TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኤርትራ እና ኮሮና ቫይረስ ስጋት!

ምንም እንኳ ኮሮና ቫይረስ በኤርትራ ሪፖርት ባይደረግም፤ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር የበሽታውን ስርጭት ቀድሞ ለመከላከል በማሰብ ዜጎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የኤርትራ ዜጋም ሆነ ነዋሪ፤ አስቸኳይ ካልሆነ በቀር በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ከሚደረጉ ጉዞዎች እንዲቆጠቡ ጤና ጥበቃ ሚንስቴሩ አሳስቧል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ዜጎች እራሳቸውን እንዲያርቁ ምክር አዘል ማሳሰቢያዎች ተላልፈዋል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤርትራ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር!

የኤርትራ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ኮቪድ-19 ቀድሞ ለመከላከል በማሰብ ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ለህዝቡ ያስተላለፈው ማሳስቢያ።

Via Yemane G.Meskel
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምክር ቤቱ ስብሰባ በኮቪድ-19 ስጋት ተሰረዘ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ሰረዘ። ምክር ቤቱ ሊያካሂድ የነበረውን መደበኛ ስብሰባ የሰረዘው በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደሆነ ነው ያስታወቀው፡፡ የስብሰባውን ጊዜ ወደፊት ለአባላቱ እንደሚያሳውቅም ገልጿል፡፡

ምንጭ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ጋር ተያይዞ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ አስተላልፏል፡፡

Tikvah University @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ፊት ለፊትና በክፍል ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶች እንዲቀሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ለተማሪዎች የተዘጋጁ መማሪያ ጽሁፎች ፣ ማጣቀሻ መፅሐፍት ፣ የመፅሐፍት ቅጂዎች እና በኢንተርኔት የሚቀርቡ ፅሁፎችን በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግላቸው/በመኝታ ክፍላቸው ሆነው እንዲያነቡ እንዲያደርግም ብሏል።

በተጨማሪም መምህራን በኢሜይል እና በተለያዩ ስልቶች የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲያስቀጥሉ እንዳያደርጌ፣ ይህም በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን በየደረጃውና በተዋረድ ክትትል እንዲደረግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በግብጽ የሟቾች ቁጥር 3 ደርሰዋል!

በግብፅ የኮሮና ቫይረስ ሟቾች 3 ደርሰዋል። 150 ሰዎች ዳግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከነዚህም ውስጥ 80 የሚያህሉት የግብፅ ዜጎች ናቸው። ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሀሙስ ጀምሮ እስከ MARCH 31 ድረስ በረራዎች እንደሚታገዱ ይፋ አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማሌዥያ ለቀጣዮቹ ሁለት (2) ሳምንታት የእምነት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች ፣ የንግድ ተቋማት ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ወስናለች።

ወደሀገሪቱ የሚደረጉ እንዲሁም ከሀገሪቱ ውጭ የሚደርጉ ጉዞዎችም ታግደዋል። ሱፐርማርኬቶች፣ የነዳጅ ማደያዎች፣ ባንኮች፣ ፋርማሲዎች ክፍት እንደሆኑ ይቆያሉ።

በማሌዥያ በ24 ሰዓት ውስጥ 138 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል። ይህም አጠቃላይ የቫይረሱን ተጠቂዎች ወደ 566 ከፍ አድርጎታል። እስካሁን በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት የተመዘገበ ሞት የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ!

ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ዋጋን በጋራ በመወሰን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር እና በነዋሪው ላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሲያደርጉ በተገኙ 83 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ችግሩን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ሀይል አስታውቋል።

ምንጭ፦ የአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19 እንደ አናዱል ዘገባ ዛሬ በሀገሯ አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባት ሱማሊያ ከረቡዕ ጀምሮ ሁሉንም አለም አቀፍ በረራዎች ለ15 ቀን ማገዷን አሳውቃለች። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
የሱማሊያ የበረራ እገዳ እሮብ ይጀምራል!

የሶማሊያ መንግሥት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ለሁለት ሳምንታት ዓለምቀፍ በረራዎች ከሃገሪቱ እንዳይወጡም እንዳይገቡም ማገዱ ቀደም ብላችሁ ሰምታችኃል።

ረቡዕ የሚጀምረው የበረራ ዕገዳው የኢትዮጵያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያ ፣ የቱርክ እና የካታር አየር መንገዶችን ጨምሮ ከእና ወደሶማሊያ የሚበሩ ዓለምቀፍ አየር መንገዶችን ይመለከታል።

በየቀኑ ወደሶማሊያ ጫት ጭነው የሚጓዙ በርካታ የኬንያ አውሮፕላኖችንም ይከለክላል። ለሰብዓዊ ረድዔት በረራዎች የተለየ ፈቃድ እንሰጣለን ሲል የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

የኮሮና ቫይረስን [COVID-19] የተመለከተ ማንኛውንም ጥያቄ እና አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ ለመስጠት በ6929 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም ትችላላችሁ ይላችኃል የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል!

እስካሁን በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቃ አንድም ግለሰብ የለም። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ጥቆማ የተሰጠባቸው 7 ሰዎች ናቸው። ከ7ቱ ውስጥ 2ቱ በWHO የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ አልነበሩም ፤ 5ቱ ግን አሟልተው በመገኘታቸው ናሙናቸው ተወስዶ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል ።

#የትግራይክልልጤናቢሮ #ኮቪድ19 #ቪኦኤ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19

በአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠረጠረ ሰው አለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨድ መረጃ ሀሰት መሆኑን ሆስፒታሉ አሳውቋል።

እስካሁን በዚህ በሽታ ተጠርጥሮ የገባ ሰው አለመኖሩን ይፋ ያሰረገው ሆስፒታሉ በቂ ዝግጅት እንዳደረገም ገልጿል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚኖሩ አዲስ መረጃዎችን በፌስቡክ ገጹ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

Via @tikvahethmagazine
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አስቸኳይ መልዕክት!

የግል ከፍተኛ ትምህርት የመደበኛ ፣ የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ትምህርትና ስልጠና ለሁለት ሳምንታት እንዲቋረጡ ትዕዛዝ ተላልፏል።

በመሆኑም የሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፣ አካዳሚክ እና የአስተዳራዊ ሰራተኞች በሙሉ ለ2 ሳምንታት በየቤታቸው እንዲቆዩ ተብሏል።

በቆይታቸው ባሉበት ሆነው ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መመሪያዎችን ተከትለው ጥንቃቄ በማድረግ በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ ለ2 ሳምንታት የሚቆዩ #HERQA ማምሻውን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመጨረሻም ይህን እናስታውሳችሁ!

ውድ ቤተሰቦቻችን ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ቀላልና ውጤታማ እርምጃዎች፦

- አዘውትሮ በአግባቡ እጅን በሳሙና መታጠብ

- ለሰላምታ በእጅ አለመጨባበጥ

- ፊትን በእጅ አለመንካት

- ትኩሳት፣ ሳል፣ ማስነጠስ ያሉ ምልክቶች ካጋጠሙን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ

- በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉበት ወቅት ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ሌሎችን እንዳይበክሉ መጠንቀቅ

ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንዴት አደራችሁ?

ውድ ቤተሰቦቻችን ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!

ለዛሬ ይህን ልንል ወደናል ፤ እያንዳንዱን በሶሻል ሚዲያ የሚሰራጭ መልዕክት፣ መረጃ ምንጭ ሳንጠይቅ የምንጠቀም ከሆነ ይህን ቫይረስ ለመከላከል አንችልም። እኛም የተወራውን ሁሉ ሳይሆን የጤና ባለሞያዎች፣ ከጤና ሚኒስቴር የሚደርሱንን መልዕክቶች ብቻ ነው የምናጋራው።

እርግጥ እኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን ውጭ ሀገራትም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ብዙ ሀሰተኛ መረጃ ይሰራጫል፤ ይህ ለሚያደርጉ ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው፥ እኛ ግን ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ የሚሰራስጩትን መረጃዎች ብቻ እንድንቀበል፣ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንድተገብር እንመክራለን።

ሀሰተኛ መረጃዎች፣ እና መልዕክቶች ኮሮና ቫይረሱስን በመከላከል ላይ ሌላተጨማሪ ችግር ይዘው መምጣታቸው አይቀርምና ተማሪዎች ፣ ሰራተኞችም ፣ ወላጆችም፣ በተለያየ መልኩ ሀገራችሁን የምታገለግሉም በእርጋታ ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰራጩ መልዕክቶችን ተግብሩ።

መደናገጥ፣ ፍራቻ ተጨማሪ ችግር ይፈጥራል!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ነዋሪዎች!

በመዲናዋ ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እንደሌለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤት ላይ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝም የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

ሆኖም ግን ይህንን ሽፋን በማድረግም መድሀኒት እንረጫለን በማለት የዘረፋ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ስለሆነም የመድሀኒት ርጭቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤትና የተገለገሉባቸው ቁሳቁሶች ብቻ ላይ የሚደረግ መሆኑን ነው የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀው።

ከዚያ ውጪ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ አለመሆኑ ታውቆ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

#FBC #MayorOfficeOfAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አሜሪካ ኮሮና ቫይረስን የሚያጠቃ እና በሽታውን ለመከላከል ያስችላል ያለችውን ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ ሙከራዋን አድርጋለች፡፡

አራት በጎ ፈቃደኛ በሽተኞችም ክትባቱን ዋሽንግተን በሚገኘው የምርምር ተቋም መቀበላቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ክትባቱ Covid-19 ወይም ኮሮና ቫይረስን የማያስከትል ሲሆን በቫይረሱ ምክንያት የሚፈጠሩ በሽታ አምጪ ተዋህሲያን ግን ሊገድል እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ባለሙያዎቹ እንደሚናገሩት ይህ ክትባት ወይም ሌሎች በምርምር ላይ ያሉ መድኃኒቶችም ቢሆን ከቫይረሱ ያድናሉ ብሎ በሙሉ ልብ ለመናገር በርካታ ወራቶችን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እባካችሁ በተጨናነቁ ታክሲዎች፣ ባሶች ጎዞ ከማድረግ ተቆጠቡ ፤ በተጨማሪ በምትሄዱባቸው ታክሲዎችና ባሶች መስኮቶች በመክፈትም በቂ አየር እንዲኖር አድርጉ። ከወረዳችሁ በኃላም በተቻለ መጠን እጃችሁን በንፁህ ውሃና ሳሙና መታጠቡን እንዳትዘነጉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia