TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጀርመን ቻንሰለር አንጌላ ሜርክል በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ዶክተር ጋር መገናኘታቻውን ተከትሎ ቻንስለሯ ኳራንታይን ላይ መሆናቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና የጸረ ኮሮና ቫይረስ ክትባት የመጀመርያ ደረጃ ሙከራ መጀመሯን አስታውቃለች። ቻይና ይህን ያስታወቀችው አሜሪካ ተመሳሳይ የክትባት ሙከራ ውጤታማነቱን በሲአትል ግዛት በሰዎች ላይ ከጀመረች በኋላ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ በምርምር ስራ ላይ የተሰማሩ ሳይንትስቶች ገዳዩን ቫይረሱን ለመከላከል ብርቱ ምርምር በማድረግ መሆናቸውንም የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

ቻይና ሙከራዋ እንደጎርጎርሳዊያኑ አቆጣጠር እስከ ዓመቱ መጨረሻ ሊዘልቅ እንደሚችል አስታውቃለች። በዚህም የኮቪድ 19 ክትባት የመጀመርያው ምዕራፍ ሙከራ ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞች ክትባቱን መውሰድ ጀምረዋል።

በጎ ዕድሜአቸው ከ18-60 ባለው ውስጥ የተካተተቱ 108 በጎ ፈቃደኞች በፕሮጀክቱ ውስጥ ተሳታፊ እየሆኑ ናቸው። በጎ ፈቃደኞቹ ሁለም የኮሮና ተሕዋሲ መጀመርያ ከተቀሰቀሰባት ማዕከላዊ የሕዋን ከተማ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ምንጭ፦ DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ የኮቪድ-19 ኬዝ 19 ደርሷል!

በሩዳንዳ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎች ቁጥር 19 ደርሰ። በዛሬው ዕለት 2 አዲስ የኮቪድ-19 ኬዞች ሪፖርት ተደርገዋል። አንደኛው የ32 ዓመት የሩዋንዳ ዜጋ ሲሆን ከዱባይ,UAE March 19 ወደ ሩዋንዳ እንደገባ ተገልጿል፤ ሁለተኛውም የ34 ዓመት የሩዋንዳ ዜጋ ሲሆን MARCH 20 ከዱባይ,UAE ወደ ሩዋንዳ የገባ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት ምሽት በሩዋንዳ መንግስት የተላለፈው ጥብቅ ትዕዛዝ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። በቪዲዮው ላይ የምትመለከቱት ከዚህ ቀደም በርካታ ሰዎች የሚተረማመሱበት የMusanze ባስ ማቆሚያ ነው። ዛሬ ባዶ ሆናል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy #Russia #COVID19

ሩስያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ በብርቱ እየተጠቃች ያለችውን ጣልያንን ለመደገፍ ሐኪሞችን እና የህክምና ቁሳቁስ እየላከች መሆኗን አስታውቃለች።

ሩስያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችዉን ጣልያንን ለመደገፍ በዘጠኝ የጭነት አውሮፕላኖች የሕክምና ባለሞያዎች እና ቁሳቁስ ወደስፍራው ለማጓጓዝ በችካሎቭስኪ ወታደራዊ ሰፈር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

በተልዕኮው ስምንት (8) ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ እና የጸረ ቫይረስ [COVID-19] ርጭት ተሽከርካሪዎች ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።

#AFP #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] እየታመሰች ነው። በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 32,356 ደርሷል። የሚገርመው 8,114 ኬዝ የተመዘገበው በ24 ሰዓት ነው። በቫይረሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 414 ደርሰዋል።

የአለም ሀገራት መሪ ነኝ ምትለዋ ፣ በሀብት ቁጥር አንዷ፣ በሁሉ ነገር ቀዳሚ ነኝ ፣ በቴክኖሎጂው ፣ በህክምናዬ ሁሉ ነገሬ የዘመነ ነው የምትለው አሜሪካ ለኮሮና ቫይረስ ተንበርክካለች። የተጠቂዎች ቁጥር ከዛሬ ነገ ይገታል ሲባል እየጨመረ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KENYA

በጎረቤት ሀገር ኬንያ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎች ቁጥር 15 ደርሷል። 8ቱ ዛሬ ሪፖርት የተደረጉ ናቸው። አፍሪካ ውስጥ ያሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቂዎች ቁጥር እያደር እየጨመረ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን!

"በሌላው ሀገር እየሆነ ያለውን የምትመለከቱ ከሆነ በእናተ በሀገራቹ ማድረግ ያለባችሁ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። መጀመሪያ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ተጋብተን ነበር አሁን ላይ ግን ምን እየሆነ እንዳለ አውቀናል። እኛ ጋር የሆነው በእናተ ላይ ሊሆን ይችላልና ለመግታት ማድረግ ያለባችሁን ከወዲሁ ጀምሩ አትቁሙ! የአንዱ ተሞክሮ ለሌላው ትምህርት ነውና ጥንቃቄን መሰረት አድርጋችሁ ተንቀሳቀሱ" - ዶ/ር ኢማኑኤላ #EBC

የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] መግታት ቀላል ነው፦

- የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
- ሰዎች በተሰበሰቡበት አይሂዱ
- ማህበራዊ ርቀትዎን ይጠብቁ
- በተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አይጠቀሙ
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ያዳምጡ
- የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን ይተግብሩ
- ስለ ኮቪድ ትክክለኛ መረጃ ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!

ተጨማሪ ፦ 8335 / 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ናቸው!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንደምን አደራችሁ?

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተሰምቷል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ እርምጃው የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።

አያይዘውም ህብረተሰቡ የትራንስፖርት ጥግግት መጠንን በመቀነስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ምንጭ፡ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ ማዕከል የመቆየት ግዴታ ተጀምሯል።

የጤና ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ ብሏል። ቆይታቸውም በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

ዲፕሎማቶች በኤምባሲዎቻቸው ተለይተው እንደሚቆዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የትራንዚት ተጓዦችም እስከ ቀጣዩ ጉዟቸው ድረስ በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ከዛሬ ጀምሮ በተወሰነው መሰረት በተለያየ መንገድ፣ ለተለያየ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖቻችን ወደ ኅብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ሁለት ሳምንታት ለየት ብለው የሚቆዩባቸውን ስፍራዎች አሰናድተናል። በተለይም ለቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን ለመሸፈን ለማይችሉ ዜጎቻችን ሙሉ ወጪያቸውን እኛ እንሸፍናለን።" - ኢ/ር ከንቲባ ታከለ ኡማ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ለመከላከል የምሽት መዝናኛ ክለቦች ዝግ እንደሚሆኑ የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ ከምሽት መዝናኛ ቤት እንዲዘጉ ከማድረግ በተጨማሪ የሺሻ እና ጫት ቤቶችን የማሸግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ከመሄዶ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ይገንዘቡ፦

- ለአንድ ታካሚ አንድ አስታማሚ ብቻ ነው መግባት የሚፈቀደው

- አሁን ያለውን የ#COVID-19 ስርጭትን ለመግታት ማንኛውንም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በስልክ ብቻ ለመጠየቅ ይሞክሩ

- ለድንገተኛ ህክምና እና የሀኪም ቀጠሮ ከሌላቹ በስተቀር ወደ ሆስፒታላችን ባለመምጣት  ከ#COVID-19 ስርጭት እራሶን እና ቤተሰቦን ይጠብቁ

- እድሜያችሁ ከ 40 አመት በላይ ሆኖ ተላላፊ ያልሆነ ህክምና (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ፣ ኩላሊት) ክትትል ያላችሁ በቀጠሮ ቀን የእርሶ ጤና አስችኳይ ሕመም ከሌሎት መድሀኒቱን የሚወስድሎት ወጣት ሰው ከቀጠሮ ካርድ ጋር አብረው እየላኩ ያለቀቦትን መድሀኒት ያሉበት ሆነው እዲወስድሎት ያድርጉ

- መግቢያ በሮች ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አድርጉ የሚሏችሁን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጉ (እጅን መታጠብ፤ የሙቀት ልየታ፤ ርቀትን ጠብቆ መሰለፍ . . .)

- በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፎን እና አፍንጫዎን በክንዶ ወይም መሀረብ/ሶፍት ይሽፍኑ

- አገልግሎት ለማግኘት በሚቆዩበት ጊዜ፤ ሰልፍ እና ወረፋ ሲጠብቁ ርቀቶን ቢያንስ በ1 ሜትር ይጠብቁ

[ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 በሽታ ይስፋፋል በሚል ስፔን በማድሪድ ከተማ የሚገኘውን የሀገሪቱን ትልቁ የኮንፈረንስ ማዕከል ጊዚያዊ ሆስፒታል /ተኝቶ መታከሚያነት/ በመቀየር አልጋ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አዘጋጅታለች።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ አስተዳደር እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ባይኖርም ችግሩ ቢከሰት ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት በነምበር ዋን ጤና ጣቢያ ከተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ በተጨማሪ የፈረንሣይ ሆስፒታልን ለዚሁ አገልግሎት ለማዋል ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ማግኘት ተችሏል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመግታት፣ ጥቆማ ለመስጠትና አጠቃላይ መረጃ እንዲሁም ምክር ለማግኘት ከፈለጉ በ6407 ነፃ የስልክ መስመር ይጠቀሙ። በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በሶማልኛ ቋንቋ የሚያስተናግዱ ባለሞያዎችን በ6407 ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጀርመን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ከሁለት (2) ሰው በላይ የሚደረግን ማንኛውንም መሰባሰብ በይፋ ከልክላለች።

ቻንስለሯ አንጌላ ሜርኬል ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት "የራሳችን ባህሪ ከሁሉም ነገር የበለጠ ውጤታማ ነው" ብለዋል።

ትላንት ከሁለት (2) ሰው በላይ መሰባሰብን የሚከለክለው ጠንከር ያለው እገዳ ከተላለፈ ከጥቂት ቆይታ በኋላ የመራሄተ መንግሥቷ ጽህፈት ቤት ቻንስለሯ ራሳቸውን ለይተው እንዳሉ የተገለፀው።

ባለፈው አርብ ቻንስለር አንጌላ ሜርኬልን የሕክምና ምርመራ ያደረገላቸው ሃኪም በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

ቃል አቀባዩ እንዳስታወቁት የ65 ዓመቷ ቻንስለር በቀጣዮቹ ቀናት ተከታታይ ምርመራዎች እየተደረጉላቸው ከቤት ሆነው ሥራቸውን የሚሰሩ ይሆናል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia