"በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው" - የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
የFDRE ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የሰራዊቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችም ተሳትፈዋል።
በጉብኝታቸውም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እየተገነባ ያለውን የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ ነው!" - ዛሬ ሹመቱን ከተቃወሙ የምክር ቤት አባላት
የዛሬው የአራቱን ሚኒስትሮች ሹመት 21 የሕወሓት አባላት ተቃውመውት ነበር፡፡ ሹመቱ የትግራይ ተወላጆችን ያገለለ እንደሆነ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት ያፈራውን ሀብት ለመቀራመት የሚደረግ ሹመት ነው የሚሉ ተቃውሞዎችም ተሰምቷል፡፡
ሌሎቹ የምክር ቤት አባላት ደግሞ በተሿሚዎቹና በሹመቱ ላይ የቀረበውን ትችት ያስተባበሉ ሲሆን ፣ ‹‹ሚኒስትሮቹ የሚሾሙት ላለፉት ዓመታት የተዘረፈ ሀብትን ለማስመለስ ነው፤›› ሲሉ ወ/ሮ ብርቱካን ታደሰ የተባሉ የምክር ቤቱ አባል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዳባ ደግሞ ዶ/ር ሊያ ከትግራይ ብሔር መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ከዚህ ቀደም ሚኒስትሮችን ለመሾም የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ቡራኬ ያስፈልግ እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሹመት መስጠት በመጀመራቸው ምክንያት የቀረበ ተቃውሞ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

የከሚሴው ግጭት ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ!
በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን በከሜሴ የተለያዩ ወረዳዎች ተነስተው በነበሩ ግጭቶች ተከሰው የነበሩ ግለሰቦች ክስ መቋረጡን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባቸው ከነበሩ ከ80 በላይ ግለሰቦች ውስጥ የእድሜ፣ የጤና እና የወንጀል ተሳትፎን በመመልከት ቁጥራቸው 14 ለሚጠጉ ተከሳሾች ሰኞ የካቲት 30/2012 ክስ አቋርጧል፡፡
በተመሳሳይም በአማራ ክልል በእስር ላይ የነበሩ አምስት የወረዳ አመራሮች ክሳቸው መቋረጡን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

#ItsMyDam
ጄኔራል አደም መሃመድ፦
"የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱ ህዝቦች ሰላምና ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮውን ለመወጣት በላቀ ብቃት ላይ ይገኛል። በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እና አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው። የመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮ በላቀ ብቃት እየተወጣ ይገኛል። ሰራዊቱ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየወሩ ከደመወዙ በመቆጠብ የዜግነት ድርሻውን እየተወጣ ነው።"

አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ፦
"የኢፌዴሪ አየር ሃይል በቀጠናው የሚቃጣን የአየር ላይ ጥቃት ለመመከት ብሎም አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነው።"

#AlJazeeraArabicLive
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን አረብኛ ፕራግራም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በአሁን ሰዓት እየተሰራጨ ይገኜ። ቃለምልልሱ ለተከታታይ ለአራት ቀናት ይተላለፋል።
ቃለምልልሱን ለመከታተል በኢትዮጵያ አቆጣጠር፦
1. ዛሬ ሀሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓም ከምሽቱ በ1:00 ሰዓት ጀምሮ እየተላለፈ ይገኛል።
2. በድጋሜ ነገ አርብ መጋበት 4 ቀን 2012 ዓም ከጧቱ በ5:30 ይቀርባል፣
3. ቅዳሜ ከቀኑ በ7:30 ይደገማል፣
4. በድጋሜ እሁድ ከሌሊቱ በ10:30 ይቀርባል፣
https://youtu.be/ueliG2kthek

ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት በተለያዩ አገራት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በመላክ ላይ ትገኛለች።
በዚሁ መሰረት በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓም ኬንያ ናይሮቢ በመገኘት ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያላትን ግልጽ አቋም ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስረድቷል።
ሁለቱ መሪዎች ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎም የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው የልኡካን ቡድን በቀጣይም በሌሎቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ ለአባል አገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያን አቋም እንደሚያስረዳ ይጠበቃል።
#EPA

በቀደሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከዛሬ ጀምሮ በአውሮፓ በመገኘት ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ፣ ከፈረንሳይ እንዲሁም ከሌሎች የህብረቱ አባል አገራት መሪዎች ጋር በመገናኘት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን አቋም ለማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

አጫጭር መረጃች፦
- ዛሬ በፖላንድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪው ሞት ተመዝግቧል። በሀገሪቱ በ24 ሰዓት ውስጥ 20 አዲስ ኬዞች የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር 51 ደርሰዋል።
- በህንድ ኒው ዴልሂ ይህ ወር እስኪጠናቀቅ ድረስ ሲኒማ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል።
- ኖርዌይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት እየተዘጋጀች ነው።
- በአይርላንድ እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል።
- በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ቢያንስ ለሁለት ሳምንት የስፔን ላሊጋ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ተላልፏል።
- በኢራን በ24 ሰዓት 1075 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 429 ደርሰዋል።
- በዛሬዕ ዕለት ብቻ በዴንማርክ 99 አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ተመዝግበዋል።
- የሳምፕዶርያው ተጫዋች ማኖሎ ጋብያዲኒ በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም የጁቬንቱሱ ተጫዋች ዳንኤል ሩጋኒ በቫይረሱ መጠቃቱ ከ @tikvahethsport ሰምተናል።
- የአውሮፓ ህብረት ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ከአውሮፓ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚደረጉ ጉዙዎችን ለማገድ ያሳለፉትን ውሳኔ አወግዟል።
- ቱርክ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምክንያት ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ለሶስት ሳምንት እንዲዘጉ ወስናለች። በሀገሪቱ የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮችም ያለተመልካች እንዲካሄዱ ውሳኔ ተላልፏል።

አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦
- አይቮሪኮስት በሀገሪቱ የመጀመሪያውን ኮኖና ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። ባይረሱ የተገኘበት የአይቮሪኮስት ዜጋ ሲሆን ግለሰቡ በቅርቡ ነው ከጣሊያን የተመለሰው።
- በአልጄሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 24 ደረሰ። ዛሬ ብቻ 4 የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። በሀገሪቱ አንድ ሰው በቫይረሱ መሞቱ አይዘነጋም።
- በግብፅ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 67 ከፍ ብሏል። ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።
- ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 4 የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ይህም አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ቁጥር ወደ 17 ከፍ እንዲል አድርጎታል።
- በሴኔጋል ዛሬ 1 በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መገኘቱ ተረጋግጧል። አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥርም 5 ደርሷል።

አጫጭር መረጃዎች ኢትዮጵያ፦
- በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው International Community School (ICS) ከነገ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 11 ትምህርት ቤቱን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደሚዘጋ አስታውቋል።
- የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ትክክለኛውን መረጃ በመጠቀም ረገድ ከመንግስት ተቋማትና ግል ማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደርጓል።
- የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ከኢትዮዽያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ እምነቶች ጋር ምክክር አድርጓል።
- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ባለሙያዎች ለማሰልጠን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለህክምና ማዕከላት የሚውል 30 ሚሊዮን ብር አፅድቋል።
- ዛሬ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም የጤና ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ላይ ምክክር አድርጓል። ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ዶክተር ኤባ አባተ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳይገባ እያደረገች ባለው ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
#ጤናሚኒስቴር #አዲስፎርቹን #EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBOT

የኮሮና ቫይረስ ስጋት በኢትዮጵያ...
በአፍሪካ ቀስ በቀስ እየተሰራጨ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገባ መንግስት አሁን እየወሰደ ካለው ጥንቃቄ በተሻለ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠይቀዋል።
በተለይም በአሁን ሰዓት በበርካታ የዓለም ሀገራት ቫይረሱ በመሰራጨቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሚደረጉ በረራዎች ላይ ለህዝብ ደህንነት ሲባል እገዳ እንዲጣልም ጠይቀዋል።
የተለያዩ ሀገራት ወደሀገራቸው የሚደረጉ ጉዞዎችን እያገዱ ነው ያሉት የቤተሰባችን አባላት ቫይረሱ የተሰራጨባቸው ሀገራት አስፈላጊውን ቁጥጥር እስኪያደርጉ ድረስ መንግስት ጠንከር ያለ እርምጃዎችን እንዲወስድ አስገንዝበዋል።
ከዚህ ቀደም የዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማቋረጥ ቫይረሱን ለመከላከል መፍትሄ አይሆንም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

#JawarMohammed
የቀድሞው የOMN ዳይሬክተር የአሁኑ የኦፌኮ አባል የሆኑት ፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ ሚዲያዎች ሚዛናዊ ዘገባ እየሰሩ እንዳልሆነ ትላንት በOMN 'ልዩ ዝግጅት' በተሰኛ ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ከሰሞኑ በOMN ላይ ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲደረግ ነበር፤ ይህም ሆን ተብሎ እና ዝግጅት ተደርጎበት የተደረገ ነው ብለዋል። OMN የህዝብ ድምፅ መሆኑ እንዲሁም ለገዢውና ለስርዓቱ ፈተና መሆኑ የሚያስፈራቸው አካላት ናቸው ይህንን ያደረጉት ብለዋል።
አቶ ጃዋር ሚዲያዎች በተለይም የመንግስት ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በሰሞኑን ክስተት ዙሪያ ተደጋጋሚ ዜናዎችን ሲሰራ ከOMN ወገን ያለውን ነገር አልጠየቀም፣ በሰራቸው ሁሉም ዘገባዎች ላይም የOMN አመራሮችን ወይም ዳይሬክተርን አስተያየት አላካተትም ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል።
ይህ ፋና ብሮድካስቲንግ ሚዛናዊ ያልሆነ የዘገባ ተግባር የማያሳየው የብሮድካስት ህጉ በOMN ላይ ብቻ ስራ ላይ እየዋለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋል። አሁን በአመራር ላይ ያሉት የብሮድካስት አመራሮችም ህጉን የገዢውን ፓርቲና ግብረ-አብሮቹን ፍላጎት ለማስፈፀሚያ ብቻ እንደሚተረጉሙት ማሳያነው ሲሉ ወቅሰዋል።
MARCH 8 በነበረው ፕሮግራም ላይ OMN እራሱ ተጋብዞ ነው የመጣው ያሉት አቶ ጃዋር፤ ስርጭቱ ቀጥታ ስለነበር፤ ማን ምን ይናገራል የሚለውን ለመገመት የሚያስችል ምንም ነገር አልነበረም ሲሉ በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ በዝርዝር አስረድተዋል። የተፈጠረው ጉዳይ በOMN ላይ ጣት የሚያስቀስር እንዳልሆነም ገልፀዋል።

#ሼር #SHARE
ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው። ዋናው የመተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ወቅት ትንፋሽ ጋር በሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል ?
- በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫዎን በክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን!
- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት!
- በውሃ እና በሳሙና መታጠብ፣ አልኮል ነክ በሆኑ የንፅህና መጠበቂያዎች እጅዎን በአግባቡ ማሸት!
- የተጠቀሙበትን ሶፍት በፍጥነት በጥንቃቄ መክደኛ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል!
#ጤናሚኒስቴር

#NewsAlert
የአርሰናሉ አሰልጣኝ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
የአርሴናል አሰልጣኝ የሆኑት ማይክል አርቴታ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው። አርሰናል በለንደን የሚገኘውን የልምምድ ሜዳ እንዲዘጋ ውሳኔ አሳልፏል። ከአሰልጣኙ ጋር ንክኪ የነበራቸው የክለቡ ሰዎችም ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ ተደርጓል።
MORE @TIKVAHETHSPORT

#COVID19
ከሰዓታት በፊት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ቀጣይ መርሃግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚካሄድ ተሰምቶ ነበር፤ ነገር የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርቴታ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው በመረጋገጡ ዛሬ ዓርብ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል።
MORE : @TIKVAHETHSPORT
@tikvahethsport @tikvahethiopia

#Nekemte
በነቀምቴ ከተማ ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት የንግድና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና በማሳደሩ አንዳንድ ባለሃብቶች ወደ ሌላ ቦታ እየሄዱ እንደሚገኙ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ገልፀዋል።
የኢንተርኔት አገልግሎትም በከተማው መቋረጡና በአብዛኛው የወለጋ ዞኖች የስልክ አገልግሎት አለመኖርም ሥራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን እንዳንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።
የነቀምቴ ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስጌን ከተማዋ በአሁኑ ሰዓት ተረጋግታለች፣ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዋም እንዲቀላጠፍ ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።
#የአሜሪካድምፅሬድዮ

የመርካቶ የአውቶብስ ተርሚናል!
የመርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የተርሚናሉ ግንባታ 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፥ በ2012 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡
የአውቶቡስ ተርሚናሉ የተሳፋሪዎችን ምቾት በመጠበቀ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል፡፡ ተርሚናሉ በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል፤ የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችን አካቷል፡፡

ተጨማሪ መረጃ ስለ መርካቶ የአውቶብስ ተርሚናል፦
- የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ ፣ የትኬት ሽያጭና የተሳፋሪ መጫኛና የማራገፊያ ቦታ አሉት።
- ዘመናዊ ስምሪት አገልግሎትን ጨምሮ የአውቶቡስ መርሃ-ግብርና የአስተዳደር ቢሮዎችን አካቷል፡፡
- ተርሚናሉ በ4,125 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሲሆን፥ በአንድ ሰዓት 6,000 ለሚጠጉ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡
- በቀን ከ50,000 እስከ 80,000 ገበያተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አገልግሎት እንደሚሰጥ ታሳቢ ተደርጎ ነው ተርሚናሉ እየተገነባ ያለው።
- የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመደበ 200 ሚሊዮን ብር በመከናወን ላይ ይገኛል።
[የትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን]

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤት ሶፊ ግሪጎሪ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሶፊ ግሪጎሪ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ንግግር አድርገው ከተመለሱ በኋላ የተወሰነ የሕመም ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ለ14 ቀናት ብቻቸውን ለመቆየት መወሰናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤናቸውን ሁኔታ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከታተሉ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ቤታቸው ሆነው እንደሚሠሩ ጽ/ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።
#BBC

ኮሮና ቀለም አይለይም፤ ሁሉንም የሰው ዘር ያጠቃል!
የኮሮና ቫይረስ በሽታ [#COVID19] ነጭ ጥቁር የቆዳ ቀለም ሳይለይ ሁሉንም የሰው ዘር የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡
ኮሮና ቫይረስ አስካሁን የተረጋገጠ መድሐኒት ወይም ክትባት የለውም፤ ይህንን በመረዳት እና የጥንቃቄ መንገዶችን በማወቅ እንዲሁም በመተግበር በሽታውን መከላከል ያስፈልጋል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ኮሮና ቫይረስ ጥቁር አፍሪካውያን አያጠቃም በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸውና ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አይለያችሁ።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot