TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል!

1 ብቻ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ የተመዘገበባቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 24 ሰዓት ሳይሞላቸው ጥብቅ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ሀገራቱ የቫይረሱን መሰራጨት ለመቆጣጠር የወሰዱት እርምጃም በርካቶች አበረታተዋል።

ሩዋንዳ ፦

- ከነገ ጀምሮ በሩዋንዳ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ
- የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘጉ
- የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ሰዎች እንዳይሰበሰቡ
- ሰርግ፣ የስፖርት ክንውኖች ወደሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ

ኬንያ፦

- ማንኛውም ሰው የሚሰበሰብበት ዝግጅት እንዳይደረግ
- በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሁ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሰረዙ
- የአደባባይ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እንዳይደረጉ

ሱዳን፦

- ለአንድ ወር ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ
- ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘጉ
- ሰው በብዛት የሚሰባሰብባቸው ዝግጅቶች እንዲታገዱ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኬንያ እርምጃ! ኬንያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምክንያት በርካታ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው ማንኛውም አይነት ዝግጅቶች በሀገሪቱ ውስጥ እንዳይደረጉ አግዳለች። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ስፖርታዊ ውድድሮችን ጨምሮ፣ በአደባባይ የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እንዳይደረጉ ታግዷል። ትምህርት ቤቶች ግን እንደማይዘጉ ተነግሯል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬኒያ የትምህርት ተቋማት እንዲዘጉ ተባለ!

ኬንያ ባለፈው አርብ ካስመዘገብችው አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በተጨማሪ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ የትምህርት ተቋማት ስራ እንዲያቆሙ ትእዛዝ መተላለፉን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በUAE ተጨማሪ 12 የኮሮና ቫይረስ ኬዞች መመዝገባቸው ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 98 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተግባራዊ ያድርጉ፦

- እጅዎን በውሃና በሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ ወይም አልኮል ባለው የጀርም ማጽጃ /ሳኒታይዘር/ እጅዎን ያፅዱ፤

- ሳል እና ማስነጠስ ካለባቸው ሰዎች ቢያንስ በ2 ሜትር ወይም በ2 እርምጃ ይራቁ፤

- እጅዎን ሳይታጠቡ አይንዎን ፣ አፍዎን እና አፍንጫዎን አይንኩ፤

- ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች አይሂዱ፤

- በእጅ መጨባበጥ ያቁሙ፤

- ያልበሰሉ የእንስሳትና የአሳ ምግቦችን አይመገቡ፤

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሶስቱ (3) ግለሰቦች የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፤ እስከ አሁን ግለሰቦቹ የሚያሰጋ ሁኔታ አልታየባቸውም። ከነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች የማግኘት ስራም መጀመሩን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦

- በጣም የሚጨናነቅ ቦታዎች ላይ አለመገኘት ይመከራል።

- አውቶብሶች ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶች እንዲከፈቱ እና አየር እንዲገባ ማድረግ ተገቢ ነው።

- በተቻለ መጠን የተጨናነቀ አውቶብስ ፣ ሌሎችም የትራንስፖርት አማራጮችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል።

- በተጨናነቁ የህዝብ ትራንስፖርቶች ከመጠቀም ይልቅ ከተቻለ በእግር መሄድ ይመከራል።

- የጉንፋን ስሜት፣ ትኩሳት፣ ህመም የሚሰማችሁ ሰዎች ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ከመገኘት ተቆጠቡ። በተጨማሪ ወደስራም፣ ወደ ትምህርት ቤትም ባይሄዱ ይመከራል።

#ሼር #SHARE

#DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ 'ሳቢያን ሆስፒታል አንድ ታማሚ ኮሮና ቫይረስ ይዞታል' በሚል የሚነዛው ወሬ ሀሰተኛ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የድሬዳዋ ዝግጅት፦

- ኮሮና ቫይረስ ወደ ድሬዳዋ ሊገባ የሚችልባቸው መንገዶች [የከተማዋ መግቢያ በሮች] ከሱማሌ ክልል ጋር በመተባበር በየዕለቱ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

- በድሬዳዋ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የምርመራ ስራ እየተሰራ ነው።

- ወደ ኢንዲስትሪ ፓርኩ የሚመጡ አዲስ ቻይናዊያንን የመነጠል ስራና በCCECC ሆቴል ተለይተው እንዲቀመጡ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰበር ዜና!

ወደ ኳታር የሚደረጉ ማንኛውም የጉዞ በረራዎች [ከትራንዚት እና ከካርጎ በስተቀር] ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለ14 ቀናት ያክል ተከልክለዋል። የቀጠር ዜጎች ከየትኛውም አገር ወደ ዶሃ መግባት ይችላሉ ተብሏል።

መንግስት ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ እንዲሁም የአገሪቱ ነዋሪ ወደ ውጭ አገር ጉዞ እንዳያደርጉ አሳስቧል። እድሜያቸው ከ 55 በላይ የሆኑ፣ ነፍሰ ጡሮች እና ከባድ ህመም ያለባቸው ሰዎች ሥራቸውን በርቀት እንዲሰሩ ተወስኗል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እንዲቆሙ ተወስኗል። የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ ትምህርታቸውን በርቀት መማር ይጀምራሉ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤምባሲ -ዶሃ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጤና ሚኒስቴር! የአምቡላንስ መኪና መስታወት ሰብሮ ያመለጠው ከሳውዲ አረቢያ የመጣው ግለሰብ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር ውሎ እንደሚገኝ ያታወቃል። ጤና ሚኒስቴር ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ግለሰቦች የመለየት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፌዴራል እና ከለጋምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩ የጋር…
#UPDATE

የለጋምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት መረጃ ከአምቡላንስ አምልጦ የጠፋው የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ግለሰብ ተሳፍሮበት በነበረው አውቶብስ ውስጥ የነበሩ 74 የሚደርሱ ሰዎች ቦሩሜዳ ወደሚገኘው የማቆያ ስፍራ ተወስደዋል።

በሌላ በኩል የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ፥ ግለሰቡ ምልክቶች ታዩበት እንጂ በበሽታው መያዙ አልተረገጠም፤ ማኅበራዊ ድረ ገፆችና አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት በገፆቻቸው ይዘውት የወጡት ዘገባ ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ተችቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- አውስትራሊያ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ወደ ግዛቷ የሚገባ ሰው ራሱን ለ14 ቀናት ለይቶ እንዲያቆይ አዛለች። ኒውዚላንድም ቀደም ሲል ተመሳሳይ ርምጃ ወስዳለች።

- አየርላንድና ታላቋ ብሪታኒያን ጨምሮ የአውሮፓ ኅብረት የኮሮናቫይረስ እገዳን ከመጪው ማክሰኞ ጀምረው ሊተገብሩ ነው።

- ብሪታኒያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ በመጨመሩ 21 ደርሷል። ይህንንም ተከትሎ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ደብዳቤ ጽፈዋል።

- ታላቋ ብሪታኒያ ወሳኝ ጉዞዎች ካልሆኑ በስተቀር ወደ ስፔን የሚደረገውን ማንኛውንም ጉዞ እንድታቋርጥ ተነግሯታል።

- ካናዳ በውጭ የሚኖሩ ዜጎቿ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርባለች። ቺሊ ደግሞ በመርከብ ተጉዘው የመጡ 1300 ዜጎቿን በለይቶ ማቆያ አስቀምጣለች። በሌላ በኩል በእስራኤል ከዛሬ ጀምሮ የንግድ ተቋማት በከፊል እንዲዘጉ ተዳርጓል።

[በቢቢሲ አማርኛ ጋዜጠኞች]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠቂዎች ቁጥር 61 ደርሷል። በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 23 አዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል።

- በሞሮኮ 10 ተጨማሪ አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ተመዝግበዋል። በሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች 28 ደርሰዋል።

- በቱሪዝያ 2 አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ዛሬ ተመዝግበዋል። የቫይረሱ ተጠቂዎች 20 ደርሰዋል።

- ጋና በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 6 ከፍ ብሏል።

- በአይቮሪኮስት 2 የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠቂዎች ዛሬ ተገኝተዋል። አጠቃላይ ተጠቂዎች 4 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ምህላ ታውጇል'

ዛሬ 3 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ምእመናን በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚሰጡ መመሪያዎችን እንዲተገብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳስበዋል።

የቤተክርስትያኗ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቀሪው የዐቢይ ፆም ጊዜያት በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት የምህላ ጸሎት እንዲደረግም አውጀዋል፡፡

#EOTCTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማጠቃለያ!

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 6,492 የደረሰ ሲሆን 168,834 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 76,598 ደርሰዋል።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች፦

- በፍፁም እርጋት እራሳችሁን ጠብቁ። ከጤና ሚንስቴር እና የጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ሳትሰለቹ ተግብሩ።

- ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በፍፁም እንዳትገኙ፣ የቫይረሱ ስርጭት ወዳለባቸው ሀገራትም ጉዞ ካላችሁ ሰርዙ።

- የእጃችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትረሱ፣ ከኮቪድ-19 ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ከተሰማችሁ በአስቸኳይ ለህክምና ተቋም ጥቆማ ስጡ፣ በሶሻል ሚዲያ ወሬዎች አትሸበሩ።

More 8335

ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጉዳዩ ፦ ማስታወቂያዎች ለጥቂት ቀናት ማቆማችንን ስለማሳወቅ!

ለድርጅት ባለቤቶች ለሆናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት!

በእንዲህ ያለ ወቅት በተለይም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየተፈጠሩ ባሉ ክስተቶች ዙሪያ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲያገኙ ፣ በተለያዩ ሚዲያዎችም የሚሰራጩ መረጃዎች በፍጥነት ይደርሳቸው ዘንድ እንደምንሰራ ይታወቃል።

እንዲህ ያለሁ ክስተቶች ሲፈጠሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልካች ቁጥር በሰዓታት ውስጥ በመቶ ሺህ የሚቆጠር እንደሆነም ይታወቃል፤ ይህን መሰል ወቅት ወቅታዊ ጉዳዮች አሳስቧቸው መረጃ በሚከታተሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ስልኮች ላይ ምንም አይነት የድርጅት ማስታወቂያ አናሰራጭም።

ይህ አሁን የጀመርነው እንዳልሆ እና ከዚህ ቀደምም ለበርካታ ጊዜያት ስናደርግ የቆየነው እንደሆነም ለማስታወስ እንወዳለን። ረጅም ጊዜ ከቲክቫህ ጋር አብራችሁ የቆያችሁ ድርጅቶችም አሰራራችን እና የምንከተለውን መንገድም እንደምታውቁት ተስፋ እናደርጋለን።

የቲክቫህ አባል የሆናችሁ የድርጅት ባለቤቶች ማስታወቂያ የማስነገር ሙሉ መብት እንዳላችሁ ብናውቅም፤ በእንዲህ ያሉ ወቅቶች ግን የድርጅቶቻችሁን ማስታወቂያ ማስተናገድ አንችልም! ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን።

ከጥቂት ቀናት በኃላ ማስታወቂያዎች ይቀጥላሉ!

[email protected]
0919743630
@tsegabwolde

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ከተመዘገበባቸው አገራት የሚመጡ ስዎች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ እገዳ የጣለች ሲሆን ኬንያዊያንና የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ብቻ መግባት የተፈቀደላቸው ሲሆን ለ14 ቀናት እራሳችውን አግልለው መቆየት ይጠበቅባቸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጃፓናዊው ኦሮሚያ ክልል የተንቀሳቀሰው 1 ቀን ነው!

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልቃድር ገልገሎ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆነው ጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች በተጨማሪ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ፥ 'ማን የት ነበር? ማን ጋር ነበር? ተብሎ እየተፈለገ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ጃፓናዊው ግለሰብ አንድ ቀን ብቻ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንደሄደ ጠቁመዋል።

ግለሰቡ በአዳማ አቋርጦ ወደ ዴራ አርሲ ሄዶበት የነበረው ዋነኛው ምክንያት ከሚሰራበት የተርአድኦ ድርጅት ስራ ጋር በተያያዘ የትምህርት ጉዳይ ለመከታተለ እንደሆነ ነው ዶ/ር አብዱልቃድር የተናገሩት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መዘናጋቱ ሀገሪቱን ዋጋ እንዳያስከፍላት!" - ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት

የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔዎች ላይ መዘግየት ይታይበታል ሲሉ መልዕክቶቻቸውን እየላኩ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ቅሬታ አሰምተዋል።

ጎረቤት ሀገራት እንኳን የወሰዱትን ፈጣን የጥንቃቄ እርምጃ የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት ሊወስድ እንዳልቻልም ጠይቀዋል። የቫይረሱ በፍጥንነት መስፋፋት እየታወቀ እንዲህ ያለ መዘንጋት መታየቱ እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።

ሩዋንዳ ፣ ሱዳን ፣ ኬንያ ሌሌችም ሀገራት ከወዲሁ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ለመግታት ድንበራቸውን መዝጋት፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት ፣ ስፖርታዊ ክንውኖችን መሰረዝ፣ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን መሰረዝ ፣ ከዚህ አለፍ ሲልም ከቫይረሱ ተጠቂ ሀገራት ማንኛውም ዜጋ እንዳይገባ እስከማገድ ደርሰዋል።

4 የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚገኙባት ኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ጠንካራ እርምጃ አለመውሰዱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አምርረው ተችተዋል። ይህ መዘናጋት ሀገሪቱን ዋጋ እንዳያስከፍላትም አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ 4 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በሩዋንዳ!

በሩዋንዳ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መጠቃታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በሀገሪቱ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 5 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ጣሊያን በትናንትናው ዕለት 368 ዜጎቿን ስታጣ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 809 አሻቅቧል።

ስፔን 97 ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 288 ደርሷል። በፈረንሳይም በትናንትናው ዕለት 29 ሰዎች ሲሞቱ በአጠቃላይ 120 ዜጎቿን በኮሮናቫይረስ ተነጥቃለች።

የዩናይትድ ኪንግደምም ትናንት ብቻ 14 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 35 አድጓል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት!

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መከላከያ ክትባትን በሙከራ ደረጃ ዛሬ መስጠት እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፣ ዛሬ የሚሰጠዉ የሙከራ ክትባት በ45 ፈቃደኛ ሰዎች ላይ የሚከናወን ሲሆን ክትባቱ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያደርስ ነዉ የተነገረዉ፡፡

ምርምሩን የሀገሪቱ ታላላቅ የጤና ተቋማት /የአሜሪካ ብሄራዊ ጤና ተቋም፣ ዋሽንግተን ሄልዝ ሪዘርች ኢንስቲትዩት፣ NIH and Moderna Inc እና ሌሎችም በጋራ ሲያካሂዱ መቆየታቸዉን ኤ ፒ ጽፏል፡፡

ሀገራት የመከላከያ ክትባቱን በእጃቸዉ ለማስገባት ከፍተኛ እሽቅድምድም ላይ በሆኑበት በዚህ ሰዓት አሜሪካ ወደ ማረጋገጫ ሙከራ ተሸጋግራለች፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ! በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ…
የ20/80 የኮንዶሚኒየም ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል!

ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 27/2011 ዓ.ም. ለ13ኛ ጊዜ ዕጣ የወጣባቸውና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የደረሳቸው ዕድለኞች፣ በየወረዳቸው ቀርበው ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ እንደተደረገላቸው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት እና አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ባስተላለፈው መመርያ መሠረት ፣ ክፍላተ ከተሞቹ ከዕድለኞቹ ጋር ውል እንዲዋዋሉ ለወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መመርያውን ማስተላልፋቸውን ነው ጋዜጣው የጠቆመው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia