TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በግብፅ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተያዙ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሰዋል። ለሀገሪቱም ለአህጉሪቱም የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ዛሬ ተመዝግቧል።

- በናይጄሪያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቃው ሰው ቁጥር ሁለት ሆኗል። ዛሬ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቃ ሁለተኛ ሰው እንዳለ ሪፖርት ተደርጓል።

- በቶጎና ቱኒዝያ፣ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ላይ ለውጥ የለም። ዛሬ አዲስ በቫይረሱ የተገኘበት ሰው ሪፖርት አልተደረገም። ትላንት በሀገራቱ አንድ አንድ ሰው ብቻ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዘ አሳውቀናል።

- ካሜሮን እና ሞሮኮ በሀገራቸው ሁለት ሁለት የኮሮና ቫይረስ ኬዞች አሉ፤ በደቡብ አፍሪካ 3፤ በሴኔጋል 4 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- በአልጄርያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 20 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኢትዮጵያ ምንም የኮሮና ቫይረስ ኬዝ የለም። ከቀናት በፊት የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት የታየባቸውና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ሰዎችም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ሰምተናል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አንድ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ሆኖ የለቦራቶሪ ምርመራ ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝም ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰምተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

UAE ስለሚገኙት እና በኮሮና ቫይረስ እንደተጠቁ ስለተነገረላቸው 2 ሰዎች ከዚህ ቀደም መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል፤ ዛሬ ከሀገሪቱ መንግስት በወጣው መግለጫ ሁለቱም እንዳገገሙ፤ በዳግም ምርመራውም ቫይረሱ እንዳልተገኘባቸው ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ፣ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዲኤታና በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ የሰሩት በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ውስጥ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

#TPLF #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikvahFamily

የዓለም ስጋት በሆነው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የትምህርት ተቋሞች እንዲዘጉ መወሰኗን በሳዑዲ አረቢያ ነዋሪነታቸውን ያደረጉና በትምህርት ላይ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

በነገራችን ላይ በትናንትናው ዕለት ብቻ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ 4 ሰዎች ሪፖርት ተደርገዋል ይህም በሀገሪቱ አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ቁጥር ወደ 15 ሰዎች ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ለመከላከል ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?

- ከሚያስነስጥሱ፣ ከሚያስሉ እና ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ

- እጅዎትን በሳሙናና ውሃ አዘውትረው መታጠብ

- አለመጨባበጥ

- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት

#share #ሼር

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
149 መንገደኞችንና ስምንት የበረራ ቡድን አባላትን አሳፍሮ፣ ወደ ናይሮቢ ለመብረር፣ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ከተነሣ ከስድስት ደቂቃ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ጊምቢቹ ወረዳ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት ጄት አደጋ ህይወታቸው ላጡ፣ የመታሰቢያ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

#አሶሼትድፕሬስ #ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ዛሬ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቋቋመ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ቢገባ የካ ኮተቤ ሆስፒታል ሌሎች ሥራዎች አቁሞ ሕክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ዶክተር ሊያ «በዚህ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሥራዎች እየተሰሩ ነው» ብለዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በአገሪቱ ምንም አይነት የነዳጅ እጥረት የለም፤ ማደያዎቹ የፈጠሩት ነው!" - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

በአዲስ አበባ ባለፉት ሦስት ቀናት ባጋጠመው የቤንዝን እጥረት ለእንግልት መዳረጋቸውን አሽከርካሪዎች እየተናገሩ ነው።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ኃይለማርያም በአገሪቷ ምንም አይነት የነዳጅ እጥረት አለመኖሩን ገልጸዋል።

ችግሩ በየወሩ መጨረሻ የሚደረግን የነዳጅ ዋጋ ተመን ማሻሻያ ተከትሎ ማደያዎች የገንዘብ ጭማሪ ይኖራል በሚል እሳቤ በራሳቸው የፈጠሩት መሆኑን ተናግረዋል።

“በመላ አገሪቷ በቀን 2 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ታደሰ ድርጅቱ ከፍላጎቱ ጋር ተመጣጣኝ ነዳጅ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የነዳጅ አስፈጻሚ አካላት ኃላፊነታቸውን በሚገባ እየተወጡ ባለመሆኑ የነዳጅ እጥረቱ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ባለፈው ዓመት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰለቦች አንደኛ ዓመት መታሰብያ ነገ ይከናወናል።

መቀመጫውን አሜሪካ አድርጎ በዚህና ሌሎች አደጋዎች ለተጎዱት ጥብቅና የሚቆም የህግ ተቋም ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ ቦይንግ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ግፊት እያደረኩ ነው ብሏል።

በዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት እየታየ ያለው ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰም ለደንበኞቼ በየጊዜው መረጃ አደርሳለሁ ብሏል ድርጅቱ።

ከደቡብ አፍሪካ የመጣውና በአደጋው ሴት ልጁን ያጣው ተጎጂ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ተሰባስበው በጋራ መታደማቸው እንዳስደሰተው ገልጾ፣ ዓለም ለሰው ልጅ ቅድሚ እንድትሰጥ ጠይቋል።

ምንጭ፦ DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,462 የደረሰ ሲሆን 101,861 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 56,108 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4,000 የደረሰ ሲሆን 114,010 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 62,832 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች፦

- ትኩሳት
- ለመተንፈስ መቸገር
- ሳል

ውድ ቤተሰቦቻችን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ዙሪያ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመር 8335 ላይ መደወል ትችላላችሁ ብለዋችኃል የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት።

#share #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከዩጋንዳ [ካምፓላ] ቲክቫህ ቤተሰብ፦

በዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኝ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በዛሬው ዕለት ሀገሪቱ ኮሮና ቫይረስን በቅድሚያ ለመከላከል የምታደርገውን ዝግጅት ምን እንደሚመስል አጋርቶናል።

ዩጋንዳ እንደኛው ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተያያዘ ሰው የለም። ሆኖም ግን የሚወስዱት ጥንቃቄና ዝግጅት የሚደነቅ እንደሆነ ነው የቤተሰባችን አባል የገለፀልን።

ለምሳሌ ካምፓላ ውስጥ አንድ ሰው ወደ ማንኛውም ሆቴል ወይም የመንግስት መስሪያ ቤት እና ሌሎችም ቦታዎች ከመግባቱ በፊት እጁን በአልኮል ማፅዳት ግዴታው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ ሊካሄዱ የነበሩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መሰረዛቸውን የሀገሪቱ ጋዜጣዎችን እያስነበቡ ነው።

በካምፓላ የተለያዩ ቦታዎች ላይ መረጃዎች ተለጥፈውም ይታያሉ። ይህ የሀገሪቱ ዝግጅት ጠቃሚ ተሞክሮ ይሆናልና አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ከሚገኘው ዝግጅት በተጨማሪ ይህ ተሞክሮ ቢወሰድ መልካም ነው።

#ጌታነህገብሬ #ካምፓላ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OMN

ከሰሞኑን ኦ ኤም ኤን በተባለ መቀመጫነቱን አዲስ አበባ ባደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት ባደረገ ዝግጅት ዙሪያ እየተሰራጨ በሚገኝ የቀጥታ ስርጭት ወቅት አንዲት ሴት የተናገረችው ንግግር ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮ፣ ብዙዎችን አስቆጥቶ በመንግስት ደረጃም ግብረ መልስ ተሰጥቶበታል።

ንግግሩ በተላለፈ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያው ቪድዮውን ከማህበራዊ ገፁ ላይ ያነሳ ሲሆን በእንስቷ ያልተገባ ንግግር ለተከፉ የቴሌቪዥኑ ተመልካቾች በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

መንግስት በበኩሉ በህዝባዊ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በሃገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ እንደሚደቅኑ ገልጾ በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቀዋል።

More https://telegra.ph/OMN-03-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰሞኑን በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ OMN የተላለፈውን አንድ መልዕክት ሰምተናል
<unknown>
#OMN

ሰሞኑን በOMN በተላልፈው መልዕክት በቀጥታ ሲከታተሉ የነበሩት የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ኦፌኮ ሊቀመንበሩር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዴት እንደተረዱት እንዲያስረዱ በሸገር ኤፍ ኤም ተጠይቀው ነበር።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የንግግሩ ችግር አይታየኝም፣ ማንኛውም ዜጋ የሚናገረውን ለመቆጣጠር ፍላጎቱ የለንም ብለዋል፡፡

ሬድዮ ጣቢያው ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሕግ ምሁር እና የብሮድካስት ባለስልጣንንም ጠይቋል፡፡ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለመከላከል በቅርቡ በጥቁር እና በነጭ ተፅፎ የፀደቀው ሕግስ እንዴት እየተተረጎመ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከኢትዮጵያ ወደሀገሩ አሜሪካ እንደተመለሰ የተነገረለት አንድ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መያዙን Talk Media News ዘግቧል። ለጊዜው ወታደሩ ከኢትዮጵያ መቼ እንደተመለሰ የሰጠው ፍንጭ የለም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጡት መረጃ የለም። በጉዳዩ ላይ የሚሰጡ መረጃዎች ሲኖሩ እንድታነቡት የምናደርግ ይሆናል።

https://www.talkmedianews.com/featured/2020/03/09/marine-back-from-ethiopia-tests-positive-from-covid-19-at-ft-belvoir-virginia/

#TalkMediaNews #EthioFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተባለ!

በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ እየተዳሰ የነበረውን የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያንን ለመገምገም ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ የመጡትና ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት ያረጉት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል።

የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቨር ቬራን ቢ ኤፍ ኤም ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ”ሬይሰተር አሁን እቤቱ አረፍ ብሏል። ደህና ነው።” በማለት ሚኒስትሩ እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የ46 አመቱ ሬይስተር በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ከአንዱ ጋር በመገናኘታቸው ቫይረሱ ሊይዛቸው እንደቻለም ተነግሯል።

ራይስተር ከፈረንሳይ ባለስልጣኖች መሀከል ግብረሰዶማዊ ነኝ በማለት በ2010 ዓ.ም መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን አጥብቀው ይደግፋሉ።

ራይስተር ዛሬ ማክሰኞ ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር። በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 25 ሰዎች ሲሞቱ 1,412 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ምንጭ፦ fidelpost.com
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ቤታቹ ሁኑ ሁሉም ነገር ይስተካከላል" - ካፑቱ

የሳሱሎው የፊት መስመር ተጫዋች ፍራንቼስኮ ካፑቱ ለክለቡ ግብ ካስቆጠረ በውሃላ በጣልያን በርካታ ሰዎችን እየጨረሰ ስለሚገኘው ኮሮርና ቫይረስ "ቤታቹ ሁኑ ሁሉም ነገር ይስተካከላል" በማለት ለጣሊያናውያን መልዕክቱን አስተላልፏል።

በጣልያን በፍጥነት እየተስፋፋ ከመጣው የኮሮና ቫይረሱ ስርጭት አንፃር የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በመላው ሀገሩቱ እንቅስቃሴ አግደዋል። ሁኔታዎች እስኪረጋጉም የትኛውም ስፓርታዊ ውድድር እንዳይካሄድ የሚል መመሪያ ማስተላለፋቸው ተነግሯል።

የኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ዓለም ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል። በስፖርቱ ዓለም የሚፈጠሩትን ጉዳዮች በቲክቫህ ስፖርት መከታተል ትችላላችሁ @tikvahethsport

@tikvahethsport @tikvahethiopia