TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19 እንደ አናዱል ዘገባ ዛሬ በሀገሯ አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባት ሱማሊያ ከረቡዕ ጀምሮ ሁሉንም አለም አቀፍ በረራዎች ለ15 ቀን ማገዷን አሳውቃለች። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
የሱማሊያ የበረራ እገዳ እሮብ ይጀምራል!
የሶማሊያ መንግሥት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ለሁለት ሳምንታት ዓለምቀፍ በረራዎች ከሃገሪቱ እንዳይወጡም እንዳይገቡም ማገዱ ቀደም ብላችሁ ሰምታችኃል።
ረቡዕ የሚጀምረው የበረራ ዕገዳው የኢትዮጵያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያ ፣ የቱርክ እና የካታር አየር መንገዶችን ጨምሮ ከእና ወደሶማሊያ የሚበሩ ዓለምቀፍ አየር መንገዶችን ይመለከታል።
በየቀኑ ወደሶማሊያ ጫት ጭነው የሚጓዙ በርካታ የኬንያ አውሮፕላኖችንም ይከለክላል። ለሰብዓዊ ረድዔት በረራዎች የተለየ ፈቃድ እንሰጣለን ሲል የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል።
ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#SHARE #ሼር
የኮሮና ቫይረስን [COVID-19] የተመለከተ ማንኛውንም ጥያቄ እና አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ ለመስጠት በ6929 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም ትችላላችሁ ይላችኃል የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ!

ትግራይ ክልል!
እስካሁን በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቃ አንድም ግለሰብ የለም። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ጥቆማ የተሰጠባቸው 7 ሰዎች ናቸው። ከ7ቱ ውስጥ 2ቱ በWHO የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ አልነበሩም ፤ 5ቱ ግን አሟልተው በመገኘታቸው ናሙናቸው ተወስዶ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል ።
#የትግራይክልልጤናቢሮ #ኮቪድ19 #ቪኦኤ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#COVID19
በአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠረጠረ ሰው አለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨድ መረጃ ሀሰት መሆኑን ሆስፒታሉ አሳውቋል።
እስካሁን በዚህ በሽታ ተጠርጥሮ የገባ ሰው አለመኖሩን ይፋ ያሰረገው ሆስፒታሉ በቂ ዝግጅት እንዳደረገም ገልጿል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚኖሩ አዲስ መረጃዎችን በፌስቡክ ገጹ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
Via @tikvahethmagazine
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠረጠረ ሰው አለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨድ መረጃ ሀሰት መሆኑን ሆስፒታሉ አሳውቋል።
እስካሁን በዚህ በሽታ ተጠርጥሮ የገባ ሰው አለመኖሩን ይፋ ያሰረገው ሆስፒታሉ በቂ ዝግጅት እንዳደረገም ገልጿል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚኖሩ አዲስ መረጃዎችን በፌስቡክ ገጹ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
Via @tikvahethmagazine
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
አስቸኳይ መልዕክት!
የግል ከፍተኛ ትምህርት የመደበኛ ፣ የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ትምህርትና ስልጠና ለሁለት ሳምንታት እንዲቋረጡ ትዕዛዝ ተላልፏል።
በመሆኑም የሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፣ አካዳሚክ እና የአስተዳራዊ ሰራተኞች በሙሉ ለ2 ሳምንታት በየቤታቸው እንዲቆዩ ተብሏል።
በቆይታቸው ባሉበት ሆነው ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መመሪያዎችን ተከትለው ጥንቃቄ በማድረግ በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ ለ2 ሳምንታት የሚቆዩ #HERQA ማምሻውን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በመጨረሻም ይህን እናስታውሳችሁ!
ውድ ቤተሰቦቻችን ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ቀላልና ውጤታማ እርምጃዎች፦
- አዘውትሮ በአግባቡ እጅን በሳሙና መታጠብ
- ለሰላምታ በእጅ አለመጨባበጥ
- ፊትን በእጅ አለመንካት
- ትኩሳት፣ ሳል፣ ማስነጠስ ያሉ ምልክቶች ካጋጠሙን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ
- በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉበት ወቅት ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ሌሎችን እንዳይበክሉ መጠንቀቅ
ሰላም እደሩ!

እንዴት አደራችሁ?
ውድ ቤተሰቦቻችን ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ለዛሬ ይህን ልንል ወደናል ፤ እያንዳንዱን በሶሻል ሚዲያ የሚሰራጭ መልዕክት፣ መረጃ ምንጭ ሳንጠይቅ የምንጠቀም ከሆነ ይህን ቫይረስ ለመከላከል አንችልም። እኛም የተወራውን ሁሉ ሳይሆን የጤና ባለሞያዎች፣ ከጤና ሚኒስቴር የሚደርሱንን መልዕክቶች ብቻ ነው የምናጋራው።
እርግጥ እኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን ውጭ ሀገራትም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ብዙ ሀሰተኛ መረጃ ይሰራጫል፤ ይህ ለሚያደርጉ ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው፥ እኛ ግን ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ የሚሰራስጩትን መረጃዎች ብቻ እንድንቀበል፣ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንድተገብር እንመክራለን።
ሀሰተኛ መረጃዎች፣ እና መልዕክቶች ኮሮና ቫይረሱስን በመከላከል ላይ ሌላተጨማሪ ችግር ይዘው መምጣታቸው አይቀርምና ተማሪዎች ፣ ሰራተኞችም ፣ ወላጆችም፣ በተለያየ መልኩ ሀገራችሁን የምታገለግሉም በእርጋታ ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰራጩ መልዕክቶችን ተግብሩ።
መደናገጥ፣ ፍራቻ ተጨማሪ ችግር ይፈጥራል!

አዲስ አበባ ነዋሪዎች!
በመዲናዋ ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እንደሌለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤት ላይ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝም የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።
ሆኖም ግን ይህንን ሽፋን በማድረግም መድሀኒት እንረጫለን በማለት የዘረፋ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ ተሰምቷል።
ስለሆነም የመድሀኒት ርጭቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤትና የተገለገሉባቸው ቁሳቁሶች ብቻ ላይ የሚደረግ መሆኑን ነው የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀው።
ከዚያ ውጪ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ አለመሆኑ ታውቆ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።
#FBC #MayorOfficeOfAA

አሜሪካ ኮሮና ቫይረስን የሚያጠቃ እና በሽታውን ለመከላከል ያስችላል ያለችውን ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ ሙከራዋን አድርጋለች፡፡
አራት በጎ ፈቃደኛ በሽተኞችም ክትባቱን ዋሽንግተን በሚገኘው የምርምር ተቋም መቀበላቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ክትባቱ Covid-19 ወይም ኮሮና ቫይረስን የማያስከትል ሲሆን በቫይረሱ ምክንያት የሚፈጠሩ በሽታ አምጪ ተዋህሲያን ግን ሊገድል እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ባለሙያዎቹ እንደሚናገሩት ይህ ክትባት ወይም ሌሎች በምርምር ላይ ያሉ መድኃኒቶችም ቢሆን ከቫይረሱ ያድናሉ ብሎ በሙሉ ልብ ለመናገር በርካታ ወራቶችን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8

#COVID19 "ከጥቂት ሳምንታት በኃላ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባት ይኖረናል!" - የእስራኤል ሳይንቲስቶች የእስራኤል ሳይንቲስቶች የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ክትባትን ለማዘጋጀት መቃረባቸው እየተነገረ ይገኛል። ጥረቱ በታሰበው ልክ የሚሄድ ከሆነ ክትባቱን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ማዘጋጀት እና ከ3 ወራት በኃላ ለገበያ ማቅረብ እንደሚቻል የእስራኤል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ኦፊር…
#COVID19
የእስራኤል ሳይንቲስቶችም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባትን አዘጋጅተው አጠናቀዋል። በመጪዎቹ ቀናት ለዓለም ህዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ ግን አገልግሎት ላይ እስኪውል ድረስ ጥቂት ወራት እንደሚወስድ ET አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእስራኤል ሳይንቲስቶችም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ክትባትን አዘጋጅተው አጠናቀዋል። በመጪዎቹ ቀናት ለዓለም ህዝብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ ግን አገልግሎት ላይ እስኪውል ድረስ ጥቂት ወራት እንደሚወስድ ET አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እባካችሁ በተጨናነቁ ታክሲዎች፣ ባሶች ጎዞ ከማድረግ ተቆጠቡ ፤ በተጨማሪ በምትሄዱባቸው ታክሲዎችና ባሶች መስኮቶች በመክፈትም በቂ አየር እንዲኖር አድርጉ። ከወረዳችሁ በኃላም በተቻለ መጠን እጃችሁን በንፁህ ውሃና ሳሙና መታጠቡን እንዳትዘነጉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty
አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸው ተገለፀ።
የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አወሉ አብዲ እና የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ምደባ መካሄዱንም ነው የገለፁት።
በቀጣይም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዞኖች እና ወረዳዎች እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።
#FBC

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፦
በሀገር ውስጥ የተመረተ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በከተማዋ ወደሚገኙ የከነማ ፋርማሲዎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛል።
በከተማዋ እየተሰራጨ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር 200 ሺህ ሊትር የሚሆን ሲሆን በከነማ ፋርማሲዎች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንጽህና መጠበቂያውን ማግኘት እንደሚችል ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

#DrTedrosAdhanom
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ምልክቱ በታየባቸው ሰዎች ላይ እየተደረገ ያለው ምርመራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ፣ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመቀነስ በሰዎች መካከል ግንኙነትን መቀነስ ፣ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት እንዲሁም ሕዝብ በብዛት የሚሰበሰብባቸው ኩነቶችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ መኖሩን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ በቫይረሱ ለተጠረጠሩ ሰዎች ምርመራ ማድረግ፣ ለይቶ ማቆየት እና ግንኙነቶችን መቆጣጠር ላይ ብዙ ሥራ ይጠይቃል ብሏል፡፡
ምንጭ፡- የዓለም ጤና ድርጅት፣ ኢቲቪ

እንደ ዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ እስከ ትላንት ምሽት ድረስ በመላው ዓለም በ120 ሀገራት ውስጥ 1.5 ሚሊየን ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪ ድርጅቱ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎጂ ቢሆኑም ፣ ወጣቶች እና ሕፃናትም በቫይረሱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተጨማሪ ድርጅቱ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎጂ ቢሆኑም ፣ ወጣቶች እና ሕፃናትም በቫይረሱ መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ ከነበሩ 113 ሰዎች መካከል 74ቱ ነፃ መሆናቸው በምርመራ ተረጋግጦ ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የቀሪዎቹ ውጤት እየተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፦
በሽታውን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት የመጡ ተጓዞችን በተጨማሪ በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን ማረጋገጥ ከተቻለው 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸውን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት (992) ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የሚደረግ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት (1285) የሚሆኑት ደግሞ ለ 14 ቀን የጤና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ጤንነታቸው በመረጋገጡ የጤና ክትትላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

ከኮቪድ-19 በሽታ ጋር ተመሳሳይ ምልክቶች በማሳየታቸው እንዲሁም ከመጀመሪያው ታማሚ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት 113 ተጠርጣሪዎች በተለያየ ጊዜ በለይቶ መቆያ ማእከል እንዲቆዩና የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ 74ቱ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
አምስቱ ( 5) የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ታማሚዎች ሲሆኑ በለይቶ ማቆያ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ሰላሳ አራቱ (34 ) ተጠርጣሪዎች በለይቶ ማቆያ ሆነው የለቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

የ5ቱ ታማሚዎች ጤናን በተመለከተ፦
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 5ቱ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ታማሚዎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በዛሬው መግለጫ ላይ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 5ቱ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ታማሚዎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በዛሬው መግለጫ ላይ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 81 ደረሰ!
በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሟቾች ቁጥር 81 መድረሱ ተሰምቷል። በዋሽንግተን ስቴት 6 ተጨማሪ ሞት ተመዝግቧል። የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል በዋሽንግተን ዲሲ ባር እና ሬስቶራንቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሟቾች ቁጥር 81 መድረሱ ተሰምቷል። በዋሽንግተን ስቴት 6 ተጨማሪ ሞት ተመዝግቧል። የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል በዋሽንግተን ዲሲ ባር እና ሬስቶራንቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሶማሊላንድ የድህንነት ኃላፊ ተገደሉ!
የሶማሊላንድ የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አብን ገኒ ጎሃድ በላስ አኖድ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ትናንት ምሽት በጥይት ተመተው መገደላቸውን አልሶማል አልጀጂድ ዘግቧል።
ግድያው የተፈፀመው በታጣቂዎች ሲሆን ገዳዮቹም ሸሽተው ማምለጣቸድ ተነግሯል። ሟቹ የደህንነት ኃላፊ ሶል የምትባል አካባቢ አስተዳዳሪ የነበሩት ሃሰን ሼክ ማህሙድ ላይ የተደረገውን ግድያ የክስ ፋይል ይመሩ ነበር ተብሏል።
ምንጭ፦ አል-ዓይን