳዕ ንበዓል ትንሳኤ ኣብፀሓኩም!
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ በየትኛውም የዓለም ክፍል የምትገኙ የቲክቫህ አባላት እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሳብ እንዲሆን እንመኛለን።
የዘንድሮው የትንሳኤ በዓል በፈተና ውስጥ ሆነን እያከበርን እንደሆነ ይታወቃልና በዓሉን ስታከብሩ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ችላ እንዳትሉ ለማስታወስ እንወዳለን!
ረጅም እድሜና ጤናን እንመኝላችኃለን!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ 1 ሺህ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ያለውን የሚሊኒየም አዳራሽ ማዕከል ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንና የተከናወነውን ስራ መገምገማቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
ሚሌኒየም አዳራሽ ለድንገተኛ ወረርሽኝ ምለሽ መስጠት በሚችል ትልቅ ሆስፒታል ደረጃ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት 360 አልጋዎች ዝግጀቱ ሆነዋል፤ ቀሪዎቹም አልጋዎች በሳምንት ውስጥ ዝግጁ እንደሚሆኑም ነው የተመለከተው።
በህክምና ማዕከሉ 40 የፅኑ ህክምና መስጫ አልጋዎች እና 60 የማገገሚያ አልጋዎችም የኖሩታል። የህክምና ማዕከሉ 700 የህክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ ሰራተኞች እንደሚኖሩትም ነው የተገለፀው።

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 667 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ62 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ፤ ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።
ታማሚ 2 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ።
ታማሚ 3 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ አረቢያ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,557
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 667
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 87
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 16
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 108
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,557
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 667
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 87
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 16
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 108
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መልካም በዓል!
በዓሉን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከል በስራ እያሳለፋችሁ የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
PHOTO : EPHI

#DrMercyMwangangi
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት 1,330 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 270 ደርሰዋል።
ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት 8 ኬዞች ሰባቱ (7) የከንያ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው (1) የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት (7) ተጨማሪ ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 67 ደርሰዋል።
እንዲሁም ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች በመሞታቸው የሟቾች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል።

#Djibouti
የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ለሁለተኛ ቀን የ24 ሰዓት የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት እስካሁን ይፋ አላደረገም። ይፋ የሚደረግ ከሆነ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ትላንትም የ24 ሰዓት የላብራቶሪ ውጤት ይፋ እንዳልተደረገ የምታስታውሱት ነው።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 596 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። የሟቾች ቁጥር ከትላንትናው መቀነስ አሳይቷል። በሌላ በኩል 5,850 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በመላው ዓለም ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ600,000 በልጧል።
- በUAE ባለፉት 24 ሰዓት 479 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ቁጥሩ በሀገሪቱ እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,781 ደርሷል።
- በኢራን በአንድ ቀን 1,343 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተሰምቷል። ባለፉት 28 ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው።
- በስፔን የ24 ሰዓት ሟቾች ቁጥር 410 ሆኖ ተመዝግቧል።
- በሩሲያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 42,583 ደርሰዋል። በ24 ሰዓት 6,060 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 361 ደርሷል።
- በዝምባብዌ የእንቅስቃሴ ገደብ በሁለት (2) ሳምንት እንዲራዘም ተደርጓል።
- በሞሮኮ የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ May 20 ተራዝሟል።
- በግብፅ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ 3,000 በልጧል።
- በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ3,000 በልጧል።

#COVID19
በደቡብ ክልል የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል በተያዘው አቅጣጫ መሰረት የቤት ለቤት ልየታ ስራ መጀመሩን የክልሉ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት የቤት ለቤት ልየታ ስራው የተጀመረው ምልክት ያሳየ ሰውን ብቻ በመመርመር የበሽታውን ስርጭት መቆጣጠር ስለማይቻል ነው።
እናም የቤት ለቤት ልየታ ስራው በክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ቀበሌዎች ይከናወናል ነው ያሉት።
በሽታው ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተሉ አስቀድሞ የቤት ለቤት ልየታ ስራውን በማከናወን በሙቀት ልኬትና በመጠይቅ ምልክቱን ያሳዩ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ይደረጋልም ብለዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ግለሰቧ ሀገር አቀፍ ኳራንቲን ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ከካናዳ ከ29 ቀን በፊት ነው ወደኢትዮጵያ የተመለሱት። በአሁን ሰዓት ደቡብ ክልል ዱራሜ ከተማ ነው ነዋሪነታቸው።
በወቅቱ ከአንድ ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው /በቫይረሱ መያዛቸው/ ካልታወቀ ወንድማቸው ጋር ንክኪ ነበራቸው። ወደሀገር ከተመለሱ ከ27 ቀን በኃላም ናሙናቸው ተወስዶ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
የግለሰቧ ወንድም እህታቸውን ለመቀበል ነበር ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ መጥተው የነበረው። መጋቢት 26 ህመም ሲሰማቸው ወደ ጤና ተቋም ይሄደሉ በወቅቱ ምንም ምልክት ያልነባራቸው በመሆኑ ወደቤታቸው ይመለሳሉ።
የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል ባለማሳየቱ ሚያዚያ 1 በድጋሚ ወደጤና ተቋም ተመልሰው ምርመራ ሲያደርጉ የኮሮና ቫይረስ ምልክት በማሳየታቸው ለብቻቸው እንዲቆዩ ተደርጎ ምርመራ ሲደረግላቸው በሽታው ተገኝቶባቸዋል።
ከእኚህ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ግለሰቦች የመለየት ስራ ሲሰራ ከካናዳ የተመለሱት እና አሁን ዱራሜ የሚገኙት እህታቸው አንዷ እንደሆኑ ለደቡብ ክልል ጥቆማ ይደርሳል።
የግለሰቧ ናሙና ለደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ተልኮ ምርመራ የተደረገ ሲሆን የምርመራ ውጤቱ ከቫይረሱ #ነፃ መሆናቸውን አረጋግጧል።

#BREAKING
ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 658 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 114 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 846 ደርሷል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 26 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 102 ደርሷል።