TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተላከ!

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከአጋር አካላት በድጋፍ ያገኘውን 16 ሚሊየን ብር የሚሆን የምግብ፣ አልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለተለያዩ ተቋማትና በችግር ውስጥ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት AWSAD ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያ ማእከል ፤ ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር፤ ወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ህጻናት ማቆያና ተሀድሶ ተቋም እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከላየንስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ እና በስሩ ከሚገኘው አዱሊጣ ኮንፈረንስና ስፓ ሪዞርት በተላከልን መልዕክት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት እየተደረገ ለሚገኘው ጥረት 3,000,000 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀውልናል።

- ላንየስን ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለኮቪድ-19 ብሄራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ 2,000,000 ብር

- አዱሊጣ ኮንፈረንስና ስፓ ሪዞርት ለኦሮሚያ ክልል የኮቪድ-19 ድጋፍ አሰበባሳቢ 1,000,000 ብር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300 ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል።

በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል።

ምንጭ ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ፦

በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።

ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።

በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።

መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።

በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት በፈረንሳይ 753 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17,920 ደርሷል። በተጨማሪ 17,164 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 165,027 ደርሷል።

- በኒውዮርክ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ MAY 15 ተራዝሟል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በቤልጂየም 1,236 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 417 ሰዎች ሞተዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ34,000 በላይ ሆኗል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ670,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በሩዋንዳ 664 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 138 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 6 ተጨማሪ ሰዎች አገግመዋል፤ አጠቅላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦ • በሩዋንዳ 923 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በኬንያ 800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በጅቡቲ 580 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባ ሁለት (72) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። • በኢትዮጵያ 431 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ…
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

• በኬንያ 704 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በሩዋንዳ 664 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በጅቡቲ 494 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ መቶ ሀምሳ ስድስት (156) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 401 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

ይሄም ያልፋል!

'በኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ያስተላለፉት መልዕክት ፦

ኢትዮጵያ-ፋሲካን ዳግማዊ ትንሳኤን እና መጪ ሰርጎችን እንደ በፊት ተሰባስቦ በአንድነት መታደም ባለመቻላችን አንዳንዶቻችን በጣም እንዳዘንን እረዳለሁ።

ዛሬም ሆነ ነገ የመጣብን ክፉ ጠንቅ እስኪያልፍ ራሳችሁን ከአካላዊ መቀራረብ ስላራቃችሁም እናመሰግናለን።

አንዳንድ ወገኖች 'እረ ለፋሲካማ ተራርቀን አይሆንም!' ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሴ ቅልጥ ባለ ጦርነት ውስጥ ጥይት አየር ላይ ከወዲህ ወዲያ እየበረረ ቦምብ እዚህም እዚያ እየፈነዳ እንሰባሰብ አትሉም አይደል?

የጦርነት አውድማው ሆስፒታል ሆነ እንጂ ይሄንንም እንደዛ አስቡት ጦርነት ላይ ነን። እኛ የጤና ባለሙያዎቹ እየተፋለምን ነው። ስለዚህ በቤቶቻችሁ ሆናችሁ በዓሉን በሐሴት አክብሩ። ገበያውም ላይ እንጠንቀቅ አይዞን ይሄም ያልፋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ እስካሁን 100 ትውልደ- ኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።

በአሜሪካ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ- ኢትዮጵያ በሆስፒታል፣ በአረጋዊያን መንከባከቢያና በማይዘጉ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስለሚሠሩ በቀጥታ ተጎጂ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እስካሁን በጣም በተቀናጀ ሁኔታ ይፋዊ ቁጥር ባይገኝም ከእድር፣ ከኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አገልግሎትና ከመሳሰሉት ቦታዎች በተሰባሰበ መረጃ መሰረት 100 ትውልደ- ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የባለቤቴን አስክሬን ሳልቀብር እኔም በኮሮናቫይረስ መያዜ ተነገረኝ " - የሦስት (3) ልጆች እናት ወ/ሮ አበራሽ ኦሮሞ

Fundraiser by Yared Estifanos : ለዮሴፍ ሲቡ ቀብር ማስፈፀሚያና ለቤተሰብ ድጋፍ Memorial Fundraiser
https://www.gofundme.com/f/bkfab?utm_source=customer&utm_medium=copy_link-tip&utm_campaign=p_cp+share-sheet

15 MB (WiFi ተጠቀሙ)

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል!!

ይህ ሁኔታችን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል!!

- በየመነኸሪያው ያለው የሰው መጨናነቅ እና ብዛት እጅግ በጣም የሚያስፈራ ነው። ከስፍራው ካሉ የቤተሰባችን አባላት እንደተነገረን አስተባባሪዎች ወይም ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ የሚየርጉ ሰዎች የሉም። በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል የሚደረግ ጉዞ በእንዲህ ያለ መልኩ መሆኑ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። ሳይረፍድ መፍትሄ ይፈለግለት!

- በጅቡቲ መስመር ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው። በጅቡቲ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከግምት ውስጥ ያስገባ ጥንቃቄ ካልተደረገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

አንዳንድ አካባቢዎች ጭራሽ የቫይረሱ ስርጭት እየተረሳ ነው። በእርግጥ ለበዓል ዝግጅት ያስፈልግ ይሆናል ወደፊት ለሚመጣው ጊዜ አብረን በደስታ እንድናሳልፍ ዛሬ የምንባለውን እናድምጥ!

PHOTO : ADDIS ABABA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋጋ እንዳያስከፍለን!

ይህ ቪድዮ አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ ያለው እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው። ከፍተኛ ጥንቄ ማድረጋችን ለእኛ እና ለቤተሰቦቻችን ጤና ወሳኝ ነው። በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከተሞች የምንሄድ መንገደኞች ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እንዲያስችሉ የላከቻቸው የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል፡፡

የሕክምና ቁሳቁሱ በእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የተገዙ ናቸው፡፡

ድጋፉ የሕክምና ማስኮች፣ የቀዶ ጥገና ጋውኖች፣ የፊት መሸፈኛዎች፣ ሙሉ አካልን የሚሸፍኑ የሕክምና አልባሳት እና ሌሎች ቁሳቁስ ተካተውበታል፡፡

ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 96 ደረሰ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 842 የላቦራቶሪ ምርመራ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ስድስት (96) ደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 96 ደርሰዋል!

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 2 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላትና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 3 - የ52 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባህር ዳር ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 4 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ ቅዳም ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት እየተጣራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በትራንስፖርት አጠቃቀምና በመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰአት ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። 

የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርአቶ አብዲሳ ያደታ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ በመመሪያዉ መሰረት የግል ወይም የቤት ተሸከርካሪዎችን መጠቀም የሚቻለዉ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑት ዛሬ ሚያዚያ 9 ቀን 2012 ዓ ም ሲሆን፤ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ጎዶሎ የሆኑት ደግሞ ነገ ቅዳሜ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል፡፡ 

በተጨማሪም የፌዴራል ሠራተኞች ሥራ መግቢያ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡30 ሲሆን ከስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9፡30 ይሆናል፤ ይህ የሥራ ሰዓት ሽግሽግ ሠራተኞቹ በስራ ሰዓት መካከል የሚያገኙትን የእረፍት ጊዜ አያሳጣቸውም ተብሏል። 

አዉቶቢሶች፣ ታክሲዎች፣ የግል ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች እንዲሁም የአዲስ አበባም ሆነ የኢትዮ-ጅቡቲ የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት በህግ ከተፈቀደላቸዉ የሠው ብዛት 50% ብቻ እንደሚጭኑ ያስገድዳል።

More https://telegra.ph/EPA-04-17

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 1,056 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጣል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 732 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia