TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETH302

ለቦይንግ 737 አውሮፕላን ሰለባዎች ሙት አመት መታሰቢያ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ጸሎት አድርገዋል። የአካባቢው ፈረሰኞች ዛሬ ለአመት የዘለቀው ሀዘን የሚያበቃበት ቀን መሆኑን ለማሣወቅ ጥቁር እና ነጭ ሰንደቅ አላማዎችን በመያዘ ተገኝተው ነበር። አባ ገዳዎችም ምስጋና አቅርበዋል።

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት ቡልቡላ ማሰልጠኛ ማእከል ለ30ኛ ዙር የሰለጠኑ የኦሮሚያ ክልል ልዩ የፖሊስ ሀይሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቀዋል። አባላቱ በቆይታቸው የተለያዩ ስልጠናዎችን ለወራት ተከታትለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EGYPT

ግብፅ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግን አቋም ለመቃወም ባወጣችው መግለጫ ድርጅቱን እና አባል አገራቱን ዘልፋለች ስትል ከሰሰች። ኢትዮጵያ የአረብ ሊግና አባላቱ ከአፍሪካውያን ስለሚኖራቸው ግንኙነት ማብራሪያ የመስጠት መብት የላትም ብላለች።

ኢትዮጵያ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የላትም፤ ድርድሩን ለውስጥ ፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል ሞክራለች ሲል የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ፦

የዮርዳኖስ ንጉስ አብደላ 2ኛ በኅዳሴ ግድብ ድርድር ግብጽን እንደምትደግፍ ለሳሜሕ ሽኩሪ እንደነገሯቸው የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። አብደል ፋታሕ አል–ሲሲ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታሕ አል–ቡርሐን በስልክ ተነጋግረዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እናት ፓርቲ!

ዛሬ የካተት 29 / 2012 ዓ/ም 'የእናት ፓርቲ' መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል። በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም ጉባኤውን ከላይ በፎቶው እንደምትመለከቱት አጋርተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EnatParty

ዛሬ የካቲት 29/2012 ዓ/ም 'በእናት ፓርቲ' ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው የእናት ፓርቲ አርማ ከላይ የምትመለከቱትን ይመስላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደብሊን የተደረገ አቀባበል! በሴቶች ብቻ የተመራው የበረራ ቡድን ደብሊን ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። የበረራ ቡድኑ በአሁን ሰዓት ወደ USA ዋሺንግተን ዲሲ በረራውን ቀጥሏል። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየርመንገድ @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በሰላም ገብተዋል!

በሴቶች ብቻ የተመራው በረራ #USA ዋሺንግተን ዲሲ አርፏል። በስፍራውም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋን ጨምሮ በርካቶች የደመቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ArbaMinch

በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዌልነስ ሪዞርት ግንባታ ጅማሮ የሚሆን የቦታ ቅየሳ ስራዎችን ባለሞያዎች ማከናወን ጀምረዋል።

በአርባ ምንጭ ከተማ በአፍሪካ ከሲሼልስ ከሚገኘው ግዙፉ ሆቴልና ሪዞርት በመቀጠል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና ሪዞርት እንደሚገነባ ከዚህ ቀደም ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ግንባታው በሚከናወነበት ስፍራ የኩባንያው ባለቤቶችና የውጪ ሀገር ባለሃብቶች ቦታው ድረስ በመምጣት ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ለሆቴሉና ሪዞርት ግንባታ ስራዎች ዝግጅት የሚረዱ የመረጃ ግብዓቶችን የመሰብሰብ ስራ ሲከናወኑም ቆይተዋል፡፡

ከዚሁ ግንባታ ስራ ጋር በተያያዘ በዚህም ሳምንት ከቀን 25 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የቦታ ልኬትና ማመቻቸት ስራዎች በአለም-አቀፍ የግንባታ ባለሙያዎች ግንባታው በሚያርፍበት ስፍራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#BrishZewde #TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

- ባንግላዴሽ በዛሬው ዕለት 3 በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ግለሰቦች በሀገሯ መገኘታቸውን አረጋግጣለች። ግለሰቦቹ 20-35 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ሁለቱ ከጣልያን የተመለሱ ሲሆኑ አንደኛው ደግሞ የግለሰቦቹ ቤተሰብ ነው።

- በኳታር በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ተጨማሪ 3 ግለሰቦች መኖራቸው ተረጋግጧል። በዚህም በኳታር በኮሮና የተጠቁ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- በኢራን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 194 ደርሰዋል። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ደግሞ 6,566 ሆነዋል። በ24 ሠዓት ውስጥ 743 አዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል።

- በሳዑዲ አረቢያ ተጨማሪ 4 ግለሰቦች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰምቷል። ይህም በሀገሪቱ በኮሮና የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር 11 አድርሶታል።

- በአርጀንቲና በኮሮና ቫይረስ የሞተ ግለሰብ መኖሩ ዛሬ ሪፖርት ተደርጓል። በሀገሪቱ 9 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

ከደቂቃዎች በኃላ በአፍሪካ ያለው ሁኔታ እንመለከታለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በአፍሪካ ኮሮና ቫይረስ የተዛመተባቸው ሀገራት 9 ናቸው። ሀገራቱም፦ ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ቶጎ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሮን፣ ቱኒዝያ ናቸው።

- እስካሁን ድረስ በቶጎ፣ ቱኒዝያ፣ ናይጄሪያ አንድ አንድ ሰው ብቻ ነው በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተያዘው።

- ካሜሮን እና ሞሮኮ በሀገራቸው ሁለት የኮሮና ቫይረስ ኬዞች አሉ፤ በደቡብ አፍሪካ 3 በሴኔጋል ደግሞ 4 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- በግብፅ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 49 ናቸው፤ በአልጄርያ ደግሞ 19 ሰዎች ተጠቅተዋል።

- ከላይ በተዘረዘሩት 9 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ በዛሬው ዕለት የተመዘገበ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ የለም።

- በኢትዮጵያ ምንም የኮሮና ቫይረስ ኬዝ የለም። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው መግለጫ የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት የታየባቸው ሁለት ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን የግለሰቦቹ ውጤት አልተገለፀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶክተር ሊያ ታደሰ፦ "የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች [UAE] ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን የኤምሬትስ ነዋሪ ሲሆኑ በዛ ሀገር ለአመታት የኖሩ እና በቅርቡም ጉዞ ያላደረጉ መሆኑን አረጋግጠናል" #EliasMeseret @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በUAE በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ በሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ከተነገረላቸው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን መካከል አንደኛው ግለሰብ ድጋሚ ተመርምረው ቫይረሱ እንደሌለባቸው ተረጋግጧል ሲሉ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ጥዋት በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እናት ፓርቲ! ዛሬ የካተት 29 / 2012 ዓ/ም 'የእናት ፓርቲ' መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል። በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም ጉባኤውን ከላይ በፎቶው እንደምትመለከቱት አጋርተዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በእናት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ የእናት ፓርቲ አመራሮች፦

- ፕሬዝደንት ፡ ዶ/ር ኃ/ኢየሱስ ሙሉቀን
- ም/ፕሬዝደንት ፡ ዶ/ር ሠይፈሥላሴ አያሌው
- ጠቅላይ ፀሐፊ ፡ አቶ ጌትነት ወርቁ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

UNICEF ለኢትዮጵያ ለኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ዝግጅት እና መከላከል የሚውል የኢንፌክሽን መከላከያ ኬሚካል (በረኪና) ለግሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ፦

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለ የዝግጅት ሁኔታ፦

• በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች አራት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ (467,280) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

• በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት (277,977) በሙቀት መለያ ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ስምንት (6,858) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

• በሽታውን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት የመጡ ተጓዞች የጤና መረጃ ቅጽ ከመሙላታቸው በተጨማሪ ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የሚደረግ የጤና ክትትል ተደርጎላቸው ያጠናቀቁ አንድ ሺህ ዘጠና ሶስት (1093) ክትትል ተደርጎላቸው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሺህ ሃያ አንድ (1021) የሚሆኑት ደግሞ የጤና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

More https://telegra.ph/COVID19-03-08

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia