TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ከአርባ ምንጭ እና ከሀዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምርመራ እንዲደረግ ናሙና መላኩ ይታወቃል። በፌደራል ጤና ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምርመራ በውጤት መሠረት ሁለቱም (2) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

(የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዩጋንዳ የ8 ወር ህፃን በኮቪድ-19 ተጠቅቷል!

ዩጋንዳ ተጨማሪ 5 የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎችን ሪፖርት አድርጋለች አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም 14 ደርሷል። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ከቫይረሱ ተጠቂዎች መካከል የ8 ወር ህፃን እንደሚገኝበት ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጡ በርካታ የውጭ ሀገር ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተሰምቷል። በሀገር ውስጥ የቀሩትም ቢሆኑ በቤታቸው እንዲሰሩ ድርጅቶቻቸው ውሳኔ ማሳለፋቸው ታውቋል። 

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሪፖርት ያልተደረገባት ሴራሊዮን ለአንድ ዓመት የሚቆይ 'የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ' አውጃለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ የጤና ባለሞያዎች ከሁቤይ ወጥተዋል!

በሁቤይ ግዛት የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመግታት ከመላው ቻይና የተውጣጡ ከ21,000 በላይ የሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር በመቻሉ ግዛቲቱን ለቀው መውጣታቸው ተነግሯል።

ቀሪ 16,558 የሚደርሱ የጤና ባለሞያዎች አሁንም በሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ሙሉ በሙሉ ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ አርሶ አደሮች የአ/አ ከተማ አስተዳደር ለ14 ቀን በማቆያ እንዲገቡ ላደረጋቸው ሰዎች የሚውል የሰብል ምርቶችን በስጦታነት አበርክተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበረከቷል፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ -19] ምርመራ የሚያገለግሉ ሁለት ተጨማሪ ላቡራቶሪዎች ሊከፈቱ መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታውቋል።

የቫይረሱን በፍጥነት የመስፋፋት ባህሪ ከግምት በማስገባት የመመርመሪያ መሳሪያ ባላቸው ተቋማት ላይ ተጨማሪ ላቡራቶሪ አንዲኖር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል።

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኤባ አባተ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኝ ናዲክ የተባለ የግብርና ምርምር ተቋምና አርማዎር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲቲዩት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በመንግስት ውሳኔ ክሳቸው የተቋረጠላቸዉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር፦

ሀ. በሙስና ወንጀል በተባባሪነት ሚና የተከሰሱና ክሳቸዉ የተቋረጠዉ ከህጻናት ጋር ማረሚያ ቤት የሚገኙ እና ነፈሰጡር መሆናቸው የተረገገጡ ሴቶች፦

1. ወ/ሮ ትዕግስት ታደሰ
2. ሌ/ኮ ለተብርሀን ደሞዝ ተ/ሚካኤል
3. ወ/ሮ ፅጌ ተክሉ
4. ወ/ሮ ሶፊያ ኑሮ
5. ወ/ሮ ቅድስት አያሌው አባተ
6. ወ/ሮ እናኑ ፋንታሁን ባዩ
7. ወ/ሮ ሱመያ ሰይፉ ግባሽ

ለ. በተለያዩ የወንጀል ጉዳዮች ተከሶ የሚገኙ ክስ የተቋረጠላቸዉ ሴቶች፦

1. ወ/ሮ ሙሊያ አብደላ ዑሰማን
2. ወ/ሮ ቤቴልሄም አወል አባፌጣ
3. ወ/ሮ መሰለች ታለዓን አሳየ
4. ወ/ሮ ሜላት ዘዉዴ ማጫ

ሐ. በእነ ቢኒያም ተወልደማርያም መዝገብ ሙስና ወንጀል በተባባሪነት ሚና የተከሰሱና ክሳቸዉ የተቋረጠዉ፦

1. አቶ ይርጋም አብረሃ
2. አቶ ማስረሻ አሰፋ

መ. በአፋር የጨው ምርት ጋር በተያያዘ በእነ ሙሉጌታ ሰይድ መዝገብ የተከሰሱና ከዚህ ቀደም በዚሁ መዝገብ በከፊል ከተለቀቁት ጋር በተመሳሳይ መዝገብ ጉዳያቸው ሲጣራ የቆየ ከመሆኑ ጋር ተያይዞና የፍትህ ሥርዓቱ ለሁሉም እኩል ተደራሽና ተገማች ለማድረግ ሲባል ክሳቸዉ የተቋረጠላቸዉ ፡-

1. ሀጂ ሰይድ ያሲንአቶ
2. ዶ/ር ሠይድ ኢሮ
3. አቶ ተፈሪ ዘውዴ
4. አቶ ወንዱአንተ ነጋሽ
5. አቶ አባይነህ ጥላሁን
6. አቶ ናደው ታደለ
7. አቶ ሀብቱ ሀጎስ
8. አቶ ይስማሸዋ ስዩም
9. አቶ ሳድቅ መሀመድ
10. አቶ አማረ አሰፋ
11. አቶ አረጋ አስፋው
12. አቶ መሀመድ አደም
13. አቶ ዋሴዕ ሳዲቅ
14. አቶ ያዮ ዋልህ ኢብራሂም
15. አቶ መሀመድ አኒሳ
16. አቶ ሰይድ ይማም
17. አቶ መህቡብ ማሄ
18. አቶ ወንድወሰን ማስረሻ
19. አቶ አብደላ ሙስጠፋ
20. አቶ ዋሴዕ አወል

ሠ. ከለዉጡ በፊት በተከፈተበት መዝገብ ሲጣራ ቆይቶ ከዉጭ ሀገር ሰመለሱ የፍርድ ወሳኔ የተሰጠዉ መሆኑ እና የፖለቲካ ምዕዳሩን ለማሰፋት በተደረገዉ ማጠራት የይቅርታ ወሳኔ የተሰጠዉ ፡-

1. ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመወርቅ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ ለDW የተናገሩት፦

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በሽታ በጣም አደገኛ የሆነበት ዋንኛ ምክንያት መተላለፊያ መንገዱ ቀላል ነው። በተለይ ደግሞ ማኅበረሰባዊ መሥተጋብራችን ቅርብ ለሆነ እጅግ በጣም በቀላሉ መተላለፍ የሚችል በሽታ ነው። እኛ እርስ በርስ በጣም ቅርብ ነን።

ኢትዮጵያ በቅጡ ካልተዘጋጀት ይኸ ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ ሊጨምር ይችላሉ። የቫይረሱ ዕድገት እየተራባ የሚሔድ (exponential growth) ነው።

ለምሳሌ እንበልና  50 ሰው መጀመሪያ ላይ ቢያዝ ከ15 ቀን በኋላ 2000 ሰው ይኖረናል። ቀጥሎ ደግሞ በአንድ ወር ውስጥ ወደ 91 ሺሕ አካባቢ ሰዎች ሊያዙ ይችላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH AFAAN OROMOO
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Gootittiin atileet Daraartuu Tulluu ergaa gabaabaa Qabdi! - "Iccitiin Milkaa'ina kiyyaa... "

@tikvahethAFAANOROMOO
አጫጭር መረጃዎች፦

- የእንግሊዙ ዘውድ ወራሽ የሆኑት ልዑል ቻርልስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንና መጠነኛ ምልክት እንደታየባቸው ከቤተ መንግሥቱ የወጣው መረጃ ያስረዳል። ባለቤታቸውም ምርመራ የተደረገላቸው ቢሆንም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል።

- በስፔን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከቻይና መብለጡ ተነግሯል። የስፔን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባወጣው አሃዝ መሠረት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3434 ደርሷል።

- በሩዋንዳ መንግሥት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሶ በመውጣት አሳ ለማስገር የሄደው ግለሰብ በአዞ መበላቱ ተሰማ።

- በሁቤይ ግዛት ውሃን የሚገኘው ኤርፖርት ከ APRIL 8 ጀምሮ ዳግም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ለጊዜው አለም አቀፍ በረራዎችን እንዲሁም ከውሃን ወደ/ከ ቤጂንግ የሚደረጉ በረራዎችን አያስተናግድም።

- ሞስኮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጨማሪ እርምጃ ወስዳለች የከተማይቱ ከንቲባ ፦ ማንኛውም አይነት ህዝባዊ ዝግጅት ሞስኮ ውስጥ እንዳይደረግ አግደዋል።

#BBC #REUTERS #XInhua
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከኢትዮጵያ፦

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለኮሮና ቫይረስ ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የአቅርቦት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቁመዋል። መንግስት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸው ተግባራትን ለመደገፍ ወጣት ባለሃብቶች ሊያደርጓቸው በሚገቡ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

- በደቡብ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል 3 ሺህ 642 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።

- የአማራ ክልል ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳልፏል።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ፓትሪያርክና መላው አህጉረ ስብከት ጽህፈት ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በከፊል እንዲዘጉ ወስኗል። ውሳኔውም ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ሲኖዶሱ መወሰኑን ቤተ ክርስቲያኗ ዛሬ በሰጠችው መግለጫ አስታውቃለች።

- በኦሮሚያ ክልል የሰራተኞች በአንድ ቦታ መቆየት እና የስራ ቦታ መጣበብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የቆየና በሀኪም ማስረጃ የተደገፈ የጤና እክል ያላቸው ሰራተኞች፣ ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁንም የጡረታ መውጫ ጊዜያቸው የደረሱ ሰራተኞች እረፍት እንዲወጡ ተወስኗል።

#FBC #ENA #PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የባንክ ቁጥሮች፦

ማንኛውም መጠን ያለውን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ተዘጋጅተዋል።

1. ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1000327017318

2. አዋሽ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 0130479475400

3. ዳሸን በንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 0444177190011

4. ዘመን ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1032410042463013

5. አባይ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦ 1022115562778011

ተጨማሪ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ይፋ የሚደረጉ ይሆናል። እስከዚያ ድረስ ተረጋግተን አስተዋጽኦ እናድርግ። በአብሮነት እንወጣዋለን!

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢትዮ ቴሌኮም፦

ጤና ይስጥልን ! የእርስዎ አስተዋፅዖ ለወገንዎ መዳን ነው! የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ከባድ ጉዳት ከወዲሁ እንከላከል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‘ምዕምኑ በሬን እዘጋለሁ፤ፈጣሪዬን አምናለሁ’ በሚል መርህ በመመራት ራሱን ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሊጠብቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳሰበ።

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጥንቃቄ እንዲደረግ በእየእምነት ተቋማቱ ጥሪ ቢተላለፍም በምዕመኑ ዘንድ የሚስተዋለው የጋራ አምልኮ ለቫይረሱ [COVID-19] መዛመት ስጋት ማሳደሩም ተጠቁሟል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 ምክንያት የሞተችው የ21 ዓመት ወጣት!

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የጤና እክል ያልነበረባት የ21 ዓመቷ ወጣት በኮሮናቫይረስ ከተያዘች በኋላ መሞቷን ወላጆቿ ተናገሩ።

"ቫይረሱ ልጃችንን ነጠቀን" ያሉት ወላጆች፤ ሁሉም እራሱን ከቫይረሱ ለመጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ክሎይ ሚድልተን የተባለችው ወጣት ምንም አይነት የጤና እክል ሳይኖርባት በዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ ከሞቱት መካከል አንዷ ነች ተብሏል።

የወጣቷ እናት ዲዓን በፌስቡክ ላይ "ይህን ቫይረስ እንደ ቀላል የምትገምቱት፤ እባካችሁ ዳግም አስቡበት። ከእራሴ ልምድ እንደተረዳሁት ይህ ቫይረስ የ21 ዓመት ሴት ልጄን ነጥቆኛል" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን ተጨማሪ 683 ሰዎች ሞቱ!

ጣልያን ውስጥ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 683 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 7,503 ደርሷል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 74,386 የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 5,210 ኬዝ በ24 ሰዓት ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን ውስጥ 4 ተጨማሪ ዶክተሮች ሞተዋል። አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የሞቱ የዶክተሮች ቁጥርም 29 ደርሷል። ከ5,000 የሚበልጡ የጤና ባለሞያችም በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#StayHomeSaveLives

ዶክተሮች ፣ ነርሶች ሁሉም የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ነው ፤ በኮቪድ-19 እየሞቱብን ነው ፣ እየተጠቁብን ነው፤ እባካችሁ ከፈጣሪ በታች ያሉን እነሱ ናቸውና #ጤና እንዲሆኑልን የሚሉንን እንስማ፤ የሚነግሩንን እንተግብር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር 4 ደረሰ!

ኤርትራ በኮሮና ቫይረስ በሽታ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ማግኘቷን የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከዱባይ ባለፈው ቅዳሜ ወደ ኤርትራ የገቡ የኤርትራ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል። በዚህም መሰረት በኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አራት ደርሷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር በተመሳሳይ አውሮፕላን የመጡና ንክኪ የነበራቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል።

ይህን ተከትሎም ከዛሬ ዕኩለ ሌሊት ጀምሮ ማንኛውም ወደ ኤርትራም ሆነ ከኤርትራ የሚደረጉ በረራዎች ለሁለት (2) ሳምንታት እንዲቆሙ ይደረጋል ተብሏል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሳዑዲ አረቢያ ለምትገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

ሳዑዲ አረቢያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ለ21 ቀናት የሚፀና (እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ድረስ የሚቆይ ሰዓት እልፍ አዋጅ የታወጀ መሆኑ ያታወሳል።

በዛሬው ዕለት የ2ቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ጠባቂ እና የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳዑዲ ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ከነገ ጀምሮ በስራ ላይ የሚውል ተጨማሪ ውሳኔዎች ይፋ አድርገዋል። እነህም፦

- ሳዑዲ አረቢያ በአስራ ሶስቱም የሳውዲ ግዛት የሚኖሩ ዜጎችን ነዋሪዎቿ በሙሉ ከሚኖሩበት ከተማ መውጣትም ሆነ ወደሌላ አካባቢ መሄድ አይፈቀድም

- ከሪያድ ፣ መካና መዲና ከተሞች መውጣትም ሆነ መግባት የተከለከለ ነው።

ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ሪያድ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia