TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዳማ የተከናወነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ!

ዛሬ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ አርቲስት ጃምቦ ጆቴ እንዲሁም አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአዳማ ከተማ ሕብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] እንዲከላከል ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት የዜግነት ግዴታቸዉን መወጣታቸውን አቶ አዲሱ አረጋ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

ንግድ ባንክ የብድር እና ወለድ ክፍያ ጊዜን እንዲያራዝምላቸው ሆቴሎች ጥያቄ አቀረቡ!

ከንግድ ባንክ የወሰዱትን ብድርና ወለዱን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስራ በመቆሙ መክፈል እንደማይችሉ የጎንደር ከተማ ሆቴሎች ለንግድ ባንክ በፃፉት ደብዳቤ ገልፀዋል።

ጎሃ ሆቴል፣ ዞብል ሪዞርት፣ ጃንተክ ሆቴል፣ ሔርፋዚ ሪዞርት መጋቢት 17/2012 ዓ/ም ለንግድ ባንክ በፃፉት ደብዳቤ በወረርሽኙ ምክንያት ተይዘው የነበሩ ክፍሎቻቸው በሙሉ መሰረዛቸውን፣ በወረርሽኙ ወቅት ምንም አይነት ገቢ ማግኘት ባይችሉም እስከ 200 ለሚደርሱ ሰራተኞች ደሞዝ እየከፈሉ መሆኑን ገልፀው ዋናውን ብድርና ወለዱን መክፈሉ እንዲቆምላቸው ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በወረርሽኙ በመጠቃቷ ምክንያት በሀገር ደረጃ እንቅስቃሴዎች መታገዳቸው፣ ስብሰባዎች መከልከላቸውና ከቱሪስት ጋር የተያያዘው ስራቸው መቆሙን ጠቅሰው ብድርና ወለዳቸውን እንቅስቃሴ ሲጀመር እንዲከፍሉ ጠይቀዋል።

መንግስት ባወጣው አዋጅ መሰረት ሰራተኞችን መቀነስ እንደማይቻል ከመግለፁም ባሻገር እንቅስቃሴዎች እንዲቋረጡ በመደረጉ የሆቴሎችና የሌሎች ተቋማት ገቢ መጎዳቱ ተገልፆአል።

የጎንደር ከተማ ሆቴሎችም ለሰራተኞች ደሞዝ በመክፈል ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዳይወድቁ በማድረግ ላይ በመሆናቸው በዚህ ወቅት ብድር መክፈለ እንደማይችሉ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 298 ደረሱ!

በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሚያዙ ሰዎች ቁጥር #በፍጥነት እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 498 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸቅ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 298 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ነበሩ ከመባል አሉ መባል ጥሩ'

ለምንዘናጋም ለምን'ዘነጋም ይህ ትልቅ የማንቂያ ደወል ነው! በዓለም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደቅጠል ሲረግፉ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ብንሰማና ብናይም፤ ሉላዊነቱ አቅርቦ እንዲሰማንና እንድንጠነቀቅ ባያደርገንም፤ አሁን ግን አጠገባችን የወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን ተገንዝበን ቀስ በቀስ በራችንን ሳያንኳኳ አብዝተን ልንጠነቀቅ ይገባል።

በማንኛውም የእምነት ትልቁን እና ከምስዕዋት የሚልቀው መታዘዝ መሆኑን ተገንዝበን በዓለም ደረጃ እየተሰዉ የሚያገለግሉንን የጤና ባለሙያዎችን ምክር ተግባራዊ በማድረግ እስትንፋሻችንን እናስቀጥል፡፡

ዛሬም እንደወትሮዉ አጠገባችን በእጃችን ያለውን ውድ ህይወታችንን የሚያስቀጥለውን ራስንና አካላዊ እርቀትን የመጠበቅ፣ እጅን አብዝቶ የመታጠብ፣ ተደጋግመው የሚባሉ ምክሮች አሰልቺ ቢመስሉንም፤ 'ነበሩ ከመባል አሉ መባል ጥሩ'ነውና ግድ የለም እንተግብረው፡፡

በዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ውድ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናት ይሁን፤ የከርሞ ሰው ብሎን የተለመደው የህይወት ዑደታችን እነዲቀጥል እመኛለሁ፡፡

ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ
From TIKVAH FAMILY
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BISHOFTU

ከቡዛየሁ ታደለ ፋውንዴሽንና ከኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግ የተላከ መልዕክት!

ብዙአየው ታደለ ፋውንዴሽን ከኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግ ጋር በመሆን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰብ እና ልዩ እርዳታ ለሚፈልጉ የቢሾፍቱ ከተማ ወገኖቻችን ለተከታታይ 60 ቀናት የሚቆይ የቁርስ፣ የምሳ፤ የእራት ምገባ ፕሮግራም የከተማው ከንቲባ እና የድርጅቶቹ የስራ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ሚያዝያ 5፣ 2012 ዓ.ም ተጀምሯል። ፈጣሪ አለማችንን ፣ ኢትዮጵያን ይጠብቅልን፡፡ ከተባበርን ይህም ያልፋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚሰማ አካል ካለ መፍትሄ ይፈልግ!

ዛሬ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱን የሚገኙት የባንክ ቤት ሰልፎች ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥሉ ፣ ለወረርሽኙ መስፋፋበት በር ከፋች ናቸው።

ይህ አደገኛ ሁኔታ በአስቸኳይ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል። ተገልጋዮችም ከጤና የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና እየተጠነቀቃችሁ።

አንድ ቀን ሞቅ፤ አንድ ቀን ቀዝቀዝ እያደረግን የምንታገለው ይህ ትግል ዋጋ እንዳያስከፍለን በድጋሚ አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ በ24 ሰዓት 11 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው ባለፉት 24 ሰዓት 674 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 8,123
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 674
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 11 (ሁሉም ኬንያውያን)
• አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ - 208
• አጠቃላይ ያገገሙ - 40
• ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ - 1
• አጠቃላይ በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 9

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- በኢኳዶር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች አስክሬን በየመንገዱ እየተጣለ ነው። በኢኳዶሯ ጉዓያኪል ከተማ ነዋሪዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዘመዶቻቸውን ሳይቀብሩ ለቀናት መቆየት ግድ ሆኖባቸዋል። የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ መንግሥት የሚሞቱ ሰዎችን አስክሬን ለመቅብር ከአቅሙ በላይ ሆኗል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 717 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 11,329 ደርሷል። በሌላ በኩል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 88,621 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህ መሃል 4,342 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ የተመዘገቡ ናቸው።

- በስፔን በ24 ሰዓት 517 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል። የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑም ተገልጻል።

- በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ የነበረው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ቢቢሲ አስነብቧል።

- በቻይና በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው ባለፉት 24 ሰዓት 108 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩ ከስድስት ሳምንት በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው ኬዝ ነው።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.8 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ434,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ116,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደም መለገስ ህይወትን መስጠት ነው!

በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ በጎ አድራጎት ማህበራት ባለፉት ሁለት ቀናት ባካሄዱት የደም ልገሳ ዘመቻ ከ300 ዩኒት በላይ ደም መሰብሰቡን የወላይታ ሶዶ ደም ባንክ ጽህፈት ቤት ገልጻል፡፡

“ደም መለገስ ህይወትን መስጠት ነው” በሚል መርህ የደም ልገሳውን ከተሳተፉት በጎ ፍቃደኛ ማህበራት መካከል ጤና አዳም፣ሄብሮን ቻሪቲ፣የወላይታ ወጣቶች ሠላም አምባሳደር፣ የኛ ጉዳይና  የስታዲየም ቃለ-ህይወት ወጣቶች ማህበራት ይገኙበታል።

እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መምህራ እና ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም ነዋሪዎች በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል። 

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን  ተከትሎ ደም ለጋሾች መቀዛቀዝ በማሳየታቸው  ከፍተኛ የሆነ የደም እጥረት መከሰቱን ተገልጿል። 

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚሰማ አካል ካለ መፍትሄ ይፈልግ! ዛሬ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱን የሚገኙት የባንክ ቤት ሰልፎች ህዝቡን አደጋ ላይ የሚጥሉ ፣ ለወረርሽኙ መስፋፋበት በር ከፋች ናቸው። ይህ አደገኛ ሁኔታ በአስቸኳይ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል። ተገልጋዮችም ከጤና የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና እየተጠነቀቃችሁ። አንድ ቀን ሞቅ፤ አንድ ቀን ቀዝቀዝ እያደረግን የምንታገለው ይህ ትግል ዋጋ እንዳያስከፍለን…
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተላለፈ መልዕክት!

ባንኩ ላለፉት ሶስት (3) ቀናት አገልግሎቱን የሚያሳልጥ የኮር ባንኪንግ ማሻሻያ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፤ በአሁን ሰዓትም አዲሱ ማሻሻያ ከነባሩ ተነጥሎ እንዲሰራ ውጤታማ ሙከራዎች እየተደጉን ይገኛሉ ብሏል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሉት ችግሮች የሚፈት በመሆናቸው ደንበኞቼ በቅርንጫፎቻችን በሚኖራችሁ ቆይታ መንግስት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ እንዳትረሱ ብላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀረር ከተማ ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ጋር በተያያዘ ተቋርጦ የሰነበተው የታክሲ አገልግሎት በከፊል መጀመሩን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ገልጿል።

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,110
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 247
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 55
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 4
• አጠቃላይ ያገገሙ - 14
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 74

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

ከኖህ ሪልስቴት የተላከልን መልዕክት ፦

ኖህ ሪልስቴት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት የሚደረገው ጥረት የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ መሆኑ አጥብቆ እንደሚያምን ገልፆ ይህን አስከፊ በሽታ ለመግታት ከመንግስትና ከህዝብ ጎን ሆኖ እንደሚሰራ አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ኖህ ሪልስቴት በመንግስት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ እና ሀገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ከተጠናቀቁና ለርክክብ ዝግጁ ከሆኑት ፕሮጀክቶች መካከል 'ኖህ ፊጋን' ለኳራንታይ እንዲሆን አስረክቧል።

ይህኛው የኖህ ሪልስቴት ሳይት አጠቀላይ የወለል ስፋቱ 9,200 ስኩ.ሜትር ሲሆን 48 የመኖሪያ አፓርትመንቶች አሉት። እያንዳንዳቸውም 184 ስኩዌር ሜትር ባለ አራት መኝታ ክፍሎችን ከሶስት መፀዳጃ ቤቶች ፣ ኪችን ካቢኔት እና ቁምሳጥን የያዘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia