UK ውስጥ የኮሮና ቫይረስን ለመግታት በሚደረገው ትግል አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ በቫይረሱ ተጠቅተው ህይወታቸው ያለፈው ሱዳናዊው ዶ/ር አደል ራህማ አልታየር አስክሬናቸው ዛሬ ካርቱም ገብቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በጎረቤት ሀገር ሱዳን አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ አልተመዘገበም። በአሁን ሰዓት በሱዳን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተያዙ ሰዎች 10 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወሻ!
- ነገ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ/ም የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት የሰንበተ ክርስቲያን ቅዳሴ ከጠዋቱ 11:30 ጀምሮ ከቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ ሥርጭት ከአዲስ ሚዲያ ኔት ዎርክ ጋር በመተባበር በአዲስ ቴሌቪዥን (Addis TV) ይተላለፋል።
- የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መሥዋዕተ ቅዳሴ ከመጋቢት 27፣ 2012 ጀምሮ እሑድ ከጠዋቱ 3፡00 – 4፡15 ሰዓት (09፡00–10፡15 a.m.) በአዲስ ቲቪ በቀጥታ ይተላለፋል።
- በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የእሁድ የአምልኮና የእግዚአብሔር ቃል መርሀ ግብር ከነገ መጋቢት 27/2012 ዓ.ም. ጀምሮ በየሣምንቱ እሁድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ ቴሌቪዥን፣ በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ፣ በአዲስ ቴቪና የፌስቡክ ገፆች ይተላለፋል።
- ነገ መጋቢት 27 ጥዋት 12:30 ጀምሮ እስከ 4:00 ድረስ በመቱ ከተማ የተመረጡ ጎዳናዎች ላይ የኮሮና ቫይረስን ስርጭትን ለመከላከል የፀረ-ተህዋስያን ኬሚካል ርጭት ይካሄዳል።
ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

#UnitedStates
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች - 311,635
• በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች - 8,454
• ከበሽታው ያገሙ - 14,825
"ለአሜሪካውያን ከባዱ ሳምንት እየመጣ ነው" - ዶናልድ ትራምፕ
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ ሞት ሊከሰት እንደሚችል የሰጉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ‘አስቸጋሪው ሳምንት’ ገና እየመጣ ስለሆነ አሜሪካዊያን እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በየዕለቱ በሚሰጡት መግለጫ ላይ በቀጣይ ቀናት ሊኖር ሰለሚችለው አደጋ እንዳሉት “ተጨማሪ ሞት ይኖራል” ብለዋል።
በአገሪቱ በበሽታው ክፉኛ የተጠቁት ግዛቶችንም አንስተው የህክምና መገልገያዎች አቅርቦትና የጦር ሠራዊት አባላት ወረርሽኙን ለመቋቋም እንደሚሰማሩ ገልጸዋል።
ጨምረውም "አገራችንን ለእንቅስቃሴ በድጋሚ ክፍት ማድረግ አለብን፤ በዚህ ሁኔታ ለተከታታይ ወራት መቆየትን አንፍልግም” ሲሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደሞው መመለስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ከምክትላቸው ማይክ ፔንስ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ማናቸውንም ሰዎች የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምርመራ እንዲያደርጉ ተወሰነ።
ምርመራው አገዳጅ እንደሆነም ነው የተገለፀው። ምርመራ የሚደረግላቸው የፕሬዘዳንቱና የምክትል ፕሬዘዳንቱ የቅርብ ሰዎች በ15 ደቂቃ ውስጥ ውጤታቸውን ማወቅ ይቻላል ነው የተባለው፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ፕሬዝዳንቱ ለሁለተኛ ግዜ የኮሮና ቨይረስ ምርመራ አድርገው ነጻ መሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርመራው አገዳጅ እንደሆነም ነው የተገለፀው። ምርመራ የሚደረግላቸው የፕሬዘዳንቱና የምክትል ፕሬዘዳንቱ የቅርብ ሰዎች በ15 ደቂቃ ውስጥ ውጤታቸውን ማወቅ ይቻላል ነው የተባለው፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ፕሬዝዳንቱ ለሁለተኛ ግዜ የኮሮና ቨይረስ ምርመራ አድርገው ነጻ መሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡
#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19
በአሁን ሰዓት በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.2 ሚሊዮን የበለጠ ሲሆን 64,787 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ከቫይረሱ ያገገሙት 247,301 ደርሰዋል።
በኮቪድ-19 ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሀገራት ዝርዝር ፦
• ጣልያን - 15,362
• ስፔን - 11,947
• ዩናይትድ ስቴትስ - 8,454
• ፈረንሳይ - 7,560
• ዩናይትድ ኪንግደም 4,313
• ኢራን - 3,452
• ቻይና - 3,326
• ኔዘርላንድ - 1,651
• ጀርመን - 1,395
• ቤልጂየም - 1,283
• ስዊዘርላንድ - 666
• ቱርክ - 501
• ብራዚል - 431
• ስውዲን - 391
• ፖርቹጋል - 266
• ካናዳ - 231
• ኢንዶኔዥያ - 191

"በአፍሪካ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ይከሰታል!" - የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/
በአፍሪካ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደሚከሰት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ፡፡
እስካ ዛሬ ድረስ 8 ሺህ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙባት አፍሪካ ወደፊት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ዶክተር ቴድሮስ ትናንት ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በቴሌ ኮንፈረስ በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በአህጉሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በቫይረሱ የተያዘባቸው ሀገራት ደቡብ አፍሪካ 1,585፣ ግብጽ 1,070 እና ሞሮኮ 960 ናቸው፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት ድንበሮቻቸውን የዘጉ የአፍሪካ ሀገራት ለሰብአዊ እርዳታ እና የሕክምና ቁሳቀስን ለማንቀሳቀስ ክፍት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማእከል በሚያዝያ ወር ውስጥ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ ሊደርስ ይችላል ብሏል፡፡
ምንጭ፡- ኒውዮርክ ታይምስ,etv

#UPDATE
- በኢራን የሟቾች ቁጥር 3,603 ደረሰ። በ24 ሰዓት የ151 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል።
- በስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ የ674 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር 12,418 ደርሷል።
- በማሌዥያ በ24 ሰዓት ውስጥ የ179 አዲስ #ፖዘቲቪ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ተመዝግቧል።

የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ምላሽ አሰጣጥን (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ!
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ 59 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ነው አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተርረጋግጧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ 59 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ነው አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተርረጋግጧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ሁኔታ ፦
- ሶስቱ ታማሚዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። አንደኛው ታማሚ ኤርትራዊ፤ ሌላኛው ታማሚ ደግሞ ሊቢያዊ ነው።
- ታማሚ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪኩ እንደሚያሳየው ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።
- ታማሚ ሁለት የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን የኮንጎ የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆይ ውስጥ የነበረ ነው።
- ታማሚ ሶስት #ለጉብኝት አዲስ አበባ የመጣ የ45 ዓመት ወንድ ከካናዳ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።
- ታማሚ አራት የ27 ዓመት ሴት ስትሆን ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ሌስተር ሲቲ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።
- ታማሚ አምስት የአዲስ አበባ ነዋሪ የ30 ዓመት ወንድ ሲሆን ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ነው።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 1843
• ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 59
• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 5
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 37
• ፅኑ ህሙማን - 1
• ህይወታቸው ያለፈ - 0
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 4
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 43
ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።
#EPHI

#NewsAlert
እስካሁን ድረስ ምንም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ ሳይመዘገብባት የቆየችው ደቡብ ሱዳን ዛሬ የመጀመሪያውን የቫይረሱን ታማሚ ሪፖርት አድርጋለች።
የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተገኘባት ግለሰብ የ29 ዓመት ወጣት ስትሆን FEBRUARY 28 ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ሱዳን የገባችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደርገላት የነበረች እንደሆነ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ሮይተርስ

#RepublicOfSouthSudan
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዛሬ መጋቢት 27/2012 ዓ/ም ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተገኘባት የ29 ዓመት ወጣት ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) በኩል ከኔዘርላንድ ወደ ደቡብ ሱዳን የገባች ናት።

#BREAKING
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
#MoH #EPHI #EBC

በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59 ደረሱ!
በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 59 ደርሰዋል።
በተጨማሪ አንድ (1) ሌላ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከበሽታው ማገገሙን የጅቡቲ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 59 ደርሰዋል።
በተጨማሪ አንድ (1) ሌላ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከበሽታው ማገገሙን የጅቡቲ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhemedAli
በኮቪድ-19 ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን እመኛለሁ። ነፍሷ ዘላለማዊ ረፍትን ታግኝ።
ዜናውን የሰማችሁ ሁሉ #እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁ።
የሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ፣ በእምነት ጸንተን ቫይረሱ በማኅበረሰባችን መካከል እንዳይሠራጭ በትጋት ልንሠራ ያስፈልጋል።
አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ። እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ።
(የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ)

#DrLiaTadesse
ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ፦
በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን የአንድ ሰው ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ታማሚዋ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ ህክምና ሲደረግላቸው ነበር።
ከቀናት በፊት ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል ተዛውረው ጥብቅ ክትትል ሲደረግላቸው የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል።
በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

#TikurAnbessaSpecializedHospital
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል የሚፈልጉ ተመላላሽ ታካሚዎቹ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።
የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በተመላላሽ ታካሚዎቹ ሞባይል ስልኮች ላይ በመደወል ማማከርን ጨምሮ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጧቸው መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።
#EBC