TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና ግብዓቶችን እያሰራጨ መሆኑን ገልጿል።

ኤጀንሲው 200 ሺ N 95 የተባለ የአፍ መሸፈኛ ጭንብል፣ ከ3.2 ሚሊዮን በላይ ሰርጂካል ጭንብል እና 1 ሚሊዮን የፊት መከላከያ ፕላስቲክ ማሰራጨቱን ተናግሯል፡፡

21 ሚሊየን ጓንት፣ አልጋዎች፣ የሙቀት መለኪያ ቴርሞ ሜትር እና ለጤና ባለሙያዎች የሚሆን የፊትና የሰውነት መከላከያ ግብዓቶችን ማሰራጨቱን ተሰምቷል።

ሜካኒካል ቬንትሌተርን ጨምሮ ሌሎች የሕክምና መሳሪያዎች ለለይቶ ማቆያዎችና ለሆስፒታሎች መሰራጨታቸው ተነግሯል፡፡

በጤና ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በአስቸኳይ እንዲገዙ የተጠየቀ 700 ሺ ሳኒታይዘር ለክልሎች መሰራጨቱ ተሰምቷል፡፡

ኤጀንሲው ሌሎች የመከላከያ ግብዓቶችን ፣ የህክምና መገልገያዎችን እና መድሃኒቶችን ገዝቶ ለማቅረብ የግዢ ሂደት እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ደረሰ!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 7 ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 92 ደርሰዋል!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 401 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባት (7) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የጀርመን እና የቤልጂየም የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 3 - የ76 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከስዊድን የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።

ታማሚ 4 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከስዊድን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 5 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከጃፓን የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 6 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊትና የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት እንዳላት በመጣራት ላይ ያለ።

ታማሚ 7 - የ61 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,389
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 401
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 7
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 72
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 15
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 92

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WorldHealthOrganization

ከኮሮና ህመም ያገገሙት የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንደ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁሉ ሃገራቸዉ ለዓለም የጤና ድርጅት የሚያደርገዉ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ድጋፍ እንዲቋረጥ ሊጠይቁ ነው።

የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] በተመለከተ በሚገባዉ ጊዜ ተገቢ እርምጃን አልወሰደም በሚል ነዉ ብሪታንያ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚሰጠዉ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠረዉ ድጋፍ እንዲቆም የተጠየቀዉ ሲል «ኤክስፕሬስ» የተሰኘ ድረገፅን ጨምሮ የተለያዩ የብሪታንያ ድረገፆች የዘገቡት።

ትላንት የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተመለከተ ከቻይና የተላለፈዉን «የተዛባ መረጃ» በማሰራጨቱ ተኅዋሲዉም በዓለም ይህን ያህል ሊስፋፋ ችሏል ፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ነገር ባልተከሰተ ነበር ሲሉ ለድርጅቱ የሚሰጡትን ድጋፍ ያቋረጡበትን ዉሳኔ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አንዳንድ አገራት የሚያወጡትን አሃዝ የሚያምን አለ?" - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ትላንት መግለጫ የሰጡት ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ጣሪያን በማለፉ አንዳንድ ግዛቶች በዚህ ወር መከፈት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

ፕሬዘዳንቱ ከአሜሪካ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ግዛቶቹ ስለሚከፈቱበት ሁኔታ ዛሬ ምሽት መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

"አሃዞች እንደሚያሳዩት በመላው አገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው" በማለት ዶናልድ ትራምፕ ገልፀዋል።

አሜሪካ 638,000 ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ30,800 በላይ ነው።

ከሌሎች አገራት በላይ በአሜሪካ በቫይረሱ የሞቱ እና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ለምን ከፍ አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሬዝደንቱ ሲመልሱ፤ "አንዳንድ አገራት የሚያወጡትን አሃዝ የሚያምን አለ?" በማለት #የቻይናን ስም ጠቅሰዋል።

ትራምፕ ጨምረውም ቫይረሱ በቻይዋ ዉሃን ከተማ ሳይሆን ከዉሃን ላብራቶሪ ነው የወጣው ስለሚባለው ያልተረጋገጠ ሪፖርት አሜሪካ ትመለከተዋለች ብለዋል።

የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በቤጂንግ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በዉሃን በሚገኙ ሁለት ላብራቶሪዎች የደህንነት ጉዳይ ያሳስበናል ሲል ሪፖርት ስለማድረጉ ዘግበዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዓለም ጤና ድርጅት የሰዎችን ህይወት ማዳንና የኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲሁም መቆጣጠር ላይ ትኩረት ያደርጋል።" - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም /የWHO ዳይሬክተር/

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በናይጄሪያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አንድ የህክምና ባለሙያ ላይ ህልፈቱ አለፈ። ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን፥ ለህልፈት የተዳረገው ዶክተር  በግሉ ክሊኒክ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘውን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት በመያዙ ነው ተብሏል፡፡

ዶክተሩ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ሌጎስ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ለህክምና ገብቶ የነበረ ሲሆን፥ በወቅቱ ከባድ የህመም ምልክቶች ይታዩበት ነበር ተብሏል።

የናይጄሪያ የህክምና ማህበር ዶ/ር ቹጎቦ ኢመካ አርብ እለት በኮሮና ቫረስ ለህልፈት የተዳረገን ታማሚ በሚያክምበት ወቅት ለቫይረሱ መጋለጡን አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ ያለፈው የ51 ዓመቱ ዶክተር የአስም በሽታ እንደነበረበት የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ የቫንጋርድ ጋዜጣ ማስነበቡ ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ፣ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'አስራን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር' የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ባመጣው የገበያ መቀዛቀዝ ሳቢያ በህንፃው ተከራይተው ለሚገኙ 54 ነጋዴዎች ከሚያዚያ 01 እስከ ሰኔ 30 ድረስ ከቤት ኪራይ ነፃ እንዲሆኑ አድርጓል። በገንዝብ 886,799 ብር ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዴይ አበባ ባቡር መሻገሪያ ያለው 'ይርገዱ ህንፃ' በኮቪድ 19 ምክንያት ስራቸውን ላቆሙ ተከራዮቹ በሙሉ መልሰው ስራ እስከሚጀምሩ ድረስ ምንም አይነት ኪራይ እንደማይቀበል ገልጿል።

በተጨማሪም ስራቸውን ላላቆሙ ተከራዮቹ የስራቸውን መቀዛቀዝ ምክንያት በማድረግ የ50% የኪራይ ቅናሽ አድርጓል።

በተያያዘም በዛው ህንፃ ላይ የሚገኘው 'ጆይ በርገር' እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚውል የ15,000 ብር ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚያበረክት ለቲክቫህ ቃል ገብቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቻይና የጤና ባለሞያዎች አዲስ አበባ ገብተዋል!

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የምታደርገው ጥረት የሚደግፉ የቻይና የጤና ባለሞያዎች አሁን አዲስ አበባ መግባታቸውን ጋዜጠኛ ኤልያስ ገ/ስላሴ በይፋዊ የትዊተር ገፁ አስፍሯል። አዲስ አበባ የገቡት የጤና ባለሙያዎች በቁጥር 12 ይደርሳሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና የላከቻቸው የጤና ባለሙያዎች አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አቀባበል አንዳደረጉላቸው ኤፍ ቢ ሲ አሳውቋል።

የጤና ባለሙያዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ልምዳቸው የሚያጋሩ ሲሆን ፥ የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ቴክኒካል ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ያካፍላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 494 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 156 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጣል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 591 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ የሶስት (3) ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ሰጠ!

(በኢዜአ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በማድረግ ለጋራ መኖሪያ ቤት ደንበኞቹ የሶስት ወራት የብድር መክፈያ እፎይታ ጊዜ መስጠቱን አስታውቋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጤና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጸው፤ ደንበኞች በወረርሽኙ ሳቢያ ብድራቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ መክፈል ይቸገራሉ በሚል የብድር መክፈያ ጊዜ እፎይታ ለመስጠት መወሰኑን ተገልጿል።

በዚህም ከሚያዝያ ወር እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ መክፈል የሚጠበቅባቸው የሶስት ወራት ክፍያ እንደተራዘመላቸው ይፋ ተደርጓል። ለዚህም ደንበኞች ባንኩ ቀርበው ምንም አይነት ውል መፈጸም አይጠበቅባቸውም።

ነገር ግን የብድር መክፈያ ጣሪያው እንደማይራዘም ገልጸው፤ ''ክፍያውን መክፈል አቅም ያላቸው ደንበኞች የወርሃዊ ብድር ክፍያቸውን እንዲከፍሉ ይበረታታሉ'' ተብሏል።

ባንኩ የብድር መክፈያ ጊዜ እፎይታ በማድረጉ 542 ሚሊየን ብር ገንዘብ መሰብሰብ ይችል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በወረርሽኙ ምክንያትም ወደቀጣይ ጊዜ አራዝሟል።

ተጨማሪ በ @TIKVAHETHMAGAZINE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ!

ብድር ወስደው መክፈል ባለመቻላቸው ንብረታቸው በጨረታ ሂደት ላይ ያሉ ደንበኞች ወረርሽኙ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ለጊዜው የጨረታ ሂደቱ እንዲቆም ተወስኗል። የብድር ማራዘሚያ የሚከፈለው የአገልግሎት ክፍያ በእነዚህ ብድሮች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 9 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል!

የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ። ባለፉት 24 ሰዓት 704 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 234 ደርሷል። በተጨማሪ መረጃ በኬንያ የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዩጋንዳ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለጠየቃችሁን የቤተሳባችን አባላት ፦

ትላንት ለሊት የዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር አውጥቶ በነበረው መግለጫ በ24 ሰዓት (ከትላንት በስቲያ መሆኑ ነው) 1,032 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል 551 የሚሆኑት በሀገሪቱ ድንበር አቅራቢያ የሚሰሩ ሹፌሮች ናቸው።

በሀገሪቱ ያሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አሁንም 55 ነው። ዛሬ ምሽት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የሚያወጣውን መግለጫ ተከታትለን መረጃውን እናስቀምጣለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia