TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ ለDW የተናገሩት፦

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በሽታ በጣም አደገኛ የሆነበት ዋንኛ ምክንያት መተላለፊያ መንገዱ ቀላል ነው። በተለይ ደግሞ ማኅበረሰባዊ መሥተጋብራችን ቅርብ ለሆነ እጅግ በጣም በቀላሉ መተላለፍ የሚችል በሽታ ነው። እኛ እርስ በርስ በጣም ቅርብ ነን።

ኢትዮጵያ በቅጡ ካልተዘጋጀት ይኸ ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ ሊጨምር ይችላሉ። የቫይረሱ ዕድገት እየተራባ የሚሔድ (exponential growth) ነው።

ለምሳሌ እንበልና  50 ሰው መጀመሪያ ላይ ቢያዝ ከ15 ቀን በኋላ 2000 ሰው ይኖረናል። ቀጥሎ ደግሞ በአንድ ወር ውስጥ ወደ 91 ሺሕ አካባቢ ሰዎች ሊያዙ ይችላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH AFAAN OROMOO
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Gootittiin atileet Daraartuu Tulluu ergaa gabaabaa Qabdi! - "Iccitiin Milkaa'ina kiyyaa... "

@tikvahethAFAANOROMOO
አጫጭር መረጃዎች፦

- የእንግሊዙ ዘውድ ወራሽ የሆኑት ልዑል ቻርልስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንና መጠነኛ ምልክት እንደታየባቸው ከቤተ መንግሥቱ የወጣው መረጃ ያስረዳል። ባለቤታቸውም ምርመራ የተደረገላቸው ቢሆንም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል።

- በስፔን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከቻይና መብለጡ ተነግሯል። የስፔን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባወጣው አሃዝ መሠረት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3434 ደርሷል።

- በሩዋንዳ መንግሥት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሶ በመውጣት አሳ ለማስገር የሄደው ግለሰብ በአዞ መበላቱ ተሰማ።

- በሁቤይ ግዛት ውሃን የሚገኘው ኤርፖርት ከ APRIL 8 ጀምሮ ዳግም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ለጊዜው አለም አቀፍ በረራዎችን እንዲሁም ከውሃን ወደ/ከ ቤጂንግ የሚደረጉ በረራዎችን አያስተናግድም።

- ሞስኮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጨማሪ እርምጃ ወስዳለች የከተማይቱ ከንቲባ ፦ ማንኛውም አይነት ህዝባዊ ዝግጅት ሞስኮ ውስጥ እንዳይደረግ አግደዋል።

#BBC #REUTERS #XInhua
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከኢትዮጵያ፦

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለኮሮና ቫይረስ ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የአቅርቦት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቁመዋል። መንግስት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸው ተግባራትን ለመደገፍ ወጣት ባለሃብቶች ሊያደርጓቸው በሚገቡ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

- በደቡብ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል 3 ሺህ 642 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።

- የአማራ ክልል ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ፓትሪያርክና መላው አህጉረ ስብከት ጽህፈት ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በከፊል እንዲዘጉ ወስኗል። ውሳኔውም ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ሲኖዶሱ መወሰኑን ቤተ ክርስቲያኗ ዛሬ በሰጠችው መግለጫ አስታውቃለች።

- በኦሮሚያ ክልል የሰራተኞች በአንድ ቦታ መቆየት እና የስራ ቦታ መጣበብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የቆየና በሀኪም ማስረጃ የተደገፈ የጤና እክል ያላቸው ሰራተኞች፣ ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁንም የጡረታ መውጫ ጊዜያቸው የደረሱ ሰራተኞች እረፍት እንዲወጡ ተወስኗል።

#FBC #ENA #PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የባንክ ቁጥሮች፦

ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ተዘጋጅተዋል።

1. ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1000327017318

2. አዋሽ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 0130479475400

3. ዳሸን በንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 0444177190011

4. ዘመን ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1032410042463013

5. አባይ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1022115562778011

ተጨማሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ይፋ የሚደረጉ ይሆናል። እስከዚያ ድረስ ተረጋግተን አስተዋጽኦ እናድርግ። በአብሮነት እንወጣዋለን!

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢትዮ ቴሌኮም፦

ጤና ይስጥልን ! የእርስዎ አስተዋፅዖ ለወገንዎ መዳን ነው! የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ከባድ ጉዳት ከወዲሁ እንከላከል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‘ምዕምኑ በሬን እዘጋለሁ፤ፈጣሪዬን አምናለሁ’ በሚል መርህ በመመራት ራሱን ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሊጠብቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳሰበ።

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጥንቃቄ እንዲደረግ በእየእምነት ተቋማቱ ጥሪ ቢተላለፍም በምዕመኑ ዘንድ የሚስተዋለው የጋራ አምልኮ ለቫይረሱ [COVID-19] መዛመት ስጋት ማሳደሩም ተጠቁሟል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 ምክንያት የሞተችው የ21 ዓመት ወጣት!

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የጤና እክል ያልነበረባት የ21 ዓመቷ ወጣት በኮሮናቫይረስ ከተያዘች በኋላ መሞቷን ወላጆቿ ተናገሩ።

"ቫይረሱ ልጃችንን ነጠቀን" ያሉት ወላጆች፤ ሁሉም እራሱን ከቫይረሱ ለመጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ክሎይ ሚድልተን የተባለችው ወጣት ምንም አይነት የጤና እክል ሳይኖርባት በዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ ከሞቱት መካከል አንዷ ነች ተብሏል።

የወጣቷ እናት ዲዓን በፌስቡክ ላይ "ይህን ቫይረስ እንደ ቀላል የምትገምቱት፤ እባካችሁ ዳግም አስቡበት። ከእራሴ ልምድ እንደተረዳሁት ይህ ቫይረስ የ21 ዓመት ሴት ልጄን ነጥቆኛል" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን ተጨማሪ 683 ሰዎች ሞቱ!

ጣልያን ውስጥ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 683 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 7,503 ደርሷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 74,386 የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 5,210 ኬዝ በ24 ሰዓት ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን ውስጥ 4 ተጨማሪ ዶክተሮች ሞተዋል። አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የሞቱ የዶክተሮች ቁጥርም 29 ደርሷል። ከ5,000 የሚበልጡ የጤና ባለሞያችም በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#StayHomeSaveLives

ዶክተሮች ፣ ነርሶች ሁሉም የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ነው ፤ በኮቪድ-19 እየሞቱብን ነው ፣ እየተጠቁብን ነው፤ እባካችሁ ከፈጣሪ በታች ያሉን እነሱ ናቸውና #ጤና እንዲሆኑልን የሚሉንን እንስማ፤ የሚነግሩንን እንተግብር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር 4 ደረሰ!

ኤርትራ በኮሮና ቫይረስ በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ማግኘቷን የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከዱባይ ባለፈው ቅዳሜ ወደ ኤርትራ የገቡ የኤርትራ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል። በዚህም መሰረት በኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አራት ደርሷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር በተመሳሳይ አውሮፕላን የመጡና ንክኪ የነበራቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል።

ይህን ተከትሎም ከዛሬ ዕኩለ ሌሊት ጀምሮ ማንኛውም ወደ ኤርትራም ሆነ ከኤርትራ የሚደረጉ በረራዎች ለሁለት (2) ሳምንታት እንዲቆሙ ይደረጋል ተብሏል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሳዑዲ አረቢያ ለምትገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ለ21 ቀናት የሚፀና (እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ድረስ የሚቆይ ሰዓት እልፍ አዋጅ የታወጀ መሆኑ ያታወሳል።

በዛሬው ዕለት የ2ቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ጠባቂ እና የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳዑዲ ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ከነገ ጀምሮ በስራ ላይ የሚውል ተጨማሪ ውሳኔዎች ይፋ አድርገዋል። እነህም፦

- ሳዑዲ አረቢያ በአስራ ሶስቱም የሳውዲ ግዛት የሚኖሩ ዜጎችን ነዋሪዎቿ በሙሉ ከሚኖሩበት ከተማ መውጣትም ሆነ ወደሌላ አካባቢ መሄድ አይፈቀድም

- ከሪያድ ፣ መካና መዲና ከተሞች መውጣትም ሆነ መግባት የተከለከለ ነው።

ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ሪያድ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልል!

የትግራይ ክልል የኮረና ቫይረስን [COVID-19] ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ። የክልሉ የካቢኔው በአካሄደው ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታውቋል። የአዋጁ ዝርዝር ይዘት በነገው ዕለት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እንደሚገለፅ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን፣ኢቲቪ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ሀገር፣ ብሄር፣ ዘር የለውም፤ ሃይማኖት፣ ቀለም አይለይም!

ከሰሞኑ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የቻይና እና አሜሪካ እርስ በእርስ መወቀቅስ አይሎ ነበር። ቻይና ቫይረሱን ያመጡብኝ የአሜሪካ ወታደሮች ናቸው ማለቷ አይዘነጋም።

ለቻይና ምላሽ በሚመስል መልኩ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ይህ ቫይረስ 'የቻይና ቫይረስ' ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ቻይና በአሜሪካ ወታደሮች ነው ሀገሬ የገባው ማለቷም አስቆጥቷቸው ነበረ።

የፕሬዘዳንት ትራምፕ ንግግርን እጅግ በጣም ብዙ ሰው አውግዞታል፣ ዘረኛም አስብሏቸዋል ፤ WHOም ፕሬዘዳንቱ በንግግራቸው ላይ የተጠቀሙት 'ቃል' አግባብ እንዳልሆነ አሳውቆ ነበር። በርካቶችም ኤዥያ-አሜሪካውያንን ያገለለ ንግግር ብለውታል። የእሳቸው ንግግር በርካታ የቻይና ዜጎችንም አስቆጥቶ ነበር።

አሁን ግን በመካከላቸው ያለውን እርስ በእርስ መወቃቀስ ለማለዘብና ይህን የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት የሆነውን ኮሮና ቫይረስ አብረው ለመዋጋት የፈለጉ ይመስላሉ።

ፕሬዘዳንት ትራምፕ ከዚህ በኃላ ኮሮና ቫይረስን "የቻይና ቫይረስ" ብዬ አልጠረም ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ቃሉን በመጠቀማቸው ግን እንደማይፀፀቱ ተናግረዋል ቻይና 'ቫይረሱ በአሜሪካ ወታደሮች' ነው የመጣው ማለቷ ትክክል እንዳልሆነ በማንሳት።

ምንጭ፦ Bloomberg Poltics
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 በሽታን አስመልክቶ ጥቆማ ለመስጠት፦

ለኦሮሚያ ክልል - 6955
ለትግራይ ክልል - 6244
ለአማራ ክልል - 6981
ለሱማሌ ክልል - 6599
ለድሬዳዋ ከተማ - 6407
ለደቡብ ክልል - 6929

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA

ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሰዓታት በፊት ለኬንያ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈው ነበር። በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ 3 ሰዎች ዛሬ መገኘታቸውንም ተናግረዋል። በጠቅላላው በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ 28 ሰዎች መድረሳቸውን አሳውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ፕሬዝደንቱ “አንድ ከቫይረሱ የዳነ ሰው አስመዝግበናል፤ ይህም ቫይረሱን ድል እንደምንነሳው በትክክል ያሳየ ነው” ብለዋል። ፕሬዝደንቱ በመግለጫቸው የሰዓት እላፊም አውጀዋል።

በዚህ መሠረት ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ስዓት ድረስ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑን ገልጸዋል። የቫይረሱ ስርጭት በሰዎች ላይ ያሳደረውን ጫና ለመቀነስ፤ መንግሥት የተለያየ መጠን ያለው ታክስ ቅነሳ ማድረጉንም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች 41 ደረሱ!

በሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 41 ደርሷል። የሩዋንዳ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ 1 ተጨማሪ የኮቪድ-19 ተጠቂ ሪፖርት አድርጓል። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከዱባይ ወደሩዋንዳ የገባ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StayHomeSaveLives

ለጤና ባለሞያዎች ክብር አለን!

በበርካታ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል፤ መስሪያ ቤቶችም ተዘግተዋል ፣ ሰራተኞችም ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተድርጓል ፣ የንግድ ማዕከላትም ተዘግተዋል ፣ በረራዎች፣ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በሁሉም ሀገራት ሆስፒታሎች 24 ሰዓት ክፍት ናቸው። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ይረባረባሉ። ዶክተሮች ፣ የጤና ባለሞያዎች የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ህመምተኞችን ለማዳን የሚችሉት ያደርጋሉ። ለእኛ ጤና እነሱ አሉልን ፤ ለእነሱ ጤና ደግሞ እኛ ቤት ውስጥ እንሁንላቸው ፤ የሚሉንን፣ የሚመክሩንን እናዳምጣቸው።

ክብር ይገባቸዋል!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንዴት አደራችሁ?

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን እየተከታተልን እንገኛለን። በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየሸኙ ነው። በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ተማሪዎች እየተንገላቱ መሆኑን ነግረውናል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት በተቀመጠው ትዕዛዝ መልኩም ማግኘት እንዳልቻሉ አሳውቀውናል። ወደበኃላ ላይ የት የት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ እያሰሙ እንደሆነ የምንግልፅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia