TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

በጋምቤላ ክልል መንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፦

- ወደ ጋምቤላ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲቆም ተወስኗል፡፡

- ከጋምቤላ ወደ ሁሉም የክልሉ ዞንና ወረዳዎች የሚደረጉ የህዝብ ማመላለሻ ከመጫን አቅማቸው 50 በመቶ ቀንሰው ህዝብ እንዲያመላልሱ።

- በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የከተማ የህዝብ ማጓጓዣ ባጃጅ፣ ሚኒባስና ሌሎች የህዝብ ማጓጓዣዎች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት ታግዷል።

- የመንግስትም ይሁን የግል ሞተር ሳይክሎች ከአሽከርካሪው በስተቀር ሰው መጫን ተከልክሏል።

- ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት ቤቶችና ሺሻ ቤቶች የቫይረሱን ተጋላጭነት ስለሚጨምሩ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል።

- ወደ ጋምቤላ ክልል ምንም ዓይነት ጫት እንዳይገባ ተወስኗል፡፡

- በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ያለባቸው መስሪያ ቤቶች ሰራተኛን በመቀነስ እንዲሁም በእድሜ የገፉ፣ ህፃናት የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች ቤታቸው ሆነው ስራ እንዲሰሩም ውሳኔ ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ሁኔታ፦

- በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስቱ (3) ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡

- የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነው፡፡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቷ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆና በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘች መሆኗ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሁለተኛው ታማሚ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡

- ሶስተኛው ታማሚ የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ሲሆን በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሶስቱም (3) ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሌሎች ሰዎች የመለይት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል ለተጨማሪ 23 ቀናት እንዲዘጉ መወሰኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

በመጋቢት ወር ከውስጥና ከውጭ ሃገር ወደ ጎንደር ከተማ የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሌሎችም ዜጎች በሃላፊነት ስሜት ጤና ማዕከል በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዬም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከንቲባው ከዚህ ጋር አያይዘውም በመጋቢት ወር በአየር መንገድ ከውጭ የመጡ ሃገር ቤት ገብተው ቆይተው ወደ ከተማዋ የሚመጡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው ማረፊያ ቦታ ለ14 ቀን ክትትል እየተደረገላቸው የሚቆዩ መሆኑን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ጎንደር ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ቤት መቀመጥ በብዙ መልኩ ይሄን በሽታ [ኮቪድ-19] ሊከላከል ይችላል" - ዶክተር ፅዮን ፍሬው

በኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬው ከአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ በአሁን ሰዓት በኒውዮርክ ስላለው የቫይረሱ ስርጭት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ምን መማር እንዳለበት አንስተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

"የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱ ያለፈ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበት እየተጣራ ነው" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ [የጤና ሚኒስትር]

የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክምና ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ትናንት ወደ ጤና ጣቢያ ለህክምና ያመራው ግለሰቡ ዛሬ ህይወቱ ማለፉንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማረጋጋጥ ናሙና ተወስዶ የምርመራ ውጤቱ እየተጠበቀ መሆኑንም አብራርተዋል። የአስከሬን ምርመራም እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የታማሚ ሁኔታ፦ ቫይረሱ የተገኘበት 26ኛው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ዓ/ም ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል። ግለሰቡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁን ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና…
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፦

- ግለሰቡ በመጋቢት 10 ነው ድሬዳዋ የገባው ከብዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል። ነገር ግን ግለሰቡ 'እራሱን አግልሎ' ስለነበር የተወሰኑ የቤተሰቦቹን አባል ለማግኘት ተሞክሯል።

- ወደድሬዳዋ ለይቶ የህክምና መስጫ ማዕከል ከመምጣቱ በፊት የግል የህክምና ተቋሞች ጋር ሄዷል፤ በህክምና ተቋሞቹ ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎችንም የመለየቱ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

- በአጠቃላይ ቫይረሱ ካለበት ግለሰቡ ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎችን በፍጥነት አግኝቶ ወደኳራንታይን ለማስገባት እየተሰራ ነው። ምልክቶችን የሚያሳዩ ካሉ እነሱንም የመለየት ስራ ይሰራል። ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በጠቅላላ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረጋል።

#DrFuadKedir

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በድሬዳዋ ከተማ በነገው እለት የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ርጭት ይከናወናል። የፀረ-ተህዋስ መድሀኒት ርጭት የሚከናወንባቸው መንገዶች፦

- ከኮኔል ድልድይ - ክርስቶስ ት/ቤት - ኮተን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ

- ከኮኔል ድልድይ - ታይዋን - አላይበዴ - ክርስቲያን መቃብር

- ከኮኔል ድልድይ - ደቻቱ - ቀፊራ - አምስተኛ

- ከድ/ዳ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ምድር ባቡር ክለብ - ሰዒዶ

ከላይ በተጠቀሱት የከተማው መንገዶች ላይ ከነገ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ቀን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- UK ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

- በስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ የ864 ሰዎች ሞት ተመዘግቧል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ9,000 በልጧል። የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም ወደ ከ100,000 በላይ ከፍ ብሏል።

- በፊሊፒንስ ተጨማሪ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት ተደርጓል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4,000 በላይ ሆኗል። የቫይረሱ ተጠቂዎችም 188,639 ደርሷል።

- ኦማን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት ሪፖርት አድርጋለች።

- ፎርድ በመቶ ቀናት ውስጥ 50,000 ቬንትሌተር ሊያመርት መሆኑን አሳውቋል።

- ጀርመን በሀገሯ 149 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሞቱ ሪፖርት አድርጋለች።

- በኢራን የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር 3,036 ደርሷል። በ24 ሰዓት ውስጥም የ138 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- በዓለም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 872,972 ደርሷል። 43,275 ሰዎች ሞተዋል፥ 184,594 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መቐለ ዩኒቨርስቲ አዲሱን የኲሓ መለስ ዜናዊ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሰቲው የዶርሚተሪ አቀማመጥ የመቀየር ፤ ሰፋፊ ወርክሾፖችን የማዘጋጅት፣ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ የማዘጋጀት፣ የምግብ አቅርቦት እና አሰፈላጊ የሆኑ ግብሃቶችን የማሟላት ስራ በማከናዎን ላይ ይገኛል። ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ ካምፓሶችን ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ የማዘገጃጀት ሂደት ላይ ይገኛል።

ምንጭ:- መቐለ ዩኒቨርስቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 3
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 25
• ፅኑ ህሙማን - 2
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 2
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 29

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#DrLiaTadesse #EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፥ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከውጭ አገሮች የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና ይሄን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለይቶ ማቆያዎችን የማስፋት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ሆኖም የተወሰነውን ውሳኔ በመጣስ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ እየወጡ በመሆኑ ሚኒስቴሩ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይሄም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከሕብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎችን በመቀበልና በማጣራት ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዶክተር ሊያ ታደሰ የዛሬው መግለጫ ፦

- መንግስት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ስራውን #ለማስፋት በትኩረት እየሰራ ነው።

- በአሁኑ በአዲስ አበባ ሶስት (3) የላብራቶሪ ምርመራ ማእከሎች አገልግሎት እየሰጡ ነው።

- በክልሎች በቅርብ ቀን የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ይጀምራል።

- ህብረተሰቡ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት ለሚተላለፉ እርምጃዎች ትኩረት በመስጠት ሊተገብር ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 81 ደረሱ!

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በአሁን ሰዓት መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። በመግለጫው ላይ እንደተሰማው በሀገሪቱ ተጨማሪ ሀያ ሁለት (22) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ሰማንያ አንድ (81) ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከኬንያ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ፦

- በ24 ሰዓት የ300 ሰዎች ናሙና ምርመራ ተደርጓል።

- ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል ሀያ ሁለቱ (22) ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

- ቫይረሱ የተገኘባቸው 13 ወንዶች 9ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው።

- 18 ኬንያውያን ፣ 2 የፓኪስታን ዜጎች፣ 2ቱ ደግሞ የካሜሮን ዜጎች ናቸው።

- ከ22ቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሀያ አንዱ (21) ኳራንታይን ላይ ያሉ ናቸው።

- በኬንያ ዛሬ ሪፖርት የተደረገው የ22 ሰዎች የኮቪድ-19 ፖዘቲቭ ኬዝ በአንድ ቀን የተመዘገበ #ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል።

- በተመሳሳይ በአንድ ቀን ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥርም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቤታቸው ብቻ እንዲጸልዩ ውሳኔ አስተላለፈች።

ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ በመምጣቱ የዕምነቱ ተከታዮች ጸሎታቸውን በቤታቸው ብቻ እንዲያካሂዱ መወሰኗን አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለኮቪድ-19 መከላከያ ስራ 3 ሚሊዮን ብር መለገሷንም ገልጻለች።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BAHIRDAR

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በባህር ዳር ከተማ የተጣለው የ14 ቀን እንቅስቃሴ እገዳ ዛሬ 23/07/2012 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን እገዳውን በማይተገብሩት ላይ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አሳውቋል።

ምንጭ፦ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከከተማው የፀጥታ አካላት ጋር አትክልት ተራ አካባቢ እየታየ ባለው መጨናነቅ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ቦታው ከፍተኛ የአትክልት ምርት ማከፋፈያ ሲሆን ከፍተኛ የሰው ጭንቅንቅ በየእለቱ የሚታይበትና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘም ለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑ ተገምግሟል።

ስለሆነም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአትክልት ግብይቱ በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር ተወስኗል። አትክልት ተራ ለጊዜው ለነጋዴዎቹ እንደ እቃ ማስቀመጫ (ስቶር) ብቻ እንዲያገለግል ተወስኗል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአጭር ቀናት በባሕር ዳር ፣ ደሴና ጎንደር ከተሞች የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቤተ ሙከራዎች እንዲኖሩ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከአቶ ተመሥገን ጥሩነህ መግለጫ ፦

- የኮሮና ቫይረስ ካለባቸው ሁለቱ (2) ግለሰቦቹ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 70 ሰዎች ወደ ለይቶ ሕክምና ክትትል ማድረጊያ ገብተዋል።

- ተጨማሪ ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ እንደነበራቸው የተገመቱ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ቀጥሏል።

- በባሕር ዳር፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳምና ቲሊሊ ከተሞች የተላለፈው የእንቅስቃሴ ገደብ የቫይረሱን የተጋላጭነት መጠን ለመቀነስ እንጅ ሙሉ በሙሉ ነፃነትን የሚጋፋ እገዳ ለመጣል ታስቦ አይደለም።

- በሌሎች ከተሞች መሠል የእንቅስቃሴ ገደብ ውሳኔ እንዲተገበር የሕዝብ ጥያቄ አለ። የሕዝቡን ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ለመቀነስ ሲባል በየተዋረዱ ያሉ ኮማንድ ፖስቶች ተግባራዊ ያደርጋሉ።

- ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለማገዝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች አገልግሎት እንዲሰጡ ተዘጋጅተዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia